በሳቄ ሸፈንኩት
172 subscribers
3 photos
8 videos
4 links
Download Telegram
.....ይቅር አትበለኝ...
ውዴ ቂም የያዝከው፣
ንገረኝ በማን ነው፣
በኔ ነው በራስህ፣
ሳምንህ በመክዳትህ፣
ወይንስ በልብህ ነው፣
ሰው መውደድ ባቃተው?
ንገረኝ አትፍራ..
እኔ አንተን መውደዴ የመሰለህ በደል፣
አንተ የኔን ያክል ባትወደኝ አይደል?
ሁሌ አንተን ማለቴን፤ሌላ አለማየቴን ከጥፋት የጣፍከው፣
ባንዴ የገፋከኝ ዛሬ ነገ ሳትል፣
አንተ ባታደርገው ባትሆነው አይደል?
ግን ምን ባደርግህ ነው ምንስ ብበድልህ፣
ምክንያቱን ሳትነግረኝ ከኔ መለየትህ
ጠዋት ደና ነበርክ
ከዛስ ምን ለወጠክ?
ነው ወይስ ያለልክ የሰጠሁክ ቦታ፣
አልመችህ አለ በመድላቱ ፈንታ?
ንገረኝ ሳትደብቅ ልወቀው ምክንያቱን፣
ሳላውቅ ያጠፋሁት ከኔ ያራቀህን፣
አንተን ያስቀየመህ ማፍቀሬ ከሆነ፣
ስህተት ነው ብሎ ልቦናህ ካመነ፣
ሂድ አይርፈድብህ ነገሩ ሄደሀል፣
ወዶ የሄደን ሰው ምን ይመልሰዋል?
አሁንም ልንገርህ...
እኔ አንተን መውደዴ ከመሰለህ በደል፣
ይቅር አትበለኝ ቂም እንደያዝክ ውለህ ቂም አርግዘህ እደር!
ሂድ እንዳትመለስ ጨርቅ ያርገው መንገዱን፣
እኔን አሳዝኖ ደስታ የሰጠህን፣
ቸር ይግጠምክ እንጂ ሌላ ምን እላለው፣
ወትሮም መንገደኛ አይንና እግር እንጂ፤ ልብ መች ታደለው?
እኔ ግን ይቅርብኝ ካንተ ወዲያ ፍቅር፣
ያንተ ነበርኩና ያንተው ሆኜ ልቅር፣
ይህን አትከልክለኝ ባትመለስ እንኳን ስጠብቅህ ልኑር!!!
Channel photo updated
#ቃል_ብዬ_ጠራሁሽ

ስላንች ለመፃፍ ብእር እቀርፅና
ቀለሙን አቅልሜ ፈቅፍቄ ብራና

ፊደልና ቃላት እንደልጅ እያማጥኩ
ሀረግ እየመዘዝኩ ምሳሌ እየጠቀስኩ

ቃል ባጣው ልሳኔ ስፅፍ ውዬ አድሬ
ገልጨሽ ሳይበቃኝ ትደርቃለች ብእሬ

ደግሞ ተመልሼ................

ደሜን አንጠፍጥፌ ቀለሙን አቀለምኩ
አጥንቴን ፈቅፍቄ ላንች ብእር ቀረፅኩ

ብእሬን በደሜ ነክሬ ሳወጣው
አንችን እገልፅበት ቅንጣት ቃላት አጣው

ለካንስ ቃልዬ!!!

በፍቅር ነሁልሎ መንፈስ ከደከመ
ናፍቆት አገርጥቶት ልብ ከታመመ

እንኳን ቃል ተዋቅሮ ቅኔ ሊመሰጠር
ደግሞ ስንኝ ሁኖ ግጥም ሊደረደር

ደህና አደርክ ሲባል ለእግዚአብሄር ይመስገን
አንደበት ቃል ያጣል ሲመርቁት ለአሜን

ለዛ ነው ቃልዬ!!!

መግለጫ ቃል ባጣ እልፍ ዘመን ሙሉ
የብራናዬ ገፅ ግራ ገብቶት ውሉ

እየደጋገምኩኝ የፃፍኩት አንድ ቃል




ብቻ ይላል

ሌላ ቃል ተገኝቶ
ወይ ልሳንህ ፈቶ

ህቡእ በሆነ ቃል እስከምትገልፃት
ቃልህ እሷ ነችና ቃሌ ብለህ ጥራት

እናም አንች ቃሌ ነሽ ሀረግና ስንኝ
ካጠገቤ ሁነሽ ሰርክ የምትርቢኝ

እናም የኔ ንግስት

ገፅሽን አድምቄ በልቤ መዝገብ ላይ
ቃሌ ብዬ ፃፍኩሽ ቃል አጣው ቃሌ ላይ።
       
ㅤㅤየማንችለው በዛ

በሳቅ መጋረጃ ሀዘን ተደብቆ
ጥርስ ከላይ በማስመሰል ስቆ

ልብ እህ እህ ይላል በስቃይ ዋይታ
ለማለፍ ሲያጣጥር ሁሉን በዝምታ

የደረሰበትን በጥርስ ሳቅ ከልሎ
ውስጥ እረመጥ ፈጀው የማይቻል ችሎ

ላያስችል አይሰጥም ይባል ነበር ድሮ
የማንችለው በዛ እኛማ ዘንድሮ።

ㅤㅤ 🎀🎀
1
በሳቅ መጋረጃ ሀዘን ተደብቆ
Channel photo updated
Channel photo updated
እጓዛለሁ እንጂ ፦
ፊቴን ተስፋ አድርጌ እገሰግሳለሁ
ወደኋላ አልልም ለምን እቆማለሁ
ሰውን ተደገፌ ሲለቁኝ አልወድቅም
አይተውኝም ብዬ አልመፃደቅም
የሰው ልጅ ያው ሰው ነው
ዛሬ አለሁኝ ብሎ ነገ ላይን ይጠፋል
መሄድ ግን አይቆምም መኖር ይቀጥላል.........😌
👏1
.........ህልሜ........
በነፋሻው አየር ሰላም በሚሰጠው፣
በደመቀው ምሽት ውስጥን በሚያረካው፣
እኔና አንተ ሆነን ሁለታችን ብቻ፣
ፍቅርን ስንሰራ ሳይኖረን ፍራቻ፣
በውስጥህ መአዛ ባንተነትህ ውበት፣
ፍፁም ተመስጬ ለኔ ባለህ ግምት፣
ራሴን ሰጥቼህ ቅንጣቱን ሳልሰስት፣
በራሳችን ህይወት በሌላ አለም ስንኖር፣
ተቃቅፈን ባንድ አልጋ ተኝተን ስናድር፣
የነበረው ደስታ የነበረው ፍቅር፣
እንዴት ያምር ነበር ህልም ሆኖ ባይቀር???
👏2
ለምን ቢሉኝ ደርሰው ብዙ ቢጠይቁኝ፣
ተስፋ የማትቆርጪ...
እጅ የማትሰጪ...
ብለው ቢሞግቱኝ፣
መልሴ ዝምታ ነው
ቃል አይወጣም ካፌ ምንም አልናገር፣
ፅናቴን እያየ ሁሉም ይደናገር
ደግሞም ይጠይቁኝ
እንዲ እየተከፋሽ ምነው አታነቢም ምንድነው ፈገግታሽ?
እንዲ እየተበደለሽ ፍርድ አትጠይቂም ወይ ምንድነው ዝምታሽ?
ይበሉኝ ደጋግመው ሌላ ሌላም ካለ ዘለፋው ይፋፋም፣
ያኔም ቢሆን እኔ ፈገግታ ነው መልሴ ካፌ ቃል አይወጣም፣
ዛሬ ለኔ ባይሆን እንደመሸ አይቀርም
ቀን እኮ ባዳ ነው፣
ለዚ ለዚ ጊዜ ከፈገግታ ጋራ መልሴ ዝምታ ነው፣
ለምን? ቢሉኝ ደርሰው፤
ጊዜው ይርዘም እንጂ ለሁሉም ቀን አለው።።።
👏1
እኔ እወድሻለሁ
ብዙ ሺህ ዘመናት
እልፍ አዕላፍ ሌሊት
ሚሊዮን መሰለኝ
ፍቅሬ አንችን ስወድሽ ቀኑ ረዘመብኝ።
እኔ እወድሻለሁ
የሰማይ መሬቱን
የባህር ስፋቱን
የዓለም ዳርቻ የርቀቱን ያህል
እንደ ፅጌ-ረዳ
እንደ አደይ አበባ
እንደሎሚ ሽታ።
እንደእጣን ጢስ እንጨት፥ እንደከርቤ ብርጉድ፥ እኔ እወድሻለሁ፥
                      አበባ እንዳየ ንብ።
እንደቢራቢሮ ጫካ እንደሚያስሰው
ፍቅርሽን በፍቅሬ በፍቅርሽ ልቅመሰው
ማር ወለላዬ ነሽ ከረሜላ ስኩዋር
አማርኛ አይበቃ፤
           ወይጉድ!
                    ባለም ቁዋንቁዋ ሁሉ ቢወራ ቢነገር፥
እኔ እወድሻለሁ
                      እንደማታ ጀንበር።
እንደ ጨረቃ ጌጥ፥
        እንደንጋት ኮከብ፥
                    እኔ እማልጠግብሽ
ስወድሽ፥ ስወድሽ፥ ስወድሽ፥ ስወድሽ።
ጡት እንዳየ ህፃን ወተት እንዳማረው
ጠጋ በይ ዘመዴ አፍሽ ሀይወቴ ነው።
ጣይ እንዳየ ቅቤ
           ገላዬ ገላሽን ሲነካ የሚያልቀው፥
አፈር መሬት ትቢያ ወሃ እንደሚበላው፤
ፍቅሬ አንቺን ስወድሽ
          ብዙ ሺህ ዘመናት
እልፍ አዕላፍ ሌሊት
እኔ እወድሻለሁ፤
አይኖችሽን ባይኔ ተዳክሜ እያየሁ
ስወድሽ ስወድሽ
          እኔ እወድሻለሁ።
       
🔥21
ዝም የምንለው የምናወራው አተን ሳይሆን ውስጣችንን ለማዳመጥ ነው
🙏2👍1
Channel photo updated
Live stream finished (44 days)
እኔ እኮ በአንተ ደስተኛ ነኝ መኖርህ የሚያኖረኝ
በአንተ መኖር ውስጥ ደስታን የማገኝ የግል ግዛቴ ነህ
ምን ቢረዝም ነው ቁመቱ
ምን ቢተልቅ ነው እርቀቱ
ፍቅር የሚሉት ሀያል
እኔ ደርሼ ሳልይዘው
እሱም ሳይዘኝ መቅረቱ

ወደድኩ ብዬ ሳስብ
አፈቀርኩ ብዬ ሳምን
ተራ ስሜት ነው ሚሰማኝ
ወዲያው ገንፍሎ ሚሰክን

ግን ምን አይነት ነው ቀለሙ
አቋሙስ እንዴት ነው ከቶ
አንዴ ከያዘ ማይለቀው
ከገባ በርን አንኳኩቶ

ስንቶች የሚሞቱለትና
ስንቶች በሱ የሚኖሩበት
ምን አይነት ስልጣን ቢይዝ ነው ?
ፍቅር ለሚባል ጀግና አለም የሚገዛለት??
እማ ዋሽተሺኛል😔

የኑሮ ሁኔታ ካቅምሽ በላይ ሆኖ
ህመሙ ጭንቀቱ ሲጽናብሽ ገኖ
በተሰበረ ልብ ካይንሽ ዕንባ ሲፈስ
ማይጠገብ ፊትሽ ባዘን ሲደፈርስ
     
          ምን ሆነሽ ነው ብዬ ያኔ ስጠይቅሽ
           ጽጕሬን እየዳበሽ እንዲ ነበር መልስሽ
        ፊቴን ታጥቤ ነው ለምን አለቅሳለው
         አንተ ካለህልኝ ሁል ጊዜ ስቃለው
 
   ብለሽ ዋሽተሺኛል እኔ እንዳልከፋ እንደዛ በለቅሶ አይንሽ እየጠፋ

ውስጥሽ የተጎዳ ክፉኛ እያመመሽ
ደናነኝ አታስብ እርሺው ትዪኛለሽ
ግን ልጅነት ሆኖ አምንሻለው ቶሎ
ከቅፍሽ ስገባ እጅሽ እንኳን ዝሎ

        ደግሞም አይቻለው ከሆድሽ አጉድለሽ   
        ጥራጊ ስትበዪ  እኔን ጥግብ አርገሽ
           ለምንስ ዋሸሺኝ ለምንስ ደበቅሺኝ
            እንደዛ እየክፋሽ ደስተኛ ነኝ አልሺኝ

እርቦሽ ሳትበዬ አንጀትሽም ታጥፎ
እኔን አብልተሻል ከጥጋብም አልፍ
ከህመምሽ በላይ ሚያሳስብሽ ነገር
ስለኔ ደስታ ነው ሳልከፋ እንድኖር

         ባይኖርሽ እንኩዋን ከሰው ተበድረሽ
           አንሼ እንዳልታይ ሁሉን ታደርጊያለሽ
            እስካለሽ እስካለሁ
             እምዬ ሁል ጊዜ ደምቄ እታያለሁ
            አንቺ እኮነሽ ወዜ😚

ባንቺ ፈገግታ ውስጥ እኔ እንድበራ
ስንት ጊዜ ስቀሻል ሆነሽ በመከራ
ቢከፋሽ ለብቻሽ ደብቀሽ ሸሽገሽ
እማዋሽተሺኛል እያነባሽ ስቀሽ

    
#እናቱን የሚወድ ይሄንን ግጥም ያንብላት 👏