Nigat Media
132 subscribers
520 photos
22 videos
277 links
Nigat Media ያልተዛባ መረጃን በተለየ አቀራረብ!
👉 https://www.nigatmedia.com
👉 https://www.am.nigatmedia.com
👉 https://www.facebook.com/nigatmedia1
👉 https://www.youtube.com/nigatmedia
Download Telegram
ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሊሰጣት ነው

⚡️እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሊሰጣት መወሰኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) ገልፀዋል።

⚡️ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚያስመርቅ የገለፁት ፕሬዘዳንቱ ፥ በዕለቱ ለተወዳጇ አርቲስት እጅጋየው ሽባባው(ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

⚡️ድምፃዊት፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ተዋናይት የሆነችው ሁለገቧ አርቲስት ጂጂ ፥ የሀገሯን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም በማስተዋወቅ እንዲሁም በኪነጥበብ የአዊን ህዝብ ቋንቋ እና ባህል በማሳደግ ላበረከተችው አስተዋፅኦ የክብር ዶክትሬቱ እንደሚበረከትላት ነው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት የተናገሩት።

ምንጭ - ፋና ቢ ሲ
ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ አንባ ጊዮርጊስ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ፋኖን ትደግፋላችሁ በሚል በካንፑ ውስጥ ባስራቸው የከተማዋ ወጣቶች  ላይ ግድያ እየፈፀመ መሆኑን የአይን እማኞች ለ #ንጋት ሚድያ ገለፁ።

በዛሬው እለትም አንድ ወጣትልጅን በአሰቃቂ ሁኔታ መረሸኑን የገለፁት ምንጮች፣ የወረዳውና የከተማው አመራሮችም ተባባሪ ሆነው ወጣቱን እያስቀጡት ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ሰበር ዜና!

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ ቤት በቦንብ ተደበደበ‼️

⚡️የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ ቤት በቦንብ መደብደቡን የአይን እማኞች ለእዮሃ ቲቪ ገለፀዋል።

⚡️የዋና አስተዳዳሪውን ቤት በቦንብ የደበደቡት አካላት ማንነት ያለታወቀወ ሲሆን፣ በቦንብ ፍንዳታው ምክንያት በሰው ላይ ጉዳት አልመድረሱን ተናግረዋል።

⚡️አሁን ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ ቤትን በመከላከያ ወታደሮች እየተጠበቀ መሆኑንም ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል።

⚡️ከሳምንት በፊት የደበር ብርሃን ከተማ ፖሊስ አዛዥ ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ነው


➤ 𝑻𝒆𝒍𝒆𝒈𝒓𝒂𝒎 :-@nigat_media1
#ሰበር

አሳዛኝ በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ በዚህ ሰዓት ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ አለ።
የምስራቅ አማራ ፋኖ አሳመነው ብርጌድ የላስታ አውራጃ "አስ ከተማ" የተባለችውን ከተማ ሲቆጣጠር፣ የከተማው ህዝብ በሚገርም ሁኔታ አቀባበል አድርገውላቸዋል።


ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇👇👇
   @nigat_media1
#ሰበር_መረጃ
ቅዱስ ሲኖዶሱ አስቸኳይ ጥሪ አስተላለፈ!!

"በተጠራው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ  የማይገኙ አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በእነሱ ላይ የሚወስነውን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል " - የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት

#ንጋት_ሚድያ

ሁሉም ብፁዓን አባቶች ሐምሌ 25 /2015 ዓ/ም ለተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በድጋሜ ጥሪውን አስተላለፈ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፅ/ቤት ፤ በትግራይ ክልል በአክሱም  ርእሰ አድባራት ወገዳማት ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 16/2015 ዓ/ም ኢቀኖናዊና ሕገወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እንደተፈፀመ በመግለፅ ይህን አስመልክቶ ለመምከር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ/ም መጠራቱ የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ በቤተ ክርስቲያኗ የገጠማት ፈተና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ ምክክር እንዲደረግበት የተጠራ አስቸኳይ  ምልዓተ ጉባኤ መኖሩ ቢታወቅም አንዳንድ ብፁዓን አባቶች ግን ከወዲሁ በተለያየ ምክንያት #እንደማይካፈሉ እየገለጹ ይገኛሉ ተብሏል።

ከአቅም በላይ ያጋጠመ ችግር ቢኖርም እንኳ ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ጉዳይ የሚበልጥ ባለመኖሩና የቤተ ክርስቲያን ቀኖናና አንድነት በከፍተኛ ደረጃ ሲፈተን እያዩ በጉባኤው አለመገኘት የተጠሩለት የቤተ ክርስቲያን እውነትን የመጠበቅ ተልእኮ እንደመግፋት ስለሚያስመስል በሀገር ውስጥና በሀገር ውጭ ባሉ አህጉረ ስብከት የሚገኙ ብፁዓን አባቶች በተጠራው ቀን በጉባኤው እንዲገኙ በድጋሜ ጥሪ ተለልፏል።

በተጠራው ምልዓተ ጉባኤ  የማይገኙ  አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  በእነሱ ላይ የሚወስነውን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል ሲል የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አሳስቧል።

መረጃው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት / EOTC TV ነው።
#ጀግና ተዋወቁ . . .
አሰከተማ፣ ጋሸና እና መቄትን የተቆጣጠረው የምስራቅ አማራ ፋኖ አሳምነው ብርጌድ ላስታ አውራጃ ኮማንደር  . . . ይሄ ነበልባል ፋኖ እስራኤል ድረስ ሄዶ የኮማንዶ ስልጠናን በብቃት የተወጣ ባለ ቀይ ቦኔት ኮማንዶ ነው።
የዐቢይ አሕመድ አስተዳደር በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን ወረራና የንፁኃን ግድያ በአስቸኳይ እንዲያቆም እያሳሰብሁ፤ የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ እንዲሁም ሚዲያዎች መንግስት የቴሌኮም አገልግሎቶችን በመዝጋት ጭምር በአማራ ክልል በከባድ መሣሪያ ታግዞ በንፁኃን ዜጎች ላይ እየፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ እንድታወግዙና አገዛዙ ላይ ጫና እንድታሳድሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

©የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ
#ድሮን

በአማራ ክልል ኢንተርኔት የዘጋው መንግስት የድሮን ጥቃት መፈጸም ጀምሯል‼️

#ንጋት_ሚድያ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉ
👇👇👇
@nigat_media1
#ሰበር_መረጃ #መረጃ

#መርጦለማሪያም ከብልፅግና መዋቅር ውጪ ሆናለች!

የአማራ ህዝባዊ ኃይል ፋኖ የምስራቅ ጎጃሟን ጥንታዊና ታሪካዊ ከተማ የሆነችዉን መረጦ ለማሪያም ከተማን ተቆጣጥሯል።

በተመሳሳይ ህዝባዊ ሃይሉ ሸበልበረንታ ወረዳንም መቆጣጠሩ ሲሰማ፣ የወረዳው የመሳሪያ ግምጃ ቤተም ሙሉ በሙሉ በፋኖ ስር ሆኗል።


#ንጋት_ሚድያ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉ
👇👇👇

@nigat_media1
ከ50 በላይ ኤርትራውያን ጉዳት ደረሰባቸው!!

በስዊድኗ መዲና ስቶክሆልም በኤርትራ የባሕል ፌስቲቫል ላይ በተከሰተ ግጭት ከ50 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውን አሶሲዬትድ ፕሬስ (ኤፒ) ዘገበ።

የስዊድን ፖሊስ ቃል አቀባይ ዳንኤል ዊክዳሀል እንዳሉት ከክስተቱ ጋር በተያያዘ ከ100 እስከ 200 የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተናግረዋል።

ኤፒ የአገሪቱን መገናኛ ብዙኃን ጠቅሶ እንደዘገበው በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል በተከሰተው ግጭት በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።

ፌስቲቫሉ እንዳይካሄድ የተቃወሙ አንድ ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ወደ ፌስቲቫሉ ስፍራ በኃይል በመግባት ድንኳኖች እና ተሽከርካሪዎችን በእሳት አያይዘዋል።

ፌስቲቫሉን በኃይል ለመበተን ከተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች የመጡ ናቸው የተባሉት ተቃዋሚዎች ድንጋይ እና ዱላ በመጠቀም የፖሊስ ፍተሻ ጣቢያዎችን በኃይል አልፈዋል ሲል 'ኤክስፕረሰን' የተባለ የአገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል።

ግጭቱን ተከትሎ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተለቀቁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች መኪኖች ሲነዱ እና ደንኳኖች ፈራርሰው አሳይተዋል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ መሸሻቸው ተሰምቷል። ርዕሰ መስተዳድሩ ከባህር ዳር ከተማ ሸሽተው ወደ አዲስ አበባ ከገቡ አንድ ወር እንዳለፋቸው የተገለፀ ሲሆን፣ ከሌሎች የክልሉ አመራሮች ጋር እንዳይገናኙ ሆነው ከጥቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የሚሰጣቸውን መመሪያ እና መግለጫ እንዲያስተላልፉ ተደርገዋል ነው የተባለው።

በትላንትናው እለት በዶ/ር ይልቃል ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤም ከአዲስ አበባ ርዕሰ ምስተደሰድር ቢሮ ተዘጋጅቶ የወጣ መሆኑም ነው የተነገረው።
የሲዳማ ኤጄቶ ለአማራ ፋኖ የላከው መልዕክት‼️

አንባገነኑ የብልፅግና መንግስት ከኦሮሞ ውጭ ያሉ ማንነቶችን ከምድር ገፅ ለማጥፋት የወጠነውን ውጥን እኛ የሲዳማ ኤጄቶ አጥብቀን በመቃዎም ከጀግናው አማራ ፋኖ ጎን በመቆም አገራችንን ከብተና ለመታደግ እንደሚንሰራ ለወንድም ፋኖ ማሳወቅ እንፈልጋለን ።

የተከበረው የአማራ ህዝብም የውስጥ ልዩነቶችን ወደጎን በመተው የጋራ ጠላቱ የሆነውን ብልጽግና አሽቀንጥረው ለመጣል በተባረሩ ክንዶች ትግል እንዲያደርግ እናሳስባለን።

እኛም የሲዳማ ህዝብና ኤጄቶ ባለማወቅ የተሸከምነውን የኢትዮጵያ ጠላና ተገንጣይ ብልጽግናን ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለመቅበር ከየትኛውም ግዜ በላይ ተዘጋጅተናል ትግልም ጀምረናል ።
ሰበር ዜና‼️

አርቲስት ዳኘ ዋለ አሁን በአዲስ አበባ ከተማ ኡራኤል አካባቢ መኪናውን እያሽከረከረ ሲጓዝ በመንግስት ደህንነቶች ታፍኖ ተወስዷል።
ሰበር መረጃ‼️
👉 የህዝብ እንደራሴው ታሰሩ‼️

ዛሬ ምሽት ፌደራል ፖሊስ ያለመከሰስ መብት ያላቸውን የፓርላማ አባል አቶ ክርስቲያን ታደለን  እየደበደበ ከቤታቸው መውሰዱ ተሰምቷል።
ሰበርርርርር . . .‼️

ከወራት በፊት ከ500 በላይ ሰዎች የተገደሉበት ደብረ ኤልያስ ወረዳ በፋኖ ቁጥጥር ስር መግባቱን ሰምተናል።
# መረጃ
በትላንትናው እለት ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ 12ኛ መልቀቂያ ፈተና ጨርሠው ሲመለሡ በመንግስት ፀጥታ ሀይሎች የታገቱ አበበ መኮንን፣ ጀግናው አስቻለው፣ ደሴው ብርሀኑ እና ለጊዜው ስማቸው ያልታወቁ አንዱ ከብልባል አንድ ከወደብዬ ቀበለ የመጡ ተማሪዎች ተለቀዋል ቢባልም እስካሁን ከቤተሰቦቻቸው አልተገናኙም።

ፈጣንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇
t.me/nigat_media1
ባህር ዳር ክተት አውጃለች🔥🔥

ከሳተላይት ዋይ ፋይ በቀር ባህር ዳር ኢንተርኔት ስለተቋረጠ ማህበራዊ ሚዲያ አይሰራም። ሆኖም በአሁኑ ሰአት የባህር ዳር ህዝብ ድባንቄ ተራራን ለመቆጣጣር ትንቅንቅ እያደረገ ይገኛል።

አቅም ያለው ሁሉ ወደቦታው በመሄድ እንዲያግዝ ለምታውቁት ሰው ሁሉ እየደወላችሁ ወደ ድባንቄ ተራራ በመሄድ ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አድርጉ ብላለች!!

ለበለጠ መረጃ👇👇
http://t.me/nigat_media1
ከሸዋ ህዝባዊ ጥምር ጦር ደብረብርሀን የተሠጠ መግለጫ!!

በበርካታ አቅጣጭ የመጣውን የአብይን ቡድን በሚያስደምም ጀግ ንነት ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀን ከፊት የመጣውን ኃይል ደምስሰን ከተ ማችን መቆጣጠራችንን ይታወቃል::

በመሆንም ቡድን የደረሰበትን ውርደትና ኪሳራ ለማካካስ በማሰብ
በርካ ሀይል ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢወች በመሰብሰብ የሀገር  መከላከያ ዩኒፎርም በማልበስ በበርካታ ከባድ መሳሪያ ታጅቦ
ወደ ከተማው መግቢያ በሮች በማስጠጋት እንቅስቃሴዎች መጀ መሩ እውን ነዉ።

ይህ ኃይል አማራ ጠልና ለአማራ ህዝብና ከተሞች ምንም ርህራሄ የሌለው ፈሪ ግን ጨካኝ ቡድን:ለንፁሃን ለሴትና ለህፃናት በአጠቃ ላይ ሲቪሊያን ላይ በብዙ እጥፍ የሚከፋ ኃይል በመሆኑ ምክንያ ት እጅግ ብስለት ስክነትና ለህዝባችን እውነተኛ አሌኝታነታችንን ለማሳየት በማሰብ ያለምንም ቶክስ ልውውጥ በኃይል በቀላሉ የተቆጣጠርነውን ከተማችንን በሰላም ለቀን ወሳኝ ስትራቴጅካዊ
ቦታን ይዘን እንገኛለን።

ህዝባችን እንዲያውቅልን የምንፈልገው እውነት ተቆጣጥረን የለቀ ቅነውን ከተማ አይደለም የትኛውንም ከተሞች በፈለግን ሰዓት የመ ቆጣጠር አቅሙ እንዳለንና የትኛውም ቡድን ሊከለክለን እንደ ማይ ችል ማወቅ ግን ይኖርበታል።

ነሐሴ 2/2015
ሸዋ ደብረብርሀን
በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ያለው የኦህዴድ ጉዳይ ፈጻሚ ጦር ተነቅሎ ወደአማራ ክልል ገብቷል። የሶማሊያን ድንበር የሚጠብቅ ሠራዊትም ተነቅሎ መጥቷል። የሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና የኬንያ ድንበር ጠባቂዎች ሁሉ አሁን ድንበሩን ክፍት አርገው ወደአማራ ክልል ገብተዋል ወይም እየገቡ ነው። ሌላው ቀርቶ የታላቁን ህዳሴ ግድብ እንኳ ያለጠባቂ ቀርቷል።  ይሄንን ሁሉ ማዝመት ያስፈለገው አማራጭ ስለሌለ ነው። ሌላው ሠራዊት አልቋል። ተበትኗል፣ ተማርኳል ወይም ተገድሏል። የአማራ ክልሉ ለየት የሚያደርገው ፋኖ በክብር ስርዓተ ቀብር ይፈጽማል።  ሠራዊት በማስጨረስ የታወቀው አብይ በትግራይ ጦርነት በተከተለው የተሳሳተ ስትራቴጂ ሰራዊቱ ሲያልቅ ሠራዊቴ አለቀ ሳይል የክልል ልዩ ሀይሎችን ነበር ያዘመተው። ፋኖ ፕሮፓጋንዳው ላይ ስለሌለበት አልተናገረውም እንጂ አሁን በመከላከያ የደረሰው እልቂት ትግራይ ላይ ደርሶ ከነበረውም የከፋ ነው።  ይሄንን መራር እውነት ወደፊት ሁሉም ይረዳዋል።

#ሙሉቀን ተስፋው