سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት
890 subscribers
6 photos
1 video
1 file
191 links
ይሄ ቻናል የቁርአንና የሀዲስን አስተምህሮቶች በሰለፎች አረዳድ ማሰራጫ ነው
ከፖለታካ ነፃ ነው።
Download Telegram
إبراهم لاقو:
s Next
ﻣﺤﺐ ﺍﻟﺪﻳﻦ ﺍﻟﻄﺒﺮﻱ
ኢስላማዊ ፊልም፣ድራማና ነሺዳ በኢስላም ምንፅር
ﺍﻟﺤﻤﺪ ﻟﻠﻪ ﻭﻛﻔﻰ ﻭﺍﻟﺼﻼﺓ ﻭﺍﻟﺴﻼﻡ ﻋﻠﻰ ﻋﺒﺎﺩﻩ ﺍﻟﺬﻳﻦ ﺍﺻﻄﻔﻰ ﻭﻋﻠﻰ ﺁﻟﻪ ﻭﺻﺤﻪ ﻭﻣﻦ ﺍﻫﺘﺪﻯ ﺑﻬﺪﻳﻪ ﺇﻟﻰ ﻳﻮﻡ ﺍﻟﺪﻳﻨﺰ ﻭﺑﻌﺪ :
ሰሞኑን በነዚህ ነገሮች ዙርያ በወጣቱ መኃል ንትርኩ በዝቷል: ከፊሉ ሐላል ነው ሌላው ሐራም ነው በሚል ለሁለት ተከፍሎ ሲሟገት ይታያል: በአመለካከትና በግምዛቤ መለያየቱ ችገር አልነበረውም: ግን ይሄን እንደ ትልቅ አጀንዳ አድርጎ በመያዝ የቀልብ መለያየት መፈጠሩ በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው: ቀደምቶች (ሰለፎች) ከዚህ በሚበልጥ የእምነትና (ዐቂዳ) የፊቅሂ ነጥቦች በአመለካከት ይለያዩ ነበር: ይሁን እንጂ ቀልባቸው አንድ ነበር: አንዱ ሌላውን ሊተችና ሊሰድብ ቀርቶ: ቅንጣት ታህል አንድነታቸውን የሚሰነጥቅ ቃልም ሆነ ተግባር አይታይባቸውም ነበር! ሁሉም በአመለካከቱና በግንዛቤው ይከባበር ነበር። የቦታ እጥረት ባይገድበን ኖሮ ብዙ ምሳሌዎችን ማቅረብ ይቻል ነበር: የፈለገ ሰው የታሪክ መዛግብትን በማገላበጥ ማግኘት ይችላል። ዲነል ኢስላምም የሚያስተምረን ይሄን ነው።
አንድ ታላቅ አሊም እነዲህ ይላሉ ((የግንዛቤ መለያየት ሀብት ነው: የቀልብ መለያየት ግን በሽታ ነው))
ከላይ የተጠቀሰው ርዕስ በዘመናችን ያሉ ዑለሞች በአመለካከት ለሁለት የተከፈሉበት ነገር ሲሆን: ሙስሊሙ ማህበረ ሰብ ከሁለቱ ለማስረጃ የቀረበውን መርጦ የመከተል መብት አለው: ግን ሌላውን አካል እኔ የመረጥኩትን ካልመረጣችሁ ብሎ በሙስሊሞች መኃል ጠብና ብጥብጥ መፍጠር፣ የሰለፎች ሳይሆን የአህሉል ቢድዓ መለያ ባህሪ ነው። ሼኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ– አላህ ይዘንላቸውና – እንዲህ ይላሉ: –ስለ አንድ በጊዚያቸው ኺላፍ የበዛበት ትንሽ አጀንዳ ከተናገሩ ቡኃላ (( ለእንደዚህ አይነት አጀንዳዎች ወገንተኝመት መፍጠር: የተከለከልነውን ልዩነት (ፊርቃ) የሚፈጥር ነገር ነው: ለደዚህም (መለያየት) የሚዳርገው በማህበረሰቡ መኃል የኺላፍ አጀንዳዎችን ማጉላት መውደድ ነው: ግን አጀንዳው በጣም ቀላል ነበር: በሸይጧን ግፊት የኺላፍ አጀንዳዎችን ማጉላት ናፍቆት ባይኖር ኖሮ። )) (መጅሙዑል ፈታዋ ሙጀለድ 22 ገፅ 436)
ይህን የመግቢያ ንግግር ከተረዳን: በሙስሊሙ መኃል ፊትና ለመፍጠር የሚነሱ የኺላፍ አጀንዳዎች ተገቢ ቦታቸውን መስጠት እንችላለን: አሊዚያ ግን ጠጠርን ተራራ፣ ሽንብራን ዱባ ያህል እያገዘፍን: በማይሆን ነገር ሙስሊሙን ማህበረ ሰብ መከፋፋል የተቀደሰ የአምልኮ ተግባር አድርገነው ልንይዘው እነችላለን! ግና የምንዘፈቅበት ኃጢያትና የሚያስከፍለው ዋጋ ቀላል አይምሰለን: የወንጀሉ ክብደት: ከኸምር፣ዚና፣ስረቆት ... ወዘተ የበለጠ መሆኑን ልናውቅ ይገባል: ምክንያቱም ሸይኹል ኢስላም እንደሚሉት: ((ኢስላም በሁለት እግር ነው የሚቆመው: ተውሂድና አንድነት። )) ስለዚህ የኢስላም ሁለተኛ እግር የሆነውን አንድነት ማፍረስ: የመጀመሪያውን እግር (ተውሂድን) ከማፍረስ የሚተናነስ አይደለም።
ወደ ርዕሳችን ስንመጣ: ከሁለቱ የዑለማዎች አመለካከት: ኢስልማዊ ነሺዳ፣ፊልምና ድራማ: ይዘታቸውና ግባቸው ኢስልምን ከመፃረር የፀዱ ከሆ: ይቻላል (ሐላል ነው) የሚለው አመለካከት ከማስረጃ አንፃር ለሐቅ የቀረበ ሆኖ እናገኘዋለን። እነደዚህም ስንል በወገንተኝነት ሳይሆን: ቀጥሎ ያሉትን ግልፅና ጠንካራ ማስረጃዎችን በመያዝ ነው:
1– ኢስላሚክ ነሺዳ:
ነሺዳ የሚለው ቃል አረብኛ ሲሆን: ትርጉሙ ግጥምን በሚያምር ድምፅና ቅላፄ ከፍ አድርጎ መዘመር ማለት ነው።
<=>: በኢስላም ያለው ሁክም (ብይን):
ነሺዳ እነደ ማንኛውም ንግግር: መልካሙ ሐላል ነው: አፀያፊው ደግሞ ሐራም ነው። ስለዚህ ነሺዳ ቀጥሎ ካሉት ክልከላዎች የፀዳ ከሆነ ሁክሙ (ብይኑ) ሐላል ነው።
ሀ– ይዘቱ ሐራም ከሆኑ ነገሮች የፀዳ ከሆነ። – ለምሳሌ: ከሺርክ፣ክህደት ፣ብለግና፣ ድንበር ማለፍና ከመሰሳሰሉ ኢስላም የሚከለክላቸው ቃላቶች–
ለ— ከሙዚቃ መሳሪያም የፀዳ ከሆነ።
ሐላል ለመሆኑ ማስረጃው:
1– ሁሉን አቀፍ የሆነ ፊቅሃዊ ቀመር (ቃዒደቱል ፊቅሂያህ) ነው።
ይህ ማለት ኢስላም ለሁሉም ነገር መሰረት(አስል) አድርጎለታል: የአንድን ነገር ሁክም (ብይን) ለማወቅ ከፈለግን:ቅድሚያ የዚያን ነገር መሰረት (አስል) ማወቅ አለብን: ያኔ የምንፈልገው ነገር ሁክሙ (ብይኑ) ቁልጭ ብሎ ይወጣልናል።
ይህ ሁሉን አቀፍ ፊቅሃዊ ቀመር እንዲህ የሚል ነው:
<< ማንኛውም ነገር ከንፁህ ዒባዳ (ዒባዳ መሕዷ) ውጭ ከሆነ: መሰረቱ (አስሉ) ሐላል ነው።>>
ዑለሞች እንዲህ በማለት ይገልፁታል:
( ﺍﻷﺻﻞ ﻓﻲ ﺍﻷﺷﻴﺎﺀ ﺍﻟﺤﻞ )
ስለዚህ ጉዳይ የበለጠ ለማወቅ በቀላሉ (ቀዋዒዱል ፊቅሂያ) በመባል የሚታወቀውን የሼኽ ናሲሩ ሰዕዲን ወይም የኢብኑ ኡሰይሚንን ኪታብ ማየት በቂ ነው።
ስለዚህ ነሺዳ፣ፊልምና ድራማን ሐራም የሚያደርጋቸው: ከቁርአንና ሐዲስ ግልፅ የሆነ ማስረጃ ከሌለ ሐላል ናቸው ማለት ነው። ሐላል ለመሆናቸው ማስረጃ አምጣ አይባልም: ይልቁንስ ማስረጃ የሚፈለገው ሐራም ነው ብሎ ከሚሞግተው አካል ነው ።
እነዚህ ነገሮች የሚፈቀዱ ለመሆናቸው ማስረጃ አምጡ ማለት: ዳቦ ሐላል ለመሆኑ ማስረጃ አምጡ እንደማለት ነው!
ይህን እውነታ ከኡሱልና ቀዋዒዱል ፊቅሂ እውቀት ጥቂት ግንዛቤ ያለው የሚያውቀው ነው: ይህን መሰረት (አስል) የተረዳና የተገበረው ሰው ብዙ ባለንበት ዘመን የሚለቀቁ ብዥታዎችን የሚያከሽፍበት ወሳኝ መሳሪያ በእጁ አለ: ከቁርአንና ከሐዲስ ግልፅ የሆነ ማስረጃ ያመጣ እንጂ ሌላ ማንም ሊረታው አይችልም: ከዚህ የእውቀት ዘርፍ ድርሻ የሌለው: በእውነት በጣም ትልቅ ኸይር የተነፈገ ነው: እንኳን ሁክም ሊሰጥ ይቅርና: የቁርአንና ሀዲስ ማስረጃዎችን መልእክትና ግብ በአግባቡ መረዳት ያዳግተዋል።
2– ሶሒህ የሆነ የነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሐዲስ ነው:
ሰዒድ ቢን ሙሰይብ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል: ((ሐሳን ቢን ሳቢት መስጊድ ውስጥ እየነሸደ: ዑመር በቆሪጥ (በቁጣ) ተመለከተው: ሐሳንም: ካንተ የሚበልጡት (ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እያሉ እንኳ እነሽድ ነበር አለው። ....)) (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ከሐዲሱ የምንማረው መልካም ነሺዳ መስጊድ ውስጥ ቢሆንም ምንም ችንግር እንደሌለው ነው።
ኢማሙ ነሳኢ (መልካምን ግጥም መስጊድ ውስጥ መነሸድ ስለመፈቀዱ) በሚል ርዕስ (ሱነኑ ነሳኢ ገፅ 488)፣
ኢማሙል ቡኻሪ (መስጊድ ውስጥ ስለመግጠም) በሚል ርዕስ (ፈትሁል ባሪ ሙጀለድ 1 ገፅ 649) መዘገባቸው:ነሺዳ መስጊድ ውስጥ ቢሆንም ምንም ችግር እንደሌለው ያመላክታል።
ኢብኑ ሐጀር ኢማሙል ቡኻሪ በዚህ ርዕስ ስር ያመጡትን ሀዲስ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ: ((የግጥሙ ይዘት ሐቅ ከሆነ መስጊድ ውስጥም ቢሆን ይፈቀዳል: ማንኛውም ሐቅ የሆነ ንግግር እንደሚፈቀደው: ሌላ ባጢል የሆኑ ንግግሮች እንደሚከለከሉት አይከለከልም))
ኢማሙ ቲርሚዚ እንዲህ ይላሉ: ((መልካም ግጥም መስጊድ ውስጥ መነሸድ እንደሚፈቀድ ብዙ ሐዲሶች ከነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ተዘግበዋል)) (ሱነኑ ቲርሚዚ ገፅ148)
የዑለማዎችን ንግግር ተመልከቱ: ነሺዳው ይዘቱ መልካም ከሆነ መስጊድ ውስጥ እንኳ ቢሆን እንደሚፈቀድ ነው የሚያመላክተው።
√ የዑመር ቢን ኸጧብ ሐሳንን መቃወም ግጥሙን ሳይሆን መስጊድ ውስጥ መሆኑን ነው።
3– በዘመናችን ያሉ ብዙ ታላላቅ ዑለሞች ነሺዳ እንደሚፈቀድ ፈትዋ ሰጥተዋል: የሁሉንም ማቅረብ የቦታው ጥበት ስለማይፈቅድልን ጥቂቱን እንመልከት:)
ሀ– የዘ
ውትር ፈትዋ ኮሚቴ (

ለጅነት አድዳኢማህ):
ጥያቄ: የሙዚቃ ሐራምነትን እናውቃለን: በኢስላሚክ ነሺዳ ብንለውጠው ሁክሙ(ብይኑ) ምን ይሆናል? ድቤ ያለበትን ነሺዳስ ማዳመጥ ይቻላልን?
መልስ: እንዳልከው ሙዚቃ ሀራም ነው። በሙዚቃ ፈንታ በኢስላሚክ ነሺዳ መለወጥ ይቻላል: ኢስላሚክ ነሺዳ ውስጧ: ተግሳፅ፣ጥበብ፣በኸይር ነገር ላይ ማበረታታት፣ ከመጥፎ ነገር ማራቅና የመሳሰሉትን ይዛለችና: ግን እንደ ዚክር የሚዘወትረው ነገር መሆን የለበትም: አልፎ አልፎ: የሰርግ፣የጉዞና የጂሃድ አጋጣሚዎች ሲኖሩ: እንደዚሁም ድብርትና የነፍስ ወደ ሀጢያት ማዘንበል ሲታይባት: መሆን አለበት።
ከዚህ ሁሉ ግን ቁርአን መቅራትና ዚክር ማድረግ በላጭ ነው። ሶሃቦች ትኩረታቸው ወደ ቁርአንና ሀዲስ ነበር: ሆኖም በተለያየ ጋጣሚ የሚዘምሩት ነሺዳም ነበራቸው።
ግን ነሺዳው የሙዚቃ መሳሪያ ካለው የሚፈቀድ አይሆንም። (ፈታዋ ለጅና አድ ዳኢማህ 4ኛ ሙጀለድ ገፅ 532–534) የቦታ እጥረት ስላለ ጥያቄውንም መልሱን አጠር አድርጌ ነው ያቀረብኩት: ሙሉን ጥያቄ ከነመልሱ ማየት የሚሻ በተሰጠው ዋቢ መግኘት ይችላል። አሊያም (ፈታዋ በለዲል ሐራም ገፅ 876—877) ላይ ያገኘዋል።
ለ– ኢማሙል አልባኒ አላህ ይዘንላቸው:
ጥያቄ: በወጣቶች መኃል ተሰራጭቶ የሚታየው ኢስላሚክ ነሺዳ የሚባለው ነገር ሁክሙ ምንድን ነው?
መልስ: ነሺዳው ያዘለው መልክት ኢስላሚክ ከሆነና ከሙዚቃ መሳሪያ ከፀዳ ምንም ችግር የለውም: ግን የሚፈቀድ ለመሆኑ ሁለት ቅድመ ሁኔታዎችን ልገልፅ እወዳለሁ:
1– ሸሪዓን ከሚፃረር ነገር የፀዳ መሆን አለበት ።
2– የዘውትር ስራ አድርገን መያዝ የለብንም: ምክንያቱም ቁርአን ከመቅራትና ዒልም ከመማር ያዘናጋልና።
ድቤን መጠቀም ሴቶች ለሰርግና ለበአል መጠቀም ይፈቀድላቸዋል: ለወንዶች ግን በፍፁም።
(ፈታዋ ኪባሩ ዑለማኢል ኡማህ ገፅ 1236)
ከዚህ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ፈትዋቸውን (ፈታዋ አል አልባኒ ፊል መዲነቲ ወል ኢማራት ገፅ 176) በተሰኘው ኪታብ ላይ እናገኛለን: ግን ለየት የሚለው: (ኢስላሚክ ነሺዳ ሳይሆን መዝናኛ ነሺዳ ነው መባል ያለበት ያላሉ።)
√ የስሙ መለያየት አያጣላንም: በፈለግነው ስም እንሰይመው: ዋናው ነገር ሐላል ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነው: የአልባኒ ፈትዋ ነሺዳው የተቀመጠለትን ቅድመ ሁኔታ ካሟላ የሚፈቀድ እንደሆነ ነው የሚያመላክተው።
ሐ– አል ኢማም አብደላ ቢን አብዲረህማን አል ጂብሪን – አላህ ይዘንላቸው–
ጥያቄ: ነሺዳ ማለት ምን ማለት ነው? ነሺዳ: ለወንዶች፣ለሴቶች፣ እንዲሁም ለህፃናት ሴቶች በኢስላም እንዴት ይታያል?
መልስ: ነሺዳ ማለት ግጥምን በአንድ ድምፅ ወይም በሁለት ድምፅ እየተቀባበሉ መዘመር ማለት ነው። ከፊል ዑለሞች ከሱፊዮችና ከዘፋኞች ጋር ያመሳስላል በማለት ጠልተውታል: ግን እኔ ዘንድ ተመራጩ ይዘቱ ሐራም ከሆነ ነገር ከፀዳና መልክቱ መልካምና ኢስላማዊ ከሆነ: የተፈቀደ መሆኑ ነው። ጥቅሙም በጣም የጎላ ነው: ከዘፈንና ወደ መጥፎ ምግባር ከሚገፋፉ ነገሮች የፀዳ ሲሆን። (አል ከንዙ ሰሚን ፊ ፈታዋ ኢብኒ ጂብሪን ገፅ 371)
2– ኢስላሚክ ፊልምና ድራማ:
ፊልምና ድራማ ማለት:የሰው ልጅ ነገሮችን በቀላሉ እንዲረዳ የሚያደር ምሳሌያዊ ተግባር ነው።
ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶችን ካሟላ የሚፈቀድ ይሆናል:
ሀ– ይዘቱ ከሀራም ነገር የፀዳ ከሆነ: ሀራም ስንል:–
– አላህን፣መላኢኮችንና ነብያቶችን መስሎ መተወን የሌለበት: መሆን አለበት። ከፊል ዑለሞች ሶሃባዎችን ይጨምራሉ: ሌሎች ደግሞ: ክብራቸውን ከማጉደፍና በነርሱ ላይ ከመቅጠፍም የፀዳ ከሆነ ችግር የለውም ብለዋል።
ሐቁም ሶሃባዎችን መስሎ መስራት ችግር የለውም የሚለው ነው: ግን ክብራቸውን ከማጉደፍና: በነርሱ ላይ ከመቅጠፍ የፀዳ ሲሆን ነው። የሼኽ ኢብኑ ጂብሪን ፈታዋ ላይ እንደሚመጣልን።
– ከተከለከሉ ቃላቶች የፀዳ መሆን አለበት: ከኩፍር፣ከስድብ፣ብልግና፣ውሸት... ወዘተ የፀዳ መሆን አለበት:
ውሸት ሲባል ግን ተዋንያኑ መስሎ የሚሰራምን አካል ገፀ ባህሪ ተላብሶ የሚናገራቸው ንግግሮች ከውሸት አይቆጠሩም: ምክንያቱም ምሳሌ እየሰጠ ነውና። የሼኽ ኢብኑ ዑሰይሚንና ኢብኑ ጂብሪን ፈታዋ ላይ እንደምንደርስበት።
– ወንድ ሴትን ሴት ወንድን መስሎ ከመስራት የፀዳ መሆን አለበት።
– አጅነቢ የሆኑ ወንድና ሴቶች: ከመጨባበጥና መተቃቀፍ ንፁህ መሆን አለበት።
ለ– መልክቱና ግቡ ኢስላምን የሚፃረር መሆን የለበትም።
√ የተቀመጥለትን ቅድመ ሁኔታዎችን ካሟላ የሚፈቀድ ለመሆኑ ማስረጃው:
ለነሺዳ ያቀረብነው የመጀመሪያው ማስረጃ ለዚህም የሚያገለግል ጠንካራ ማስረጃ ነው።
ሐራም ነው የሚለው አካል ግልፅና የማያሻማ ማስረጃ ማቅረብ መቻል አለበት: ግን ማምጣት አይችልም: ምንአልባት የተለጣጠፉ ከሸረሪት ድር የማይሻል ነገር ሊያመጣ ይችላል: ግን ይህን ጠንካራ ፊቅሃዊ ቀመርን ሊቋቋም የሚችል አይደለምን: ምክንያቱም አንድን ነገር ከመሰረቱ ለማውጣት የተለጣጠፈ ማስረጃ ሳይሆን ግልፅና የማያሻማ ማስረጃ ነው የሚያስፈልገውና።
ሌላ ቀመሮችንም ማምጣት ይቻላል:
( ﺍﻷﻣﻮﺭ ﺑﻤﻘﺎﺻﺪﻫﺎ ‏)
‏( ﺍﻟﻮﺳﺎﺋﻞ ﻟﻬﺎ ﺃﺣﻜﺎﻡ ﺍﻟﻤﻘﺎﺻﺪ )
መዳረሻዎች የግባቸውን ሁክም (ብይን) ነው የሚይዙት:
– ግቡ ሐላል ከሆነ መዳረሻውም ሐላል ይሆናል።
– ግቡ ሐራም ከሆነ መዳረሻውም ሐራም ይሆናል።
ስለዚህ የፊልሙና የድራማው ግብ ጥሩ ከሆነ: ሰውን ለማስተማር፣ኢስላም ለማስተዋወቅና ሰዉ ከመጥፎ ተግባር እንዲቆጠብ ለማድረግ ከሆነ: ይፈቀዳል ማለት ነው: ግን የፊልሙና የድራማው አላማ ኢስላምን የሚፃረር ከሆነ ሐራም ለመሆኑ ሁሉም ይስማማበታል።
√ የፊልምና ድራማ ተውኔት ይፈቀዳል የሚሉ የዘመናችን ዑለማዎች:
ሀ– ሼኽ መሐመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሰይሚን አላህ ይዘንላቸው:
ጥያቄ: ቲያትርና ድራማ ለዳዕዋና ለመዝናኛ ከሆነ ሁክሙ (ብይኑ) ምንድን ነው?
መልስ: ድራማው ይዘቱ ከሐራም ነገር ከፀዳ ችግር አለው ብዬ አላስብም:ከሐራም ነገር የፀዳ ሰንል: ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፣ሶሃቦችንና ታላላቅ ዑለማዎችን መስሎ መተወን፣ውሸት፣ ወንድ ሴትን:ሴት ወንድን መምሰል፣ካፊር ፋሲቅና ሙናፊቅን መስሎ መተወን የሌለበት ማለት ነው። ተውኔት ማለት በተግባር ምሳሌ መስጠት ስለሆነ: ሐራም ከሆኑት ነገሮች አይቆጠርም። ይህ ደግሞ ውሸት ነው አይባልም: ምክንያቱም ተዋንያኑ በተውኔት ውስጥ አንድ ሰውን መስሎ ሲሰራ ምሳሌ ለመስጠት እንጂ እኔ ያ ሰው ነኝ ለማለት አይደለም። (ፈታዋ ኪባሩ ኡለማኢል ኡማህ ገፅ 1132)
ተቀራራቢ የሆኑ ተጨማሪ የሼኹን ፈትዋ ማግኘት የሚሻ (ሲልሲለቱ ፈታዋ ኑሪ ዓለ ደርብ ካሴት ቁጥር 328፣ ሲልሲለቱ ሊቃኢል ባቢል መፍቱህ ቁጥር: 70&77)
ለ–የሳኡዲ የፈትዋ ኮሚቴ አባል የነበሩት: ሼኽ አብዱላሂ ቢን አብዲረህማን አል ጂብሪን አላህ ይዘንላቸው:
ጥያቄ: ሶሓባዎችን፣ዑለማዎችና ሙጃሂዲኖችን መስሎ መተወን: ወይም አንድን መህበረሰባዊ ችግር ለመፍታት፣ሰውን በመልካም ለማዘዝና ከመጥፎ ለመከልከል: ድራማ መተወን ሁክሙ (ብይኑ) ምንድን ነው?
መልስ: ቁርአንና ሐዲስ ነገሮችን በሚታወቁ ነገሮች ምሳሌ ሰጥተው እነደሚያስተምሩ ይታወቃል: ተውኔት ነፍስ ላይ በጣም ተፅኖ ፈጣሪና አዕምሮ ላይ የሚቀረፅ ነገር በመሆኑ: ያዳመጠው ወይም የተመለከተው ሰው: በቀላሉ አይረሳውም: ስለዚህ በቁርአን ውስጥ የተሰጡ ምሳሌዎችን መተወን ምንም ችግር የለውም: ...(ሁለት ምሳሌዎችን ሰጡ) : ስለዚህ ጠቃሚ ተውኔቶች: ታሪክን ወይም ጠቃሚ የሆነ ምሳሌን በመስጠት የሚያሰተምሩ ከሆነ: ችግር የለውም።
እንደዚ
ያውም ሶሃባዎችን መስሎ
ለዒድ #ማስታወሻ
1- በዒድ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት መለዋወጥ ከሰለፎች የተገኘ ስራ ነው።ዒድ ሙባረክ፣ ዒድ ሰዒድ እና መሰልየመልካም ምኞት መግለጫዎችን እንድሁም ዱዓዎችን መባባል በራሱ አምልኮት አይደለም። ዐዳ( ባህል ) ዉስጥ ነው የሚመደበው።ስለሆነም ከዒድ ሶላት ቀድሞ የደስታ መግለጫዎቹን መለዋወጥ ይቻላል። ነገር ግን ሰለፎች የሚጠቀሙት ዒድ ሶላትን ሰግደው ካጠናቀቁ በኋላ ነበር።ስለዚህ ሶላታችንን ሰግደን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቶቻችንን ብንለዋወጥ በላጩና የተሻለው መንገድ ነው። ቀድሞ መልእክት የላከም አይወቀስም::
2- ዒድ የደስታ ቀን ነው።ስለሆነም ሀዘንን የሚቀሰቅሱ፣ናፍቆትን የሚጭሩ መልእክቶችን ማስታወስ አይገባም።በዒድ ቀን ጸብና ጭቅጭቅም ተገቢ አይደለም። ያጠናቸው ሁሉ አይመለሱምና ባለፈው አመት ዒድ ከኛ ጋ የነበሩትን በማነሳሳት የዛሬን ደስታ ማደፍረስ ተገቢ አይደለም።
3- ቤተሰብና ወዳጆችን መዘየርም የሚበረታታ ስራ ነው።ዒድ በሙስሊሞች መካከል ያለዉን ጥብቅ ትስስር የሚናሳይበት አጋጣሚ ነው። መልእክተኛው "ጎረቤቱ እየተራበ እሱ ጠግቦ ያደረ ሰው ወላሂ እሱ እምነቱ ሙሉ አይደለም" ብለዋልና የራስ የራሳችሁን ብቻ አታስተካክሉ።የጎረቤትም ሀቅ አለ።ስታረዱ ከፍያለዉን እረዱ(ከቻላችሁ)።ስትቀቅሉ መረቁን በርከት አድርጉት።የጎረቤቶቻችሁን ሁኔታ ተከታተሉ።
4- ዒድ ሶላት በእያንዳንዱ ግለሰብ ላይ የተጣለ ግዴታ ነው።ስለዚህ ሴቶች የቤት ዝግጅት ላይ በማተኮር የዒድ ምንዳ እንዳታጡ።ሌባ እስካልተሰጋ ድረስ የቤት ሰራተኞቻችሁንም ለኢድ ሶላት እንድሄዱ መፍቀድ ብቻ ሳይሆን ማዘዝም አለባችሁ።ሀይድ ላይ ያሉ ሴቶች ሳይቀሩ መሳተፍ አለባቸው።ባይሆን ሶላት እንዳይሰግዱ።
5- የዒድ አልፊጥር ሶላት በማለዳ መሰገዱ ሱና መሆኑን አትዘንጉ።ስለዚህ ፈጥናችሁ በመስገጃ ቦታ ተገኙ።
6- ረመዳን መጠናቀቁ ከተረጋገጠበት ደቂቃ ጀምሮ ተክቢራ ማድረግ እና አላህን ማመስገን የተወደደ ስራ መሆኑን አትዘንጉ። ተክቢራው የተደነገገው ለኢድ ሶላት ጉዞ ሲጀመር አይደለም። ረመዳን መውጣቱ ሲታወቅ ጀምሮ ነው።
7- በሁሉም ቦታዎች ድምጽን ከፍፍ አድርጎ ተክቢራ ማድረጉ ሱና ነው።ሆን ብሎ በማሰብ ወይም በአንድ መሪ ተከትሎ በአንድ ድምጽ ተክቢራ ማለቱ የማይገባ ስራ ነው። ሁሉም በግል በግሉ ይጩህ። ሳይታሰብበት የሁሉም ሰው ድምጽ በአንድ ላይ ከወጣ ግን ችግር የለዉም።
8- ሶላቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ኹጥባዉን መከታተል ሱና ነው።እንደግዴታ በመቁጠር (ተቀመጡ፣ ኹጥባው የሶላቱ ክፍል ነው ...) እያሉ ሰዎችን ማስቸገር ተገቢ አይደለም። ነብያችን የፈለገ ይከታተል. ያልፈለገ ይሂድ የሚል መልእክት ያለው ሀዲስ ተናግረዋል።
9- የዒድ አልፊጥር ሶላቱ እንደተጠናቀቀ ተክቢራዉም አብሮ ይጠናቀቃል።
10- ዒድ እለተ ጁሙዐ ከሆነ የጁሙዓን ሶላት መስገድ ግዴታ አይደለም። አስተዉሉ ዙህር የቀረ እንዳይመስላችሁ። በጁሙዓ ምትክ ዙህር መስገድ ግዴታ ነው።
11- ዒድ የምግብና የመጠጥ ቀን ነው። ነገር ግን ሁሉም በልክ ሊሆን ይገባል። ምግብ ማብዛት ለዲንም ለጤናም ጥሩ አይደለም። ምናልባት ከጠቀመ የሚጠቅመው የግል- የህክምና ተቋማትን ብቻ ነው።
12- ለኢድ ሶላት ከመዉጣታችን በፊት ማፍጠር ግዴታ ነው። በቴምር ማፍጠሩ ሱና ነው።በሀገራችን ገንፎ የተለመደበት ምክንያት ምን ይሆን? ብቻ በገንፎም ቢሆን ባህላችን ነውና ችግር የለዉም። ነገር ግን ሱናው እንድያብብ የዒድ እለት በቴምር ማፍጠር ሱና መሆኑን እናሳይ።ቴምሮቹ ደግሞ ነጠላ ቁጠር ይኑራቸው።1፣ 3 ፣5፣ 7 ... ስለዚህ ስንበላ እየዘገን ሳይሆን እየቆጠርን ይሁን።
13- የዒድ ቀን መተጣጠብ መቀባባት ይወደዳል። ባይሆን ሴቶች የሚጠቀሙት ኮስሞቲክስ መልካቸውን የሚቀይር፣ማራኪ መዓዛ ያለው እንዳይሆን። እህቶች በኢድ ቀን የዝሙተኝነት ወንጀል መሸከም የለባችሁም።ትጥበቱ ደግሞ ፈጅር ከወጣ በኋላ ቢሆን ይመረጣል።
14- ለዒድ ያማሩ ልብሶ ችን መለባበስም ይወደዳል።#ለኢድ ያለሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ ይባል የለ።ባይሆን አለባበሳችሁ ሸሪዓው ያስቀመጠዉን መስፈርቶች መጠበቁን አትዘንጉ።ጠባብ፣ አጭር፣ ስስ፣ ወጣ ከማለቱ የተነሳ መጠቋቆሚያ የሚደረግን ልብስ ተጠንቀቁ።
15- ወንዶች ደግሞ አጉል ባህል ጀምራችሁብናል።ለሀጅ ስርአት የተደነገገውን አለባበስ ለዒድ መልባስ የሀጅን ልዩ መገለጫ ማራከስ ነውና ነጭ ፎጣና ሽርጥ እየለበሳችሁ ሀጃጆችን ወይም ዑምራ ላይ ያሉ ሰዎችን ለመምሰል አትሞክሩ።
16-
ለሚስኪኖች ልብስ መስጠት ካልቻላልን እናውሳቸው። ትውስትም ከመልካም ስራ ይመደባል።በተለይ የዒድ ቀን አድስ ልብስ ለሌላቸው ወንድምና እህቶች ልብሶችን ማዋስን የሚመለከት ሀዲስም ተላልፏል።
17- የዒድ ዕለት የምንጓዝባቸውን መንገዶች ማለያየት ተወዳጅ ስራ ነው።የምንሄድበትና የምንመለስበት ቦታ የተለያየ ይሁን።ጠላቶች ይቆጩ ዘንድ በሁሉም አቅጣጫ መንገዱን ሁሉ እናጥለቅልቀው። ብዛታችንን ይወቁ። አላህ ዘንድ መስካሪ ቦታዎችም ይብዙልን።
18- የዒድ ሶላት የሚሰገደው ሙስሊሞች ሁሉ በሚሰበሰቡበት ሰፊ ቦታ ነው። በመካከላችን በሚንጸባረቁ አንዳንድ ልዩነቶች ምክንያት በየጓዳና በየጎድጓዳው መስገድ ተገቢ አይደለም።
19- የዒድ ቀን የተለያዩ ጨዋታዎችን ማዘጋጀትና በጨዋታዎቹ መሳተፍም ይፈቀዳል።ሸሪዓዉን ባማከለ መልኩ ጦር መወራወር፣ሩጫ፣ኳስ......መሳተፍ ይቻላል።መመልከትም ጭምር
20- የዒድ ሶላት ከኢማሙ ጋር መስገድ ያልቻለ ( ያመለጠው ) ሰው ብቻዉን የዒድ ሶላት አሰጋገድን ተከትሎ መስገድ ይችላል። ይህ የአነስ፣ የዐጧእ፣ የኢክሪማ እንድሁም የኢማሙ ቡኻሪ አቋም ነው።
21- ወደ መድገጃ ቦታ የሚጓዝ ሰው በመኪና፣ፈረስ......... ከሚጠቀም ይልቅ በእግር መጓዙ በላጭ ነው። ከያዛችሁ ደግሞ ብቻችሁን አታሽከርክሩ ደካሞችን መርዳት አትርሱ።
#መጨረሻም
ዒድን በብቸኝነት የምታከብሩ ሁሉ አላህ ከቤተሰቦቻችሁ ጋር በሚያምር ኑሮ የምታከብሩበትን ጊዜ ያቅርብላችሁ።
ሸሪዓዉን በጠበቀ መልኩ --- ፏ ብትን ----የምትሉበት የደስታ ዒድ ይሁንላችሁ።
ዉዱ ነብያችን ሙሀመድ{ሰዐወ} በመጨረሻ ሀጅ ላይ ያደረጉት
ንግግር ይህን ይመስላል።
ሠዎች ሆይ ከዚህ አመት በኃላ ከመካከላችሁ እንደገና ለመገኘት
መብቃቴን አላውቅምና ልብ ብሎ የሚያዳምጥ ጀሮ አውሡኝ።
ዛሬ የምነግራችሁ ቁም ነገር በጥሞና አዳምጡ በእለቱ
ከመከላችሁ ለመገኘት እድል ላልገጠማቸው መልክቴን
አድርሡ።
ሠዎች ሆይ የዛሬውን ወር የዛሬውን ቀን ይህች ከተማ
የተቀደሡና የተከበሩ መሆናቸውን የምታውቁትን ያህል
የእያንዳንዱ ሙሥሊም ህይወት እና ንብረት በክብር እንድትይዙ
አደራ ተጥሎባችኃል በእጃችሁ የሚገኙ የአደራ እቃዎች
ለባለቤቶቻቸው መልሡ።
ማንም ሠው እንዳያጠቃችሁ በማንም ሠው ላይ ጥቃት
አታድርሡ። እርሡም ተግባራችሁን ይመዝናል። አራጣ እንዳትበሉ
አላህ(ሱወ) ከልክሎዋችኃል። ሥለዚህም ለመክፈል ቃል
የገባችሁትን የብድር ወለድ መክፈል ከእንግዲህ እርም
ተደርጎባችኃል።
ሀይማኖታችሁን ለመንከባከብ ከሠይጣን ተጠንቀቁ። በትልቅ
ጉዳዮች እናንተን አሣሥቶ በዚህች ምድር ላይ አዘቅት ውሥጥ
ለመጣል ሚያደርገው ሙከራ ተሥፋ ሥለቆረጠ በጥቃቅን
ጉዳዮች ሠይጣንን ተከታዮች እንዳትሆኑ ነቅታችሁ ጠብቁ።
ሠዎች ሆይ በሤቶቻችሁ ላይየተወሠኑ መብት ያላችሁ በመሆኑ
እርግጥ ነው። ነገር ግን እነርሡም በእናንተ ላይ መብት
አላቸው። በእናንተ ቁጥጥር እሥካሉ ድረሥ የመመገብ
የማልበሥና በርህራሄ የመያዝ ግዴታ ይኖርባችኃል። ሤቶቻችሁ
የኑሮ ጓደኞቻችሁ እና የቅርብ ደጋፊዮቻችሁ በመሆናቸው
በርህራሄ አግባብ ባለው ሁኔታ ተንከባከቡዋቸው። እናንተ
ከማትፈልጉት ሠው ጋር ጓደኝነት እንዳይመሥርቱ ቤታችሁ
በጭራሽ እንዳይደፈር ማድረግ የናንተ መብት ነው።
ሠዎች ሆይ በሚገባ አድምጡ! አላህን ተገዙ! በቀን አምሥት
ጊዜ ሠላት ሥገዱ የረመዳን ወር ፆምንም ፁሙ ከሀብቶቻችሁ
ዘካን አውጡለት ከተቻላችሁ ሀጅንም አድርጉ። እያንዳንዱ
ሙሥሊም ለሌላው ሙሥሊም ወንድም መሆኑን ታውቃላችሁ።
ሁላችሁም እኩል ናችሁ። ማንም ሠው ከሌላው የሚበልጥበት
መንገድ የለም አላህን በመፍራትና በጥሩ ምግባሩ እና ተግባሩ
ቢሆን እንጂ ።
አሥታውሡ!!! አንድ ቀን በአላህ ፊት ቀርባችሁ ለሠራችሁት ሥራ
ትጠየቃላችሁ ሥለዚህም ተጠንቀቁ እኔ ካለፍኩ በኃላ አላህን
ከመፍራት ጎዳና እንዳታፈነግጡ
ሠዎች ሆይ፦ ከእኔ በኃላ አዲሥ ነብይ አይመጣም አዲስ
እምነትም አይወለድም በሚገባ ተመራመሩ።
ይህ የድንቆች ድንቅ የሆነን የዉዱ ነብያችን(ሰዐወ) መልክት
አንብበው ሢጨርሡት በፍፁም እርሦ ዘንድ እንዲቀመጥ
አይፈቀድም። ቢያንሥ ለሀያ ሙሥሊም ወንድሞችና እህቶች ሼር
ያድርጉ የትኛው ሥራችን ለጀነት ሠበብ እንደምትሆነን
አናውቅምና፤ አንድ ሀሠናት(አጅር) አዱንያ በውሥጧ እና
ውጭዋ ከያዘችው ነገር ትበልጣለችና።
ማንበብ ሠውን ምሉእ ያደርጋል ማንበብ የሥኬት መንገድን
ይጠቁማል ካላነበብክ በእውቀትህ አትጨምርም ካላነበብክ
በአሥተሣሠብህ አትሻልም ካላነበብክ ለነገ ብትደርሥም ከዛሬ
አትሻልምና።
Ebadurehman Abu Hamza
ዒድ ሙባረክ!
እንኳን ለ 1439ኛው የኢድ አል ፊጥር በዓል በሰላም አደረሰን፡፡
አቡ ዳውድ ኡስማን
የሸዋል ወር ጨረቃ በሌሎች ሃገራት እና በሳኡዲ አረበያ በመታየቷ የታላቁ የረመዳን ፆም በዛሬው እለት ሐሙስ ጁን 14/2018 መጠናቀቁ ታውቋል፡፡ የኢድ አል ፊጥር በዓል በነገው ዕለት ጁምአ ጁን 15/2018 መሆኑ ተገልፆል፡፡
አላህ ፆማችንን ይቀበለን
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም!
ሰበር ዜና
የደሴዎቹ ጀግኖች ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተፈቱ!
ሙጂብ አሚኖ ዘ ኢስላም
የፌደራሉ መንግት ከአቃቤ ህግ ጋር በመተባበር ለ 300 እስረኞች ምህረት ማድረጉን ከሰአታት በፊት መዘገባችን ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም በአሁኑ ሰአት የደሴ ጀግኖቻችን የመዝገቡ ተጠሪ አህመድ ኢድሪስ ገበየሁ፣ይመር ሁሴን ሞላ፣ ሷሊህ መሀመድ አብዱ፣ አንዋር ኡመር ሰዒድ ፤ ዑመር ሁሴን ከቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት እየወጡ እንዳለ ታውቋል።
በአህመድ እድሪስ መዝገብ የተካተቱት ሙሀመድ ዩሱፍ መሀመድ እስከአሁን አልተፈቱም። ምናልባት በአንዱ ክሳቸው የገንዘብ ቅጣት ስላለባቸው ከሱ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ሊዘገዩ እንደቻሉ መረጃዎች ጠቁመዋል።
በእስረኞች መፈታት ጉዳይ ገፃችን በከፍተኛ ሁኔታ የፕሮፖጋንዳና መንግስትንና አቃቤ ህግን እንዲፈቱ ለተከታታይ ወራት ሲጠይቅ የነበረ በመሆኑ ፍሬውን በአላህ ፈቃድ እያየን በመሆኑ ደስታችን ወደር የለውም።
አላሃምዱሊላህ!
۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
ላይክ ያላደረጋችሁ፤ ይህን ክፈቱና የሙጂብ አሚኖን ፔጅ like አድርጉ
https://www.facebook.com/blogger.mujib
*ሰበር ዜና!*
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የሕዝበ ሙስሊሙን ጥያቄ ሁሉ በቀጣይ ሳምንት በመነጋገር ለመፍታት መንግሥታቸው ዝግጁ መሆኑን ዛሬ ምሽት ሰኔ 8 ቀን 2010 ከምሽቱ በ3:50 ላይ ዒድ አል-ፊጥርን አስመልክተው በጽሕፈት ቤታቸው መግለጫ በሰጡበት ወቅት ገለጹ፡፡

© *Abubeker alemu muhe*
[١٦/‏٦ ١:٢١ م] منتهي: #የስድስቱ_ቀን_የሸዋል_ፆም- ድንጋጌዎች እና ትምህርቶች

ከረመዷን በኋላ የስድስቱ ቀን የሸዋል ፆም ሱና ሙአከዳ (ወደ ግዴታ የሚጠጋ ጠንከር ያለ ሱና) ነው። ስለዚህ ስለ ፆም በሚያነሳሳው ንግግራቸው የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም ከረመዷን በኋላ እነኚህን ስድስት የሸዋል ቀናት የፆመ ሰው አመቱን ሙሉ እንደፆመ እንደሚቆጠርለት ተናግረዋል።

ከዚህም በመነሣት ረመዷንን አስከትሎ እነኚህን ስድስት ቀናት በየአመቱ መፆምን ያዘወተረ ሰው እድሜውን በሙሉ እንደፆመ ነው ማለት አንችላለን። ከአቡ አዩብ አል-አንሷሪ በተላለፈው ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም

من صام رمضان ثم أتبعه ستًا من شوال فكأنما صام الدهر كله

“ረመዷንን የፆመና ከሸዋልም ስድስቱን ያስከተለ ሰው አመቱን በሙሉ እንደፆመ ነው።” ብለዋል (ሙስሊም፣ አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚና ኢብኑ ማጃ ዘግበውታል)።

“ደህር” ማለት አመት ማለት ሲሆን አመቱን በሙሉ እንደፆመ ነው ማለት ነው። በየአመቱ ይህንን ፆም የፆመ እድሜውን በሙሉ አንደፆመ ስንልም ለማብራሪያ የሚከተለውን ሀዲስ በመጠቀም ነው፡-

“አንድ ወር መፆም እንደ አሥር ወር የሚቆጠር ሲሆን ስድስቱን ቀን መፆም ደግሞ እንደ ሁለት ወር ናቸው። ይህም በአጠቃላይ የዓመት ፆም ማለት ነው።” (ኢማም አህመድና ኢብኑ ሂባን ዘግበውታል)

ከረመዷን በኋላ ፆምን መላመድና ለፆም መነሣሣት ላለፈው ረመዷን ፆም ተቀባይነት ማግኘት ምልክት ነው። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ከአንድ ባሪያው ሥራውን የተቀበለ እንደሆነ ከዚያ በኋላም ቢሆን ለሌላ መልካም ሥራ ያነሣሣዋል፤ እንዲፀናም ያደርገዋል። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም የሸዋልን ስድሰት ቀን ፆም እንድንፆም መክረውናል። ይህም ታላቅ ምንዳን እንደሚያስገኝልን ጠቁመውናል። ምንዳው ለመግለፅ የሚከብድ ነው። ይህም ለኛ ለሙሀመድ ህዝቦች ከአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የሆነ ችሮታና ልግስና ነው። ምንም እንኳን በምድር ላይ የተሠጠን እድሜ አጭር ቢሆንም እነኚህንና የመሳሰሉትን ምንዳቸው ተነባብሮ የሚከፈልባቸውን ሥራዎች በመሥራት በተዘዋዋሪ የረጅም እድሜ ባለቤት የሆነ ሰው የሚያገኘውን ጥቅም ልናገኝ እንችላለለን። የታደለና አላህ ያደለው ሰው ማለት ይህን እድል በአግባቡ የተጠቀመና እነኚህ ጥቂት ቀናት ሳያልፉም የተጠቀመባቸው ነው። ኢማም ነወዊ ረሂመሁሏሁ ዑማኦች እንዲህ ብለዋል ይላሉ “አንድ አመት ፆም ሊሆን የቻለበት ምክኒያት መልካም ሥራ በአሥር ስለሚባዛ ረመዷን በአሥር ወር ስድስቱ የሸዋል ቀናት ደግም በሁለት ወር ማለትም ስልሣ ቀናት ስለሚታሰቡ ነው።” ብለዋል።

#ስድስቱን_ቀናት_አከታትሎ_ስለመፆም

እነኚህን የሸዋል ቀናት ልክ ረመዷን እንዳለቀ በዒድ ማግስት አከታትለን መፆም ይኖርብናል ወይንስ በሸዋል ውስጥ በማንኛውም ቀን ስድስት ቀን መፆም ይገባናል በሚለው ላይ ዑለማኦች ተወዛግበዋል። ሐነፊዬች እና ሻፊዒዬች ማከታተሉ በላጭ መሆኑን ሲያስረዱ ኢማም አህመድ ግን በሁለቱም መልክ ፆሙን መፈጸም እንደሚቻልና አንዱ ከሌላኛው ተመራጭ እንዳልሆነ ያስገነዝባሉ (ሰይድ ሳቢቅ፡- ፊቅህ አስ-ሱና )። ሁሌም ቢሆን ሸዋል የረመዷንን ወር ተከትሎ የሚመጣ ነውና ከዚህ ወር ስድስት ቀናትን አከታትሎ ቢፆም ወይም ነጣጥሎ ቢፆም መፆሙ አጅሩን (ምንዳውን) ሊያስገኝ መቻሉንና ችግርም እንደማይኖረው ዶ/ር ዩሱፍ አል-ቀረዳዊ በፈትዋቸው ገልጸዋል።

#ጠቃሚ_ነጥቦች

1. አንዳንድ ሰዎች የሸዋል ስድስቱን ቀን የፆመና አንዴ የጀመረ ሰው በየአመቱ መፆሙ ግድ ይሆንበታል ብለው የሚያስቡ አሉ። ይህ ትክክለኛ አመለካከት አይደለም። አንድ ሰው ቢፈልግ መፆም ቢሻው ደግሞ መተው ይችላል። ይህን አመት ቢያፈጥርና ቀጥሎ ያለውን አመት ቢፆም ችግር የለውም። በየአመቱ መፆም ግድ አይደለም።

2. አንዳንድ ሰዎች ደግሞ አንድ ሰው ከረመዷን በኋላ የሸዋልን ፆም በቀጥታ የጀመረ እንደሆነ ስድስቱን መሙላቱ የግድ ነው፤ ለችግር እንኳን ቢሆን ማቋረጥ የለበትም ይላሉ። ይህም ትክክል አይደለም። የሱና ፆሞችን የሚፆም ሰው ምርጫው በራሱ እጅ ነው። ፆሙን በየትኛውም ሁኔታና ጊዜ ባሻው ሰዓት ማቋረጥ ይችላል። ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም እንዲህ ብለዋል፡-

“የሱና ፆም የሚፆም ሰው የራሱ አዛዥ ነው። ቢፈልግ መፆም ቢፈልግ ደግሞ ማፍጠር ይችላል።” (ቲርሚዚ ዘግበውታል)

3. የሸዋልን ፆም መፆም የፈለገ ሰው ከለሊቱ ኒያውን /ለመፆም ሀሣቡን/ ማሣደር ይኖርበታል። ለተወሠነ ጊዜ የሚፈፀም የተወሠኑ ቀናት የተለየ ምንዳ ያለው ፆም ነውና እንደሌሎች የሱና ፆሞች መታየት የለበትም።

4. የረመዷን ፆም ቀዷ ያለበት ሰው መጀመሪያ እነኚህን ቀዷውን ከፆመ በኋላ ነው ስድስቱን የሸዋል ቀን ፆም መፆም ያለበት። የረመዷን ወር ፆም ግዴታ የሸዋል ፆም ደግሞ ሱና በመሆኑ ግዴታው ከሱና መቀደም አለበት። ሆኖም ግን ጥያቄው በዑለማኦች መካከል ልዩነት ማስነሣቱ አልቀረም።

5. ስድስቱን የሸዋል ቀናት ለመፆም መፍጠኑ ተወዳጅ ነገር ነው። የሸዋል ቀን ፆም የሚጀምረው ወሩ በገባ በሁለተኛው ቀን ነው። የመጀመሪያው ቀን ዒድ ነውና። ወደ መሃል አሊያም መጨረሻ አካባቢ አድርጎ መፆምም ችግር የለውም።

#የሸወል_ፆም_ሚስጢርና_የተደነገገለት_ዓላማ

1. አንድ ሰው ስድስቱን የሸዋል ቀን ፆም መፆሙ የአመት ፆም እንዲሆንለት ያግዘዋል። እሷ ማሟያ ናትና።

2. የሸዋልን እና የሸዕባንን ፆም ከሰላት በፊት እና በኋላ እንደሚሰገዱ ሱና ሰላቶች አድርገን መውሰድ እንችላለን። ይህም በግዴታው ላይ ክፍተት እና ጉድለት ካለ ለሟሟያነት ይጠቅማል። የቂያማ ቀን አንድ ሰው መልካም ሥራ የጎደለው እንደሆነ ከሱናዎቹ ነው የሚሟላለት። አብዛኞቻችን በፆማችን ክፍተት እና የጉድለት ችግር አያጣንም። ስለዚህም ይህን ለመጠገን እና ለማሟላት የሚጠቅሙን ሥራዎች ያስፈልጉናል።

3. የረመዷን ወር ፆም ያለፈውን ሀጢኣታችንን ያስምርልናል /እንዲማርልን ምክንያት ይሆናል/። ከረመዷን ፍፃሜ በኋላ ደግሞ ፆምን መቀጠል እነኚህን ከአላህ የተቸሩንን ታላላቅ ፀጋዎች እንደማመስገን ይቆጠራል። ወንጀልን ከመማር በላይ ምን ፀጋ አለና!

4. አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ባሮቹ እሱን በማውሣትና ሥሙን ግልፅ እና ከፍ በማድረግ በመሣሰሉት ፀጋውን እናመስግን ዘንድ አዟል። እንዲህ በማለት

“ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩትና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገግንላችሁ)።” (አል-በቀራ 2፤ 185)

ለረመዷን አድርሦ እንድንፆም ስላቻልን፣ ለምህረት ወርም ስላበቃን አላህን በእጅጉ ልናመሰግነው ይገባል። ስለዚህ የረመዷንን ወር ፆም ስንጨርስ ለዚህ ችሮታው ውለታ ፆም በመፆም አላህ ማመስገን ይኖርብናል።

5. አንድ የአላህ ባሪያ በረመዷን ውስጥ ወደ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ይቃረብባቸው የነበሩ የአምልኮ ሥራዎች በረመዷን መውጣት የሚቋረጡ አይደሉም። ባሪያው በህይወት እስካለ ድረስ ይኖራሉ። ከፆም ካፈጠረ በኋላ ወደ ፆም የሚመለስ ሰው አሁንም አላህ ወደሚወደው ነገር መመለስ የሚችልና የማይሠለች መሆኑን እንዲሁም ከአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ አድርግ ተብሎ ትእዛዝ የተሠጠው እንደሆነ ሁሌም ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ያመላክታል።
______________________
በ⇒ ethiomuslims.net
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ቤተሰብ ይሁኑ↷
https://t.me/juedm
https://t.me/joinchat/AAAAAEEef28lpL2nzT
ZHgg
[١٦/‏٦ ١:٢١ م] منتهي: => ፆም አያልቅም
=> ቁርአን አይነሳም
=> መስጅዶች አይዘጉም
=> የዱዓእ ተቀባይነት አይጠናቀቅም
=> አጅርም አይቋረጥም

☞ የረመዳን ሳይሆን
° የአላህ እንሁን አላህ እንዳለንም °

واعبد ربك حتى
يأتيكل اليقين

تقبل الله منا ومنكم
صالح الأعمال
عيدكم مبارك


🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
ከህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠ መግለጫ
ቀን፣ ሰኔ 10/2010

ለክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ
የኢ/ፌ/ዴ/ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
አዲስ አበባ
ጉዳዮ፣ ለህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች መልስ የመስጠት ተነሳሽነትዎን ይመለከታል
የተከበሩ ጠ/ ሚኒስትር፣
በሰኔ 8/2010 በዒድ አልፈጥር በዓል እለት በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ መስጠትዎ ይታወቃል። በመግለጫዎ ወቅታዊ የአገራችንን ፓለቲካዊ ትኩሳቶችን እልባት ለመስጠት እንደሚሰሩ እና በተለይም የህዝበ ሙስሊሙን ማንኛውንም ጥያቄዎች ለመመለስ ዝግጁ መሆንዎን መግለፅዎ በህዝበ ሙስሊሙ ውስጥ አዲስ ተስፋ የፈጠረ አጋጣሚ ሆኗል።
እኛ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላለፋት አመታት መንግስት ከሁሉም ሃይማኖቶች በእኩል ርቀት ነፃ እና ፍትሀዊ በሆነ አግባብ መቆም ሲገባው በሙስሊሙ ተቋማት እና የእምነት ጉዳዮች ውስጥ በግልፅ ጣልቃ በመግባቱ የተነሳ የመነጩ የመብት ጥሰቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመቃወም እና ለመታገል አደባባይ ከወጣን ስድስት አመታት ተቆጠሩ። በሙሉ የሀገራዊ ሃላፊነት ስሜት እና ኢትዮጵያ ሀገራችን የሁሉም እምነቶች እና የሃይማኖቶች መብቶች የተከበሩባት ሆና ማየትን በማለም ያደረግነው ሰላማዊ ትግል እነሆ ለመሰል ትግሎች በር ከፍቶ የለውጥ ቀንዲል መሆን ቢችልም ህዝበ ሙስሊሙን ግን ያለ ስሙ ስም ያለ ግብሩም የከፋ ስቃይ እና መከራ እንዲደርስበት አድርጎል።
እነዚያ አመታት አልፈው በሀገሪቱ ፈጣን የሆኑ የፓለቲካ ለውጦች ቢስተናገዱም ያነሳነው ጥያቄ መልስ ሊያገኝ እንደሚችል የሚጠቁም የአመለካከትም ሆነ የተግባር ፍንጭ ማየት ሳንችል እስካለፈው የረመዳን ፍች በዓል ድረስ ቆይተናል።
ክቡር ጠ/ ሚኒስትር፣
መንግስትዎ እና ያዋቀሩት ካቢኔ በዓይነቱ የተለየ እና ለሀገራችን ታሪክና ለህዝባችን ክብር የሚመጥን ምክንያታዊ ፓለቲካ ማራመድ በመጀመራችሁ መንግስትዎ ሰፊ ተቀባይነትን ማግኘት ችሏል።የዚህ ቅቡልነት ምንጩን ጠለቅ ብለን ስንፈትሸው በዋናነት የምናገኘው ለህዝቦች ማንነት፣ሀገራዊ ድርሻ እና ሃላፊነት በሚመጥን መልኩ ከላይ ከአመራሩ የታየው የአመለካከት ለውጥ ሆኖ እናገኘዋለን።
ክቡር ጠ/ሚኒስቴር፣
ከላይ በተጠቀሰው መግለጫዎ የህዝበ ሙስሊሙን ማንኛውንም ጥያቄ ለመፍታት ያለዎን ዝግጁነት መግለፅዎን በሁለት መሠረታዊ ምክኒያቶች በመልካምነት ተቀብለነዋል። በመጀመሪያ ለአመታት በፅናት እንደ ህዝብ ዋጋ ስንከፍልለት የኖርነው ጥያቄ ደጋግመን እንደምንለው ያልተመለሰ ጥያቄ መሆኑን ዕውቅና መቸሩ ነው። የጥያቂያችን አለመመለስ ሳያንስ ጥያቂያችን ተቀልብሶ የሚዲያ ፕሮፖጋንዳ እና የሃይል እርምጃ ሰለባ ተደርገን ከመቆየታችን አንፃር ላልተመለሰው ጥያቂያችን እልባት ለመስጠት የመጀመሪያው እርከን የሆነውን "ህዝብ ያልተመለሰለት ጥያቄ አለው" ብሎ የሚነሳን መሪ ዕውቅና ስንሰጥ ችግሩን በሚገባ የተረዳ መሪ ለመፍትሄውም ቁርጠኛ እንደሚሆን ስለምናምን ነው።
ተነሳሽነትዎን በበጎ የወሰድንበት ሁለተኛው ምክኒያት ችግሩን ከስሩ የመፍታት አቅም እንዳለዎ በማመን እና በመግለጫዎም ይህንኑ በመጠቆምዎ ነው። በሁለት ወራት የስልጣን ላይ ቆይታዎ እዛም እዚህም ለሚነሱ ጥያቄዎች እሣት የማጥፋት ስራ ሳይሆን እንደ መንግስት ለህዝብ ጥያቄ ሊኖር የሚገባውን አመለካከት ስር ነቀል በሆነ መልኩ በመቀየርዎ ችግሮቹ በአፈፃፀም ደረጃ በቀላሉ የሚፈቱበት አየር እየተፈጠረ መሆኑ ግልፅ ነው። ህዝበ ሙስሊሙ ላነሳቸው ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ያልቻለው የመሪ ድርጅቱ (መጅሊስ) መዋቅር ውስብስብ ሆኖ ሣይሆን መንግስት በጉዳዩ ለይ የያዘው አሉታዊ አቋም በመኖሩ ነበር።
በመሆኑም መንግስትዎ ማንኛውንም ችግር በመወያየት ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን በሚዲያ ማሳወቁ ቀጣዩ ሂደት አተገባበር እንደሚሆን ይታመናል።የአሁኑን መግለጫ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ጊዚያዊ የፓለቲካ ግለት ማብረጃ ሳይሆን ወደ መሬት ወርዶ የሚተገበር እንደሚሆን እናምናለን።በዚህም ም ክንያት አተገባበሩ ለጥያቄዎቹ መሠረታዊነት፣ህዝቡ ካደረገው ሰላማዊ ትግል እና መንግስትም ለህዝብ ፍትሃዊ ጥያቄዎች ከሚሰጠው ዋጋና ክብደት አንፃር ተመጣጣኝ በሆነ ሂደት እና ጥልቀት እንዲከናወን እንፈልጋለን፣አጥብቀንም እንጠይቃለን።ችግሮቹ በሙሉ የመንግስትን ትኩረት በሚያመላክትና የባለመብቶቹን ስነልቦና ሊያረካ በሚችል መልኩ ይፈቱ ዘንድ የበኩላችንን ለማበርከት በህዝበ ሙስሊሙ ተወክሎ ሲንቀሳቀስ እንደነበረ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ዝግጁነታችንን ስንገልፅ የጥያቄዎቹ መመለስ እና የሚመለሱበት መንገድ መሰረታዊ በሆነ መልኩ የተሣሠሩ እንደሆኑ በማስታወስ ጭምር ነው። ይህንን የምንለው ለችግሩ የሚሰጠው መፍትሄ ዘለቄታዊነቱ አስተማማኝ የሚሆነው የጉዳዩ ባለቤትን እና ግንባር ቀደም ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ በሚደረግ ቀጥተኛ ውይይት ሲካሄድ በመሆኑ ነው።

በመጨረሻም በሀገራችን ላይ አንዣቦ ከነበረው አስፈሪ አደጋ በተወሰነ ደረጃ እያገገምን ባለንበት በዚህ ወቅት የለውጥ ሂደቱን የሚያደናቅፋ ክስተቶች እዚህም እዚያ እየተስተዋሉ በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን *ለመንግስትዎ* ሁለንተናዊ ድጋፋን እንደሚቀጥል ልናረጋግጥ እንወዳለን።
ለህዝቦች ጥያቄ መልስ የመስጠት ሂደት ውስጥ እንድንገባ ላደረገን አላህ ምስጋና እያቀረብን እየተወሰዱ ላሉ ፖለቲካዊ እርምጃዎች አክብሮታችንን ለመግለፅ እንሻለን ። መንግስታዊ ብልሹ አስተሳሰብና አሰራር የፈጠሯቸውን ችግሮች በመንግስታዊ እና ህዝባዊ ወገንተኝነት ለመፍታት በሚደረገው ጥረት በራሳችንም ሆነ ከሌሎች የሀገራችን ህዝቦች ጋር በመሆን ለስኬታማነቱ የበኩላችንን እንደምንወጣ እየገለፅን ለሃገራችን እና ለክቡር ጠቅላይ ሚኒሰትራችን መልካሙን ሁሉ እንመኛለን።

ሃገራችን ኢትዮጵያን አላህ የሰላም፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የብልፅግና ሃገር ያድርግልን! አሚን

የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ
أبوياقوت:
ስራችን ተቀባይነት አግኝቷልን?
አንድ ሰው የሰራው ስራ ተቀባይነት የማግኘቱ ምልክት በዚያ በሰራው ዒባዳ ላይ መዘውተሩ ሲሆን በተቃራኒው ተቀባይነት የማጣቱ ምልክት ደግሞ በዒባዳው ወረተኛ መሆኑ ነው።
ስራው ተቀባይነት ያገኘ ሰው አላህ ጋር ያለው ግንኙነት እንዲታሰር ይቀራል። የዒባዳን በርን አይዘጋም ግንኙነቱን ቁርአን በመቅራት፤ ጀመዓና ጁመዓ በመሳተፍ ይቀጥላል።
ስራው ተመላሽ የሆነበት ሰው፤ ከተወሰነ የዒባዳ ሽርጉድ በኃላ ከቦታው ይጠፋል፤ በዚህም ከፈጣሪው ጋር በዒባዳ ይቆራረጣል። ቁርአን መቅራትና መስጂድ መሄድ እንኳ ቀርቶ ግዴታ ሶላቶችን መስገድ ጥያቄም መልክት ወስጥ ይገባል።
የዒባዳ ተቀባይነት ማግኘት ሌላው ምልክት ለምሳሌ ከረመዷን በኃላ ለዒባዳ ሁሌም በራችን ክፍት መሆኑ ነው። ይህ መሆኑ ይህ ሰው በሰራው ስራ ምንዳ ማግኘቱና በዱንያ ብስራት ማገኘቱን ያረጋግጣል። ምንዳ ማግኘት በአኼራ ብቻ የሚወሰን አይደለም። እንደውም በዱንያም የምንዳ ማግኘት አንዱ መገለጫ ለዒባዳ ዝግጁ መሆንና ዘውታሪ ሆኖ መቀጠል እንዲሁም ለሌላ በጎ ስራ መነሳሳት ነው። በዚህ የተነሳ ለሌላ ቅንነት አንዲበቃ በር ከፋች ይሆናል። አላህ እንዲህ ይላል፡-
ﻭَﻳَﺰِﻳﺪُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺍﻫْﺘَﺪَﻭْﺍ ﻫُﺪًﻯ
“እነዚያንም የቀኑትን ሰዎች አላህ ቅንነትን ይጨምርላቸዋል፡፡” (መርየም፤ 76)።
ﻭَﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺍﻫْﺘَﺪَﻭْﺍ ﺯَﺍﺩَﻫُﻢْ ﻫُﺪًﻯ ﻭَﺁﺗَﺎﻫُﻢْ ﺗَﻘْﻮَﺍﻫُﻢْ
“እነዚያም የተመሩት (አላህ) መመራትን ጨመረላቸው፡፡ (ከእሳት) መጥጠበቂያቸውንም ሰጣቸው፡፡” (ሙሀመድ፤ 17)
ወንጀልና መጨረሻው
የወንጀል ትርፉ ሌላ ወንጀል ማስከተል ነው። የወንጀል መጠን እየተደራረብ የቀልቡን መጨለም ይጨምርራል። ቀልቡም ቀስ በቀስ በወንጀል ጨለማ ይጠቀጠቃል። ይህን “ዝገት” ነው አላህ በቁርአኑ እንዲህ ሲል የጠቀሰው።
ﻛَﻠَّﺎ ۖ ﺑَﻞْ ۜ ﺭَﺍﻥَ ﻋَﻠَﻰٰ ﻗُﻠُﻮﺑِﻬِﻢ ﻣَّﺎ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﻳَﻜْﺴِﺒُﻮﻥَ
“ይከልከል፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሠሩት የነበሩት (ኀጢአት) ደገደገባቸው፡፡” (አል-ሙጠፊፊን፤ 14)
በመልካም ስራ መዘውተር
በመልካም ስራ የመዘውተር ልምድ የሙዕሚኖች አርማ ነው። እንዲሁም እጅግ በጣም ተወዳጅና ወደ አላህ መቃረቢያ መንገዳቸው በመልካም ስራ ላይ ዘውታሪነታቸው ነው። ዓኢሻ (ረ.ዐ) በዘገቡት ሐዲስ እንደተዘገበው ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)
ﺍﻛْﻠﻔﻮﺍ ﻣﻦ ﺍﻟﻌﻤﻞ ﻣﺎ ﺗﻄﻴﻘﻮﻥ؛ ﻓﺈﻥ ﺍﻟﻠﻪ ﻻ ﻳﻤﻞ ﺣﺘﻰ ﺗﻤﻠﻮﺍ، ﻭﺇﻥ ﺃﺣﺐ ﺍﻟﻌﻤﻞ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﺩﻭﻣﻪ ﻭﺇﻥ ﻗﻞ
“በአቅማችሁ ልክ ስራ ስሩ፤ እናንተ ትሰለቻላችሁ እንጅ አላህ አይሰለችም። ከስራ ሁሉ እጅግ በጣም ተወዳጅ፤ ጥቂትም ቢሆን ዘውታሪነት ያለው ነው” (ሶሂህ)
ሙዕሚን ስራ ሲሰራ በቋሚነት ነው። ማለትም ሁልጊዜ በስራው ላይ ይዘወትራል ማለት ነው። ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) በስራ የመዘውተራቸው ማሳያ የሚሆነን የተሐጁድ ሶላት (የሌሊት ሶላት) ነው። በእንቅልፍ ወይም በህመም ምክንያት መስገድ ካልቻሉ ቀን ላይ አስራሁለት ረከዓ ሶላቶችን በመስገድ ያካክሱ ነበር።
በመልካም ስራ ላይ የመዘውተር ትሩፋቱ፡-
1. ቀልብን ከንፍቅና ማፅዳትና ከጌታው ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከ ፡-
ቀልብ እንደሚታወቀው የአካላችን መሰረት ነው። አቡሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳሉት
ﺍﻟﻘﻠﺐ ﻣﻠﻚ ﺍﻷﻋﻀﺎﺀ , ﻭﺍﻷﻋﻀﺎﺀ ﺟﻨﻮﺩﻩ , ﻓﺈﺫﺍ ﻃﺎﺏ ﺍﻟﻤﻠﻚ ﻃﺎﺑﺖ ﺟﻨﻮﺩﻩ , ﻓﺒﻌﻼﺝ ﺍﻟﻘﻠﺐ ﻳﺼﻠﺢ ﺍﻟﺒﺪﻥ ﻛﻠﻪ، ﻭﺑﻔﺴﺎﺩﻩ ﻳﻔﺴﺪ ﺍﻟﺒﺪﻥ ﻛﻠﻪ، ﻛﻤﺎ ﺟﺎﺀ ﻓﻲ ﺍﻟﺼﺤﻴﺢ : ” ﺃﻻ ﻭﺇﻥ ﻓﻲ ﺍﻟﺠﺴﺪ ﻣﻀﻐﺔ، ﺇﺫﺍ ﺻﻠﺤﺖ ﺻﻠﺢ ﺍﻟﺠﺴﺪ ﻛﻠﻪ، ﻭﺇﺫﺍ ﻓﺴﺪﺕ ﻓﺴﺪ ﺍﻟﺠﺴﺪ ﻛﻠﻪ، ﺃﻻ ﻭﻫﻲ ﺍﻟﻘﻠﺐ ”.
“ቀልበ የአካል ንጉስ ነው። አካላት የቀልብ ወታደሮች ናቸው። ንጉስ ካማረ ወታደሮችም ያምርባቸዋል። የቀልብ ደህነት የቀሪው አካል ደህንቱ ነው። የቀልብ መላላት የሌላ አካል መበላሸት ነው።” በሐዲስ አንደተረጋገጠው «ንቁ! አካል ውስጥ የተላመጠ ስጋ የመሰለች ነገር አለች ። እሷም ጥሩ ከሆነች፤ ሁሉም አካል ጥሩ ይሆናል። እሷ ከተበላሸች ደግሞ ቀሪው አካል ይበላሻል። እሷም ቀልብ ነች” ብለዋል።
ኢማሙ ኒብኑልቀይም እንዳሉት “አላህ ዘንድ የሚበላለጠው ስራ መብዛቱ ሳይሆን ቀልብ ውስጥ በተቀመጠው ነገር ነው።” ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-
ﺇﻥ ﺍﻟﻠﻪ ﻻ ﻳﻨﻈﺮ ﺇﻟﻰ ﺻﻮﺭﻛﻢ ﻭﺃﻣﻮﺍﻟﻜﻢ ﻭﻟﻜﻦ ﻳﻨﻈﺮ ﺇﻟﻰ ﻗﻠﻮﺑﻜﻢ ﻭﺃﻋﻤﺎﻟﻜﻢ
“አላህ የላይ ገጽታችሁ እና ገንዘባችሁን አይመለከትም። ነገር ግን ቀልቦቻችሁንና ስራዎቻችሁን ይመለከታል።”
አንድ ሰው ቀልቡ በኢማን ሲያበራ ከተለያዩ አቅጣጫዎች መልካም ነገሮች ሁሉ ወደሱ ይጎርፋሉ። በዚህም ከአንድ በጎ ነገር ወደ ሌላ በጎ ነገር ይሸጋገራል። የአንድ ሰው የቀልብ ጤነኛነቱ ትልቁ መገለጫው በሰራው ስራ ላይ ጉድለት እየተሰማው ተቀባይነት አገኝ ይሆን በማለት በመልካም ስራ ላይ መዘውተር መቻሉ ነው። አላህ እንዳለው፡-
ﻭَﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳُﺆْﺗُﻮﻥَ ﻣَﺎ ﺁﺗَﻮﺍ ﻭَّﻗُﻠُﻮﺑُﻬُﻢْ ﻭَﺟِﻠَﺔٌ ﺃَﻧَّﻬُﻢْ ﺇِﻟَﻰٰ ﺭَﺑِّﻬِﻢْ ﺭَﺍﺟِﻌُﻮﻥَ
“እነዚያም የሚሰጡትን ነገር እነርሱ ወደ ጌታቸው ተመላሾች መኾናቸውን ልቦቻቸው የሚፈሩ ኾነው የሚሰጡት፡፡” (አል-ሙዕሚኑን፤ 60)
2. የአላህን ውዴታ ያስገኛል
ግዴታ በሆኑና ሱና በሆኑ መልካም ስራዎች ላይ መዘውተር የአላህን ውዴታ ያስገኛሉ። በሐዲስ አል-ቁድሰይ እንዲህ ይላል:-
ﻣﻦ ﻋﺎﺩﻯ ﻟﻲ ﻭﻟﻴًّﺎ ﻓﻘﺪ ﺁﺫﻧﺘﻪ ﺑﺎﻟﺤﺮﺏ، ﻭﻣﺎ ﺗﻘﺮﺏ ﺇﻟﻲَّ ﻋﺒﺪﻱ ﺑﺸﻲﺀ ﺃﺣﺐَّ ﺇﻟﻲَّ ﻣﻦ ﺃﺩﺍﺀ ﻣﺎ ﺍﻓﺘﺮﺿﺘﻪ ﻋﻠﻴﻪ , ﻭﻻ ﻳﺰﺍﻝ ﻋﺒﺪﻱ ﻳﺘﻘﺮَّﺏ ﺇﻟﻲَّ ﺑﺎﻟﻨﻮﺍﻓﻞ ﺣﺘﻰ ﺃﺣﺒَّﻪ , ﻓﺈﺫﺍ ﺃﺣﺒﺒﺘُﻪ ﻛﻨﺖ ﺳﻤﻌﻪ ﺍﻟﺬﻱ ﻳﺴﻤﻊ ﺑﻪ، ﻭﺑﺼﺮﻩ ﺍﻟﺬﻱ ﻳﺒﺼﺮ ﺑﻪ , ﻭﻳﺪﻩ ﺍﻟﺘﻲ ﻳﺒﻄﺶ ﺑﻬﺎ , ﻭﺭﺟﻠﻪ ﺍﻟﺘﻲ ﻳﻤﺸﻲ ﺑﻬﺎ، ﻭﺇﻥ ﺳﺄﻟﻨﻲ ﺃﻋﻄﻴﺘﻪ، ﻭﺇﻥ ﺍﺳﺘﻌﺎﺫ ﺑﻲ ﺃﻋﺬﺗﻪ
“ወዳጆቼን በላንጣ የሆነ፤ ከኔ ጋር ጦርነት እንደከፈተ ነው። አንድ ሰው ወደ አላህ ከሚቃረብባቸው ሰራዎች መካከል የበለጠ ተወዳጁ ግዴታዎችን ሲወጣ ነው። ሱና ሰራዎችንም ከመስራት አይወገድም እኔ እስክወደው። እኔ ስወደው መሰሚያ ጆሮው፤መመልከቻ አይኑ፤ የሚሰራበት እጁ እንዲሁም የሚጓዝበት እግሩ እሆነዋለሁ። ሲጠይቀኝ እሰጠዋለሁ። ጥበቃ ሲያሻው እጥብቀዋለሁ (ከመጥፎ ነገር)።”
3.ከመከራና ከችግር ለመዳን ምክንያት ነው ፡-
በበጎ ስራ የመዘውተር ትልቁ ትሩፋት ከመከራና ከችግራ መዳን መቻል ነው። አንድ በድሎት ወይም በፍስሐ ወቅት ወደ አላህ ለመቃረብ የተጋ፤ በችግር ጊዜ አላህ አይተወውም። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ለኢብኑ ዓባስ (ረ.ዐ) እንዲህ የሚል (አደራ) አስተላልፈዋለወ።
ﻳﺎ ﻏﻼﻡ، ﺃﻻ ﺃﻋﻠﻤﻚ ﻛﻠﻤﺎﺕ ﻳﻨﻔﻌﻚ ﺍﻟﻠﻪ ﺑﻬﻦ ” ﻓﻘﺎﻝ : ﺑﻠﻰ، ﻓﻘﺎﻝ : “ ﺍﺣﻔﻆ ﺍﻟﻠﻪ ﻳﺤﻔﻈﻚ، ﺍﺣﻔﻆ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﺠﺪﻩ ﺗﺠﺎﻫﻚ، ﺃﻭ ﻗﺎﻝ : ﺃﻣﺎﻣﻚ، ﺗﻌﺮﻑ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻲ ﺍﻟﺮﺧﺎﺀ ﻳﻌﺮﻓﻚ ﻓﻲ ﺍﻟﺸﺪﺓ , ﺇﺫﺍ ﺳﺄﻟﺖ ﻓﺎﺳﺄﻝ ﺍﻟﻠﻪ، ﻭﺇﺫﺍ ﺍﺳﺘﻌﻨﺖ ﻓﺎﺳﺘﻌﻦ ﺑﺎﻟﻠﻪ؛ ﻓﺈﻥ ﺍﻟﻌﺒﺎﺩ ﻟﻮ ﺍﺟﺘﻤﻌﻮﺍ ﻋﻠﻰ ﺃﻥ ﻳﻀﺮﻭﻙ ﺑﺸﻲﺀ ﻟﻢ ﻳﻜﺘﺒﻪ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻚ ﻟﻢ ﻳﻘﺪﺭﻭﺍ ﻋﻠﻰ ﺫﻟﻚ ,

ﺟﻔﺖ ﺍﻷﻗﻼﻡ , ﻭﻃﻮﻳﺖ ﺍﻟﺼﺢ
(ﺣﺴﻦ)
“አንተ ልጅ ሆይ! የሚጠቅምህ የሆኑ ቃላትን አላስተምርህምን? አሉት። እሱም አስተምሩኝ አ
ላቸው። እሳቸውም አላህን ጠብቀው እሱም ይጠብቅሀል፤ አላህን ጠብቅ ፊት ለፊት ላይ ታገኘዋለህ። አላህን በፍስሐ ጊዜ እወቀው፤ በመከራ ጊዜ ያውቅሀል፤ ስትጠይቅ አላህን ጠይቅ፤ መታገዝ ስትፈልግ በሱ ታገዝ፤ ሰዎች በሙሉ ተሰባስበው አንተን ለመጉዳት ቢሞክሩም በመጎዳትህ አላህ አስካልወሰነው ድረስ በፍፁም አይጎዱህም። ቀለሞች ደርቀዋል። መፅሀፉም ተጠቅልሏል።” (ሐሰን የሆነ ሐዲስ)
4.ለመጨረሻ (ኻቲማ) ማማርና ጀነትን ለማግኘት ምክንያት ነው
አል-ሐፊዝ ኢብኑ ከሲር “ቸር ሰው በቸርነት ልምዱ ይቀላል። በአንድ ነገር ላይ ፀንቶ የኖረ ሰው በዚያው ይሞታል። በልምዱ የሞተ ሰው ደግሞ በዚያው ይቀሰቀሳል። አንዱ ሙዕሚን አጨራረሱ እስኪያምር ድረስ አላህ ከመገዛት አይቦዝንም።” ይላሉ:: አላህ እንዲህ ይላል፡-
ﻭَﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺟَﺎﻫَﺪُﻭﺍ ﻓِﻴﻨَﺎ ﻟَﻨَﻬْﺪِﻳَﻨَّﻬُﻢْ ﺳُﺒُﻠَﻨَﺎ ۚ ﻭَﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻟَﻤَﻊَ ﺍﻟْﻤُﺤْﺴِﻨِﻴﻦَ
“እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፡፡ አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር ነው፡፡” (አል-አንከቡት፤ 69)።
ﻳُﺜَﺒِّﺖُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﺑِﺎﻟْﻘَﻮْﻝِ ﺍﻟﺜَّﺎﺑِﺖِ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺤَﻴَﺎﺓِ ﺍﻟﺪُّﻧْﻴَﺎ ﻭَﻓِﻲ ﺍﻟْﺂﺧِﺮَﺓِ ۖ ﻭَﻳُﻀِﻞُّ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺍﻟﻈَّﺎﻟِﻤِﻴﻦَ ۚ ﻭَﻳَﻔْﻌَﻞُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻣَﺎ ﻳَﺸَﺎﺀُ
“አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብር) በተረጋገጠው ቃል ላይ ያረጋቸዋል፡፡ ከሓዲዎችንም አላህ ያሳስታቸዋል፡፡ አላህም የሚሻውን ይሠራል፡፡” (ኢብራሂም፤ 27)።
ከሀዲስ ደግሞ፤ አነስ (ረ.ዐ) በዘገቡት ሐዲስ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-
ﺃﻥ ﺍﻟﻨﺒﻲ - ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ - ﻗﺎﻝ : “ ﺇﺫﺍ ﺃﺭﺍﺩ ﺍﻟﻠﻪ ﺑﻌﺒﺪ ﺧﻴﺮًﺍ ﺍﺳﺘﻌﻤﻠﻪ ” ، ﻗﻴﻞ : ﻭﻛﻴﻒ ﻳﺴﺘﻌﻤﻠﻪ؟ ﻗﺎﻝ : “ ﻳﻮﻓﻘﻪ ﺇﻟﻰ ﻋﻤﻞ ﺻﺎﻟﺢ ﺛﻢ ﻳﻘﺒﻀﻪ ﻋﻠﻴﻪ
( ﺃﺣﻤﺪ ﻭﺍﻟﺘﺮﻣﺬﻱ )
“አላህ አንድ ሰው ላይ በጎን ሲሻለት ያሰራዋል።” ሲሉ እንዴት ነው የሚያሰራው ተብለው ተጠየቁ ። እሳቸውም “መልካም ስራን እንዲሰራ ያደርገዋል በዚያው ሞት ይመጣበታል” አሏቸው።
(አህመድና ቲርሚዚ የዘገቡት)
አላህ ለመልካም ስራ መትጋትንና ዘውታሪነት ከሰጠን እንዲሁም በዚያው ሞት ከመጣብን በአላህ ፍቃድ በመልክም ስራችን እንቀሰቀሳለን።
5.ሞት ሲመጣ የመላኢካን ብስራት ማገኘት
አላህ እንዲህ ይላል፡-
ﺇِﻥَّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻗَﺎﻟُﻮﺍ ﺭَﺑُّﻨَﺎ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺛُﻢَّ ﺍﺳْﺘَﻘَﺎﻣُﻮﺍ ﺗَﺘَﻨَﺰَّﻝُ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻢُ ﺍﻟْﻤَﻠَﺎﺋِﻜَﺔُ ﺃَﻟَّﺎ ﺗَﺨَﺎﻓُﻮﺍ ﻭَﻟَﺎ ﺗَﺤْﺰَﻧُﻮﺍ ﻭَﺃَﺑْﺸِﺮُﻭﺍ ﺑِﺎﻟْﺠَﻨَّﺔِ ﺍﻟَّﺘِﻲ ﻛُﻨﺘُﻢْ ﺗُﻮﻋَﺪُﻭﻥَ
ﻧَﺤْﻦُ ﺃَﻭْﻟِﻴَﺎﺅُﻛُﻢْ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺤَﻴَﺎﺓِ ﺍﻟﺪُّﻧْﻴَﺎ ﻭَﻓِﻲ ﺍﻟْﺂﺧِﺮَﺓِ ۖ ﻭَﻟَﻜُﻢْ ﻓِﻴﻬَﺎ ﻣَﺎ ﺗَﺸْﺘَﻬِﻲ ﺃَﻧﻔُﺴُﻜُﻢْ ﻭَﻟَﻜُﻢْ ﻓِﻴﻬَﺎ ﻣَﺎ ﺗَﺪَّﻋُﻮﻥَ
ﻧُﺰُﻟًﺎ ﻣِّﻦْ ﻏَﻔُﻮﺭٍ ﺭَّﺣِﻴﻢٍ
እነዚያ ‘ጌታችን አላህ ነው’ ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ ‘አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ’ በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡(30) እኛ በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም ረዳቶቻችሁ ነን! ለእናንተም በእርሷ ውስጥ ነፍሶቻችሁ የሚሹት ሁሉ አልላችሁ፡፡ ለእናንተም በእርሷ ውስጥ የምትፈልጉት ሁሉ አልላችሁ፡፡ (31) መሓሪ አዛኝ ከኾነው አላህ መስተንግዶ ሲኾን (ይባላሉ)፡፡” (ፉሲለት፤ 30-32)።
ይህ አንቀፅ በመልካም ለሚያዙና ለአላህ ለተወዳጅ ሰዎች ብስራት ነው። እነዚህ ሰዎች “ጌታችን አላህ ነው።” ብለው በእምነትና በበጎ ሰራዎቻቸው በሱ ጎዳና ላይ ቀጥ ብለው የቆሙ ናቸው። ስለሆነም አላህ መላኢካን በማዘዝ ቀልባቸው ላይ የደህንነትንና የመረጋጋር መንፈስ እንዲያሳድሩባቸው ያደርጋል። በጀነትም ያበስራቸዋል። የዱንያንና የአኼራን ጉዳዩቻቸውንም አንደሚሰናዱላቸውም ቃል ያስግባል። “ጌታችን አላህ ነው” በሚለው ነገር ላይ ቀጥ ማለት ስንል ቃሉ የሚፈልገውን የቃሉን መልዕክት ተገንዝበን ቀጥ ማለት የሚጠይቅ ነው። ማለትም በውስጥ እሱን ማሰብ፤ በሕይወት ጎዳና እሱን መተግበር፤ ቃሉ የሚጠይቀውን ትልቅና መራራ ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ቁርጠኛ መሆን (መታገስ) ነው። ታዲያ በዚህ ምክንያት ነው አንድ ሰው የመላኢካን ጓደኝነትና የወዳጅነታቸውን ፀጋ ማግኘት የሚገባው።
ለመልካም ስራ አጋዥ ነገሮች
1. በአላህ መታገዝ
አላህ ያገዘው ሰው ትክክለኛው እገዛ አገኘ። እሱ ያራቀው ደግሞ መድረሻ ቢስ ነው። ስለሆነም እሱ የሚወደው የሆነ በጎ ስራን ያመላክተንና ይገጥመን ዘንድ ከእሱ እገዛን መጠየቅ ይኖርብናል። ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሙዓዝን (ረ.ዐ) እጁን ይዘው እንዲህ አሉት፡-
ﻳﺎ ﻣﻌﺎﺫ، ﺇﻧﻲ ﻭﺍﻟﻠﻪ ﻷٌﺣﺒﻚ؛ ﻓﻼ ﺗﺪﻋﻦ ﻓﻲ ﺩﺑﺮ ﻛﻞ ﺻﻼﺓ ﺃﻥ ﺗﻘﻮﻝ : ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺃﻋﻨﻲ ﻋﻠﻰ ﺫﻛﺮﻙ ﻭﺷﻜﺮﻙ ﻭﺣﺴﻦ ﻋﺒﺎﺩﺗﻚ
“ሙዓዝ ሆይ! እኔ በአላ ይሁንብኝ በትክክል እወድሀለሁ በሶላት የመጨረሻ ከፍለ ላይ ‘አላህ ሆይ አንተን በማስታወስና በማመስገን እንዲሁም በጥሩ ዒባዳህ ላይ እገዘኝ’ የሚለውን ዱዓ አትተው” (ሰሒህ ሀዲስ)።
ስለዚህ ከአላህ እገዛን መጠየቅ አለብን ይህን ካደረግን እሱ በመልካም ስራዎች ላይ ያግዘናል።
2. ሚዛናዊ መሆን
በመልካም ስራዎች ላይ ለመዘውተር ሌላው አጋዥ ነገር፤ በዒባዳ ላይ ሚዛናዊ መሆን ነው። በዒባዳ ላይ ከሚገባው በታች መውረድም ሆነ ከሚፈለገው በላይ መውጣት አያስፈልግም። የነገሮች ሁሉ መልካሙ መካከለኛው ነው። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጽንፈኛነትን አስጠንቅቀዋል። ምክንያቱም ይህ ባሕሪይ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ አይደለም። ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) አቡሁረይራ (ረ.ዐ) በዘገቡት ሐዲስ
ﺇﻥ ﺍﻟﺪﻳﻦ ﻳﺴﺮ، ﻭﻟﻦ ﻳﺸﺎﺩ ﺍﻟﺪﻳﻦ ﺃﺣﺪ ﺇﻻ ﻏﻠﺒﻪ، ﻓﺴﺪﺩﻭﺍ ﻭﻗﺎﺭﺑﻮﺍ ﻭﺃﺑﺸﺮﻭﺍ، ﻭﺍﺳﺘﻌﻴﻨﻮﺍ ﺑﺎﻟﻐﺪﻭﺓ ﻭﺍﻟﺮﻭﺣﺔ ﻭﺷﻲﺀ ﻣﻦ ﺍﻟﺪﻟﺠﺔ
“ይህ ዲን ገር ነው ዲኑን ከሚገባው በላይ ያጠባበቀው ሰው ዲኑ ያሸንፈዋል። ትክክለኛውን መንገድ ያዙ፣ ተቃረቡም አንዲሁም በበጎ ነገር ተበራቱ፤ በቀኑም በጧቱ፤ በረፋዱ እና በማለዳው ጊዜ በአላህ ታገዙ” ። (ሶሂህ ሐዲስ)
በሌላ ሶሂህ በሆነ የሀዲስ ዘገባ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)
ﻭﻓﻲ ﺍﻟﺼﺤﻴﺢ ﺃﻧﻪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﺩﺧﻞ ﺍﻟﻤﺴﺠﺪ ﻣﺮﺓً ﻓﺮﺃﻯ ﺣﺒﻼً ﻣﻤﺪﻭﺩًﺍ ﺑﻴﻦ ﺳﺎﺭﻳﺘﻴﻦ، ﻓﻘﺎﻝ : “ ﻣﺎ ﻫﺬﺍ ﺍﻟﺤﺒﻞ؟ ﻗﺎﻟﻮﺍ : ﻫﺬﺍ ﺣﺒﻞ ﻟﺰﻳﻨﺐ، ﻓﺈﺫﺍ ﻓﺘﺮﺕ ﺗﻌﻠَّﻘﺖ ﺑﻪ، ﻓﻘﺎﻝ ﺍﻟﻨﺒﻲ - ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ :- “ ﻻ .. ﺣﻠُّﻮﻩ، ﻟﻴﺼﻞ ﺃﺣﺪﻛﻢ ﻧﺸﺎﻃﻪ، ﻓﺈﺫﺍ ﻓﺘﺮ ﻓﻠﻴﻘﻌﺪ ”
“አንድ ጊዜ መስጅድ ሲገቡ ከሁለት ወጋግራ እንጨቶች ላይ የታሰረ ገመድ ተመልክተው ‘ምንድን ነው ይህ ገመድ’ ብለው ጠየቁ። ሰዎችም ይህ ገመድ የዘይነብ ነው፤ ከሰላት ስትደክም የምትይዘው ነው ብለው ነገሯቸው።፡

ﻭﻓﻲ ﺍﻟﺼﺤﻴﺢ ﺃﻧﻪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﺩﺧﻞ ﺍﻟﻤﺴﺠﺪ ﻣﺮﺓً ﻓﺮﺃﻯ ﺣﺒﻼً ﻣﻤﺪﻭﺩًﺍ ﺑﻴﻦ ﺳﺎﺭﻳﺘﻴﻦ، ﻓﻘﺎﻝ : “ ﻣﺎ ﻫﺬﺍ ﺍﻟﺤﺒﻞ؟ ﻗﺎﻟﻮﺍ : ﻫﺬﺍ ﺣﺒﻞ ﻟﺰﻳﻨﺐ، ﻓﺈﺫﺍ ﻓﺘﺮﺕ ﺗﻌﻠَّﻘﺖ ﺑﻪ، ﻓﻘﺎﻝ ﺍﻟﻨﺒﻲ - ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ :- “ ﻻ .. ﺣﻠُّﻮﻩ، ﻟﻴﺼ
ﻞ ﺃﺣﺪﻛﻢ ﻧﺸﺎﻃﻪ، ﻓﺈﺫﺍ ﻓﺘﺮ ﻓﻠﻴﻘﻌﺪ ”
“አንድ ጊዜ መስጅድ ሲገቡ ከሁለት ወጋግራ እንጨቶች ላይ የታሰረ ገመድ ተመልክተው ‘ምንድን ነው ይህ ገመድ’ ብለው ጠየቁ። ሰዎችም ይህ ገመድ የዘይነብ ነው፤ ከሰላት ስትደክም የምትይዘው ነው ብለው ነገሯቸው።፡ እሳቸውም ‘ይህ አይሆንም.ገመዱን ፍቱት አንደኛችሁ በተነቃቃበት ጊዜ ሶላት ይስገድ፤ ሲደክም (ሲታክት) ይቀመጥ (ይተኛ)’ አሉ።” (ሶሂህ ሐዲስ)
3. መልካም ጓደኛ
መልካም ጓገኛ በመልካም ስራ ላይ ለመዘውተር ሌላው አጋዥ ሐይል ነው። ሰው ጓደኞቹ የሚሰሩት መልካም ስራ ሲመለከት እሱም ያን ስራ ለመስራት ይነሳሳል። እነሱ ለመልካም ስራ ሲተጉ እያየ እሱ አለመስራቱ የሀፍረት ስሜት እንዲያድርበት ያደርገዋል። ስለሆነም ሲመለከቷቸው አላህን የሚያስታውሱ፤ ንፁህ፣ ደረጃቸው ከፍ ያለና መልካሞች ጋር ጓደኝነት መመስረት ያስፈልጋል። ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እንዳሉት
ﺇﻥ ﻣﻦ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﻣﻔﺎﺗﻴﺢ ﻟﻠﺨﻴﺮ ﻣﻐﺎﻟﻴﻖ ﻟﻠﺸﺮ
“ከሰዎች መካከል የበጎ ነገር ቁልፍ በእጃቸው የተዳረገላቸውና የመጥፎ ነገር መዝጊያም በእጃቸው የተደረገላውቸው ሰዎቸ አሉ” (ሐሰን ሐዲስ)
ጉዳዩ እንዲህ ከሆነ ለበጎ ነገር ቁልፍ የሆኑ ሰዎችን መጎዳኘን ይገባናል። ቀልባችንን ለውዴታውና እሱን ለማስታውስ ይከፍትልን ዘንድ አላህን እንጠይቀዋለን።
ምርጥ ተምሳሌት፡-
ከዚህ በመቀጠል እስኪ ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች መካከል በዱንያ ላይ በህይወት እያሉ የጀነት ሰዎች የተባሉትን እንተዋወቅ። ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) አቡሁረይራ በዘገቡት ሐዲስ ስለ አቡበከር እንዲህ አሉ፤
ﺃﻥ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻗﺎﻝ ﻳﻮﻣًﺎ ﻣﻦ ﺃﺻﺒﺢ ﻣﻨﻜﻢ ﺍﻟﻴﻮﻡ ﺻﺎﺋﻤًﺎ؟ ﻗﺎﻝ ﺃﺑﻮ ﺑﻜﺮ : ﺃﻧﺎ، ﻗﺎﻝ : ﻣَﻦ ﺍﺗﺒﻊ ﻣﻨﻜﻢ ﺍﻟﻴﻮﻡ ﺟﻨﺎﺯﺓ؟ ﻗﺎﻝ : ﺃﺑﻮ ﺑﻜﺮ : ﺃﻧﺎ، ﻓﻘﺎﻝ : ﻣﻦ ﻋﺎﺩ ﻣﻨﻜﻢ ﺍﻟﻴﻮﻡ ﻣﺮﻳﻀًﺎ؟ ﻗﺎﻝ ﺃﺑﻮ ﺑﻜﺮ : ﺃﻧﺎ، ﻗﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ : ﻣﺎ ﺍﺟﺘﻤﻌﻦ ﻓﻲ ﺭﺟﻞ ﺇﻻ ﻭﺩﺧﻞ ﺍﻟﺠﻨﺔ
(ﺻﺤﻴﺢ)
“ከእናንተ መካከል ዛሬ ጾመኛ ማነው? አቡበከር እኔ አሉ። ዛሬ ከእናንተ መካከል ጀናዛ (ሬሳ) የሸኘ ማነው? አሉ አቡበከር እኔ አሉ። ከእናንተ መካከል ዛሬ በሽተኛን የጠየቀ ማነው? ሲሉ አቡበከር እኔ አሉ። ረሱልም (ሰ.ዐ.ወ) እነዚህ ነገሮችን በአንድ ላያ ያስገኘ ሰው ጀነት ገባ አሉ።” (ሶሂህ)
ቀጣዩ ደግሞ ቢላል ኢብኑ ረሃሕ ነው። የሐበሻ ባሪያ የነበረው ቢላል ኢስላም ደረጃውን ከፍ አደረገው። በአንድ ወቅት ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)
ﻳﺎ ﺑﻼﻝ، ﺣﺪﺛﻨﻲ ﺑﺄﺭﺟﻰ ﻋﻤﻞ ﻋﻤﻠﺘﻪ ﻓﻲ ﺍﻹﺳﻼﻡ؛ ﻓﺈﻧﻲ ﺳﻤﻌﺖ ﺩُﻑَّ ﻧﻌﻠﻴﻚ ﺑﻴﻦ ﻳﺪﻱَّ ﻓﻲ ﺍﻟﺠﻨﺔ، ﻓﻘﺎﻝ ﻣﺎ ﻋﻤﻠﺖ ﻋﻤﻼً ﺃﺭﺟﻰ ﻋﻨﺪﻱ ﻣﻦ ﺃﻧﻲ ﻟﻢ ﺃﺗﻄﻬَّﺮ ﻃﻬﻮﺭًﺍ ﻓﻲ ﺳﺎﻋﺔ ﺑﺎﻟﻠﻴﻞ ﺃﻭ ﺍﻟﻨﻬﺎﺭ ﺇﻻ ﺻﻠﻴﺖُ ﺑﺬﻟﻚ ﺍﻟﻄﻬﻮﺭ، ﻣﺎ ﻛُﺘِﺐَ ﻟﻲ ﺃﻥ ﺃﺻﻞ
“ጀነት ውስጥ የጫማህን ኮቴ ሰምቻለሁ። ቢላል ሆይ! ኢስላም ውስጥ ሆነህ በጣም ጥሩ የሆነ የሰራኸውን ስራ አስኪ ንገረኝ አሉት። ቢላልም ውዱእ ካደረኩ በኋላ በቀንም ይሁን በማታ አላህ የፃፈልኝን ያህል ሰላት እሰግዳለሁ። ከዚያ ውጪ ሰራሁት የምለው ስራ የለኝም አላቸው።”
ስለሆነም አቅማችንን አሟጠን በመጠቀም ወደ አላህ ዒባዳ በመስራት መቃረብን ልናበዛ፤ ይህንንም የመጀመሪያም የመጨረሻም ልናደርገው ይገባል። በሱም በመታገዝ መፈክራችንን
ﻭَﻋَﺠِﻠْﺖُ ﺇِﻟَﻴْﻚَ ﺭَﺏِّ ﻟِﺘَﺮْﺿَﻰٰ
“አንተ ትወደኝ ዘንድ ወደ አንተ ተቻኮልኩ” የሚለው ቁርአን አንቀፅ ይሁን።
ይህ ነው አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነው ዘውታሪ መልካም ስራ። አላህ ሁላችንንም መልካሞችና በበጎ ስራ ቀጥ ብለው ከሚቆሙት ያድርግን። ሞት ሲመጣባቸውም በጀነት ከተበሰሩትና እሱ ካልተቆጣቸው አላህ ያድርገን!
[١٥/‏٦ ١٠:٤٤ م] عاش مح: ሸዋል እና ስድስቱ የጾም ቀናት!

በአቡ ሀይደር

ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡

የረመዷን ወር ፆም መገባደድን ተከትሎ (አላህ ይቀበለን) የሚመጣው የሸዋል ወር ፆም ነው፡፡ እሱን በተመለከተ መጠነኛ ማስታወሻን እንካችሁ ለማለት ወደድኩ፡፡ ወማ ተውፊቂ ኢልላ ቢላህ፡፡

1/ ሸዋል የወር ስም እንጂ የፆም ስም አይደለም፡፡ ይህ ወር እንደ ረመዷን ወር 29/30 ቀናት አሉት፡፡ ከረመዷን በኋላ ተከትሎ የሚመጣ 10ኛ ወር ነው፡፡

2/ በዚህ ወር ውስጥ የሚፆም የስድስት ቀናት ፆም አልለ፡፡ ይህንን ስድስት ቀናት ከረመዷን ጋር አብሮ ለፆመ ሰው፡ የአንድ ዓመት ፆምን ያህል አጅር ያገኛል፡፡ መልካም ስራ መነሻ ብዜቱ በአሥር ነውና (አል-አንዓም 6፡160) የአንድ ወር የረመዷን ፆም በአስር ወር ሲባዛ፣ የሸዋል ወር ስድስት ቀን ፆም ደግሞ በስልሳ ቀናት (ሁለት ወር) ይባዛና፡ በድምሩ አስራ ሁለት ወራት (ሙሉ አንድ ዓመት) ፆም ይሆናል ማለት ነው፡፡

3/ የሸዋል ወር ፆም የአባቶችና እናቶች፡ ወይንም የኢማሞችና የትልልቅ ሰዎች ፆም ብቻ አይደለም፡፡ የረመዷንን ፆም የተሳተፈ የአላህ ባሪያ ሁሉ፡ የሸዋልን ወር ፆምም መሳተፍ ይችላል፡፡ ዕድሉ ለሁሉም ክፍት ነውና፡፡

ወይንም፡- ባልፆመው የማስጠይቀኝ፡ ግዴታ ያልሆነ ተግባር ነው ብለን አንሳነፍ፡፡ በመፆማችን ደግሞ የምናገኘውንም አጅር እናስላ፡፡ አንድ ወር ሙሉ በተከታታይ በአላህ ተውፊቅና እገዛ መፆም ከቻልን፡ ስድስት ቀናትን መፆም ደግሞ እንደምን ይጠናብናል?
አንዳንዱ ደግሞ ፆሙ ይከብዳል እንደ ረመዷን አይቀልም ይላል፡፡ እውነት ነው የሸዋል ወር ፆም ይከብዳል፡፡ ምክንያቱም፡-
አንድ፡- በረመዷን የታሰረው ቀንደኛው ጠላታችን ሸይጧን ከዒድ ሶላት መጠናቀቅ በኋላ ተፈትቷልና ወደ ስራው ይመለሳል፡፡ እኛንም ለማሳሳት ይጥራል፡፡

ደግሞም ይህንን የሸዋልን ፆም ልክ እንደ ረመዷኑ ቤተሰብ፣ ጓደኞችና የመስጂድ ጀመዓዎች ሁሉም በአንድ ስለማይፆሙት፡ በሚፆሙት ላይ (አላህ ያገራለት ሲቀር) ሊከብድ ይችላል፡፡ ቢሆንም አላህ ዘንድ የሚገኘውን ሽልማት ያሰበና ያመነ ባሪያ ሊከብደው አይገባም፡፡

4/ የሸዋል ወር ፆም እንደ ረመዷን ወር ዋጂብ (ግዳጅ) የሆነ ፆም ሳይሆን፡ ድርጊቱ ሙስተሐብ (የተወደደ) የሆነ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም ፆሙን ያልተሳተፈ ሰው ኃጢአተኛ ተደርጎ አይቆጠርም፡፡ ትልቅ አጅር አመለጠው እንጂ፡፡

5/ የሸዋልን ወር ፆም መሳተፍ የሚፈልግ የአላህ ባሪያ፡- ከፈለገ ከዒዱ ማግስት አንስቶ በተከታታይ ስድስት ቀናት፣ ወይንም አፈራርቆ በተመቸው ቀን ስድስት ቀናትን መርጦ፣ ወይንም ከሰኞና ሀሙስ ፆም ጋር በአንድ ኒያ ሁለቱንም በማገናኘት (የሰኞና የሀሙስን እንዲሁም የሸዋልን ስድስቱን)፣ ወይም ከአያመል-ቢድ (የወሩ 13.14.15ኛው ቀን) ጋር በማቆራኘት፣ ወይም እሱ በተመቸው መንገድ ወሩ ከመጠናቀቁ በፊት መፆም ይችላል፡፡ (ፈታዋ ኢስላሚያህ፡ ኢብኑ ዑሠይሚን 2/154)፡፡

6/ መቼም ይሄ (shortcut) አቋራጭ መንገድ የሚባለው ነገር ተላምዶናል፡፡ በሰላምታ ወቅት (as wr wb) በሰላዋት ጊዜ (s.a.w) በምስጋና ተግባር ላይ (jzk)… ታዲያ አሁንም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንዲሉ፡ የረመዷንን ቀዷእና የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆም በአንድ በመነየት አጣምሮ መፆም ይቻላል ወይ? የሚል ጥያቄ ከተነሳ፡፡
ይህን ጥያቄ ፈዲለቱ-ሸይኽ ሙሐመድ ቢን-ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይመልሱታል፡-

‹‹የረመዷን ቀዷ እያለበት የዐረፋን ቀን ወይም የዐሹራእን (የሙሐረምን 10ኛ ቀን) የፆመ ሰው ፆሙ ትክክል ነው፡፡ ደግሞም እነዚህን ቀናት የረመዷንን ቀዷእ በመክፈል ኒያ በአንድ ላይ ቢፆማቸው ሁለት አጅርን ያገኛል፡፡ የዐረፋ ቀን ፆምና የዐሹራእ ፆምን አጅር ከረመዷን ቀዷእ አጅር ጋር ማለት ነው፡፡ እሱም እነዚህ የሱና ፆሞች ቀጥታ ከረመዷን ጋር ቀጥታ ግንኙነት የሌላቸው በመሆናቸው ነው፡፡ የሸዋል ወር ስድስት ቀናት ፆም ግን ከረመዷኑ ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ምክንያት በአንድ ኒያ ሰብስቦ መፆሙ አይሆንም፡፡ ቅድሚያ ቀዷውን ከፍሎ ከዛም የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆም ያስከትል›› (ፈታዋ-ሲያም 438)፡፡

በዚህም ሰበብ የረመዷን ቀዷ ያለበት ሰው፡ በሸዋል ወር ውስጥ ከሸዋል ስድስቱ የሱና ፆሞች ጋር በአንድ ኒያ ሰብስቦ መፆም እንደማይችል የኢስላም ሊቃውንት ገልጸዋል፡፡ ምክንያቱንም ሲያብራሩ፡- የረመዷን ቀዷእ ሊከፈል የሚገባው ግዴት (ዕዳ) ሲሆን፡ የሸዋል ወር ስድስቱ ቀናት ፆም ግን በግለሰቡ ምርጫ ላይ የተወሰነ ነው፡፡ ከፈለገ ሊፆመው ካልፈለገ ሊተወው ይችላልና፡፡ ስለሆነም የግድ ኒያውን ከአላህ መብት በመጀመር ግዴታውን መክፈል ይጠበቅበታል፡፡

7/ የረመዷን ቀዷእ ያለበት ሰው፡ ቀዷውን ከመክፈሉ በፊት የሸዋልን ወር ስድስት ቀናት ፆም መፆምና ከዛ በኋላ በተመቸው ወቅት የረመዷንን ቀዷእ ማውጣት ይችላል ወይ? የሚለው ጥያቄ፡ በዑለማዎች ዘንድ የሀሳብ ልዩነት የተንጸባረቀበት ነው፡፡ የሀሳብ ልዩነቱ መነሻ የሆነውም ቀጣዩ ሐዲሥ ነው፡-

عَنْ أَبِي أَيُّوبَ الْأَنْصَارِيِّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: "مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ كَانَ كَصِيَامِ الدَّهْرِ". أخرجه أحمد (5/417 رقم 23580) ، ومسلم (2/822 رقم 1164) ، وأبو داود (2/324 ، رقم 2433) ، والترمذى (3/132 ، رقم 759).

ከአቢ አዩብ አል-አንሷሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ረመዷንን የፆመና ከሸዋል ወርም ስድስት ቀናትን ያስከተለ፡ አመቱን ሙሉ እንደፆመ ሆኗል" (ሙስነድ ኢማሙ አሕመድ 23580፣ ሙስሊም 1164፣ አቡ ዳዉድ 2433፣ ቲርሚዚይ 759)፡፡

በዚህ ሐዲሥ ላይ የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆም ያስከተለ የተባለው ረመዷንን የፆመው ሰው ነው፡፡ በዑዝር ምክንያት የረመዷን ቀዷእ ያለበት ሰው ደግሞ ወሩን ባለማጠናቀቁ፡ ‹ረመዷንን የፆመ› የሚባለው ውስጥ የሚካተት አይደለምና፡ ቃል የተገባለትን ሙሉ የአመት ፆም አጅር ያገኝ ዘንድ ቅድሚያ ከቀዷእ መጀመር አለበት የሚለው የከፊል የኢስላም ሊቃውንት አቋም ነው፡፡

1. ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁላህ) ፡- ፈታዋ ኑሩን ዐለ-ደርብ ካሴት ቁ 918

2. ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) ፡- ፈታዋ አል-ሐረሙል መኪይ ካሴት ቁ 7

ነገር ግን የሸዋልን ወር ስድስት ቀናት አስቀድሞ ቢፆምና ከዛ በኋላ በተመቸው ወቅት የረመዷንን ቀዷእ ቢያስከትል፡ የረመዷኑ ፆም ምንም እንደማይሆንበትና ፆሙም ችግር እንደማይፈጥርበት አክለው ገልጸዋል፡፡ ችግሩ ያለው የሸዋል ወር ስድስቱ ቀናት ፆም ላይ ነው፡፡ የነዚህን ስድስት ቀናት ፆም አጅር ለመሸመት፡ በሐዲሡ በተነገረው መሰረት ቅድሚያ የረመዷን ወር ፆም (ከነ-ቀዷው) መጠናቀቅ አለበት የሚል ነው፡፡
ከኺላፍ መውጣት በራሱ ተወዳጅ ተግ
ባር ነውና፡ ሁሉንም ሊያስማማና የኛንም
[١٦/‏٦ ١٠:٢٠ ص] عاش مح: እናትህን ትወዳታለህ ከወደድካት ለእናትህ ውለታ ይህቺን ፅሁፍ አንብብላት ። ከሁሉም በላይ ግን ሼር አድርግ።
:
◣የእናት ውለታዋ◥

:
"እናቴ አንድ አይና ስለነበረች በጣም እጠላት ነበር።"

ይላል ባለ ታሪኩ.....
"እጅግም ታሳፍረኝ ነበር ፣ እኔ የምማርበት ትምህርት ቤት ለተማሪዎችና ለአስተማሪዎች ምግብ በማዘጋጀት ነበር ቤተሰባችንን የምታስተዳድረው።
:
የአንደኛ ደረጃ ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ እናቴ ትምህርት ቤት ሰላም ልትለኝ ስትመጣ እጅግ እሸማቀቅ ነበር። እንዲያውም "እንዴት እንዲህ ልታደርግ ቻለች?" በማለት በመጥፎ አስተያየት ገላመጥኳትና ዘግቻት ከፊቷ ሄድኩ። በሚቀጥለው የትምህርት ክፍለ ጊዜ አንዱ ጓደኛዪ " አንተ! እናትህ አንድ አይን ነው ያላት?" ሲለኝ ያኔ ምድር ብትውጠኝ በወደድኩ : ራሴን ባጠፋ ደስ ባለኝ ነበር። ስለዚህ ከዚህ ሁሉ ነገር እናቴም አንደኛውን ብትጠፋልኝ ምኞቴ ነበር።
:
ያን ቀን ቤት ከሄድኩ በኋላ "መሳቂያና መሳለቂያ ከምታደርጊኝ ለምን አትሞችም?" ብዬ ጮህኩባት ፣ እናቴ ግን ምንም አልመለሰችልኝም ፣ እኔ በጣም ተበሳጭቼ ስለነበር የምናገረውን አላወኩም፣ በተናገርኳት ነገር ምን ሊሰማት እንደሚችል ደንታም አልሰጠኝ።
ከዚህ በኋላ ግን ከእሷ ጋ መኖር ስላልፈለኩ ከቤት ወጣሁና ጠንክሬ እየተማርኩ ባለሁበት ጊዜ የውጭ ትምህርት እድል አጋጥሞኝ ከሀገር ወጣሁ ፣ ከዚያም ሚስት አገባሁ ፣ ልጆችን ወለድኩ ፣ ቤት ገዛሁ ፣ ደስ የሚል ህይወት ነበረኝ።
:
ከአመታት በኋላ ተገናኝተን የማናውቀው እናቴ ወዳለሁበት መጣች ፣ በሬ ላይ በቆመችበት ወቅት ልጆቼ በሹፈት አይን እየተመለከቱ ሳቁባት፣ እኔም "ማን ነይ ብሎሽ ነው ፣ የመጣሽው? ፣ አንቺን ማየት አልፈልግም ፣ ከዚህ ውጪ በቃ" ብዬ ጮህኩባት....እሷም በለሰለሰ ድምፅ " ወይኔ! በጣም ይቅርታ አድራሻ ተሳስቻለሁ ማለት ነው" ብላ በፍጥነት ወጥታ ሄደች።
:
ይህ ከሆነ በኋላ የስብሰባ ደብዳቤ ከድሮው ትምህርት ቤት ደረሰኝ ባለቤቴን ተሰናብቼ ሄድኩ ፣ ስብሰባዬን ጨርሼ ስመለስ በዚያውም አሮጊቷን እናቴን ልያት ብዬ ወደ እናቴ ቤት አቀናሁ ፣ እሷ ግን ቤት አልነበረችም ፣ ጎረቤት የነበሩትን ሰዎች ስጠይቃቸው ሞታለች አሉኝ። ይህን ስሰማ ምንም የተሰማኝ ነገር አልነበረም።
ግን ልታገኘኝ ፈልጋ እንደነበረና ደብዳቤ እንዳስቀመጠችልኝ ነገሩኝ።

:
ደብዳቤው እንዲህ ይላል ..."
:
" ውድ ልጄ! ምን ጊዜም አስብሃለው ፣ ያኔ ቤትህ መጥቼ ልጆችህን ስላሳፈርኩብህ በጣም ይቅርታ። ለትምህርት ቤት ስብሰባ ልትመጣ ነው ሲባል በሰማሁ ጊዜ ደስ ብሎኝ ነበር ፣ ነገር ግን የአልጋ ቁራኛ ስለነበርኩ ላገኝህ አልቻልኩም።

በህይወትህ ዘመን በጓደኞችህ ፊት ሁሉ ስላሳፈርኩህና ስላሸማቀኩህ ይቅርታ ፣ አየህ ልጄ ......
በህፃንነትህ ጊዜ አደጋ ደርሶብህ ነበር ፣ በዚያ አደጋም ሳቢያ አንድ አይንህን አጣህ ...ነገር ግን እኔ እናትህ አንተ አንድ አይና ሆነህ እንድታድግ እድሜህን ሙሉ በሙሉ እንድትሆን ብዬ አይኔን ሰጠውህ። በሁለት አይንህ አለምን ስትቃኝ ሳይህ እጅግ ደስ ይለኝና እኮራም ነበር ፣ ውድ ልጄ ...በእኔ ምትክ አንተ ሙሉ ስለሆንክ ደስ ይለኛል።"
:
አፍቃሪ እናትህ !
።።።።።።።።።።።።።
:
ስንቶቻችን በወላጆቻችን እናፍር ይሆን? ስንት አይነት መስዋዕት ከፍለው አሳድገውን ይሆን? ዛሬስ ምላሻችን ምንድነው?
ጊዜው ያልመሸባችሁ በቻላችሁት አቅም ሁሉ ‘አለሁልህ አባቴ ፣ አለሁልሽ እናቴ’ በሏቸው። እኛን ሰው ለማድረግ ከሰውነት ተራ ወጥተው ያሉ ወላጆችን ቤቱ ይቁጠራቸው። እናስተውል! እንዳይቆጨን!
:
ብዙ ወላጆች እኛን ራሳችንን እንጅ የእኛን ነገር አይፈልጉም ፣ በተቃራኒው ደግሞ እኛ የእንሱን ነገር እንጅ እነሱን አንፈልግም። እነሱን በመፈለግ ፍቅራችንን እናሳያቸው!

ይህ ታሪክ ከደረሳችሁ እናንተ ጋር እንዲቀር አትፍቀዱ ፣አስተማሪ ስለሆነ ሼር አድርጉት!

📮 @QedmiyaLaislam
[١٧/‏٦ ٨:٣٣ ص] عاش مح: ዒባዳ ላይ ፅና ወደ ኋላ አትሽሽ
በፆም አሳምረህ ሲወጣ አታበላሽ
ረመዳን ሲወጣ ከጌታው የሚሸሽ
ምንኛ ሞኝ ነው የሰራውን አፍራሽ

የረመዳን ዓቢድ በፆም ብቻ ሰጋጅ
መስጂድ አጨናንቆ ሲወጣ ተወጋጅ
ረመዳን ሲወጣ ወደ ወንጀል ነጓጅ
መሆኑን አውጇል የእስረኛው ወዳጅ

እባክህ ወንድሜ ጌታን ሁሌ አምልክ
በሰላትህ ዘውትር ትሆናለህ ብሩክ
ከሸይጣን ወጥመድ ራቅ ለሱ አትንበርከክ
ዓላማህ ላይ ፅና እውነት ወንድ ከሆንክ

እህቴዋም ፅኚ በጌታሽ መንገድ ላይ
በሰላት በሂጃብ አትሁኝ ወላዋይ
ወንድን ምታሳስት አትሁኝ አማላይ
ራስሽንም ጠብቂ ከፋጂር አታላይ

እንዴት ያምር ነበር ረመዳን ነሻጣው
ፆሙ ተራዊሁ ድባቡ ሞቅታው
ቲላወቱል ቁርአን ብዛቱ የኺትማው
ተሰናብቶን ሄደ ሁሉም ተወጋጅ ነው

ቀድሞም ተነግሮናል ቶሎ እንደሚሄድ
አያመል መዕዱዳት ፈጥኖ ሚገባደድ
ለነገ ቤታችን በቂ ስንቅ ሳንሰንቅ ባግባቡም ሳንነግድ
ገባ ሲባል ወጣ እየተቻኮለ እያየን ሲነጉድ

ግን ተሰፋ አልጨለመም በረመዳን መውጣት
ሀጅም ተከትሏል ፆም በሄደ ማግስት
ሰላት ሁሌም አለ በቀንም በሌሊት
ሱና ፆምም አለ ዚክርም ማታ ጠዋት

በዒባዳ ፅና አታቁም ስራህን
ረሱልን ተከተል አታምፅ ወዳጅህን
በሱና ፆም በርታ አታቁም ሰላትክን
ፅናት እንዲሰጥህ ተማፀን ጌታህን






[١٧/‏٦ ٨:٣٣ ص] عاش مح: ውዲቷ እህቴ ሆይ!
---------//--------
መሪየም ቢንት ኢምራን ታውቃያትለሽ?
ቁርዓኑስ አንብበሺዋል ስለሷ ምን እንደሚል? ጌታችን በተከበረ ቃሉ ምን ያህል የተከበረችና ንፁህ ሴት እንደነበረች ሲያሞግሳት እንደነበር! ይህ ነገር ቁርዓኑ ውስጥ አላነበብሽም?

ምን ነካሽ እህቴ?
አንቺ እኮ አንድ ነሽ! ልትሆኚውም የምትችይው ለአንድ ሰው ነው። ለምን በአደባባይ በካፊሩም በሙስሊሙም ወንድ ሆድ ቁርጠት የሚያስነሱ ቃሎች ትሸመገያለሽ? በቃ ቆንጆ ነሽ! ጌታሽ የሰው ልጅ ባማረ መልኩ ፈጥረነዋል ብሎሻል! ታዲያ ያማረሽ መሆንሽ ከጌታሽ ከነገረሽ የመጣልሽን ቃል ስለምን ጀርባ ሰጠሺው?! ከአላህ ፍቃድ ውጭ ተሰብስቦ ሊጎዳሽም ሊተቅምሽም የማይችል ፍጡር ቃል በለጠብሽን? እህቴ ሆይ! ስትጎጂ ማየት አልሻም! እኔ ካንቺ በልጬ አይደለም ይህን የምነግርሽ ግና አድምጪኝ "በስጋ ከተዛመደ ይልቅ በእምነት የተዛመደ ይበልጣልና" አድምጪኝ! ወደ እሳት ስትጎተቺ በፍፁም ላይ አልፈልግም! አንቺ የአንድ ሆነሽ ሳለ አደባባይ ላይ ፎቶሽ ለጥፈሽ ስንቱን ወንድ ፈተንሽ? አስበሺው ታውቃለሽ? ስንቱን ወንጀል ሸምተሽ ፌስ ቡክሽን እንደምትዘጊ አስተውሰሽዋልን? በአንቺ ፎቶ የመጣ በኮሜንት ሲያበረታታሽ የነበረውም ሰው ወንጀል ሳይቀነስ ላንቺም እንደሚሆን ዘነጋሺው? ስንቱ መላኢካ እረገበሽ መሆኑን ታውቂዋለሽ? ለምን ግን ማሰብ ተሳነን እህቴ? መግቢያዬ ላይ መርየምን ታውቃታለሽ ብዬ ለምን እንደጠየኩሽ ታውቃለሽ አይደል? ልገርሽማ አድምጪኝ መርየም ማለት በተቀደሰ በአላህ ቃል(ቁርዓን)ላይ ስሟ ለ24 ጊዜ የተጠቀሰች ምርጥ የአላህ ባለሟል ነበረች! እርሷ እንዳቺና እንደኔ ሴት ነች ነገር ግን ከጌታዋ ባላት ግንኙነት እጅጉን ትበልጠናለች! የቁርዓን ምዕራፍም በስምዋ የተሰየመላት ብቸኛ ሴት ነች እሱም ምእራፍ(19)ሱረቱ መርየም የሚል ምእራፍ አላት ይህም ምእራፍ ስለ ህወት ታሪክዋ የሚአወራ ሲሆን መርየም በቁርዓን ላይ በስማቸዉ ምእራፍ ከተሰየመላቸዉ ስምንት ሰዎች ዉስጥ አንዷ ነች መርየም በተለይ
ከቁርዓን ላይ የተጠቀሰችው ከአስያ ጎን ለጎን ነዉ። ቁርዓን(66:11) ማንበበብ ትችያለሽ!

መርየም በእስልምና በጣም ግዴታ የሆነ ህግን ነበር ያከበረችው! እኔና አንቺስ? በሚዲያ ፊትና እንሁን እህቴ? በጭራሽ ይህ መሆን የለበትም። አሁንም የምልሽ አለኝ ስለ መርየም! በቁርዓን ምዕራፍ ዘወትር የተወራላት በቤተ መቀደስ (በመስጅድዶች ዉስጥ)በቁርዓን ላይ እንደተጠቀሰው ኢሳ(ዐለይሂ ሰላም )በአለማቱ ጌታ አላህ (﷽)ፍላጎት በተአምር ከአባት ውጭ ወይንም ያለ ግብረ ስጋ ግንኙነት ነበር በአላህ ተዓምር የተወለደው። መርየም አላህ በምድር ላይ አልቆ የመረጣት ሴት ስትሆን ከአራት ምርጥ ሴቶቻችን ውስጥ አንድዋ ነች

የተመረጠች መሆኗን ለማረጋገጥ ከፈለክሽ ቅዱስ ቁርዓን(3:42)ከፍተሽ አንቢቢው። እዚህ ልፅፍልሽ አልሻም ለምን ብትይኝ የጌታሽ ቃል ቁርዓን ገልፀሽ እንድታነቢ ስለፈለኩ! ታውቂያቸዋለሽ አራት ለሙስሊም ሴቶች አራያ ለአማኞች ምሳሌ የሆኑት እነማን እንደሆኑ? ይኸውልሽ አንቢቢማ፦ መርየም ቢንት ኢምራን፣ አስያ ቢንት መህዙም፣ ኽዲጃ ቢንትኹወይሊድ፣ ፋጢማ ቢንት ሙሃመድ(ﷺ)!

እኔና አንቺስ እህቴ ምንድነው አላማና እቅዳች?ን ሚዲያ ላይ ፎቶ መለጠፍ ወንዶችን ሰብስቦ የእነርሱ እሬት ቃል ማንበብ? በጣም እኮ ነው የሚያስጠላው እንዴት ግን አስቻለሽ ሁሉ የኔ እያለ በለጠፍሺው ፎቶ የሚጠራሽና ማሻ አላህ እያለ የሚያሞግስሽ? ኧረ አዑዙቢላህ! ከባልሽ እና ከዘመድ አዝማድሽ ውጪ እያቆለማመጠና ለእርሱ ሳትሆኚ የእኔ እያለ የሚጠራሽ በአድ ወንድ ያውም በሚዲያ እውነት የሱ ነሽ ነው? እህቴ ለማን ተውበሽ መቅረብ እንዳለብሽ አታውቂም? አንቺ አንድ ነሽ ልትሆኚም የምትችይው ለአንድ ወንድ ነው። ለእርሱ ነው አምረሽ ተውበሽ መቀረብ ያለብሽ እንጂ ለሚዲያ አይደለም! አስታውሺ እራስሽን አትጠብቂ ንፁህ ውብ አትኙ እያልኩሽ አይደለም። እንደውም ነብዩ (ﷺ)ለንፅህና ትኩረት በመስጠት እንዲህ ብለዋል፦ "ንፅህና የእምነት ግማሽ ነው።"(ሙስሊም)

ከዛም ከዚህ መጥቶ ያሻውን ይፅፋል ፊቱና ሆዱን አታውቂ ቀይ ይሁን ቢጫ
እርሱ ግን እየመራሽ ነው ወደ እሳት መቀጣጫ!

እህቴ ሆይ! ከዚህ ማቅ እናምልጥ እደግምልሻለሁ እኔ ከአንቺ ተሽዬ አይደለም። ግና ለመሻሻል ተፍ ተፍ የምል ሴት ነኝ! ለእኔና ለአንቺ ተምሳሌቶች አሉን እነርሱን ለመከት መሞከሩ የተሻለ ነው። እነርሱ ይበቁናል።!!
Telagram
https://t.me/yeswnaehitochmena
"ክርስቲያኖች ይህንን ምስጥር የውቃሉ
እንግዲያውስ.....
ሰይጠራጣሩ #እየሱስ 100% #የአላህ በሪያና መልእክተኛ መሆኑን../ወይም ሰውና ነብይ መሆኑን የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃብ አንብቦ ስጨርሱ የካፍሉ

1. ሉቃስ ወንጌል 7:15 “ታላቅ ነብይ በኛ መካከል ተነስቷል።”

2. ዮ ሐንስ ወንጌል 5:26 “የሰው ልጅ ስለሆነ ይፈርድ ዘንድ ስልጣን ሰጠው ”

3. ዮ ሐንስ ወንጌል 5:19 “አብ ሲያደርግ ያየውን እንጂ ወልድ ከራሱ ምንም ሊያደርግ አይችልም።”
4. ዮ ሐንስ ወንጌል 5:30 “እኔ ከራሴ ባደርግ አንዳች አይቻለኝም እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴ ቅን ነው። የላከኝን ፍቃድ እንጂ ፍቃዴን አልሻም።”
5. ዮ ሐንስ ወንጌል 4:6 “እየሱስ መንገድ በመሄድ ደክሞ ጉድጓድ አጠገብ ተቀመጠ ጊዜውም ስድስት ሰአት ነበር።”
6. ዮ ሐንስ ወንጌል 8:28 “እኔን ከፍ ከፍ አታድርጉኝ ከራሴ ምንም ማድረግ አልችልም።” ይላል እየሱስ ሙሊ ቃሉን ከመጽሐፍ ቅዱስ ያገኛሉ።
7. ዮሐንስ ወንጌል 14:28 አብ (እግዚአብሔር) ከእያሱስ ይበልጣል “የምትወዱኝ ከሆነ አብ ከኔ ይበልጣል” ይላል እየሱስ።
8. ዮሐንስ 20:17 “እየሱስ ወንድማችን ነው አምላክም አለው። ” ሙሉ ቃሉን ከመጽሐፍ ቅዱስ ያንቡ።
መጽሐፍ ምሳሌ 8:12 “የፍጥረቱ ሁሉ መጀመሪያ አደረገኝ” ይላል (እየሱስ ) የእግዜአብሔር ፍጡር እንጅ ፈጣር አይደለም። 1980 መጽሐፍ ቅዱስ ላይ።
9. 1 ኛ ጢሞቲዎስ 2:5

“አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው መካከለኛ ደግሞ አንድ አለ እሱም ሰው የሆነ ከርስቶስ ነው።” እየሱስ ሰው ነው።

ታዲያ ብዙ ወንጌላውያን ለምን እየሱስ ጌታ ነው ብለው ይሰብካሉ ? ትሉ ይሆናል።
2ኛ ጢማቲዮስ 4:3 “ሕይወት የምገኝበትን ትምህርት ያማትታገሱበት ዘመን ይመጣል።” ነገር ግን ጆሮ አችሁን የሚያሳክክ ስለሆነ እንድ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ።
ለዚህ ነው መሰለኝ አስተማሪዎች በዚህ ዘመ ን የበዙትና የገዛ ምኞታቸውን ያለ ማስረጃ የሚሰብኩት
የለመስራጃ ጉዞ የለም ኑ
#ክርስቲያኖች ጥርጣሬን አስወግዱ ኑ ወደ እስለም!!
ሀያሉን አምላከችንን #አላህን ኑ በጋራ እነምልክው እንስገድለት!! ስድብ ዘለፋ እስቶፕ!! ካቻሉ በመስራጃ።
*የማለዳ ወግ...ብልህ መሪና ብልህ የሙስሊም ተወካዮች !!*
==============================
👉🏼አዎ ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት

በዛሬውን የንጉስ ዶር አብይ አህመድ የፖርላማ ጥያቄና ምላሽ የዜግነት ኩራቴ ከፍ ብሏል ። በዚህ ቅዱስ ቀን ብልህ መሪያችን አመስግኖ ብልህ የሙስሊም ተወካዮች ስለ ሀገር ታጋሽነት አለማዘከርና አለማመስገን አይቻልም ። ለምሰጋና መነሻየ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ለንጉሱ ለዶር አብይ አህመድ ያስተላለፉት መግለጫ ነው ። እናም ትንሽ ምስጋና ለማቅረብ ስላነሳሳኝ ምክንያት ልጠቃቅስ !

ንጉሱ ስልጣን ከተረከቡ ጀምሮ በወሰዷቸው መሰረታዊ በርካታ ለውጦችን በተመለከትን ማግስት አልፎ አልፎ የአማራ ብሔር መፈናቀል ፣ የመሳጅዶች መፍረስና የመሳሰሉት ችግሮች እንደ አዲስ ተከስተው ተመልክተናል ። ወደ ተነሳሁበት" የሙስሊማን ጥያቄ ምላሽ ይሰጥ !" የሚል ሁነኛ ጥያቄ ስመለስ ይህ ጥያቄ የአክሱም ሙስሊሞች መብት ይከበር ከሚለው ጋር ተዳምሮ ባሳለፍናቸው ሳምንታት መልክ ተደጋግሞ እየተሰማ ሰንብቷል።

እኔ በምኖርበት የአረብ ሀገር ስደተኛ ኢትዮጵያውያነ አንድ ጥያቄው እየጋመ ሄዶ " ዶር አብይ ይህን ጥያቄ ካልመለሱ ፣ ኮሚቴዎችን ካላነጋገሩ እንደ መሪ አንቀበላቸውም ጉልቻ ቢለዋዎጥ ወጥ አያጣፍጥም " አይነት ተረት በአብዛኛው ሙስሊም ዘንድ መቅረብና መነገሩም እውነት ነው። ጥያቄ ተገቢ ሆኖ ሳለ በዶር አብይ አስተዳደር ላይ ከተጫነው ተደራራቢ የሀገር ፖለቲካ ተስፋ ሰጭ የለውጥ ሒደቱን እንዳያደናቅፍ ከሰጉት ዜጎች መካከል አንዱ ብሆን አትፍረዱብኝ ። ጥያቄውን እንዲመለስ ዘመቻ ሲካሄድ ሒደቱን ወዳልተፈለ አቅጣጫ እንዳይወስደው እንደ ዜጋ ሰግቸም ሰንብቻለሁ። የስጋቴ ምንጭ መሬት ያለውን የወገኖቸን ህመም አሳምሬ ማወቄ ነበር ነው ። ዜጎች እንደ ዜጋ "መብታችን ይከበር!"ማለታቸው ትክክለኛ ጥያቄ ነው ። ሆኖም በሒደት መብታችን ይከበር ያሉ ዜጎች ጥያቄ በክፉዎች ተጠልፎ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንዳያመዝን ከሚል በመነሳትና በሀገሪቱ ካለው የገዘፈ ክምር ችግር አንጻር ለንጉሱ በቂ ጊዜ ይሰጥ ከሚሉት ባይ ነበርኩ ። ንጉሱ ምሉዕ ናቸው ። በቅርቡ ያልተፈቱ ችግሮች መኖራቸውን ጠቁመው ምክክር እንደሚያደርጉ ፍንጭ መስጠታቸውን የፈጠረው እፎይታ በሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ተቀባይነት አግኝቶ ኮሚቴው አዎንታዊ የሆነ ወቅታዊ መግለጫ አውጥቶ መመልከቴ አስደስቶኛል ።

በሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ትናንት አሸባሪ ተብለው ያሳለፉት መከራ የከበደ ነበር ። ዛሬ ያ ስም የእነሱ አይደለም ። በዛሬው ልዩ የፖርላማ ውሎ አንድ አባል ዶር አብይ ለምን አሸባሪ የተባሉትን ፈቱ ተብሎ ተጠይቀው በሰጡት መልስ "አሸባሪነት ምንድነው ? ሽብርተኛ ብሎ ያሰራቸውን ሰዎች መግረፍ ጨለማ ቤት ማስገባት አካል ማጉደል የመንግስት አሸባሪነት ተግባር ነው" ብለው እንቅጩን የህመማችን አንኳር ነግረውናል ። እናም ዘመን ተቀይሮ በሽብር ተከሰው ለአመታት በወህኒ መከራ የገፉት የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን አሸባሪ ያለውን የቀደመ የመንግስትን አካሄድ የሀገሪቱ የበላይ ነቀወፈው አሰወደምመውናል ። እናም የትናንት አሸባሪዎች የዛሬ ሰላማዊ ዜጎችን የሆናችሁት የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት መንገዱን ተመችቷችሁ ዶር አብይን አህመድን መፍትሔ በትግስት እየጠበቅን ፣ መሪያችን እንደግፋለን ማለታችሁን አለማድነቅ አይቻልም !

*"የሙስሊማንን ያልተመለሰ ጥያቄ እንዲመልሱልንና ችግሩን በምክክር እንዲፈቱልን ጊዜ እንሰጥዎታለን"*

የሚል አንድምታ ያለው የሙስሊ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መግለጫ ከስሜት ነጻ የሆነ ፣ አብሮነትና በሀገሪቱ ነባራዊ የፖለቲካ ሁኔታዎችን ከግምት ያስገባ ፣ ከምንም በላይ በኃላፊነት የሚደማቸው ወገኖች በሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች እንዳሉበት የሚጠቁም ድንቅ የአጋርነት የአቋም መግለጫ ነው ። ወቅቱ የሚያስፈልገው እንዲህ አይነት ብልህ አርቆ አሳቢ የሙስሊም ተወካዮችን ነው!
የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራሮች ሆይ እናንተም ስለ ኢትዮጵያ ስትሉ ስላደረጋችሁት ትዕግስት ትመሰገናላችሁ !

*ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት*

ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓም
ወሳኝ የድል መርሆች!

ከቀዳሚ መርሃችን ውስጥ ግልጽነት እና ተሳታፊነት ከምንግዜውም በላይ የሚያስፈልገን ወቅት ላይ እንገኛለን።በኢትዮጵያ መሬት ለተፈጠረው መልካም የነፃነት እድል ከማንም በፊት ፈጣሪ ጌታችንን እናመሰግነዋለን። እንዲሁም ለጌታቸው ብቻ ያደሩ እና የግል ጥቅማቸውን ወደጐን ትተው ሂወታቸውን እና ንብረታቸውን ለገበሩ ምስጋና ይድረሳቸው።ለዚህ ላለንበት የነፃነት ድባብ ሂወታቸውን ያጡ፣ለእስርና እንግልት የተዳረጉና አገር ለቀው በስደት በየቦታው ተበትነው ለቆዩ ሁሉ እንደከፈሉት መስዋእትነት ሁሉን አዋቂው አምላክ አላህ ምንዳቸውን ደራርቦ ይክፈላቸው።በማንኛውም ሁኔታ ምንዳቸውን ከአላህ ብቻ ፈልገው በሚችሉት ሁሉ ከልባቸው ለአገር ነፃነት ያበረከቱ ሁሉ የምንዳው ተካፋይና በውጤቱም ዘውታሪ ደስታን እንዲለግሳቸው ፈጣሪ አላህን እለምነዋለሁ።ከመርሆቻችን እውነተኛ የነፃነት ታጋዮች በደጉም ሆነ በክፉ አጋጣሚ መመሪያቸው ኢስላም ነው።በመጥፎው ክስተቶች ሁሉ ስሜታቸውን ለጌታ በማስገዛት የበደላቸው አካል ላይ ሳይቀር ፍትሃዊ ናቸው። ሰላማዊነትን በትግስት ተላብሰው ከጌታቸው ትእዛዝ ሳይዛነፉ የነብያቸውን ሰ.ዐ.ወ. ፈለግ ተከታዮች ናቸው።ከመርሆቻቸው ድል እንደተቀዳጁ ከተሰማቸው በቁርአኑ ላይ በድል ወቅት ሙስሊም ሊያሳየው የሚገባን ባህሪ ጠንቅቀው ያውቃሉ።በምእራፍ አልነስር (ድል) የታዘዙትን በመተግበር አላህ የቸራቸውን እርዳታ እና እገዛ በትክክለኛው አካሄድ ያስተናግዱታል።"የአላህ እርዳታ በመጣ ግዜ" ያሰብነውና የታገልንለት ነፃነት የተገኘ ግዜ፣"ጌታህን በማመስገን አጥራው" እንዲሁም ምህረትንም ለምነው እርሱ ፀፀትን ተቀባይ ነውና" ይላል።ቆም ብለን እኒህን አንቀፆች ብናጤናቸው እናም አተገባበራቸውን ከነብያችን ሰ.ዐ.ወ. ብንማራቸው መልካም ነው።በሃገራቸው በመካ ስቃይን በእርሱ ትእዛዝ ውስጥ እንዳለፉት ሁሉ እርዳታውና እገዛው ሲመጣ እና ድል ሲቀዳጁም የእርሱን ትእዛዝ አክብረዋል።በመርሀቸው በሌሎች የሚታየው ደስታን መግለጫ ፌሽታ እና ሁካታ፣መስከርና ድንፋታ፣ጉራና ውስለታ ፈጽሞ አይነካካቸውም። የድል ንፋስ በነፈሰ ግዜ አላህን በማመስገን እራሳቸውን ከፍ ከማድረግና ከማድነቅ ይቆጠባሉ።እኛ፣እኔ ከሚሉት ለራስ ድርሻን ከመቁረስ ይታቀባሉ። መልእክተኛው ሰ.ዐ.ወ.መካን በድል ሲከፍቱ አንገታቸውን ደፍተው ለጌታቸው በመተናነስ አቀርቅረው እንደገቡ ያውቃሉ።በሌላ በኩል በሰዎች መሀል እነገሌ እና እኛ በሚል የውድድር ዓለም ተውጠው እራስን ከፍ ሌላን ዝቅ ማድረግ ላይ አይታዩም።እንደመርህ በትግል ወቅት ከአላህ ትእዛዝ ውጪ ድንበር ያለፉበት አጋጣሚዎች ይኖራሉና ለዛም ምህረትን ይጠይቃሉ።ስግደትን እንኳ ፈጽመን መደምደሚያው ምህረትን መጠየቅ የመሆኑ ምስጢርም እርሱ ነው።ከዚህም ባሻገር የተጀመረውን የመልካም ተስፋ ጮራ ሊያጨልም ከሚችል ተግባር መጠንቀቅ ያሻናል።ብዙዎቻችን በተከሰተው ለውጥ እየተደሰትን እንደሆነ ሁሉ የሚከፋቸውና የተለመደው የጭቆና ዘመን ናፋቂዎችም እንዳሉ ልንዘነጋ አይገባም።ድል የተቀዳጁ እና ነገሮች ሁሉ ቦታቸውን የያዙ መስሏቸው ከቅርቢቱ ዓለም ብልጭልጭ የምርኮ ሀብት ለመቐደስ ሲሯሯጡ እንደከሰሩት እንዳንሆን ያሰጋል።ሁሉም የቻለውን ሁሉ አዋጥቶ ለተገኘው ድል ያንበሳ ድርሻ ይገባኛል በሚሉ የእውቅና ገመድ ጉተታ ሜዳ በመዋል ድሉንም ሳናጣጥም በቀጣይነቱም ላይ ድርሻ ሳይኖረን እንዳያልፈን ልንፈራ ይገባል። ከውስጥም ሆነ ከውጪ ይህን የተስፋ ዳመና ለማክሰም ከሚራወጡ ሁሉ ልንታደገው ያሻል።በግልጽነት የሃገር ወዳድነት ስሜታችን ከራስ ወዳድነት ስሜት ያየለ መሆኑን በተግባር የምናሳይበት እርከን ላይ እንከሰት።ለሃገርም ሆነ ለሃገሬው ስጋት ለሰላሙ መደፍረስና መተክረት ሰበብ እንዳንሆን እንጠንቀቅ።ይቅርታን፣አንድነትን፣መደመርን እየሰበክን እና ሰባኪውን እያደነቅን በተግባራችን አፍራሽ ከሆኑ ገቢሮች እንወገድ። ከአሉባልታ፣ከጉራ፣ከአጉል ጥርጣሬ፣ከቅጥፈት እና ጥላቻ ዓለም ወጥተን እውነትን ፍቅርን እና መተባበርን እናንግስ። ጥላቶቻችንን እንኳ ቢሆን የማምለጫ መስኮቶቻቸውን በበቀል፣በምፀትና ጀብደኝነት አጥር በመዝጋት ለአፀፋዊ ክፋት አናነሳሳቸው።ይልቁንም የመካ ሰዎች በሙስሊሙ ላይ ያደረሱት ግፍና በደል በምህረትና በይቅርታ እንደታለፈው ሰዎች ከጥፋታቸው መመለሻን እና መታረሚያን መንገድ እናመቻችላቸው። በመጨረሻም የነገሮች ሁሉ ማማር በአላህ በፈጣሪያችን እጅ ነውና የእርሱን መንገድ ከምንም በላይ አጥብቀን በመያዝ ተስፋችንን ሁሉ በእርሱው ላይ በመጣል በዱዓ እንታገዝ።ከድል መርሆች በጥቂቱ የተሰማኝን ለማካፈል ሞክሪያለሁ አላህ ሰምተው መልካሙን ብቻ ከሚከተሉት ያድርገን አሚን።

ጀማል በሽር አሕመድ