Natnael Mekonnen
167K subscribers
30.3K photos
3.13K videos
28 files
6.55K links
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21
Download Telegram
በባህርዳር ከተማ ሰማዕታት ሀውልት ተብሎ በሚጠራው ግቢ ውስጥ የነበረው ሀውልት ተነሳ!

#Ethiopia : በአማራ ክልል በባህርዳር ከተማ ሰማዕታት ሀውልት ተብሎ በሚጠራው ግቢ ውስጥ የክልሉን ህዝብ የማይወክልና የማይገልፅ ነው ተብሎ የታመነበትን ሀውልት በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲወገድ ተወስኖ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ።

ፓርቲው በለውጡ ለህዝብ ከገባቸው ቃሎች መካከል የተሳሳቱ ታሪኮችንና ትርክቶችን የማረም ተግባር በከፍተኛ ቁርጠኝነት እያከናወነ መሆኑን የገለጸ ሲሆን አጠቃላይ ተቋሙን የሚመለከቱ የሪፎርም ስራወችንም በዝርዝር እንደሚያሳውቅ ገልጿል። (አብመድ)
Forwarded from Natnael Mekonnen
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔊🔊🔊🔊🔊 በተመጣጣኝ ዋጋ 🔊🔊🔊🔊🔊
FASICAL GUN MASSAGER
(ህመም እና ድካሞን በቤቶ የሚያክሙበት)

🔷 በማሳጅ ማሽኑ ሲታሹ የቫይብሬሽን ሲስተሙ የደም ዝውውርን በማስተካከል ከደም ግፊት እና ደም ብዛት በሽታ በመከላከል ጤናማ የደም ዝውውር እንዲኖረን ይረዳናል።
🔷 የትከሻ ፣ የጀርባ ፣ የወገብ እና የእግር ህመም ካለቦዎ ትክክለኛ ፈውስ የሚያገኙበት መሳርያ ።
🔷 በስራ ወይም በስፖርት የዛለ የደከመ ሰውነትን ለማነቃቃት በቀዳሚነት የሚመረጥ
🔷 Rechargeable መሆኑ መብራት ባይኖርም ያስጠቅማል 4 የተለያየ የማሳጅ ማድረግያ ያለው
🔷 ክፍለ ሃገር ከሆኑም በፖስታ ቤት እንልካለን።
✔️(ዋጋ-2500 ብር📞 0961276575📩 @theo41)
📌አድራሻ:ቦሌ(አትላስ ፪ሺ ሀበሻ ጎን) ግሬስ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
For Other Products➡️ @tedtechofficial
Forwarded from Natnael Mekonnen
🎁🎁 BUNION CORRECTOR 🎁🎁

አውራ ጣቶን በተለያየ ምክንያት እያመሞት

የአውራ ጣቶ አጥንት አቀማመጥ ትክክል ካልሆነ

ለጫማ ምቾት አየነሳዎ ከሆነ በአጭር ጊዜ የሚያስተካክል ዘመናዊ አማራጭ አምጥተንሎታል

አንዱን ለሁለቱም እግር መጠቀም መቻላችን ተመራጭ አድርጎታል

💵 600 ብር ብቻ 😮 🟢 ያሉበት በነፃ እናደርሳለን 🏍
ፈጥነው ያዘዘን 📲 0913849228 📩 @habworld

📍ቁጥር 1:- ከ ልደታ ቤ/ክ ፊት ለፊት ባለዉ ዳሸን ባንክ 200ሜትር ገባ ብለው በግራ በኩል የሚያገኙት , AIA BUSINESS CENTER GROUND FLOOR

ቁጥር 2: ቦሌ መድሀኒአለም አካባቢ ኦሮምያ ህንጻ ፊት ለፊት SELAM CITY MALL 3ኛ ፎቅ

JOIN @habmartofficial for more products
የአማራ ክልል መንግሥት በመተከል የሚፈጸመውን ጥቃት ለማስቆም ለፌዴራል መንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን አስታወቀ!

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ዘርን መሠረት ያደረገ ጭፍጨፋ፣ የፌዴራል መንግሥት ሥራ በዝቶበት ከሆነና ማስቆም ካልቻለ፣ የአማራ ክልል መንግሥት ጥቃቱን ለማስቆምና ሕግ ለማስከበር ዝግጁ መሆኑን ገልጾ፣ ይሁንታን ለማግኘት ሐሳብ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡‹‹በመተከል ዞን እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ የቤንሻንጉል ክልል ባለሥልጣናት ቀን ቀን ስብሰባ ላይ ከእኛ ጋር ሲላቀሱ ይውላሉ፡፡ ማታ ማታ ግን ግድያውን ማስቆም አልቻሉም፤›› በማለት የተናገሩት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ናቸው፡፡

በመተከል ዞን በአማራ ተወላጆች ላይ ዘር እየተመረጠ በየትኛውም ዓለም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ዘግናኝና ጭካኔ በተሞላበት ድርጊት ሰዎች ሲገደሉ፣ የፌዴራል መንግሥት ግዴታና ኃላፊነቱን ካልተወጣ የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይል ዝግጁ እንደሆነ ኮሚሽነር አበረ ለሪፖርተር ገልጸዋል።ኮሚሽነሩ የችግሩን ቀጣይነት አስመልክተው ሲያብራሩ፣ ከአካባቢው አመራሮች ጋር በተደጋጋሚ ውይይት የተደረገ ቢሆንም፣ ‹‹የችግሩ መንስዔዎች ቀን ቀን አብረውን ስብሰባ ላይ ሲላቀሱ ውለው፣ ማታ ግድያውን ማስቆም የተሳናቸው የሕወሓት ርዝራዦች ናቸው፤›› ብለዋል።‹‹አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች የሚገደሉት አማራ ተብለው ስለሆነ ምናልባት የፌዴራል መንግሥት ሥራ በዝቶበት ከሆነ፣ ለእኛ ይስጠን ብሎ ክልሉ ለፌዴራል መንግሥት ሐሳብ አቅርቧል፤›› ሲሉ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

አንድ ክልል የራሱን የፀጥታ ችግር ማስከበር ካልቻለ የፌዴራል መንግሥት ኃላፊነትና ግዴታ አለበት ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ‹‹አቅጣጫ ያስቀምጥልን፣ ሕዝባችን እንታደግ፤›› ሲሉም የፌዴራሉን መንግሥት ጠይቀዋል።‹‹እንደ ክልል ልናደርግ የምንችለው ወደ ፌዴራል መንግሥት አቤት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን አሁንም በአማራ ክልል በኩል የሕዝብን ደኅንነት ለማስጠበቅ ዝግጁ ነን፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡የፌዴራል መንግሥት ከፈቀደ ‹‹የአማራ ክልል የአቅም ውስንነት የለበትም›› ያሉት ኮሚሽነር አበረ፣ በሕወሓት ኃይሎች ላይ እንደተደረገው ዘመቻ ከመከላከያ ጋር በመሆን ሥራውን ለማከናወን ፍላጎት እንዳለ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማንም ይሁን ማን፣ በየትኛውም ቦታ እኩል የመኖር መብት አለው ብለዋል። ‹‹ነገር ግን በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ ያሉ የወያኔ ተላላኪዎች ሰው ሲገደል ከመከላከል ይልቅ፣ ለምን ተገደለ ብላችሁ ጠየቃችሁን ብለው ያኮርፋሉ፡፡ እንዲህ ዓይነት አካላት የተሰባሰቡበት የአመራር ቡድን በመሆኑ የሰውን ሕይወት ለመታደግ ሲሠሩ አይታዩም፤›› ብለዋል።የአማራና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በጉዳዩ ላይ እየመከሩ እንደሆነ የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ ‹‹ለችግሩ መፍትሔ ያመጣሉ ብለን እናስባለን፡፡ ነገር ግን እንደ ክልል የፀጥታ ኃይል ትዕዛዝ እየተጠባበቅን እንገኛለን፤›› ብለዋል።

Via Reporter
Forwarded from Natnael Mekonnen
ምርጥ ምርጡን ለደንበኞቹ በማቅረብ የሚታወቀው Henok Mobile ደረጃቸውን የጠበቁ Original ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርቦሎታል። 👌 ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር !👌 📞0913748289 📩@lookhenok 📍አድራሻ :- ቦሌ መድሀኒዓለም, ኤድና ሞል Join us on Telegram ➥@highmrk
Forwarded from Natnael Mekonnen
የልጆች ታብሌት ሀዋሳ እና ባህር ዳር ገባ
16gb በ3500 ብር ብቻ
32gb በ4500 ብር ብቻ
+251911522626 / +251953120011
ላይ ይደውሉ ቤቶ ድረስ እናመጣለን
👍ለነገ ፍሬዎች ዘመን የሚሻገር ስጦታ‼️
🚴‍♂️ ይዘዙን ያሉበት ድረስ እናመጣለን‼️
👉ትምህርታዊ አፕልኬሽኖች ያሉበት
👉 ቢወድቅ የማይሰበር ለልጆች ታስቦ የተሰራ
👉 የፊትና የኋላ ካሜራ፤
👉 አስተማማኝ ባትሪ፤
👉 በ4 የቀለም አማራጭ ለልጆች አመቺ
ለልጁ የተሻለውን ለሚመርጥ ወላጅ የቀረበ‼️
Inbox @natyendex
Join us @natcomputers1
በልደታ ክ/ከተማ ስልጤ መስኪድ ጀርባ በፈነዳ ቦንብ የሰው ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ስልጤ መስኪድ ጀርባ በፈነዳ ቦንብ የሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ዛሬ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ተኩል በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ስልጤ መስኪድ ጀርባ ለልማት በፈረሰ ክፍት ቦታ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ተጥሎ በተገኘ የእጅ ቦንብ ጎዳና ተዳዳሪ የሆኑ የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በአምስት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ኮሚሽኑ ገልጿል።

በኮሚሽኑ የልዩ ልዩና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር አለማየሁ አያልቄ ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ ያለው የምርመራ ሂደት እየተጣራ መሆኑን ገልፀው፤ የምርመራ ውጤቱ እንደተጠናቀቀ ለህብረተሰቡ ግልጽ ይደረጋል ነው ያሉት።

በተለያዩ ቦታዎች እንደ አልባሌ በሚጣሉ ቦንቦችና ፈንጂዎች ንፁሀን ሰለባ መሆናቸውን አስታውሰው ያሰታወሱት ዳይሬክተሩ፤ ህብረተሰቡ ምንነታቸው ያልታወቁ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ከመነካካት በመቆጠብ ለሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጥቆማ ማድረግ እንደሚገባ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል ሲል ኢዜአ ዘግቧል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኬንያ፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲ ፕሬዝዳንቶች ጋር ተወያዩ፡፡

ለ38ኛው የኢጋድ ልዩ የመሪዎች ጉባዔ ጅቡቲ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣናችን (ምስራቅ አፍሪካ) ያለው መረጋጋት በእድገት እና ልማት ትብብር ላይ የተመሰረተ ነው ብለዋል፡፡



እንደ መሪ በጠረጴዛ ዙሪያ ተሰባስበው በቀጣናው አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት በመቻላቸው የተሰማቸውን ደስታም ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር ዐቢይ ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ርብቃ ንያንዴንግ ደ ማቢዮርም ጋር ሁለትዮሽንና የደቡብ ሱዳን ሰላምን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡



በባህር የድንበር ይገባኛል ጉዳዮች ላይ ወትሮውኑ ይወዛገቡ የነበሩት ኬንያ እና ሶማሊያ ከሰሞኑ ወደ ሻከረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መግባታቸው ይታወቃል፡፡

የኬንያን አምባሳደር እስከማባረር የደረሰችው ሶማሊያ የናይሮቢ ኤምባሲዋን እስከመዝጋት ደርሳም ተመልክተናል፡፡

በኢጋድ አባል ሃገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ሊያጠናክሩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ያስታወቁት ዶ/ር ዐቢይ ይህን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከመሪዎቹ ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀደም ሲል ከሱዳንና ሶማሊያ መሪዎች ጋር ያደረጉትን ምክክር በተመለከተ አል ዐይን አማርኛ መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡
ሰበር ዜና ‼️

#Ethiopia : በውጭ ሀገራት እየኖሩ ከጁንታው ጋር ተባባሪ በመሆናቸው የእስር ማዘዣ የወጣባቸውን ተጠርጣሪዎች ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) ጋር በመነጋገር በቁጥጥር ስር ለማዋል እንደሚሰራ የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

በፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል መላኩ ፋንታ ዛሬ በመቐለ ከተማ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

ምክትል ኮሚሽነር በዚህን ወቅት ጁንታው ከተሞችን ለቆ ከመሸሹ በፊት በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የነበሩ ወንጀለኞችን መሳሪያ አስታጥቆ በመልቀቅ በከተሞች አካባቢ ዝርፊያ እንዲፈጽሙ ማድረጉን ነው የገለጹት።

ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት በህግ የሚፈለጉ ወንጀለኞቹን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አስታውቀዋል።

በእስካሁኑ ሂደት በቁጥጥር ስር የዋሉና በቅርበት ክትትል እየተደረገባቸው ያሉ ተፈላጊዎች መኖራቸውን ጠቁመው፤ አስፈላጊው ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ መረጃው ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የእስር ማዘዣ የወጣባቸውን ሁሉንም የጁንታው አባላትን ለመያዝ አሁንም ጥብቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

በውጭ ሀገራት እየኖሩ ከጁንታው ጋር የወንጀል ተባባሪ በመሆናቸው የእስር ማዘዣ የወጣባቸውን ተጠርጣሪዎች ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) ጋር በመነጋገር በቁጥጥር ስር ለማዋል እንደሚሰራም መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የፌደራል ፖሊስ በክልሉ ትልልቅ ከተሞች ተልዕኮ ወስዶ ወደ ስራ መግባቱንም ነው ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራሉ ያስታወቁት።

“በክልሉ መደበኛ የፖሊስ ሥራ ለማስጀመርም የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ መኮንኖች መቀሌ ገብተዋል” ብለዋል።

መኮንኖቹ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ከዚህ በፊት መመሪያን ብቻ አክብረው ሲሰሩ የነበሩ የክልሉ ፖሊስ አባላትን በህዝብ በማስተቸት መደበኛውን የፖሊስ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያደርጉ መሆኑንም አመልክተዋል።

በክልሉ የሚኖሩ በርካታ ዜጎች የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረበውን ጥሪ ተቀብለው የጦር መሳሪያዎችን እየመለሱ መሆኑንም ተናግረዋል።

በቀጣይም ፍተሻዎችን በማካሄድ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እንደሚሰራም ጨምረው ገልጸዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ የፌደራል ፖሊስ እያከናወነ ያለውን ተግባር በመደገፍ የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለህብረተሰቡ ምስጋና አቅርበዋል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
breaking news

የአፍሪካ ህብረት ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ለወሰደችው የህግ ማስከበር ዘመቻ እውቅና ሰጠ!

#Ethiopia : የህብረቱ ሊቀመንበር ሙሳፋቂ መሃመድ በኢጋድ ድንገተኛ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የሀገርን አንድነትና ሰላምን ለማስጠበቅ እንዲሁም ህገ መንግስትን ለማስከበር ማንኛውም ሀገር ቢሆን የሚወስደው እርምጃ እንደሆነ ተናግረዋል። ነገር ግን እርምጃውን ተከትሎ የሰብዓዊ ቀውስ መድረሱ እንደማይቀር ያልሸሸጉት ሊቀመንበሩ የኢጋድ አባል ሀገራት ትብብርና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢቀመማ በትግራይ ክልል ውስጥ በግጭት ለተጎዱ ወገኖች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉን አሳውቋል !

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በትግራይ ክልል ተከስቶ በነበረው ግጭት ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው 2000 ወገኖች ከብር 3 ሚሊዮን በላይ ወጪ በማድረግ ልዩ ልዩ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ማኅበሩ በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ካደረገው ድጋፍ መካከል ብርድ ልብስ፣ ምንጣፍ የመመገቢያ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና መሠረታዊ መድኃኒት ድጋፍ ይገኝበታል፡፡

ኢቀመማ ግጭቱ ከተከሰተ በኋላ ከዓለም ዓቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አስቸኳይ ሠብዓዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ከዚህም መካከል የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና እርዳታ ፣ የአምቡላንስ አገልግሎት፣ የተጠፋፉ ቤተሰቦችን የማገናኘት፣ የተለያዩ የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ማኅበሩ በመቀለ ከተማ ተፈጥሮ የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውሀ እጥረትን ተከትሎ ለከተማዋ ነዋሪዎች መጠጥ ውሀ ድጋፍ እንደተደረገ ይታወቃል፡፡

(የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር
🎁 POSTURE CORRECTOR🎁

👉ከትከሻዎ እየጎበጡ ተቸግረዋል? እንግዲያውስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከትከሻዎ ቀና ብለው እንዲሄዱ የሚረዳ

ከጀርባ ጋር ተያያዥ ህመም ካለቦት ትክክለኛ ምርጫ ነው
ውጤታማ የሆነ፣ ለእንቅስቃሴ የሚመች፣ ለማንኛውም የእድሜ ክልል የሚሆን
በስራ ወቅት ከማንኛውም ልብስ ስር ለማድረግ የሚመች

💵900 ብር 📞0913849228 📩 @habworld

ADDRESS :-
📍 ቁጥር 1:- ከ ልደታ ቤ/ክ ፊት ለፊት ባለዉ ዳሸን ባንክ 200ሜትር ገባ ብለው በግራ በኩል የሚያገኙት , AIA BUSINESS CENTER GROUND FLOOR

ቁጥር 2: ቦሌ መድሀኒአለም አካባቢ ኦሮምያ ህንጻ ፊት ለፊት SELAM CITY MALL 3ኛ ፎቅ

JOIN @habmartofficial for more products