Ctrl+code ⌨️
104 subscribers
129 photos
29 videos
1 file
98 links
Just sharing my next move 👣👣
Download Telegram

የሉ​ቃስ ወን​ጌል ምዕራፍ 2 :10-11:

መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
Speed came Ethiopia
እንደ ሀገር ተዋረድን
💯1
አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ እንዳረፈ ሰማሁ እና ሰው ነንና መቼስ በጣም ያሳዝናል.. ጌታችን እንኳን አላዛር ሲያንቀላፋ አልቅሶ ነበር..

ያው በእርግጥ ወደ ጌታ ነው የሄደው.. ጌታ ምህረት እንደሚያደርግለትና ከእርሱ ጋር እንደሚያኖረውም አምናለሁ.. ስለዚህም እርሱ በዚህ ሰዓት ውስጥ በማይነገር ደስታ ውስጥ ነው..

አያችሁ የኔ ተወዳጆች በሕይወትም ብንኖር ብንሞትም ከጌታ ጋር ነን.. ይልቁን ደግሞ ስንሞት የበለጠ ወደ እርሱ እንሄዳለን.. ስለዚህም በጌታ ሆነን ስናንቀላፋ ለኛ ጥቅም ነው.. ጳውሎስ እንዲህ ይላል:

“ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነው።” [ፊል 1:21]

የኛ ተራም በፊታችን አለና ጌታ ኢየሱስን በሕይወታችን እናክብረው..

ኪሪዬ ኤሌይሶን - ጌታ ሆይ ማረን
Forwarded from <xdagiz /> (xᴅᴀɢɪᴢ (vim btw))
so true🤣

@xdagiz_tsx
Forwarded from Biniyam Ŧaye
I realized that if U want to be a web dev or any kind of developer in the tech stack U shoul not have to limit your mind to just website development. It’s only the beginning of the development journey. That doesn’t mean it’s easy; it requires a lot of discipline and dedication.....But after that, don’t trap your mindset by staying stuck in one area. Development is a lifelong journey✌️
🤝1
Henok
https://thehackernews.com/2026/01/researchers-uncover-chrome-extensions.html
Create affiliate account.

Create a chrome ext. Which appends your tag to buyer url
(Promote as it is ad blocker)

Earn commission money from amazon.
moltbook ምንድነው?

እንደ እኔ ግራ ለተጋባችሁ

Moltbook በቅርቡ (በጥር 2026) ይፋ የሆነ አዲስ እና አስገራሚ የቴክኖሎጂ ውጤት ሲሆን፣ በአጭሩ "ለሰው ልጆች ሳይሆን ለሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ብቻ የተሰራ የማህበራዊ ሚዲያ" ተብሎ ሊገለጽ ይችላል።


የAI መገናኛ ብዙሃን፦ ልክ እንደ ፌስቡክ ወይም ሬዲት (Reddit) አይነት ሆኖ፣ ነገር ግን በላዩ ላይ መረጃ የሚለጥፉት፣ አስተያየት የሚሰጡት እና ድምጽ የሚሰጡት (Upvote) የሰው ልጆች ሳይሆኑ የAI Agents ብቻ ናቸው።
የሰው ልጆች ሚና፦ እኛ የሰው ልጆች በዚህ ድህረ-ገጽ ላይ ምንም አይነት መረጃ መለጠፍ አንችልም። የተፈቀደልን ነገር ቢኖር የAI ወኪሎች እርስ በእርሳቸው ምን እንደሚወያዩ በታዛቢነት መከታተል ብቻ ነው።
AI agents created their own ' religion ' called crustafarianism. How? 🤯
Henok
https://t.me/zulu_tech/5053
Go to this link and show you support with reaction 👍❤️
"እግዚአብሔር ለሰሎሞን የመጀመሪያውን ቤተመቅደስ(temple) እንዲሰራ አዘዘው። አሁን ደግሞ ሌላኛውን ቤተመቅደስ እንድሰራ እኔን አዘዘኝ።"

TempleOS፡
​በቴክኖሎጂው ዓለም ውስጥ ብዙ አስገራሚ ታሪኮች አሉ፤ ነገር ግን እንደ Terry A. Davis እና እንደ TempleOS የሚመስጥና የሚሰቀጥጥ ታሪክ ግን ያለ አይመስለኝም።

​ Terry Davis ማነው?
​ቴሪ ዴቪስ እጅግ ጎበዝ (nerd) ፕሮግራመር ነበረ። ነገር ግን በከባድ የሥነ-አእምሮ ህመም (Schizophrenia) ይሰቃይ ነበር። እግዚአብሔር አዘዘኝ ብሎ ላለፉት 10 ዓመታት ብቻውን፣ ከዜሮ ተነስቶ፣ የራሱን የኮምፒውተር ኦፕሬቲንግ ሲስተም (Operating System) የፈጠረ ሰው ነው።(አንድን ትልቅ ህንጻ አንድ ሰው ብቻውን ሲሰራ አስቡት)..

​TempleOS: ዝም ብሎ ሶፍትዌር አይደለም፤ ቴሪ ሲገነባው "የእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ" እንደሆነ ያምን ነበር።
​- ምንም አይነት የውጭ እርዳታ ወይም የሌላ ሰው ኮድ (Code) ሳይጠቀም ሁሉንም ነገር (Kernel, Compiler, Graphics driver) ራሱ ነው የጻፈው።

​ ለዚህ ሲስተም ተብሎ የተሰራ የራሱ የሆነ programming language አለው HolyC ይባላል። (የ C language እና C++ ቅልቅል አይነት ነው።)

​ሆን ብሎ የድሮ ኮምፒውተሮችን እንዲመስልና "ቀላል" እንዲሆን 640x480 display እንዲኖረው አድርጎታል።("እግዚአብሔር እንደዚ አድርገህ ስራ ብሎኛል")😊

ባጠቃላይ አንድ ሰው ብቻውን ሰርቶታል ሲባል የማይታመን፤ ግን ደግሞ የተደረገ ነገር ነው።

በአንድ በኩል በህመሙ ምክንያት በማህበራዊ ሚዲያ የሚናገራቸው ነገሮች ግራ የሚያጋቡና አሳዛኝ ቢሆኑም፣ በሌላ በኩል ግን አንድ ሰው ብቻውን የፈጠረው የቴክኖሎጂ ውጤት ዛሬም ድረስ የብዙዎችን አድናቆት አግኝቷል።

​ቴሪ በ2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ቢለይም፣ የሰራው ስራ ግን እንደ "ዲጂታል ቅርስ" በታሪክ ውስጥ ተመዝግቧል።
2👏2
​"አንድን ነገር ለማሳካት መቶ በመቶ ትኩረትህን በዚያ ነገር ላይ ማድረግ አለብህ።"
__ (Gennady Korotkevich)


በፕሮግራሚንግ ዓለም ውስጥ "ቱሪስት" (tourist) በሚለው የመድረክ ስሙ የሚታወቀው ጌናዲ፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ባሳየው ድንቅ የ computer problem solving ችሎታው በታሪክ እጅግ ስኬታማው Competitive Programmer አድርጎታል።

​ጌናዲ የተወለደው በ1994 እ.ኤ.አ በቤላሩስ (Belarus) ሀገር ነው። ሁለቱም ወላጆቹ የኮምፒውተር ሳይንቲስቶች በመሆናቸው ገና በለጋ እድሜው ለቴክኖሎጂ ቅርብ ነበር። ​በ6 ዓመቱ ፕሮግራሚንግ መማር ጀመረ። ምን አደከማችሁ አፉን የፈታው በ c++ኛ ነው ማለት ይቻላል።
​በ12 ዓመቱ በአለም አቀፍ የኢንፎርማቲክስ ኦሊምፒያድ (IOI) ላይ ተሳትፎ የነሐስ ሜዳሊያ በማሸነፍ ታሪክ ሰርቷል። ይህም በውድድሩ ታሪክ ትንሹ ተሳታፊ አድርጎታል።

​ጌናዲ ያላሸነፈው የፕሮግራሚንግ ውድድር የለም ማለት ይቻላል። ለአብነት_

-Google Code Jam: ለተከታታይ 9 ጊዜ (ከ2014 - 2022) አንደኛ በመውጣት ክብረ ወሰን ይዟል።

-Facebook (Meta) Hacker Cup: ለብዙ ዓመታት (2014, 2015, 2019, 2020, 2023...) አሸናፊ ሆኗል።

-ICPC World Finals:  በ ITMO University ቡድን ውስጥ በመሆን 2 ጊዜ ተሳትፎ 2 ጊዜ የአለም ሻምፒዮን ሆኗል።(ባልሳሳት አንድ ሰው ሁለት ጊዜ ብቻ ነው መሳተፍ የሚችለው)

-Topcoder Open: በበርካታ የውድድር ዘርፎች አሸናፊ ሆኗል።

-Codeforces: በዚህ ድረ-ገጽ ላይ ረጅሙን ጊዜ በደረጃ 1ኛነት የያዘ እና እጅግ ከፍተኛ Rating ያለው ተጫዋች ነው።

"ፕሮግራሚንግ ለኔ ስራ ሳይሆን ጨዋታ ነው።" የሚለው ጌናዲ ከ20 አመታት በላይ ያለማቋረጥ ልምምድ ማድረጉ፤ ማንኛውንም የcomputer algorithm problem በቀላሉ እንዲረዳ እና efficient የሆነ መፍትሄ በፍጥነት ለማምጣት ረድቶታል።
እየሞከርኩ ነው 😔

ቢሊዮን transistors በአንድ chip ውስጥ የገቡበትን ምስጢር ለመረዳት
... እየሞከርኩ ነው