NETRO TECH -AM
427 subscribers
493 photos
175 videos
24 files
201 links
🚀 Daily AI & Tech Updates | የየቀኑ AI እና Tech መረጃዎች
💻 Developer Tips & Useful Tools | ጠቃሚ Tools እና Tips
🌍 Tech Opportunities | Remote Jobs
📢 Stay Updated with NetroTech | ከቴክኖሎጂ ዘርፍ ጋር ዘመናዊ ይሁኑ
🔐 Cybersecurity Updates & Aware

📩 Contact: @Opengrowth
Download Telegram
Forwarded from Buna Tech ቡና ቴክ (Biruk Buraa)
6ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በይፋ ተከፈተ

“የሳይበር ደህንነት - የዲጂታል ኢትዮጵያ መሰረት” በሚል መሪ ቃል በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA የተዘጋጀው 6ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የሀገሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የፌዴሬሽን ም/ቤት አባላት፣ የግል ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA ዋና መ/ቤት ተጀምሯል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የሳይበር ደህንነት ወር በአለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ6ተኛ ጊዜ በመከበር ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ የሳይበር ወር መከበር ዋና አላማ ሀገራት ለዜጎቻቸው እንዲሁም ለተቋማቶቻቸው የሳይበር ደህንነት ግንዛቤን ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መርሃ ግብሮችን ለማከናወን እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

የእለቱ የክብር እንግዳ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ክብርት አለምጸሃይ ጳውሎስ 6ተኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በይፋ አስጀምረዋል፡፡ በመክፈቻ ንግግራቸውም አለም ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በገባችበት በዚህ ጊዜ “ከሳይበር ደህንነት” ርእሰ ጉዳይ ውጪ ወቅታዊ እና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ሌላ አብይ ጉዳይ ሊኖር አይችልም ብለዋል። “የሳይበር ደህንነት - የዲጂታል ኢትዮጵያ መሰረት” በሚል መሪ ቃል በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተዘጋጀውን 6ኛውን የሳይበር ደህንነት
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://www.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
GM fam
ቻይና AI በመታገዝ አርቴፊሻል ፀሀይ መገንቢያ አዲስ የ physics ዘዴ ሰርተዋል።

@netrotech9
🔥2
🔥2
Forwarded from Birhan Nega
Motivation ጥሩ ነው ግን 😀
Focus on Descpline
👍1👏1
Forwarded from Buna Tech ቡና ቴክ (Biruk Buraa)
አሁን ይሄ Computer ብባል አያስቅም
#info
🖲የኦፕንኤአይ (OpenAI) ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳም አልትማን፣ "አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ሥራህን ካጠፋው፣ ምናልባት ያ 'እውነተኛ ሥራ' አልነበረም" ብለዋል። ይህ ንግግር ብዙ ክርክር አስነስቷል።

የሳም አልትማን አቋም:
● "ሥራ" ማለት ምን ማለት እንደሆነ ዘመኑ ሲለዋወጥ ይለወጣል ብለው ያምናሉ።
● ከ50 ዓመት በፊት የነበሩ ሰዎች የዛሬውን ዲጂታል ሥራ አይተው "ይህ እውነተኛ ሥራ አይደለም" ሊሉ ይችሉ ነበር ይላሉ።
● AI በተደጋጋሚ የሚሰሩና አሰልቺ የሆኑ ሥራዎችን ያጠፋል፤ በምትኩ ግን የበለጠ ትርጉም ያላቸው፣ ፈጠራን የሚጠይቁ እና ሰብዓዊ የሆኑ አዲስ ሥራዎችን ይፈጥራል።
ተቺዎች የሚሉት:
● አንዳንድ ሰዎች፣ ይህ አባባል በAI የመተካት አደጋ የተጋረጠባቸውን ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አስፈላጊ ሠራተኞች ዋጋ የሚያቃልል ነው ይላሉ።
● ሌሎች ደግሞ፣ የሳም አልትማን ንግግር ግልጽ እውነት ነው፤ ሁሉም ሥራዎች ለዘላለም መኖር የለባቸውም ብለው ይከራከራሉ።

የአልትማን እውነተኛ መልዕክት:
➛ የወደፊቱ ጊዜ የAIን ኃይል ሰብዓዊ ብቃትን ለማሳደግ (ለማጎልበት) የሚጠቀሙ ሰዎች ነው እንጂ፣ ማሽን የሚሠራውን ሥራ ለመምሰል የሚሞክሩ ሰዎች አይደለም።

@netrotech9 | @netrotech9
👍1
#info

🔥 ጎግል ሁሉንም ሰው ሊያስደምም ነው። በዝምታ በጣም ግዙፍ የሆነ ነገር ሲያሰለጥኑ ቆይተዋል።
እ.ኤ.አ. በ2025 መጨረሻ፣ “ኮድ ማድረግ” ማለት መጻፍ ሳይሆን “ልማድ” ማለት ይሆናል።
ሀሳብዎን ብቻ ይገልጻሉ፣ ጥቂት አነቃቂ ነገሮችን ያስተካክላሉ፣ እና ጨዋታዎ ወይም መተግበሪያዎ ወደ ሕይወት ሲመጣ ይመለከታሉ።
C++ን እርሳው፣ የአገባብ ስህተቶችን (syntax errors) ይርሱት።
ንጹህ ፈጠራ ብቻ። በምናብ እና በሶፍትዌር መካከል ያለው ግርዶሽ ሊጠፋ ነው።
ከኮድ-በኋላ ዘመን እየገባን ነው።
ቢሊዮኖች ይገነባሉ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ፈጠራዎችን ያመጣሉ። የጎግል ሞዴል "ኮድ ማድረግ አልችልም" የሚለውን ነገር በ1995 ዓ.ም. “type አልችልም” እንደ ማለት እንዲመስል ያደርገዋል።

@netrotech9 | @netrotech9
1
🔔Grokipedia by xAI has just launched

The website of Grokipedia is now online on grokipedia(.)com. This is version 0.1, an early beta release.

To try: https://x.ai/
👍2
Forwarded from Cyber Security + Coding
የኢመደአ የሳይበር ታለንት ሰልጣኞች በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ አሸናፊ ሆነዋል

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA የሳይበር ታለንት ልማት ሰልጣኝ የነበሩት ቶማስ ብርቅነህ እና አለሙ ተስፋ በቻይና ጉዋንዡ በተካሄደው የብሪክስ አባል ሀገራት የክህሎት ውድድር ላይ የብርና የነሃስ ሜዳሊያ በማግኘት አሸንፈዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለሁለቱም አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ እያለ፤ የአስተዳደሩ የክህሎት ልማት ውጤት በመሆናቸው የተሰማውን ደስታ ይገልጻል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በ2017 ዓ/ም ባዘጋጀው የሳይበር ታለንት የክረምት መርሃ ግብር ሰልጣኝ የነበረው ቶማስ ብርቅነህ በውድድሩ ላይ ባቀረበው ፕሮጀክት፤ በ Artificial Intelligence ዘርፍ በ “LUCY: Advanced AI Robotics and IoT Integration”  የብር ሜዳልያ አሸናፊ ሆኗል፡፡ 

በተመሳሳይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በ2017 ዓ/ም ባዘጋጀው የሳይበር ታለንት የክረምት መርሃ ግብር ሰልጣኝ የነበረው አለሙ ተስፋ በ Future Technology ዘርፍ በ “Digital Business Card” ፕሮጀክት ላይ የነሃስ ሜዳልያ በማግኘት አሸናፊ ሆኗል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ላለፊት ተከታታይ አራት አመታት ባካሄደው የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም የተሳተፉና የተመረቁ ባለልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ ወጣቶች በተለያዩ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እያሳደሩ ሲሆን፤ የሀገራችንን የሳይበር ደህንነት አቅም በማሳደግ ባማቀጣጠል ረገድ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡


https://www.facebook.com/100064697533028/posts/pfbid02GBtKmfcpwVvjn4GZ79PiuxvbiknDaYzWGiDgpEJGZUS28WKusL46G32qyvb8b1sDl/