ONLY ARSENAL
445 subscribers
116 photos
14 videos
12 links
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

💥የዝዉዉር ዜና
💥የአሰልጣኞች አስተያየት
💥ጎሎች እና አዝናኝ ቪዲዮዎች
💥የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
💥ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
Download Telegram
√ህይወት ከባድ ናት እግር ኳስም አንዳንዴ ከባድ ነው፣ግን አንድ ነገር አቃለው መቼም ተስፋ አልቆርጥም እዚህ የመጣሁት ከትልቅ አላማ ጋር ነው እናም ለዛ እስከመጨረሻው እፋለማለሁ።

ደጋፊዎችን ለድጋፋችሁ እጅግ አመሰግናለሁ መቼም አልደበቅም ማሸነፍ ወይም መሸነፍ !!!

@onlyarse
Gary Nevile በሊቨርፑልና አርሰናል ጨዋታ ዙሪያ በሰጠው አስተያየት አርሰናል 3-1 ቢሸነፍም ከሽንፈቱ ባሻገር ግን ከዚህ ቀደም አርሰናል ላይ ያላየናየው ብዙ Posetive የሆኑ ነገሮች አይተናል።
አርሰናል በዚ አመት የተሻሻለ ይመስላል ሌላው ቀርቶ ደጋፊዎቹ ሌላ ጊዜ 3ጎል ከገባ በኃላ እስቴዲየሙን ለቀው ሲወጡ እንመለከት ነበር አሁን ግን እስከመጨረሻው ጨዋታው ሲከታተሉ ነበር ይህ የሚያሳየን እስከመጨረሻው ቡድኑ ላይ የተመለከቱት የሆነ ተስፋ ሰጪ ነገር ስለነበር ነው፡፡

አርሰናል ዛሬ ያሳዩት ብቃት ብዙ ከሜዳ ውጪ ጨዋታዎችን ሊያሸንፉበት የሚያስችላቸው ነው፡፡ ግን መርሳት የሌለብን በአሁኑ ሰአት የአውሮፓ ምርጡን ቡድን ሊቨርፑል ነው ብሎ ሀሳቡን አጠናቋል።

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች Gary Nevile ትናንት በአንፊልዱ ጨዋታ ላይ የሰጠው ትንታኔ ነው።

"SHARE" @onlyarse
​​አርሰናል 1 3 ሊቨርፑል
ሊቬዎች ኮንግራ ውጤቱ ይገባቹሃል
ጫወታውን ስናየው ገና ከአስላለፉ ነበር የተሸነፍነው የዚህን ጫወታ ውጤት ሙሉ በሙሉ የአሰልጣኙ ነው ሃላፍትናውን የሚወስደው
ምክንያቱም ለሊቨርፑል አይነት ከባድ ቡድን የሚያሰልፈውን ተጫዋች እንኳን ለይቶ የማያውቅ የወረደ አሰልጣኝ ነው በዚህ ሰው እሰከዛሬዋ ቀን ድረስ ተስፋዬ ጫፍ ድረስ ነበር ግን ከንግዲህ ቡሃላ ዋንጫውን ቢያነሳ የማለተማመንበት አይነት ሰው ሆኖ አግንቼዋለው
ወደዋናው ነጥብ ስመጣ የሊቬን አይነት ቡድን ስትገጥም አይደለም አሰላለፍ የምትቀይረው ቢያንስ አሰላለፍ የመቀየር እቅድ ካለው ቀለል ባሉ ክለቦች ላይ ነበር ሞክሮ ተጫዋቾቹ ይህን አሰላለፍ እንዲለምዱት ማድረግ ይጠይቃል
በርግጥ እስካሁን የገጠምናቸው ቡድኖች ቀለውን ነበር እያልኩ አይደለም ግን በለመዱት አሰላለፍ 4 2 3 1 ን ነበር መጠቀም የነበረበት የዛሬው 4 3 3 አሰላለፍ በለፉት ጫወታዎች ምርጥ የነበረውን ሴባሎስን እንኳን ከጫወታውያደረገው ውጪ አድርጎታል
ለምሳሌ የተሰለፈበት ቦታ ምቾት አልሰጠውም ስለነበር ወደሇላ እና ወደማሃል እየተመለስ ለመጫወት ሲሞክር ነብር ሌላው ደግሞ ይህ አሰላለፍ ነው ላካዜቴን ጫወታውን ከመጀመሪያው እንዳይጀምር
ሌላው ደግሞ በቴክኒኩ ብቻ ሳይሆን በአካል ብቃቱ የዳበሩ ተጫዋቾችን መጠቀሙን ትቶ ዊሎክን ያለ አግባብ ከመጀመሪያው ማስጀመሩ ሌላኛው ትልቁ ስትቱ ነው ዊሎክ ምርጥ ማደግ የሚችል ተስፈኛችን ነው ይህን ልጅ በእንደዚህ አይነት ጫወታ ላይ አይደለም ሪስክ ወስደህ የምታጫውተው
ሌላኛው ደግሞ ከሚገባው በላይ ጎንዶዚ ላይ ያለው እምነት ነው ይህን ጎንዶዚ ላይ ያለውን እምነት ቀንሶ ማሃል መዳው ላይ ቶሬራንና ዣካን አጣምሮ ፊት አጥቂውን በላካና በኦባ ፔፔን አድርጎ ሴባሎስን 10 ቁጥር ላይ ማድረግ ይችል ነበር
ኦዚል ቢኖር ኦዚልን 10 ቁጥር ላይ አድርጎ ሴባሎስን ከቶሬራ አጣምሮ ቢሆንም የተሻለ ነገር ልናይ እንችል ነበር ይህን ሁሉ ማድረግ እየቻለ አጉል ልፈላሰፍ ባይ ለመፈላሰፍ እንኳን ጫወታዎችን መመርጥ የማይችል አሰልጣኝ ሆኖ አግንቼዋለው
ሌላው የተከላካይ ክፍሉ ላይ ምንም ተቃውሞ የለኝም አማራጭም የለም የሚጠበቀው ነው እና የተከላካይ ክፍላችን ግን ከበፊቱ የተሻለውን የተከላካይ ክፍል ማየት ችያለው ምንም እንኳን በቡድኑ ድክመት 3 ጎሎችን ብናስተናግድም የተረጋጋ ሆኖ አግንቼዋለው ዴቪድ ልዊዝ ስተቱ እንዳለ ቢሆንም የተከላካይ ችግራችንን ቀርፎልናል ለማለት ነው
እኔ ግን የሚያሳዝነኝ ይህ ቡድንና አሰልጣኝ አንድም ቀን ምርጥ 11 ዳቸውን ሳይመርጡ ግዜው እየሄደ መሆኑ ነው ለማየት ያብቃቹህ ኤምሬ መቼም ምርጥ 11 መስራት አይችልም
ምክንያቱም የዛሬውን ጨምሮ ያለፉትን ሶስት ጫወታዎች መርጦ ማዘጋጀት ይችል ነበር አንዴ ፊትነሱ ሙሉ አልሆነም አንዴ ከተጫዋችች ጋር ሰጣ ገባ ውስጥ ይገባና በህምም ምክንያት እያለ ቡድኑን እየጎዳው እንደሆነ ይሰማኛል
ኦዚል መመለስ አለበት ቡድኑን በአግባቡ እየመራ ምርጥ 11 ዱን መምረጥ ግድ ይለዋል የራሱን ክብር በተጫዋቾች ላይመሸነፍ ከፍ ለማድረግ ከመሞከሩ ይልቅ ለቡድኑ ውጤት የሚጠቅመውን ማድረግ አለበት ባይ ነኝ
በተረፈ ማንኛውም ቡድን ላይ በኳስ አለም መሸነፍና ማሸነፍ ያለ ቢሆንም በአሰልጣኝህ እንዝላልነት ያበሳጫል ሊቬዎች በተለይ በመጀመሪያው 45 እና በሁለተኛው 45 እሰከ 70ኛው ደቂቃ መሰለኝ ባልሳሳት በጣም ቀለል ያለ ልምምዳቸውን ነበር የሰሩት አሁንም በድጋሚ ሊቬዎች እንኳን ደስ አላቹህ
@onlyarse
ቀጣይ ሳምንት እሁድ
Arsenal vs Tottenham
የዛሬው የቶትንሃም ሽንፈት ለመድፈኞቹ ጥሩ ነገር አለው ምክንያቱ ሁለቱም የለንደን ክለቦች መሸነፋቸው ለአርሴናል ለቀጣይ ጨዋታ በሞራል እንዲጫዎት ያደርጋል ግን ኡናይ ኤምሬ የአሰላለፍ ስተት ከፈፀም ቶትንሃም ቀላል አይፈትነንም
@onlyarse
▪️እውነቱን ለመናገር አርሰናል ድንቅ ተጫዋች አስፈርሞዋል።በጫወታው ከማንም በላይ ጎልቶ ወቶዋል በመጀመሪያ የቋሚነት አሰላለፍ ላይ እንዲ አይነት ድንቅ ብቃት በማሳየቱ ሊደነቅ ይገባል።እውነት አርሰናል ሁነኛ የመስመር ተጫዋች አግኝቶዋል።

በአውኑ ወቅት የአለማችን አይደፈሬው ተከላካይ የሚባለውን ቨርጂል ቫንዳይክን ሲፈትነው አምሽቶዋል።ከፈረሳይ ሊግ መቶ ቶሎ አይላመድም ሚሉ ወሬዎች ሲናፈሱ ቢቆዩም ፔፔ ግን ድንቅ ብቃቱን አስመልክቶዋል።

የአርሰናል መሸነፍ እንደ ምክንያት ሚታየው የአሰልጣኙ የቴክኒክ ችግር ነው እየተባለ ነው።ለጨዋታው ማይመጥኑ ተጫዋቾችን በማሰለፍ።"ለኒኮላ ፔፔ ከ ኦባምያንግ ይልቅ ላካዜት ይሻለዋል"

በባለፈው ጨዋታ 82' ደቂቃ ላይ ወደ ሜዳ የገባው ላካዜት ሙሉ ጨዋታውን ቢሰለፍ ኖሮ ማጥቃቱ ላይ አርሰናል በጣም የተሻለ ይሆን ነበር። ከኦባምያንግ የተሻለ የአጨራረስ ብቃቱን እናይ ነበር አርሰናል ፕረስ አርጎ እንዲጫወት ትልቁን ስራ ሚሰራው ደግሞ ቶሬራ ነው ይህ ኡራጋዊ አማካኝ በአንድም ጨዋታ ላይ ቋሚ ሆኖ አልጀመረም በሱ ምትክ ብዙ ልምድ የሌለውን ማትዮ ጎንዶዚ የኤምሬ ተቀዳሚ ምርጫ ሆኖዋል። ኤምሬ ግን ምን አስበው ነው......🤔በቀጣይስ የሰሜን ለንደን ደርቢ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ምን አይነት ፎርሜሽን ያሳዩን ይሆን። በአሁኑ ሳምንት ትችት ስለደረሰባቸው ጥሩ ፎርሜሽን ያሳዩናል ብዬ እገምታለው።

"SHARE" @onlyarse
▪️ትችት ሁሌ ከአፉ የማይጠፈው የSky Sport ተንታች ቶምሰን ቫርድ እንዲ ሲል ተደምጦዋል።አርሰናል እንዲሸነፍ ዋናውን ሚና የተጫወቱት ሁለቱ ፀጉራሞች ናቸው።ዴቪድ ሊውዝ እና ማትዮ ጎንዶዚ በቶተንሀሙ ጫወታ ላይ እነዚን ተጫዋቾች ሚሰለፉ ከሆነ እመኑኝ አርሰናል የአሁኑን ሳምንት ጫወታ ይደግመዋል።ግን እንደኔ እይታ ሁለቱንም ተጫዋቾች ቁጭ ማድረግ መፍትሄው ነው።ሲል ተደምጦዋል። እኔ ግን የምለው ስተት በእግር ኳስ አለም ያለ ነገር ነው ከስተታቸው ተምረው በቀጣዩ ጨዋታ ጥሩ ነገር ያሳዩናል ብዬ እገምታለው።

"SHARE" @onlyarse
​​ሁለቱ ወሳኝ የመስመር ወታደሮች ልምምዳቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል በቅርብ ቀን ወደ ጨዋታ ይመለሳሉ።
@onlyarse
አንድ የአርሰናል ደጋፊ የጉንዶዚን እና ዴቪድ ሉይዝን ስም በአንድ ማልያ ላይ የሁለቱንም ከሃላ አፅፎ ስቴዲዮም ውስጥ በመግባት በብዙዎቹ ደጋፊዎች ፎቶ ሲነሳ ታይቷል እንዲሁም የሁለቱንም ፀጉር (Hair force 1 ብሎታል)

@onlyarse
ኦዚል እና ሞኖሪያል አርሰናልን ሊለቁ ይችላሉ የሚሉ ወሬዎች መተዋል!

የአውሮፓ ክለቦች የተጨዋቾች መግዣ መስኮት ሚዘጋው September 2 2019 ነው ይህም ማለት ሊዘጋ 7 ቀን ብቻ ይቀረዋል
አርሰናልን ከ 7 ቀን በፊት ሊለቁ ይችላሉ ተብለው የተገመቱ ተጨዋቾች ዝርዝር ይህን ይመስላል
Ozil
Monreal
Mustafi
Elneny
Mavropanos

@onlyarse
ዴቪድ ሉዊዝ ስለ አርሰናል አጨዋወት የሰጠው አስተያየት፦

" እኛ ለመጫወት እየሞከርን ያለነው ኳስን ከኃላ መስመር አደራጅተን ለመውጣት ነው፤ ለዚህ አየጨዋታ ስታይል የሚሆኑ ተጫዋቾች አሉን። እኛ በእየንዳንዱ ጨዋታ እራሳችንን ለማሻሻል እንሞክራለን፣ በጣም ወደፊት ለማጥቃት እንዲሁም ኳሶችን በመስመሮች መካከል ለመጫወት እየሰራን ነው። " - (source:-football planet)

@onlyarse
የቀድሞው እንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን እና የቸልሲ ተከላካይ ጆን ቴሪ በእግር ኳስ የተጫዋችነት ዘመንህ ላንተ እጅግ በጣም አስቸጋሪው እና ፈተኛኙ የተጋጣሚ ቡድን ተጫዋች ማን ነው? ተብሎ ተጠይቆ የሰጠው ምላሽ፦

"ቴሪ ሄነሪ ፤ ምን ልበላችሁ ሄነሪ ጨዋታውን ልክ እንቅልፍ እንደሌለው ለሊት ነው የሚያደርግብኝ። እኔ ቸልሲን በተቀላቀልኩበት ወቅት ሄነሪ ምርጡ ተጫዋች ነበር እንዲሁም አርሰናል ደግሞ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጡ ቡድን ነበር በዛን ወቅት በአለማችን ላይ እንደ አርሰናል አይነት ምርጥ ቡድን አነበረም። "

@onlyarse
🔻 አርሰናል በኤምሬትስ ስቴዲየም ከቶተንሀምን ጋር ያደረጋቸው የመጨረሻ 8 ጨዋታዎች ውጤት፦

2011-12 አርሰናል 5-2 ቶተንሀም
2012-13 አርሰናል 5-2 ቶተንሀም
2013-14 አርሰናል 1-0 ቶተንሀም
2014-15 አርሰናል 1-1 ቶተንሀም
2015-16 አርሰናል 1-1 ቶተንሀም
2016-17 አርሰናል 1-1 ቶተንሀም
2017-18 አርሰናል 2-0 ቶተንሀም
2018-19 አርሰናል 4-2 ቶተንሀም
2019-20.??? እሁድ ምሽት 12፡30.....

@onlyarse
🔝ኤምሬ በሰሜን ለንደን ደርቢ ላይ ስለ ሚኖረው 3ቱ የፊት ለፊት ጥምረት ላይ ፍንጭ ሰጥተዋል ፡፡

በዋናነት ከተነሱት ነጥቦች መካከል :-
🔜 ስለ 3ቱ አጥቂዎች ጥምረት::
🔜 ስለ ላካዜቲ አካል ብቃትና::
🔜 ስለ ሌሎች አማራጭ ተጨዋቾች::

• ኤምሬ.... ላካዚት በቁርጭምጭሚቱ ላይ ጉዳት ከደረሰ በኋላ የአካል ብቃት እንቅስቃሴውን በእጅጉ እንዳሻሻለ ተናግረዋል......ስለዚህም ከኦባ እና ከፔፔ ጎን ለጎን የመጀመር እድሉ አለው....ውሳኔም የሚሆነው በጨዋታው ዕቅድ አሰላለፍ ላይ የተመሠረተ ነው።
ከ አንፊዱ የ 3-1 ሽንፈት በኋላ ብዙ ተንታኞች(Pundits) ኡናይ ኤምሬን ከጅምሩ አሌክስ ላካዜትን ባለማስገባታቸው በነገር ሲውርፏቸው ሰንብተዋል ፡፡

• ስፔናዊው አሰልጣኝ ከሊቨርፑል ጋር የበለጠ ጥንቃቄ የተሞላበትን አካሄድ መርጠዋል.....ይልቁም ዳኒ ሴባሎስን በ ቋሚ 11 ውስጥ የፈረንሣዊውን ቦታ ሰጥተውታል ፡፡ አለቃውንም የኦባ ፣ ላካ እና የፔፔ ሦስቱ ተጣምረው ሊጀመር ይችሉ እንደሆን በፕሬስ ኮንፈረንስ ተጠይቀዋል

• "አዎ...! ነገር ግን ትንሽ ተረጋጉ በእያንዳንዱ ውሳኔዬ እንዴት እንደሚሆን እያሰላሰልኩ ነው ፡፡ ለምሳሌ ላካዜት ቁርጭምጭሚቱ ላይ ጉዳት ነበረበት...ይህ ሳምንት ግን ካለፉት ሶስት ሳምንታት ጥሩው ሳምንት ነው ፡፡"
“እሱ እየተሻሻለ ነው እናም በቁርጭምጭሚቱ ላይ ጥሩ ስሜት እየተሰማው ነው አሁን በጣም ደህና ነው ፡፡

• ከፔፔ ጋር ከሌሎቹ ሁሉ በኋላ ነው ወደዚህ የመጣው ነገር ግን በእያንዳንዱ ግጥሚያ ላይ እየተሻሻለ ነው ፡፡

• ኦባምያንግ ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው በመጀመሪያዎቹ ሁለት ግጥሚያዎች ሁለት ግቦችን አስቆጥሮልናል በሊቨርፑል ውስጥ ሁለት ወይም ሶስት ጥሩ ተግባሮች ነበሩት ፡፡
ለእኔ በጣም አስፈላጊው ነገር ዕድሎች መኖራቸው እና እንደ ኦቤሜንግን ፣ ላካዚዜ ፣ ፔፔ ፣ ሚኪ፣ ኔልሰን፣ ሴባሎስና ፣ኦዚል ፣ ከኋላ ካሉ በተለያዩ ተጫዋቾች ጎሎችን አስቆጥረን ነጥብ መያዝ እንችላለን ፡፡

• እነርሱ አብረው ሊጀምሩም ይችላሉ ብዬ አስባለው እናም በጨዋታ ጊዜ እነሱ 3ቱም ተናበው መጫወት ይችላሉ.....ነገር ግን ይሄ ሁሉ ሊሆን የሚችለው የጨዋታውን ታክቲክ(ስልት) በምንወስንበት መንገድ ላይ የተመሠረተ ነው....እኔም ያ ይሆናል ብዬ በጣም ተስፋ አደርጋለሁ .........ነገር ግን እነዚያን ሶስት ተጫዋቾች ብቻ ሳይሆኑ ኔልሰን ፣ ሚክተንያን ፣ ዊሎክና ፣ ኦዚል አሉን ስለእዚህ እኛም የተሻሉ ውሳኔዎችን መወሰን መቻል አለብን ፣ • ከሁሉም በላይ ግን ከተጫዋቾቹ ውስጥ የተለያዩ አማራጮች እንዲኖሩን ማድረግ አለብን ፡፡

@onlyarse
አርሰናል ከ ቶተንሃም

በዕለተ ሰንበት ዕሁድ

ከምሽቱ 12:30 ሲል ይጀምራል፣


የአርሰናል እና የቶተንሃም ጠላትነት፣

የደርቢው ትንቅንቅ ጅማሮ፣

ታሪካዊ መነሻውስ ?

ከክፍል ሁለት የቀጠለ፣

አብራችሁን ሁኑ፣


👉የሰሜን ለንደን ደርቢ ታሪክ፣ ኬት ተጀመረ፣ አለማችን ላይ ከፍተኛ ትኩረት ከሚሰጣቸው የአንድ ከተማ ቡድኖች የደርቢ ትንቅንቆች ውስጥ፣ አንዱ የሆነው ኖርዝ ለንደን ደርቢ መነሻው በ 18ተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ነዉ፣ ያኔ አርሰናል በደቡብ ለንደን ነበር መቀመጫዉ፣ በ 1913 ላይ ግን መድፈኞቹ ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ ሰሜን ለንደን አመሩ፣ በ 4 ማይል እርቀት ብቻ ሃይበሪን ከ ኋይትህርትሌን አፋጠጡ፣

ነገሩ የቶተንሃም ክለብን አበሳጨ ሰሜን ለንደን በእግርኳስ የማያውቁት ባላንጣ ብቅ ያለባቸው ስፐርሶች በግዛታቸው መቶ የተጋፋቸውን አርሰናልን ይጠሉ የጀመሩት ወቅት የተቀናቃኝነቱ መንፈስ ጅማሮ፣

በ 1913 አርሰናል ወደ ሰሜን ለንደን ካቀና ቦሀላ፣ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከቶተንሃም አካሄደ መድፈኛው ያኔ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ነበር፣ ቶተንሃም ደግሞ በመጀመሪያው መድረክ ይገኛል፣ ኋይትህርትሌን ላይ የተገናኙት ሁለቱ ጎሮቤታሞች ከአንደኛው አለም ጦርነት በፊት ያካሄዱት ጨዋታ፣ ነጭ ለባሾቹን በማያስደስት ሁኔታ ተጠናቀቀ፣ አርሰናል 5-1 አሸነፈ፣

አዲስ የቅርብ ጊዜ ባላንጣ ያዉም በነገሱበት ግዛት ብቅ ያለባቸው የቶተንሃም ደጋፊዎች፣ የአርሰናልን ዕድገት ለማቀጨጭ ያሴሩም ጀመር ሆኖም በጊዜው የነበሩት ባለስልጣናት ከአርሰናል ጎን ቆሙ፣

አርሰናል ወደ ሀገሪቱ ከፍተኛ ዲቪዚዮን እንዲቀላቀል፣ መንገድንም ጠረጉለት በመሀል ግን የአንደኛው አለም ጦርነት ጅማሮ ኳሱ ላይ ተፅዕኖ አሳደረ፣ ጦርነቱ የክለቦቹን እንቅስቃሴ አደበዘዘ፣

በ 1921 አርሰናል እና ቶተንሃም በተዳከመ መንፈስ ተገናኙ፣ አሁንም ጨዋታው ኋይትህርትሌን ላይ ነበር፣ አርሰናል 2-1 አሸነፈ ከአንደኛው አለም ጦርነት ሀንጎቨራቸዉ ሳይወጡ የተቀናቃኝነት መንፈሱን እንደያዙት፣ እግርኳስን በሰሜን ለንደን ከተማ ለማሳደግ የተንቀሳቀሱት አርሰናል እና ቶተንሃም፣

በሁለተኛው አለም ጦርነት ህልውናቸውን በሚፈታተን መልኩ ድባቅ ተመቱ፣

በመጥፎዉ ዘመን ግን ተቀናቃኞቹ የጥላቻ ጉዟቸውን ወደጎን በመተው፣ እርስበርስ ተረዳዱ በግዜው በጦርነቱ ምክንያት ክፉኛ የተጎዳው ሃይበሪ፣ ኳስ ጨዋታን ማካሄድ ተሳነው፣ በ 4 ማይል እርቀት የጎረቤታቸውን አርሰናልን ችግር የተረዱት ቶተንሃሞች፣ ነግ በኔ በሚል ሜዳቸው ኋይትህርትሌንን አርሰናል እንዲጫወትበት ፈቀዱ፣

የሁለተኛው አለም ጦርነት ቀውስ፣ የሰሜን ለንደን ባላንጣዎችን የለየለት ተቀናቃኝነት ቢያሻሽለውም፣ ጠላት ያው ጠላት ነዉ እንዲሉ፣ አርሰናል እና ቶተንሃም ከጦርነቱ ፍፃሜ ማግስት፣ የሃይል ሚዛኑን ለመድፋት ይዋደቁ ጀመር፣


👉ክፍል ሦስት ይቀጥላል..
"SHARE" @onlyarse
​​√በቶተንሃም ቤት ጉዳቶች እየተባባሱ እየሄዱ ነው ቶተንሀም ለኤምሬትሱ ጉዞ የተከላካዮች ጉዳት እራስ ምታት ሆኖባቸዋል::
·
የቶተንሀም አለቃ ማውሪሲሆ ፖቸቲንሆ እሁድ በሰሜን ለንደን በሚደረገው ፍልሚያ ላይ የቀኝ መስመር ተከላካዩ ኬይል ዎከር-ፒተርስ ከደረሰበት የጡንቻ መሳሳብ ጉዳት ለማገገም እለመቻሉ አሳስቧቸዋል ፡፡
·
የእሱ መጎዳት የፖቼትኖን አማራጮች በጣም ያጠቡታል ተብሏል...........፣ በዚህ ዓመት በቀኝ መስመር ተከላካይነት እንዲጫወት የታሰበው ጁዋን ፎይም (Foyth) እንዲሁ በቅድመ-ውድድር ወቅት ቁርጭምጭሚቱ ላይ ጉዳት ስለደረሰበት እርሱ ደግሞ እስከ International break ላይመለስ ይችላል::
·
ሰርጌ ኦሪየር እስከዚያ ጊዜ ድረስ ይቆያል እናም ሰኞ የአውሮፓን የዝውውር ቀነ-ገደብ ከማለቁ በፊት ለመልቀቅ ዝግጁ ነው ስለዚህ ፖቼቲኖ ኢቪጎሪያን ለመጥራት ፈቃደኛ አልሆነም ፡፡
·
ስለሆነም እእሰልጣኙ በበኩላቸው ፊታቸውን ሙሳ ሲሶኮ ሊመለሱ ይችላሉ...በባለፈው የ ኒውካስትል ጨዋታ 1-0 በተሸነፉበት ለ 30 ደቂቃ ያህል ቦታውን(ቀኝ-ተከላካይ) ሸፍኖ ተጫውቷል የ ኤሪክ ዳየርም ነገር አለየለትም የአስልጥይኙን ውሳኔ ይጠብቃል::
·
የአርጀንቲናዊው ውሳኔ በኒውካስትል የታፋ ጉዳት ባስተናገደው ታንጉይ ንዶምቤሌ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይችላል ፡፡
·
ደሌ አሊ ከጡንቻ መሳሳብ ውጥረት ችግር በኋላ ወደ ሙሉ ስልጠና ተመልሰዋል እናም ለመጀመሪያ ጊዜ ሊሰለፍ ይችላል ግን ራያን ሴሴኒዮን በ(Hamstring) ቋንጃ ጉዳት ምክንያት አሁንም እይደርስም ነው ፡፡
·
ይህ በእንዲህ እንዳለ ክለብ ብሩዥ በዚህ ሳምንት የቪክቶር Wanyamaን ስምምነቱን ለማጠናቀቅ ተስፋ በማድረግ ላይ ናቸው::
·
ስለዚህም እሁድ በሰሜን ለንደን የ ሚደረገውን የሁለቱ ታሪካዊ ተቀናቃኞች ፍልሚያ ወደ አርሰናል ያደላ ነው እየተባለ ነው ነገር ግን በአርሰናል በኩል ሁልጊዜም አዳዲስ አሰላለፍ እና 11 ይዝእው ብቅ የሚሉት አሰልጣኙ በሚወስኑት ውሳኔም ጨዋታው ይወሰናል::
@onlyarse