በሳቄ ሸፈንኩት
172 subscribers
3 photos
8 videos
4 links
Download Telegram
በሳቅ መጋረጃ ሀዘን ተደብቆ
Channel photo updated
Channel photo updated
እጓዛለሁ እንጂ ፦
ፊቴን ተስፋ አድርጌ እገሰግሳለሁ
ወደኋላ አልልም ለምን እቆማለሁ
ሰውን ተደገፌ ሲለቁኝ አልወድቅም
አይተውኝም ብዬ አልመፃደቅም
የሰው ልጅ ያው ሰው ነው
ዛሬ አለሁኝ ብሎ ነገ ላይን ይጠፋል
መሄድ ግን አይቆምም መኖር ይቀጥላል.........😌
👏1
.........ህልሜ........
በነፋሻው አየር ሰላም በሚሰጠው፣
በደመቀው ምሽት ውስጥን በሚያረካው፣
እኔና አንተ ሆነን ሁለታችን ብቻ፣
ፍቅርን ስንሰራ ሳይኖረን ፍራቻ፣
በውስጥህ መአዛ ባንተነትህ ውበት፣
ፍፁም ተመስጬ ለኔ ባለህ ግምት፣
ራሴን ሰጥቼህ ቅንጣቱን ሳልሰስት፣
በራሳችን ህይወት በሌላ አለም ስንኖር፣
ተቃቅፈን ባንድ አልጋ ተኝተን ስናድር፣
የነበረው ደስታ የነበረው ፍቅር፣
እንዴት ያምር ነበር ህልም ሆኖ ባይቀር???
👏2
ለምን ቢሉኝ ደርሰው ብዙ ቢጠይቁኝ፣
ተስፋ የማትቆርጪ...
እጅ የማትሰጪ...
ብለው ቢሞግቱኝ፣
መልሴ ዝምታ ነው
ቃል አይወጣም ካፌ ምንም አልናገር፣
ፅናቴን እያየ ሁሉም ይደናገር
ደግሞም ይጠይቁኝ
እንዲ እየተከፋሽ ምነው አታነቢም ምንድነው ፈገግታሽ?
እንዲ እየተበደለሽ ፍርድ አትጠይቂም ወይ ምንድነው ዝምታሽ?
ይበሉኝ ደጋግመው ሌላ ሌላም ካለ ዘለፋው ይፋፋም፣
ያኔም ቢሆን እኔ ፈገግታ ነው መልሴ ካፌ ቃል አይወጣም፣
ዛሬ ለኔ ባይሆን እንደመሸ አይቀርም
ቀን እኮ ባዳ ነው፣
ለዚ ለዚ ጊዜ ከፈገግታ ጋራ መልሴ ዝምታ ነው፣
ለምን? ቢሉኝ ደርሰው፤
ጊዜው ይርዘም እንጂ ለሁሉም ቀን አለው።።።
👏1
እኔ እወድሻለሁ
ብዙ ሺህ ዘመናት
እልፍ አዕላፍ ሌሊት
ሚሊዮን መሰለኝ
ፍቅሬ አንችን ስወድሽ ቀኑ ረዘመብኝ።
እኔ እወድሻለሁ
የሰማይ መሬቱን
የባህር ስፋቱን
የዓለም ዳርቻ የርቀቱን ያህል
እንደ ፅጌ-ረዳ
እንደ አደይ አበባ
እንደሎሚ ሽታ።
እንደእጣን ጢስ እንጨት፥ እንደከርቤ ብርጉድ፥ እኔ እወድሻለሁ፥
                      አበባ እንዳየ ንብ።
እንደቢራቢሮ ጫካ እንደሚያስሰው
ፍቅርሽን በፍቅሬ በፍቅርሽ ልቅመሰው
ማር ወለላዬ ነሽ ከረሜላ ስኩዋር
አማርኛ አይበቃ፤
           ወይጉድ!
                    ባለም ቁዋንቁዋ ሁሉ ቢወራ ቢነገር፥
እኔ እወድሻለሁ
                      እንደማታ ጀንበር።
እንደ ጨረቃ ጌጥ፥
        እንደንጋት ኮከብ፥
                    እኔ እማልጠግብሽ
ስወድሽ፥ ስወድሽ፥ ስወድሽ፥ ስወድሽ።
ጡት እንዳየ ህፃን ወተት እንዳማረው
ጠጋ በይ ዘመዴ አፍሽ ሀይወቴ ነው።
ጣይ እንዳየ ቅቤ
           ገላዬ ገላሽን ሲነካ የሚያልቀው፥
አፈር መሬት ትቢያ ወሃ እንደሚበላው፤
ፍቅሬ አንቺን ስወድሽ
          ብዙ ሺህ ዘመናት
እልፍ አዕላፍ ሌሊት
እኔ እወድሻለሁ፤
አይኖችሽን ባይኔ ተዳክሜ እያየሁ
ስወድሽ ስወድሽ
          እኔ እወድሻለሁ።
       
🔥21
ዝም የምንለው የምናወራው አተን ሳይሆን ውስጣችንን ለማዳመጥ ነው
🙏2👍1
Channel photo updated
Live stream finished (44 days)
እኔ እኮ በአንተ ደስተኛ ነኝ መኖርህ የሚያኖረኝ
በአንተ መኖር ውስጥ ደስታን የማገኝ የግል ግዛቴ ነህ
ምን ቢረዝም ነው ቁመቱ
ምን ቢተልቅ ነው እርቀቱ
ፍቅር የሚሉት ሀያል
እኔ ደርሼ ሳልይዘው
እሱም ሳይዘኝ መቅረቱ

ወደድኩ ብዬ ሳስብ
አፈቀርኩ ብዬ ሳምን
ተራ ስሜት ነው ሚሰማኝ
ወዲያው ገንፍሎ ሚሰክን

ግን ምን አይነት ነው ቀለሙ
አቋሙስ እንዴት ነው ከቶ
አንዴ ከያዘ ማይለቀው
ከገባ በርን አንኳኩቶ

ስንቶች የሚሞቱለትና
ስንቶች በሱ የሚኖሩበት
ምን አይነት ስልጣን ቢይዝ ነው ?
ፍቅር ለሚባል ጀግና አለም የሚገዛለት??
እማ ዋሽተሺኛል😔

የኑሮ ሁኔታ ካቅምሽ በላይ ሆኖ
ህመሙ ጭንቀቱ ሲጽናብሽ ገኖ
በተሰበረ ልብ ካይንሽ ዕንባ ሲፈስ
ማይጠገብ ፊትሽ ባዘን ሲደፈርስ
     
          ምን ሆነሽ ነው ብዬ ያኔ ስጠይቅሽ
           ጽጕሬን እየዳበሽ እንዲ ነበር መልስሽ
        ፊቴን ታጥቤ ነው ለምን አለቅሳለው
         አንተ ካለህልኝ ሁል ጊዜ ስቃለው
 
   ብለሽ ዋሽተሺኛል እኔ እንዳልከፋ እንደዛ በለቅሶ አይንሽ እየጠፋ

ውስጥሽ የተጎዳ ክፉኛ እያመመሽ
ደናነኝ አታስብ እርሺው ትዪኛለሽ
ግን ልጅነት ሆኖ አምንሻለው ቶሎ
ከቅፍሽ ስገባ እጅሽ እንኳን ዝሎ

        ደግሞም አይቻለው ከሆድሽ አጉድለሽ   
        ጥራጊ ስትበዪ  እኔን ጥግብ አርገሽ
           ለምንስ ዋሸሺኝ ለምንስ ደበቅሺኝ
            እንደዛ እየክፋሽ ደስተኛ ነኝ አልሺኝ

እርቦሽ ሳትበዬ አንጀትሽም ታጥፎ
እኔን አብልተሻል ከጥጋብም አልፍ
ከህመምሽ በላይ ሚያሳስብሽ ነገር
ስለኔ ደስታ ነው ሳልከፋ እንድኖር

         ባይኖርሽ እንኩዋን ከሰው ተበድረሽ
           አንሼ እንዳልታይ ሁሉን ታደርጊያለሽ
            እስካለሽ እስካለሁ
             እምዬ ሁል ጊዜ ደምቄ እታያለሁ
            አንቺ እኮነሽ ወዜ😚

ባንቺ ፈገግታ ውስጥ እኔ እንድበራ
ስንት ጊዜ ስቀሻል ሆነሽ በመከራ
ቢከፋሽ ለብቻሽ ደብቀሽ ሸሽገሽ
እማዋሽተሺኛል እያነባሽ ስቀሽ

    
#እናቱን የሚወድ ይሄንን ግጥም ያንብላት 👏
        
      
Channel photo updated
እነንትና የምታቁኝ እየመሰላችሁ አገምቱኝ እንኳን እናንተ ልታውቁኝ ይቅርና እራሴን እራሱ አላቀውም


😁😁😁😁😁
በጥቂት ግዜ አውቀናቸው ትዝታቸውን ትተውልን ለሄዱት