Nigat Media
268 subscribers
579 photos
22 videos
1 file
285 links
Download Telegram
ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ባዶ ቢሮ ሊወርሱ ነው?‼️

250 የሚሆኑ የኢዜማ አመራርና አባላቶች ከኢዜማ መልቀቃቸውን ዛሬ አስታውቀዋል።

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉን 👉 @nigat_media1
በደቡብ ጎንደር ካድሬዎች ሴራ የተሰዋው የደብረ ታበሩ ፋኖ!!!

ለመላው የፋኖ አማራ በጎንደር አባላት እና ለመላው የፋኖ ወዳጂ የጎንደር ከተማ ህዝብ ፤ የአባላችን የፋኖ ተዘራ ጀምበር  ስርዓት ቀብር የሚፈጸመው በደብረ-ታቦር ከተማ  ስለሆነ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ  ወደ ደብረ -ታቦር የቀብር አሸኛኘት ስነ-ስረአት ስለሚደረግ በቦታው በመገኘት ስነ-ስርአቱን እንድትታደሙ እና ሌላኛው የፋኖ ጓዳችንንም ስርዐተ ቀብር እንድትታደሙ ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን።

ከስርዓተ ቀብሩ በፊት ወይም በኋላ የመያዳግም እርምጃ ያስፈልጋል።

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር
በአሁኑ ሰዓት በአማራ ትግል ዳር የቆመ አማራ ማለት በርሃብ ጊዜ የተነፈገ ምግብ ማለት ነው!! ለብልፅግና የሚያገለግል አማራ ማለት አማራ የታረደበት ገጀራ፣ በአማራ ላይ የተተኮሰ ጥይት ማለት ነው!! ትግላችን እየጠነከረ እያደገ ነው።
አማራጫችን ማሸነፍ ብቻ ነው!!!

Abebe Belew

ለትኩስ መረጃዎች አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇👇👇

* ቴሌግራም   @nigat_media1
🇪🇹 በዳይመንድ ሊግ የኢትዮጵያ አትሌት በፈጣን ሰዓት አሸነፈ

#Ethiopia | የኢትዮጵያ አትሌት በሪሁ አረጋዊ በወንዶች ዳይመንድ ሊግ አምስት ሺ ሜትር ሩጫ ውድድር ቀዳሚ ሆኖ አጠናቋል።

በስዊዘርላንድ ሉዛን ዳይመንድ ሊግ የ5000 ሜ አትሌት በሪሁ አረጋዊ 12:40.45 በሆነ ሰዓት በመግባት በርቀቱ ታሪክ አምስተኛ ፈጣን ሰዓት አስመዝግቧል ።

የርቀቱ ክብረውን ባለቤት የኡጋንዳው አትሌት ጆሽዋ ኪፕቴጌ 12:41.61 በሆነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ ሲያጠናቅቅ ሌላኛው የኢትዮጵያ አትሌት ሀጎስ ገብረ ሕይወት ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል ።

የሃገሩ ልጆች ሃጎስ ገ/ህይወት 3ኛ፣ ጥላሁን ኃይሌ 4ኛ፣ ሰለሞን ባረጋ 5ኛ፣ ኩማ ግርማ 7ኛ፣ ገመቹ ዲዳ 8ኛ ሆነዋል።

2023 ሲውዘርላንድ ላውዛን ዳይመንድ ሊግ 1500 ሜ ወንዶች ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ በፈጣን ሰዓት 3:29'51 PB NR በመሮጥ ሁለተኛ ሆኗል!
ፋኖ አሚኮን ተቆጣጠረ

"..ፋኖ አሸባሪ አይደለም ዜናዉን እናተ አንብቡት ብሎ ለአለቆቹ ወርውሮ ወጣ

የአሚኮ ጋዜጠኛ ሀብታሙ ሙሃባ በዛሬ የአማራ ቴሌቪዥን ዜና ላይ «አሸባሪው ፋኖ» የሚል ዜና እንዲያነብ ቀርቦለት ዜናውን ለማንበብ ከተቀመጠበት መድረክ ማይክራፎኑን ወርውሮ በመጣል ጥሎ ወጥቷል!!!

ለትኩስ መረጃዎች አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇👇👇
.
.
* ቴሌግራም   @nigat_media1
ሰበር ዜና

⚡️በምስራቅ ጎጃም ደጀን ከተማ ገልገሌ ደንበዛ ተብላ በምትጠራ ቦታ ላይ  የፖሊስ አዛዡ ዘውዱ ታደለ  እና ምክትል አዛዡ ሳጅን ወርቁ መገደላቸው ተሰማ።

⚡️ሹፌራቸው ቆስሎ ሆስፒታል ገብቷልም ተብሏል።

#Mereja

ለትኩስ መረጃዎች አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇👇

@nigat_media1
ህወሃት..!

ህወሓት የፌደራል መንግስቱን አጋልጦታል። የፌደራል መንግስቱ ህወሓት ትጥቅ ፈትቷል ቢልም ህወሓት ግን የቀበራቸውን ከባድ መሳርያዎች እያወጣ ነው።

የሰላም ስምምነቱም፣ የፌደራል መንግስቱ ደባም በአደባባይ የተጋለጠባቸው እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል።

በሱዳን፣ በጠለምት፣ በወልቃይት፣ በኤርትራ ድንበሮች ህወሓት የጀመራቸው በከባድ መሳርያ ጭምር የታገዙ ስልጠናዎች የፌደራል መንግስቱም ውሸትን ያጋለጡ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ነው። #ጌታቸው ሽፈራው

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇
@nigat_media1
ፓርላማ ላይ ለ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር  አብይ አህመድ የቀረቡ ጥያቄዎች:-
.
.
.
. የተከበሩ አቶ መሀመድ አህመድ
  " ህወሓት አሁንም ከዉድቀቱ ያልተማረ መሆኑ እና ዛሬም የትግራይ ክልልን እና መላዉ ኢትዮጵያን መልሶ ጦርነት ዉስጥ ለመክተት እየተንቀሳቀሰ እንዳለ አሁንም ይነሳል። ወቅታዊ የትግራይ ክልል ሁኔታ ማብራሪያ ይሰጥበት?"

የተከበሩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ "ሙሉ አማራ ክልል አዲስ የጦርነት ቀጠና ሆኗል ፤ ከፊል ኦሮሚያ በተመሳሳይ የጦር ቀጠና ናቸዉ። ከ 200 ሺህ በላይ ሰዎች በመንግስት ቤታቸዉ ፈርሶ ሜዳ ላይ ወድቀዋል። እንደ ብልጽግና ሹማምንት አባባል ህጋዊ ደሃ ተደርገዋል። በሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በጦርነቱ እና በማንነት ጥቃት ተፈናቅለዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ለዚህ ሁሉ ቀዉስ ዋነኛ ተጠያቂው የብልጽግና መንግስት እና የእርሶ(የጠ/ሚኒስተሩ ) የወደቀ አመራር ነዉ።
ጠ/ሚኒስትሩ ወደስልጣን ከመጡ ወዲህ ኢኮኖሚዉ ታሟል፣ ወጣቶች ሀገራቸዉ ዉስጥ ተስፋ በማጣታቸው ስደትን ምርጫቸዉ አድርገዋል ፣ ዜጎች በጠራራ ፀሀይ ይታገታሉ ፣ ብልጽግና መራሹ ፓርቲ ሀገሪቱ ከገባችበት ቅርቃር ማዉጣት ስለማይችሉ ስልጣኖን ለጊዜያዊ አስተዳደር እንዲያስረክቡ ሲሉ ጠይቀዋል።


* ቴሌግራም @nigat_media1
ምክትል ሳጅን ያለለት ደጉ ተገሏል!

ምክትል ሳጅን ያለለት ደጉ ትላንት ማታ በሸዋሮቢት ከተማ 08 ቀበሌ ከምሽቱ 4 ስዓት ላይ በተከፈተው የተኩስ ልውውጥ በጥይት ተገሏል፡፡ወደ ሸዋሮቢት የሚያስገቡም ሆነ የሚያስወጡ መንገዶች ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል። መንግስት ያለ የሌለ ጦሩን አሰማርቶ ህዝቡን እያሸበረ ይገኛል።

@nigat_media1
ነዋሪዎችን ያስደነገጠው የአዳማ/ናዝሬት ህዝብና የቤት ቆጠራ‼️

⚡️የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአዳማ ከተማ ሕዝብ ቆጠራ ማካሄድ መጀመሩ "ግርታ" እና "ስጋት" እንደፈጠረባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ለዋዜማ ተናግረዋል።

⚡️የመንግሥት መረጃ መዝጋቢዎች ቤት ለቤት እየዞሩ የብሄር ማንነት፣ ሃይማኖት፣ የቤተሰብ ብዛት፣ ጾታና ሌሎች መረጃዎችን እየሰበሰቡ እንደኾነ ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

⚡️የከተማዋ ኮምንኬሽን ጽሕፈት ቤት ግን፣ መረጃዎቹን መሰብሰብ ያስፈለገው በቅርቡ በከፍተኛ ደረጃ የሰፋችውን ከተማ በአዲስ መልክ በክፍለ ከተማና ወረዳ ለማደራጀት መኾኑን ገልጿል።

⚡️የብሄር ማንነትን በቆጠራው ለምን ማካተት እንዳስፈለገ ዋዜማ ላቀረበችው ጥያቄ፣ ጽሕፈት ቤቱ የመረጃው መካተት "ምንም ፖለቲካዊ ዓላማ የለውም" ብሏል።


ለትኩስ መረጃዎች አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇👇👇
* ቴሌግራም  @nigat_media1
#ሰበር #መረጃ #መተከል

⚡️ዛሬ ከመሸ በግምት 12:00 አካባቢ በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ የጉምዝ ታጣቂዎች ማንነትን ኢላማ ያደረገ ጥቃት መፈፀማቸው ተሰምቷል።

⚡️በታጣቂዎቹ ጥቃት በርካታ ሰዎች ሳይሞቱ አይቀርም ያሉት የመረጃ ምንጮች እንዳሉት፣ በአሁኑ ስዓት የከተማው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የቆመ ሲሆን፣ ባስቸኳይ የፀጥታ ስምሪት ያስፈልጋል ሲሉም አክለዋል።

ለትኩስ መረጃዎች አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇👇👇

* ቴሌግራም  @nigat_media1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከእንግሊዙ የአውሮፕላን ሞተር አምራች “ሮልስ ሮይስ” ኩባንያ ጋር በቀጣይ ለሚረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ሞዴል ሞተሮች አጠቃላይ የሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከ4ሺህ በላይ  ታራሚዎች ተፈቱ‼️

⚡️በአማራ ክልል በ2015 በጀት ዓመት የይቅርታ አሰጣጥ አዋጅና መመሪያን ያሟሉ 4 ሺህ 401 ታራሚዎች የይቅርታው ተጠቃሚ ሲሆኑ፣ ከዚህ ውስጥ 4ሺህ 308 ወንዶች ሲኾኑ ቀሪዎቹ ሴቶች ናቸው ተብሏል።

⚡️በክልሉ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በየማረሚያ ቤቱ ያሉ ታራሚዎች በፊዴራል ይቅርታ አወሳሰንና አሰጣጥ መመሪያ 966/2015 መሠረት በቀጣይ ይቅርታው ተጣርቶ ለፌዴራል ይቅርታ ቦርድ እንዲላክ ለማረሚያ ቤት መመሪያ መተላለፉንም ክልል ፍትሕ ቢሮ ኀላፊ ገረመው ገብረፃድቅ ገልጸዋል።

via #አሚኮ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላም ልኡካን ወደ ትግራይ ክልል መዲና መቀሌ አመሩ

⚡️የሰላም ልኡኩን በመምራት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የሀገር ሽማግሌዎች መጓዛቸዉን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

⚡️በዕለቱም ብፁዕ አቡነ እርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጀና የባህርዳር ሀገረ ስብከት  ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ተገኝተው ለቅዱስ ፓትርያርኩንና ለልኡካኑ ሽኝት አድርገዋል።

Via EOTC
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሰላም ልኡካኑ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በመቐለ አሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት ተገናኝተዋል።

Via፦EOTC TV