የዋህ ስትሆኑ ትጎዳላችሁ ብልጥ ስትሆኑ እራሳችሁን ታታልላላችሁ ሰው ጀል ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ከእናንተ በላይ ጅል የለም እናም ወዳጄ ብልህ ከሆናችሁ የራሳችሁን መድረሻ ታገኛላችሁ
የትላንት ውሎዩን ላስቀኛችሁ እኔ በተመሳሳይ ህይወት ከአንዴም ሁለቴ ጎድተውኝ ለሶስተኛ ግዜ እድል ስጪኝ አሉኝ ቆይ በዚህ ውስጥ ማነው እራስ ወዳድ
እራሴን ከማንም ጋር አላወዳድርም እኔን መሆን ስለማይችሉ በፈለጉት መንገድ ይረዱኝ እራሴን ለእነሱ የማብራራበት አቅም የለኝም ምክንያቱም እራሴን እራሱ አላቀውም 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹መልካም ቀን 🌹🌹🌹
ዳስ ጣል (አንሳው)
ዳስ ጣል ልቤ፣ ለውስጤ ሀዘን ለቅሶ
ሰው አይችልህ ደርሶ
አለ ጊዜ፣ ገና ነው እያልኩት
እራሴን በደልሁት
ለካ እንዲህ ነው ማለቅ፣ እህ እያሉ ነዶ
ሀገር የሞተበት፣ የት ያለቅሳል ሄዶ?
ዳስ ጣል
ዳስ ጣል
ዳስ ጣል ልቤ
ለውስጤ አዘን ለቅሶ
ሰው አይችልህ ደርሶ
አለ ጊዜ፣ ገና ነው እያልኩት
እራሴን በደልሁት
ለካ እንዲህ ነው ማለቅ፣ እህ እያሉ ነዶ
ሀገር የሞተበት፣ የት ያለቅሳል ሄዶ?
ዳስ ጣል
ዳስ ጣል
አክሱም ላሊበላን፣ በአንድ አለት አጽንቶ
አልራመድ አለ፣ ሀገር ተለያይቶ
ምሰሶው ዘመመ፣ ጣራውም ያፈሳል
ሀገር የሞተበት፣ የት ሄዶ ያለቅሳል!
ባሳደገኝ ቅየ፣ ባደኩበት መንደር
ባይተዋር ሰው ሁኜ፣ እንደሌለው ሀገር
ያቆምኋትን ሰንደቅ፣ ተፈትኜ በእሳት
እንዴት አቀርቅሬ፣ ባንዲራዬን ላንሳት
አባይ ለዘዴው፣ በአፍ ይቀድማል
አምኖ መከዳት፣ እንዴት ያማል
ወርቅ ያበደረ ደርሶት አለት
እንዴት ይችላል ዝም ማለት
ከነገ ዛሬ፣ ይሻል ባልኩኝ
የራሴን ጩኸት፣ ተነጠቅኩኝ
ተጣላሁና ከወንዜ አድባር
እንዴት ልታረቅ፣ ከራሴ ጋር
አዲስ አበባ፣ አዶ ሸገሩ
እንኳን ሸገሩ
የሁሉ አይደል ወይ? ሞላው ሀገሩ
በፍቅር ጠርተው፣ ከዳር እስከ ዳር
መሃል ገቡና፣ አቆሙን ከዳር
ባቆዩት ሀገር፣ ጀግኖች በአንድነት
በአርበኝነት
እንዴት ይገፋ፣ ኢትዮጵያዊነት
ኧ . . .ኧ . . ና ና
ባቆዩት ሀገር ፣ ጀግኖች በአንድነት
እንዴት ይገፋል፣ ኢትዮጵያዊነት🌹🌹
ዳስ ጣል ልቤ፣ ለውስጤ ሀዘን ለቅሶ
ሰው አይችልህ ደርሶ
አለ ጊዜ፣ ገና ነው እያልኩት
እራሴን በደልሁት
ለካ እንዲህ ነው ማለቅ፣ እህ እያሉ ነዶ
ሀገር የሞተበት፣ የት ያለቅሳል ሄዶ?
ዳስ ጣል
ዳስ ጣል
ዳስ ጣል ልቤ
ለውስጤ አዘን ለቅሶ
ሰው አይችልህ ደርሶ
አለ ጊዜ፣ ገና ነው እያልኩት
እራሴን በደልሁት
ለካ እንዲህ ነው ማለቅ፣ እህ እያሉ ነዶ
ሀገር የሞተበት፣ የት ያለቅሳል ሄዶ?
ዳስ ጣል
ዳስ ጣል
አክሱም ላሊበላን፣ በአንድ አለት አጽንቶ
አልራመድ አለ፣ ሀገር ተለያይቶ
ምሰሶው ዘመመ፣ ጣራውም ያፈሳል
ሀገር የሞተበት፣ የት ሄዶ ያለቅሳል!
ባሳደገኝ ቅየ፣ ባደኩበት መንደር
ባይተዋር ሰው ሁኜ፣ እንደሌለው ሀገር
ያቆምኋትን ሰንደቅ፣ ተፈትኜ በእሳት
እንዴት አቀርቅሬ፣ ባንዲራዬን ላንሳት
አባይ ለዘዴው፣ በአፍ ይቀድማል
አምኖ መከዳት፣ እንዴት ያማል
ወርቅ ያበደረ ደርሶት አለት
እንዴት ይችላል ዝም ማለት
ከነገ ዛሬ፣ ይሻል ባልኩኝ
የራሴን ጩኸት፣ ተነጠቅኩኝ
ተጣላሁና ከወንዜ አድባር
እንዴት ልታረቅ፣ ከራሴ ጋር
አዲስ አበባ፣ አዶ ሸገሩ
እንኳን ሸገሩ
የሁሉ አይደል ወይ? ሞላው ሀገሩ
በፍቅር ጠርተው፣ ከዳር እስከ ዳር
መሃል ገቡና፣ አቆሙን ከዳር
ባቆዩት ሀገር፣ ጀግኖች በአንድነት
በአርበኝነት
እንዴት ይገፋ፣ ኢትዮጵያዊነት
ኧ . . .ኧ . . ና ና
ባቆዩት ሀገር ፣ ጀግኖች በአንድነት
እንዴት ይገፋል፣ ኢትዮጵያዊነት🌹🌹
እምዬ እናቴ
የኔ የግል ሀብቴ
ተቀምጠሽ ከጎኔ
እያየውሽ ባይኔ
ላኑርሽ ዘላለም ህይወቴ ነሽ ለኔ
ስታዘዝሽ ልኑር
ህይወቴ እንዲሰምር
ምክርሽ ህይወቴ ነው
ቁጣሽ ተስፋዬ ነው
ደስታሽ አለሜ ነው
እምዬ አበባዬ ካንቺ ጋራ ኖሬ
ምንም ሳልደብቅሽ የውስጤን ዘርዝሬ
ሀዘኔን ደስታዬን ላንቺ ተናግሬ
ልኑር ካንቺ ጋራ
ህይወቴ እናቴ
የኔ የግል ሀብቴ
ተቀምጠሽ ከጎኔ
እያየውሽ ባይኔ
ላኑርሽ ዘላለም ህይወቴ ነሽ ለኔ
ስታዘዝሽ ልኑር
ህይወቴ እንዲሰምር
ምክርሽ ህይወቴ ነው
ቁጣሽ ተስፋዬ ነው
ደስታሽ አለሜ ነው
እምዬ አበባዬ ካንቺ ጋራ ኖሬ
ምንም ሳልደብቅሽ የውስጤን ዘርዝሬ
ሀዘኔን ደስታዬን ላንቺ ተናግሬ
ልኑር ካንቺ ጋራ
ህይወቴ እናቴ
❤2
አንዳንዴ እኮ የውስጥን ቃል ለመናገር ይከብዳል ብቻ የውስጥን ጩኸት እንዴት መደበቅ ይቻላል ብቻ ሁሌም ብቻዬን መሆኔ ያስገርመኛል እኔ ማነኝ መፈተኔስ ለምን በዛ ዙሪያዬ እንደ ገደል ማሚቱ በውሸት እንዴት ተከበብኩ ያልፋል እያልኩ እራሴን እንዴት ላታለው ኡፍ አሁንስ ስልችት አለኝ ምክንያት ያጣ ህይወት ደህና ነኝ ብዬ መሳቅ ስጀምር መልሼ መታመሜ ልቤ በቃ መከራህን ላበዛችብህ ነፍሴ ይቅርታ
አንዳንዴ እኮ እውነትን ይዘን ስንሄድ ፍቅር እያልን ለእውነት ስንኖር ጉዳቱ ሲበዛ ያማል ግን የውሸት አለሁ እያላችሁ ሰው የምትጎዱ ሰወች እኔም እንደናንተ የውሸት ፍቅር ፍቅር ባልኩኝ ቆይ ግን ማፍቀር ሀፂያት ነውለአፈቀሩት መኖር ጅልነት ነው አልገባኝም ፍቅር ምንድን ነው እንዴት ነው ነገሩ
ወዳጄ ለራስህ በመታመን የምታገኘው ሰላም ወደር የለውም ፍቅር ከውሸት የራቀ ነው ነገን ተስፋ በማድረግ ነው ሁለት ሆኖ እንደ አንድ መኖር ነው
ግን እኛ በማስመሰል የምናገኘውን ደስታ መርጠሀናል አይ ግዜ
ወዳጄ ለራስህ በመታመን የምታገኘው ሰላም ወደር የለውም ፍቅር ከውሸት የራቀ ነው ነገን ተስፋ በማድረግ ነው ሁለት ሆኖ እንደ አንድ መኖር ነው
ግን እኛ በማስመሰል የምናገኘውን ደስታ መርጠሀናል አይ ግዜ







