ONLY ARSENAL
445 subscribers
116 photos
14 videos
12 links
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

💥የዝዉዉር ዜና
💥የአሰልጣኞች አስተያየት
💥ጎሎች እና አዝናኝ ቪዲዮዎች
💥የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
💥ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
Download Telegram
🔝ኤምሬ በሰሜን ለንደን ደርቢ ላይ ስለ ሚኖረው 3ቱ የፊት ለፊት ጥምረት ላይ ፍንጭ ሰጥተዋል ፡፡

በዋናነት ከተነሱት ነጥቦች መካከል :-
🔜 ስለ 3ቱ አጥቂዎች ጥምረት::
🔜 ስለ ላካዜቲ አካል ብቃትና::
🔜 ስለ ሌሎች አማራጭ ተጨዋቾች::

• ኤምሬ.... ላካዚት በቁርጭምጭሚቱ ላይ ጉዳት ከደረሰ በኋላ የአካል ብቃት እንቅስቃሴውን በእጅጉ እንዳሻሻለ ተናግረዋል......ስለዚህም ከኦባ እና ከፔፔ ጎን ለጎን የመጀመር እድሉ አለው....ውሳኔም የሚሆነው በጨዋታው ዕቅድ አሰላለፍ ላይ የተመሠረተ ነው።
ከ አንፊዱ የ 3-1 ሽንፈት በኋላ ብዙ ተንታኞች(Pundits) ኡናይ ኤምሬን ከጅምሩ አሌክስ ላካዜትን ባለማስገባታቸው በነገር ሲውርፏቸው ሰንብተዋል ፡፡

• ስፔናዊው አሰልጣኝ ከሊቨርፑል ጋር የበለጠ ጥንቃቄ የተሞላበትን አካሄድ መርጠዋል.....ይልቁም ዳኒ ሴባሎስን በ ቋሚ 11 ውስጥ የፈረንሣዊውን ቦታ ሰጥተውታል ፡፡ አለቃውንም የኦባ ፣ ላካ እና የፔፔ ሦስቱ ተጣምረው ሊጀመር ይችሉ እንደሆን በፕሬስ ኮንፈረንስ ተጠይቀዋል

• "አዎ...! ነገር ግን ትንሽ ተረጋጉ በእያንዳንዱ ውሳኔዬ እንዴት እንደሚሆን እያሰላሰልኩ ነው ፡፡ ለምሳሌ ላካዜት ቁርጭምጭሚቱ ላይ ጉዳት ነበረበት...ይህ ሳምንት ግን ካለፉት ሶስት ሳምንታት ጥሩው ሳምንት ነው ፡፡"
“እሱ እየተሻሻለ ነው እናም በቁርጭምጭሚቱ ላይ ጥሩ ስሜት እየተሰማው ነው አሁን በጣም ደህና ነው ፡፡

• ከፔፔ ጋር ከሌሎቹ ሁሉ በኋላ ነው ወደዚህ የመጣው ነገር ግን በእያንዳንዱ ግጥሚያ ላይ እየተሻሻለ ነው ፡፡

• ኦባምያንግ ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው በመጀመሪያዎቹ ሁለት ግጥሚያዎች ሁለት ግቦችን አስቆጥሮልናል በሊቨርፑል ውስጥ ሁለት ወይም ሶስት ጥሩ ተግባሮች ነበሩት ፡፡
ለእኔ በጣም አስፈላጊው ነገር ዕድሎች መኖራቸው እና እንደ ኦቤሜንግን ፣ ላካዚዜ ፣ ፔፔ ፣ ሚኪ፣ ኔልሰን፣ ሴባሎስና ፣ኦዚል ፣ ከኋላ ካሉ በተለያዩ ተጫዋቾች ጎሎችን አስቆጥረን ነጥብ መያዝ እንችላለን ፡፡

• እነርሱ አብረው ሊጀምሩም ይችላሉ ብዬ አስባለው እናም በጨዋታ ጊዜ እነሱ 3ቱም ተናበው መጫወት ይችላሉ.....ነገር ግን ይሄ ሁሉ ሊሆን የሚችለው የጨዋታውን ታክቲክ(ስልት) በምንወስንበት መንገድ ላይ የተመሠረተ ነው....እኔም ያ ይሆናል ብዬ በጣም ተስፋ አደርጋለሁ .........ነገር ግን እነዚያን ሶስት ተጫዋቾች ብቻ ሳይሆኑ ኔልሰን ፣ ሚክተንያን ፣ ዊሎክና ፣ ኦዚል አሉን ስለእዚህ እኛም የተሻሉ ውሳኔዎችን መወሰን መቻል አለብን ፣ • ከሁሉም በላይ ግን ከተጫዋቾቹ ውስጥ የተለያዩ አማራጮች እንዲኖሩን ማድረግ አለብን ፡፡

@onlyarse
አርሰናል ከ ቶተንሃም

በዕለተ ሰንበት ዕሁድ

ከምሽቱ 12:30 ሲል ይጀምራል፣


የአርሰናል እና የቶተንሃም ጠላትነት፣

የደርቢው ትንቅንቅ ጅማሮ፣

ታሪካዊ መነሻውስ ?

ከክፍል ሁለት የቀጠለ፣

አብራችሁን ሁኑ፣


👉የሰሜን ለንደን ደርቢ ታሪክ፣ ኬት ተጀመረ፣ አለማችን ላይ ከፍተኛ ትኩረት ከሚሰጣቸው የአንድ ከተማ ቡድኖች የደርቢ ትንቅንቆች ውስጥ፣ አንዱ የሆነው ኖርዝ ለንደን ደርቢ መነሻው በ 18ተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ነዉ፣ ያኔ አርሰናል በደቡብ ለንደን ነበር መቀመጫዉ፣ በ 1913 ላይ ግን መድፈኞቹ ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ ሰሜን ለንደን አመሩ፣ በ 4 ማይል እርቀት ብቻ ሃይበሪን ከ ኋይትህርትሌን አፋጠጡ፣

ነገሩ የቶተንሃም ክለብን አበሳጨ ሰሜን ለንደን በእግርኳስ የማያውቁት ባላንጣ ብቅ ያለባቸው ስፐርሶች በግዛታቸው መቶ የተጋፋቸውን አርሰናልን ይጠሉ የጀመሩት ወቅት የተቀናቃኝነቱ መንፈስ ጅማሮ፣

በ 1913 አርሰናል ወደ ሰሜን ለንደን ካቀና ቦሀላ፣ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከቶተንሃም አካሄደ መድፈኛው ያኔ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ነበር፣ ቶተንሃም ደግሞ በመጀመሪያው መድረክ ይገኛል፣ ኋይትህርትሌን ላይ የተገናኙት ሁለቱ ጎሮቤታሞች ከአንደኛው አለም ጦርነት በፊት ያካሄዱት ጨዋታ፣ ነጭ ለባሾቹን በማያስደስት ሁኔታ ተጠናቀቀ፣ አርሰናል 5-1 አሸነፈ፣

አዲስ የቅርብ ጊዜ ባላንጣ ያዉም በነገሱበት ግዛት ብቅ ያለባቸው የቶተንሃም ደጋፊዎች፣ የአርሰናልን ዕድገት ለማቀጨጭ ያሴሩም ጀመር ሆኖም በጊዜው የነበሩት ባለስልጣናት ከአርሰናል ጎን ቆሙ፣

አርሰናል ወደ ሀገሪቱ ከፍተኛ ዲቪዚዮን እንዲቀላቀል፣ መንገድንም ጠረጉለት በመሀል ግን የአንደኛው አለም ጦርነት ጅማሮ ኳሱ ላይ ተፅዕኖ አሳደረ፣ ጦርነቱ የክለቦቹን እንቅስቃሴ አደበዘዘ፣

በ 1921 አርሰናል እና ቶተንሃም በተዳከመ መንፈስ ተገናኙ፣ አሁንም ጨዋታው ኋይትህርትሌን ላይ ነበር፣ አርሰናል 2-1 አሸነፈ ከአንደኛው አለም ጦርነት ሀንጎቨራቸዉ ሳይወጡ የተቀናቃኝነት መንፈሱን እንደያዙት፣ እግርኳስን በሰሜን ለንደን ከተማ ለማሳደግ የተንቀሳቀሱት አርሰናል እና ቶተንሃም፣

በሁለተኛው አለም ጦርነት ህልውናቸውን በሚፈታተን መልኩ ድባቅ ተመቱ፣

በመጥፎዉ ዘመን ግን ተቀናቃኞቹ የጥላቻ ጉዟቸውን ወደጎን በመተው፣ እርስበርስ ተረዳዱ በግዜው በጦርነቱ ምክንያት ክፉኛ የተጎዳው ሃይበሪ፣ ኳስ ጨዋታን ማካሄድ ተሳነው፣ በ 4 ማይል እርቀት የጎረቤታቸውን አርሰናልን ችግር የተረዱት ቶተንሃሞች፣ ነግ በኔ በሚል ሜዳቸው ኋይትህርትሌንን አርሰናል እንዲጫወትበት ፈቀዱ፣

የሁለተኛው አለም ጦርነት ቀውስ፣ የሰሜን ለንደን ባላንጣዎችን የለየለት ተቀናቃኝነት ቢያሻሽለውም፣ ጠላት ያው ጠላት ነዉ እንዲሉ፣ አርሰናል እና ቶተንሃም ከጦርነቱ ፍፃሜ ማግስት፣ የሃይል ሚዛኑን ለመድፋት ይዋደቁ ጀመር፣


👉ክፍል ሦስት ይቀጥላል..
"SHARE" @onlyarse
​​√በቶተንሃም ቤት ጉዳቶች እየተባባሱ እየሄዱ ነው ቶተንሀም ለኤምሬትሱ ጉዞ የተከላካዮች ጉዳት እራስ ምታት ሆኖባቸዋል::
·
የቶተንሀም አለቃ ማውሪሲሆ ፖቸቲንሆ እሁድ በሰሜን ለንደን በሚደረገው ፍልሚያ ላይ የቀኝ መስመር ተከላካዩ ኬይል ዎከር-ፒተርስ ከደረሰበት የጡንቻ መሳሳብ ጉዳት ለማገገም እለመቻሉ አሳስቧቸዋል ፡፡
·
የእሱ መጎዳት የፖቼትኖን አማራጮች በጣም ያጠቡታል ተብሏል...........፣ በዚህ ዓመት በቀኝ መስመር ተከላካይነት እንዲጫወት የታሰበው ጁዋን ፎይም (Foyth) እንዲሁ በቅድመ-ውድድር ወቅት ቁርጭምጭሚቱ ላይ ጉዳት ስለደረሰበት እርሱ ደግሞ እስከ International break ላይመለስ ይችላል::
·
ሰርጌ ኦሪየር እስከዚያ ጊዜ ድረስ ይቆያል እናም ሰኞ የአውሮፓን የዝውውር ቀነ-ገደብ ከማለቁ በፊት ለመልቀቅ ዝግጁ ነው ስለዚህ ፖቼቲኖ ኢቪጎሪያን ለመጥራት ፈቃደኛ አልሆነም ፡፡
·
ስለሆነም እእሰልጣኙ በበኩላቸው ፊታቸውን ሙሳ ሲሶኮ ሊመለሱ ይችላሉ...በባለፈው የ ኒውካስትል ጨዋታ 1-0 በተሸነፉበት ለ 30 ደቂቃ ያህል ቦታውን(ቀኝ-ተከላካይ) ሸፍኖ ተጫውቷል የ ኤሪክ ዳየርም ነገር አለየለትም የአስልጥይኙን ውሳኔ ይጠብቃል::
·
የአርጀንቲናዊው ውሳኔ በኒውካስትል የታፋ ጉዳት ባስተናገደው ታንጉይ ንዶምቤሌ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይችላል ፡፡
·
ደሌ አሊ ከጡንቻ መሳሳብ ውጥረት ችግር በኋላ ወደ ሙሉ ስልጠና ተመልሰዋል እናም ለመጀመሪያ ጊዜ ሊሰለፍ ይችላል ግን ራያን ሴሴኒዮን በ(Hamstring) ቋንጃ ጉዳት ምክንያት አሁንም እይደርስም ነው ፡፡
·
ይህ በእንዲህ እንዳለ ክለብ ብሩዥ በዚህ ሳምንት የቪክቶር Wanyamaን ስምምነቱን ለማጠናቀቅ ተስፋ በማድረግ ላይ ናቸው::
·
ስለዚህም እሁድ በሰሜን ለንደን የ ሚደረገውን የሁለቱ ታሪካዊ ተቀናቃኞች ፍልሚያ ወደ አርሰናል ያደላ ነው እየተባለ ነው ነገር ግን በአርሰናል በኩል ሁልጊዜም አዳዲስ አሰላለፍ እና 11 ይዝእው ብቅ የሚሉት አሰልጣኙ በሚወስኑት ውሳኔም ጨዋታው ይወሰናል::
@onlyarse
4ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ

ሰሜን ለንደን ደርቢ

🔴አርሰናል Vs ቶትንሃም⚪️
ሠዓት 12:30
🏟ቦታ ኤምሬት ስታዲየም

⚽️የቡድን ዜና
:
:
☞በመድፈኞቹ በኩል ለረጅም ጊዜ ጉዳት ላይ የነበረው ሄክቶር ቤለሪን እና አዲሱ ፈራሚ ኬሪን ቴርኔይ ጉልበታቸው ላይ፣ ዲኖስ ማቭሮፓኖስ በቁርጭምጭሚቱ ላይ ባጋጠማቸው ጉዳት ከዛሬው ጨዋታ ውጭ ናቸው [ሶስቱም ተጫዋቾች በመስከረም መጨረሻ ላይ ወደ ሙሉ ልምምድ ይመለሳሉ]
:
:
☞እንዲሁም ሮብ ሆልዲንግ እና ስሚዝ ሮው በሳምንቱ መጨረሻ ከ 23 እና 21 አመት በታች ቡድን ጋር ለ 90 ደቂቃ መጫወት ችለዋል።
:
:
☞ኦናይ ኤምሬ ሜሱት ኦዚል ከእኛ ጋር ይቆያል ሲሉ ማረጋገጫ እንደሰጡ ከዚህ በፊት መረጃውን አቅርበናል፣
"በቦታው ላይ ጠንክሮ ሰርቶ ጥሩ ነገር እንደሚያሳየን አምናለሁ" ብለዋል።

▪️በሁለቱ ክለቦች መካከል ያሉ እውነታዊ መረጃዎችን ልጠቁማችሁ።
:
:
☞አርሰናል ቶትንሃምን በገጠመበት ካለፉት 10 ጨዋታዎች ውስጥ ማሸነፍ የቻለው ሁለቱን (2) ብቻ ነው፣ [2 አሸነፈ, 5 አቻ ሲለያይ, 3 ተሸንፏል] ሁለቱንም ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ በኤምሬትስ ነው።
:
:
☞ቶትንሃም ከአርሰናል ጋር በኤምሬት ካደረጋቸው 26 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ (1) ብቻ ነው [ 1አሸነፈ 10አቻ 15 ሽንፈት] በኤምሬትስ ለመጨረሻ ጊዜ ያሸነፈው እኤአ 2010 ላይ 2–0 ከመመራት ተነስቶ 2–3 ማሸነፍ የቻሉት
:
:
☞በአርሰናል እና ቶትንሃም መካከል ከተቆጠሩት የመጨረሻዎቹ 14 ግቦች ውስጥ አምስቱ (5) ግቦች የተቆጠሩት በፍፁም ቅጣት ምት ነው [በሊጉ ታሪክ ኤቨርተን እና ኒውካስትል ዩናይትድ ሲገናኙ ብዙ ፔናሊቲ ግብ የተቆጠረባቸው ጨዋታ የሁለቱ ክለቦች ነው 18 ፍፁም ቅጣት ምት ጎል በሁለቱም በኩል ተቆጥሯል።
:
:
☞ሃሪ ኬን በሰሜን ለንደን ደርቢ ካደረጋቸው ያለፉት ዘጠኝ ጨዋታዎች ላይ 9 ግቦችን አርሰናል መረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል [ አርሰናል ላይ ብዙ ግብ በማስቆጠር ዋይኒ ሩኒ 12 እና ሮቢ ፎለር 10 ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል]
:
:
☞ክርስቲያን ኤሪክሰን በቶትንሃም መለያ 50ኛ ግቡን ለማስቆጠር 1 ግብ ብቻ ይቀረዋል ዛሬ ግብ ማስቆጠር ከቻለ በቶትንሃም መለያ 50 ግብ ማስቆጠር የቻለ 5ኛው ተጫዋች ይሆናል። [ ክለቡ አርሰናልን በገጠመበት ያለፉት 11 ጨዋታዎች ተሰልፎ መጫወት ቢችልም አርሰናል ላይ ኳስ እና መረብን ግን ማገናኘት አልቻለም፣ ይህም በሊጉ ካሉት ክለቦች ማስቆጠር የተሳነው አርሰናል ላይ ብቻ ነው]

የዛሬው ግምቴ 2–1 እናሸንፋለን



"SHARE" @onlyarse
ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ እኛን ከአርሰናል ጋር አታወዳድሩን ፕሮጀክታችን የተለያየ ነው፡፡ አርሰናል ባለፉት ሁለት አመታት የቡንደስሊጋውን ምርጡን አጥቂ ኦባምያንግ፡ የፈረንሳይ ሊግ ምርጡን አጥቂ ላካዜት አስፈርሟል፡ በአመቱ ፔፔን ጨምረዋል፡፡ የኛ የባለፉት አመታት ዋነኛ አጥቂያችን ኬን ነው፡ ተጠባባቂው ደግሞ የ17 አመት ታዳጊ ትሮይ ፓሮት ነው ብሏል ፖች፡፡
👉አርሰናል ወደ ሜዳ ይዞት ሚገባዉ አሰላለፍ ይፋ አርጓል።

@onlyarse
▪️የመድፈኞቹ አጥቂ ፔር ኤምሬክ ኦባምያንግ ከ ቶትንሃሙ ጎል አዳኝ ሀሪ ኬን ጋር ያለው ቁጥራዊ ንፅፅር በምስሉ የምትመለከቱትን ይመስላል።

"SHARE" @onlyarse
▫️እንግዳዉ ቡድን ቶትንሀም ሆትስፐር ቋሚ 11 አሰላለፍ።

@onlyarse
ባሁኑ ሰአት ሁለቱም ቡድኖች ወደ ሜዳ በመግባት ላይ ይገኛሉ።
🇬🇧ዛሬ ምሽት በ 4ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ሚከናወን ተጠባቂ ጨዋታ።

👉ጨዋታዉ ተጀመረ⌚️

🔴አርሰናል 0⃣ - 0⃣ ቶትንሀም
⚪️
👉'2 ደቂቃ⌚️

🔴ኒኮላስ ፔፔ ግሩም ኳስ ሹት ቢያደርግም በጎሉ አናት ላይ ወቶበታል
👉'6 ደቂቃ⌚️

⚪️ቶትንሀም ሆትስፐሮች ተደጋጊሚ ጫናዎችን እያስተናገዱ ይገኛሉ
👉'6 ደቂቃ⌚️

🔴ሜትላንድ ናይልስ ግሩም ኳስ ሹት ቢያደርግም ተደርበው አወጡበት
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በርናርድ ሌኖ የተፋዉን ኳስ ኤሪክሰን በበቀላሉ አስቆጠረ።
👉ቶትንሀም (ኤሪክሰን)⚽️