ኦርቶዶክስ:የዘላለም:ቤቴ
289 subscribers
1.98K photos
191 videos
111 files
160 links
☦️እመን:እንጂ፡አትፍራ
ምስጉነው:በክፉዎች:ምክር:ያልሄደ:በዋዘኞችም:ወንበር:ያልተቀመጠ።
ኦርቶዶክስ:የዘላለም:ቤቴ:በመንፈሳዊ:ሕይወታችን:እንድንበረታ:የሚያግዙ:ትምህርቶች፣መዝሙሮች፣ጸሎቶች:እንዲሁም:የተለያዩ:መንፈሳዊ:ጉባኤዎች:ሲዘጋጁ:የሚነገርበትና:የሚለቀቅበት:መንፈሳዊ:channel:ነው።
@orthodox30 @orthodox30
@orthodox30
Download Telegram
Forwarded from ኤላዊት💖🙏
🙏እኛን በህማሙ ህመማችንን አጠፋልን በመስቀሉም አስታረቀን እግዚአብሔር ይመስገን 🙏
ጸሎተ-ሐሙስ የሕፅበተ እግር ስነ ሥርዓት ተከናወነ

ዛሬ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክሃይማኖት መሪነት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የሕፅበተ እግር ስነ ሥርዓት ተከናወነ።

በስነ ሥርዓቱ ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ቆሞሳት ፣ ካህናትና በርካታ ምዕመናን ተገኝተው እንደነበር ከቤተክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ኦርቶዶክስ የዘላለም ቤቴ 🙏🙏🙏🙏🙏🌿🌿🌿🙏🙏🙏
🌿ዛሬ ከሲኦል እስራት ነፃ የወጣንበት እኛ ያዳም ልጆች የዳንበት ልዩ ቀን ናት እግዚአብሔር ይመስገን🌿መልካም በአለ ትንሳኤ ክርስቶስ ተንስአ ሙታን በአብይ ሀይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አጋዞ ለአዳም ሰላም እምዝኤሰ ኮነ ፍስሀ ወሰላም🙏🌿🌿🌿🌿🌿

ኦርቶዶክስ የዘላለም ቤቴ
🌿🌿🌿ዛሬ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ለደት ነው ከጨለማ ወደ ብርሃን የወጣችበት በአሉን በደማቅ ሁኔታ እክብረናል እግዚአብሔር ይመስገን 🌿🌿
ግንቦት 1።
ኦርቶዶክስ የዘላለም ቤቴ
@orthodox30                ውድ ቤተሰቦቻችን እንደምን አላቹህ ስለምትከታተሉን በጣም እናመሰግናለን🙏አስተያየት መስጠት  የመትፈልጉ ይስተካከል የምትሉት ነገርም ካለ ከስር ባለው ሊንክ አስተያየቶን መስጠት ይችላሉ👇👇👇
           👍@Jo1267
0978317215 ኦርቶዶክስ የዘላለም ቤቴ
🙏እንዴት አደራቹ ቤተሰቦች 🙏ዛሬ ላወጋቹ የምፈልገው እኔ በጣም አዝኛለሁ ስለቤተክርስቲያን ስለ ሀገር ጠባቂዋ ጥሩ ነገር እየተሰማኝ አደለም ወዴት እያመራን ነው ሁላችንም ዝም ብለናል ብዙ አድባራት አባቶቻችን እየተገደሉ ነው እየተዘረፍን ነው እኛ አሁንም ተኝተናል እኔ እያስፈራኝ ነው ያለው በውጪው ሀገር እግዚአብሔር የፈቀደለት መንግስት እንደዚህ ከላይ በምስሉ👆👆👆👆👆እንደምታዩት ውብ ቤተክርስቲያን ይገነባል ባህር ዳር ላይ የኛ አልን የምንለው ያው እሱም ይቃጠልብናል እና ዝም ባንል ባይ ነኝ በጸሎት እንበርታ ምንድነው የያዘን አንዲት ሀገር አንዲት ቤተክርስቲያን አንድ ሲኖዶስ ነው ያለን ብቻ ያለንበት ሁኔታ በጣም የሚያሳዝን ነው እህት ወንድሞቼ ልላቹ ያሰብኩት ነገር የገባቹ ይመስለኛል🙏

🙏 ኦርቶዶክስ የዘላለም ቤቴ 🫶
Forwarded from Samson Hailu
ከሀና ማህጸን የአዳም ተስፋ ታየች
በኀጢአት የደረቀው የሰው ህይወት በድንግል መወለድ በተስፋ ለመለመ
ጨለማው ዓለም በድንግል መወለድ ብርሃን ሆነ
የሊባኖስ ተራራ በብርሃን ተከበበ
ሊባኖስ የብርሃን መቀነት ታጠቀች
ሊባኖስ በብርሃን አጥር ታጠረች
ኢያቄም የደስታ ካባ ደረበ
ሀና የደስታ አክሊል ደፋች
የብርሃን እናት ድንግል ተወልዳለታለችናችና
የዓለም ሞት በህይወት ተቀየረ
ሰማይ ከሀና ማኅፀን ተወለደች
የሐና ማሕጸን የሰማዯ መውጫ ሆነ
የውርስ ኀጢአት ከድንግል ራቀ
ሰወች ሁሉ በውርስ ኀጢአት በሚወለዱበትን ያለውርስ ኀጢአት ንጹህ ሁና ወላዲተ አምላክ ተወለደች
ከኢያቄም አብራክ ነጭ እንቁ አበራች
ከሀና ማኅጸን ጸአዳ ርግብ ወጣች
የሀና ታሪክ ተቀየረ
ሀና የእግዚአብሔር ወልድ አያቱ ተባለች
ሰማያት ሰለሰማዯ መወለድ ዝማሬ ዘመሩ
ምድር ሰማይን በመሸከሟ እልል አለች
ሰማዯ በምድር ታየች
የአበው ተስፋ መሰረት ተጣለ
አይሁድ አፈሩ
ቤተ ክረርስቲያን የድንግልን መወለድ አበሰረች
በ5485 ዓመተ ዓለም ድንግል ተወለደች
ፀሐይ ሊወጣ ሰማይ ተገኘች
ሰማዯ ከሰው ተወልዳ ፀሐይን ወለደች
እመቤቴ በመወለድሽ የአበው ተስፋ እውን ሆነ።
የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለያችሁ🙏🙏
የሰንበት ት/ቤታችን አባል በሆነው በወንድማችን በዲ/ን ዮሴፍ እምሻው እንዲሁም በቀበና ምዕራፈ ፃዲቃን አቡነ ተክለሃይማኖት እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከሳቴ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት አባል ወጣት ፍቃዱ ዲባባ ከፃድቃኔ ማርያም ንግስ በዓል ሲመለሱ በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን፤ የወንድሞቻችንን ነፍስ ከደጋጎቹ አባቶቻችን ከአብርሐም፣ ከይስሓቅ፣ ከያዕቆብ አጠገብ ያሳርፍልን። ከቅዱሳኑ ይደምርልን፤ ረፍተ ነፍስን ይስጥልን። ሰንበት ትምህርት ቤታችን ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለአብሮ አደግ ጓደኞቻቸው ፣ ለሰንበት ት/ቤቶቹ አባላት እና ለደብራችን አገልጋዮች በሙሉ መፅናናትን እየተመኘን የቀብር ሥነ-ስርዓቱ የሚፈፀምበትን ቀን እና ሰዓት የምናሳውቅ መሆኑን እየገለፅን። አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ነፍሳችሁን ያሳርፍልን፤የቅዱሳን ዕረፍት ያድርግልን! ነፍስ ይማርልን።