በሳቄ ሸፈንኩት
172 subscribers
3 photos
8 videos
4 links
Download Telegram
Channel photo updated
ሰላም ነህ አልልህ አንተ የለህ ከኔ
ደግሞ ትናፍቀኛለህ ካላንተ የማልሆር እኔ
ብቻ ትዝታህ ወደኋላ እየመላለሰኝ
አንዴ ሄድኩ ስል ከመንገድ ሊያስቆመኝ
ወይ የለህ ከኔ ወይ አልኖርኩ ለኔ
ብቻ መመላለስ ከራስ ጋር መታገል ሆኖብኛል ለኔ
በል ልሸኝህ ስቄ በፍቅር ልሸኝህ ከአይኔ
ላውጣህ ደግሞ ከልቤ በል አንተም ሂድ
እኔም ሰላም ላግኝ ትተው የሀሳብ መንገድ
አትሁን አለሜ አርቄ ልቅበርህ ልሸኝህ በፍቃድ
እኔስ በቃሀኝ ስትሄድ ስትመጣ
ብቸኝነትን አስለመድከኝ ልሁንልህ ለብቻዬ
እኔው ለኔ ብዬ ልኑር ለብቻዬ
Live stream started
በሳቄ ሸፈንኩት
Live stream started
😍 ᴠᴏɪᴄᴇ ᴄʜᴀᴛ sᴛᴀʀᴛᴇᴅ 🥳
የዋህ ስትሆኑ ትጎዳላችሁ ብልጥ ስትሆኑ እራሳችሁን ታታልላላችሁ ሰው ጀል ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ከእናንተ በላይ ጅል የለም እናም ወዳጄ ብልህ ከሆናችሁ የራሳችሁን መድረሻ ታገኛላችሁ
የትላንት ውሎዩን ላስቀኛችሁ እኔ በተመሳሳይ ህይወት ከአንዴም ሁለቴ ጎድተውኝ ለሶስተኛ ግዜ እድል ስጪኝ አሉኝ ቆይ በዚህ ውስጥ ማነው እራስ ወዳድ
እራሴን ከማንም ጋር አላወዳድርም እኔን መሆን ስለማይችሉ በፈለጉት መንገድ ይረዱኝ እራሴን ለእነሱ የማብራራበት አቅም የለኝም ምክንያቱም እራሴን እራሱ አላቀውም 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹መልካም ቀን 🌹🌹🌹
ዳስ ጣል (አንሳው)

ዳስ ጣል ልቤ፣ ለውስጤ ሀዘን ለቅሶ
ሰው አይችልህ ደርሶ
አለ ጊዜ፣ ገና ነው እያልኩት
እራሴን በደልሁት

ለካ እንዲህ ነው ማለቅ፣ እህ እያሉ ነዶ
ሀገር የሞተበት፣ የት ያለቅሳል ሄዶ?

ዳስ ጣል
ዳስ ጣል

ዳስ ጣል ልቤ
ለውስጤ አዘን ለቅሶ
ሰው አይችልህ ደርሶ
አለ ጊዜ፣ ገና ነው እያልኩት
እራሴን በደልሁት
ለካ እንዲህ ነው ማለቅ፣ እህ እያሉ ነዶ
ሀገር የሞተበት፣ የት ያለቅሳል ሄዶ?

ዳስ ጣል
ዳስ ጣል

አክሱም ላሊበላን፣ በአንድ አለት አጽንቶ
አልራመድ አለ፣ ሀገር ተለያይቶ

ምሰሶው ዘመመ፣ ጣራውም ያፈሳል
ሀገር የሞተበት፣ የት ሄዶ ያለቅሳል!

ባሳደገኝ ቅየ፣ ባደኩበት መንደር
ባይተዋር ሰው ሁኜ፣ እንደሌለው ሀገር

ያቆምኋትን ሰንደቅ፣ ተፈትኜ በእሳት
እንዴት አቀርቅሬ፣ ባንዲራዬን ላንሳት

አባይ ለዘዴው፣ በአፍ ይቀድማል
አምኖ መከዳት፣ እንዴት ያማል

ወርቅ ያበደረ ደርሶት አለት
እንዴት ይችላል ዝም ማለት

ከነገ ዛሬ፣ ይሻል ባልኩኝ
የራሴን ጩኸት፣ ተነጠቅኩኝ
ተጣላሁና ከወንዜ አድባር
እንዴት ልታረቅ፣ ከራሴ ጋር

አዲስ አበባ፣ አዶ ሸገሩ
እንኳን ሸገሩ
የሁሉ አይደል ወይ? ሞላው ሀገሩ

በፍቅር ጠርተው፣ ከዳር እስከ ዳር
መሃል ገቡና፣ አቆሙን ከዳር

ባቆዩት ሀገር፣ ጀግኖች በአንድነት
በአርበኝነት
እንዴት ይገፋ፣ ኢትዮጵያዊነት

ኧ . . .ኧ . . ና ና

ባቆዩት ሀገር ፣ ጀግኖች በአንድነት
እንዴት ይገፋል፣ ኢትዮጵያዊነት🌹🌹
Channel photo updated
አንዳንድ 😐ሰዎች ዛሬን የሚያስደስታቸውን🌟 ሲያገኙ
ትላንት መስዋት የሆነላቸውን ይረሳሉ!
Channel photo updated
Channel photo updated
Live stream finished (14 days)
በሳቄ ሸፈንኩት
Live stream finished (14 days)
😕 ᴠᴏɪᴄᴇ ᴄʜᴀᴛ ᴇɴᴅᴇᴅ 💔
እምዬ እናቴ
የኔ የግል ሀብቴ
ተቀምጠሽ ከጎኔ
እያየውሽ ባይኔ
ላኑርሽ ዘላለም ህይወቴ ነሽ ለኔ
ስታዘዝሽ ልኑር
ህይወቴ እንዲሰምር
ምክርሽ ህይወቴ ነው
ቁጣሽ ተስፋዬ ነው
ደስታሽ አለሜ ነው
እምዬ አበባዬ ካንቺ ጋራ ኖሬ
ምንም ሳልደብቅሽ የውስጤን ዘርዝሬ
ሀዘኔን ደስታዬን ላንቺ ተናግሬ
ልኑር ካንቺ ጋራ
ህይወቴ እናቴ
2
Channel photo updated
Channel photo updated
Channel photo updated
አንዳንዴ እኮ የውስጥን ቃል ለመናገር ይከብዳል ብቻ የውስጥን ጩኸት እንዴት መደበቅ ይቻላል ብቻ ሁሌም ብቻዬን መሆኔ ያስገርመኛል እኔ ማነኝ መፈተኔስ ለምን በዛ ዙሪያዬ እንደ ገደል ማሚቱ በውሸት እንዴት ተከበብኩ ያልፋል እያልኩ እራሴን እንዴት ላታለው ኡፍ አሁንስ ስልችት አለኝ ምክንያት ያጣ ህይወት ደህና ነኝ ብዬ መሳቅ ስጀምር መልሼ መታመሜ ልቤ በቃ መከራህን ላበዛችብህ ነፍሴ ይቅርታ
Channel photo updated
Channel photo updated