STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#ማስታወቂያ

👩‍🎓🧑‍🎓 *Competent research hub * 👩‍💻🧑‍💻
💻በጥናትና ምርምር ዙርያ የማማከር አገልግሎት እንሰጣለን።

ማንኛውንም የትምህርት እና የሪሰርች መፅሃፍት
ለሪሰርች ፕሮፖዛል - Proposal
ለመጠይቅ - Questionnaire
ለመረጃ ትንተና - Data Analysis
ለየውሂብ አቀራረብ እና ትርጓሜ - Data Interpretation and presentation

O U R S E R V I C E S (አገልግሎት)
--------------------
      + Assignment / አሳይመንት
      + Research / ሪሰርች
      + Proposal / ፕሮፖዛል
      + Term Paper /  ተረም ፔፐር
      + Case study/ ኬዝ ስተዲ
      + Article Review
      + Mini research
👇👇👇👇👇👇👇
We are accessible 24/7 on call, text and telegram through* 
Contact as via
@ResearcherETH
@ResearcherETH
@ResearcherETH
ሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አዳዲስ የቅድመ እና የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞችን ላልተወሰነ ጊዜ እንዳይከፍቱ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ዛሬ ነሐሴ 09/2015 ዓ.ም ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች በጻፉት ሰርኩላር እንዳሉት በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎችን በትኩረትና በተልዕኮ የመለየት ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ፤ በዚህም ተቋማቱ የትምህርት ፕሮግራሞቻቸውን የመከለስ ተግባር እንዲፈፅሙ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በመሆኑም የዩኒቨርሲቲዎቹ የትምህርት ፕሮግራሞች ተገምግመው ከተለዩበት ተልዕኮና ትኩረት ጋር መጣጣማቸው እስኪረጋገጥ ድረስ አዳዲስ ፕሮግራሞች መክፈት እንደማይቻል ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

የታቀዱ አዳዲስ ፕሮግራሞች ለመክፈት የሚደረጉ ጥናቶች ባሉበት እንዲቆዩ እንዲሁም በቦርድ የፀደቁና በትምህርት ሚኒስቴር የተመዘገቡ አዳዲስ ፕሮግራሞች ተማሪ መቀበል እንዳይጀምሩ ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

(ሚኒስትሩ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች የጻፉት ሰርኩላር ከላይ ተያይዟል፡፡)

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
«400 የEBC ሰራተኞች የትምህርት ማስረጃቸው ሀሰተኛ መሆኑ ተረጋግጧል ይህን ስናጋልጥ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው" አሉ!

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) በተቋሙ ሰራተኞች ላይ ባደረገው የትምህርት ማስረጃ ሰነድ ማረጋገጥ የ400 ሰራተኞች ሰነድ ሀስተኛ በመሆኑ የትምህርትና ስልጠና አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ቢያሳውቅም አመራሮቹ በጥቅም በመተሳሰር የህግ ተጠያቂነት እንዳይኖር መረጃ ስለመስወራቸው ሁለት ግለሰቦች ለፌዴራል የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጥቆማ ማቅረባቸውን ፋስት መረጃ የደረሰው የሰነድ መረጃ ያመለክታል።

በዚህ ምክንያት የድርጅቱ አመራሮች በጥቆማ አቅራቢዎች ላይ ከስራ ለማሰናበት ዛቻ እና ማስፈራራት እየደረሰባቸው መሆኑን ጠቅስው የህግ ከለላ እንዲሰጣቸው በቀን 02/12/2015 ዓ.ም በፌዴራል የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በኩል የህግ ከለላ እንዲሰጣቸው ለፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ አቃቢ ህግን ጠይቀዋል።

© ፋስት መረጃ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
በሀገሪቱ ትክክለኛ ጁስ የሚያመርት አንድ ተቋም ብቻ መኖሩን እወቁልኝ ሲል የኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በሀገሪቱ እስከ 30 የሚሆኑ “የፍሩት ድሪንክ” ወይም “ፍሩት መጠጦችን” የሚሸጡ ተቋማት መኖራቸውን ባለስልጣኑ ገልፃል፡፡

በሀገር ደረጃ ትክክለኛ ጁስ የሚያመርት አንድ ድርጅት ብቻ መኖሩን ገልፀዋል፡፡

በሀገሪቱ ከዚህ ቀደም ጁስ እየተባሉ የሚሸጡ ነገር ግን ጁስ መያዝ ያለበትን መስፈርት ያማያሟሉት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የባለስልጣኑ የምግብ ተቋማት ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ በትረ ጌታሁን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ደረጃ ከፍራፍሬ ጋር የተያያዙ ምርቶች በሶስት የሚከፈሉ እንደሆነ የሚገልፁት ዳይሬክተሩ፣ አንደኛ ጁስ ሲሆን አንድ ጁስ ጁስ ለመባል ቢያንስ 30 በመቶ የተፈጥሮ ፍርራፍሬ ሊኖረው እንደሚገባ ያነሳሉ፡፡

በተቃራኒው ከ10 እስከ 30 በመቶ የፍራፍሬ ይዘት ከሌለው ግን “ፍሩት ድሪንክ” ወይም “ፍሩት መጠጥ” እንጂ “ጁስ” እንደማይባሉ ተናግረዋል፡፡

በህብረተሰቡ ዘንድ ብዥታ መኖሩን የሚናገሩት ዳይሬክተሩ፣ ከዚህ በኃላ ፍሩት ድሪንኮችን ጁስ እያለ የሚሸጥ ወይም የሚያስተዋውቅ ማንኛውም ተቋም ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል፡፡

©ሀገሬ ቲቪ

የተጣሩ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
To all Remedial Students ‼️

Unituy university students union

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
AI ( አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) + ፎቶ ሾፕ
ጉድ አፈላ😁

@NATIONALEXAMSRESULT
ሰላም እንዴት ናችሁ ይህን መልዕክት የምናስተላልፍላችሁ ከጂግጂጋ ዩንቨርስቲዬ የpetroleum Engineering ተማሪዎች ነው።በበፊቱ የመቀሌ ዩንቨርስቲይ ተማሪ ነን ነገር ግን በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ወደ ጂግጂጋ ዩንቨርስቲይ ተቀይረን ትምህርታችንን ጨርሰናል ።

ነገር ግን ቀደም ሲል ወደ ጥር አካባቢ ለጂግጂጋ ዩንቨርስቲይ ማኔጅመንት exit exam ተፈታኞች ከሆንን እንድንዘጋጅ ውሳኔ አሳውቁን ብለን ጠይቀን እናንተ exit አትፈተኑም ተብለን ጊዜያችንን ካለ ጥናት አባከንን ነገር ግን exit 20 ቀን ሲቀረው እንደገና ሰብስበውን ፈተናው አልቀረም ትፈተናላችሁ ብለው ነገሩን እኛም ጊዜያችንን እንዳንጠቀም የለም ብላችሁ አዘናግታችሁናል ከዚህም በተጨማሪ blue prit አልተሰጠንም ስለዚህ በ20ቀን ውስጥ አንደርስም የሚል ጥያቄ አቀርበን ነበር። ከዚያም እነሱ ተወያይተው እናንተ ሌላው ተማሪ ወደ ቤቱ ሲሂድ እናንተ እንዳትሄዱ እግቢ ቆዩ 1ወር ለማጥናት የሚሆን ጊዜ እንሰጣችኋለን ብለውን እስካሁን እግቢ ነን ።

ነገር ግን አሁንም ይህ ችግራችን ሊፈታልን አልቻለም እኛ ፈተናው ዛሬ ነገ ይመጣል እያልን በጉጉት ስንጠብቅ ከጂግጂጋ ዩንቨርስቲ የተሰጠን መልስ መቀሌ ሄዳችሁ ተፈተኑ እዚያ ነው የምትፈተኑት አሉን የመፈተኒያውንም ቀን አናውቅም አሉን እኛም ይሄው በጭንቀት ውስጥ ነን ለምን እንደዚህ ይደረግብናል ፈተናው online እንደመሆኑ መጠን ለምን በዚሁ ባለንበት ፈተናውን ተፈትነን አንወጣም የሚል ጥያቄ አለን።ይህን ችግራችንን ወደ ትምህርት ሚኒስተርና ወደ ሚመለከተዉ አካል ሁሉ አድርሱልን ።🙏

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
⬇️⬇️⬇️ የይድረሱልን ጥሪ ⬇️⬇️⬇️

https://t.me/nationalexamsresult/15657
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
ሴት ልጅ እንኳን ከቤት ውጪ በቤቷ ውስጥም መቀመጥ የማትችልበት ሀገር!

(https://t.me/nationalexamsresult/15656?single )

20 በሚሆኑ ወንዶች የተጠለፈችው የ17 አመቷ ወጣት አምሮት ገብሩ

አምሮት ገብሩ ወይም በቤት ስሟ  ስመኝ  ትባላለች የ17 ዓመት ልጅ ስትሆን የ11ኛ ክፍል ተማሪም ናት። በነሐሴ 2 ሃያ በሚደርሱ ወጣቶች በጉራጌ ዞን ደቡብ ሶዶ ወረዳ  ልዩ ስሙ  ዘሙቴ ከሚባል አካባቢ  ተጠልፋና ተደፍራ ተወስዳለች  እስካሁን ጠላፊዎቹም ልጅቷም የት እንዳሉ አልታወቀም።

ዝርዝሩ እንደሚከተለው ነው

አስቀድሞ ግንቦት 24/2015 ዓ.ም ታናሽ እህቷ ሰላም ገብሩ በድንገተኛ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። ግንቦት 25/ 2015 ዓ.ም አስክሬኗ ከሚኒሊክ ሆስፒታል ተቀብለን ጉራጌ ዞን ደቡብ ሶዶ ወረዳ ማህበራዊ ሳያት ቀበሌ ማህበር ልዩ ስሙ ዘመቴ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ተቀበረች። በዚህም ምክንያት አምሮት /ስመኝ ከለቅሶ ጊዜ ጀምሮ አንዴ እዛ አንዴ እዚህ እየተመላለሰች ትጠይቃቸዋለች። እናም ከምትማርበት አልፋ ኮልፌ ቀራንዮ ትምህርት ቤት ትምህርት ስላለቀ እረፍቱን እዛው ቤተሰብ እያገዝኩ ባሳልፍ ይሻላል በሚል ለሰላም 40 ትገባለች።

በገባች በ3 ሳምንቷ ነሐሴ 1 ለገሰ ጥላሁን የሚባል እዛው አካባቢ የሚኖር ለማፅናናት በሚል እነርሱ ቤት ይመጣል። ከዛ በፊት ታላቅ ወንድሟ በመታመሙ ለብዙ ጊዜ በህክምና ቆይቶ መፍትሔ ስላልተገኘ ደጋ ኑረና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን እንደሚከታተል ስለሚያውቅ እንዴት እንደሆነ በመጠየቅ አባቱም እዛው እርሱን እያፀበለ መሆኑን ያረጋግጥና እራቱን በልቶ ቡናውን ጠጥቶ ወደቤት ይሄዳል።

በማግስቱ ነሐሴ 2/ 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 1:30 አስቀድሞ ነገሮች ስላረጋገጠ ቤት ይመጣል አምሮትም እንደቤተሰብ ስለምታየው ቡና ልታፈላለት ስትነሳ ያለው በለጠ ዋናው ጠላፊ በር ያንኳኳና እንዲገባ ይጋብዘዋል። ያለው ቤት ገባ አምሮትን ሰላም በይኝ ይላል ። ሰላም አለቺውና ልትቀመጥ ስትል ይህ ብቻ በቂ አይደለም ብሎ ከለገሰ ጋር ገፍትረው ወደውጭ ይጥሏታል በዚ ጊዜ  ወንድሟ ምን ማድረጋችሁ ነው ሲላቸው እርሱን እግሩና እጁን በከባዱ ይደበድቡታል። ውጭ ላይ የነበሩ ግብረአበሮቹ ጋር በመሆን አምሮትን ሊወስዷት ይሞክራሉ ልጅቷን አልሞት ባይ ተጋዳይ እየታገለች ከላይ የለበሰቸው ቲሸርት ትታላቸው ትሮጣለች።

በዚ ጊዜ  ሌሎች እንሰት ውስጥ ተደብቀው የነበሩ ግብረ አበሮች  ስለነበሩ ይየዟት እና ሊያስደፍሯት ቀሚሷን ያወልቃሉ። በመቀጠልም ለዋናው ጠላፊ  ያለው በለጠ  እንዲደፍራት ይጋብዙታል። ለብቻው ጊዜ ለመስጠት በሚመስል መልኩ ዞር ዞር ይላሉ። ብቻውን መሆኑን ስታረጋግጥ ያለ የሌለ ሀይሏን ተጠቅማ ታመልጣቸዋለች። እግሯን ወደመራት ስትሮጥ ጎረቤት የሚገኝ አቶ በረክ ጡረሞ የሚባል ቤት ትገባለች። በዚ ጊዜ የአቶ በረክ ባለቤት የሆነቺው በየነች በሆነው ነገር እያዘነች  የራሷን ቀሚስ አልብሳ አጥባ ትደብቃታለች።

እነርሱም አስከ 4:00 እየፈለጉ፣  ሌሎች ረድተው የመጡ ጎረቤቶች እየደበደቡ ከቆዩ በኋላ ማን እንደጠቆማቸው ሳይታወቅ በር ከፍተው ይዘዋት ሄዱ። ከዛ ቀን ጀምሮ የት እንዳሉ አይታወቅም። ፖሊስ መረጃ በማሰባሰብ ከ20ዎቹ 8ቱ ስለታወቁ በተገኙበት ይያዙ የሚል የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል።

ቤተሰብም ግማሹ እነርሱን በማፈላለግ እንዲሁም የተጎዱትን በማሳከም ላይ ይገኛል።

እናት መጀመሪያም የልጇን መታመም እና የታናሽ ልጇ ያልተሰብ ሞት የእግር አሳት ሆኖባት ነበር ይሄኛው ሲጨምር በከፈተኛ ጉዳት እና ድብርት ውስጥ ትገኛለች። ቤተሰቡም በተደጋጋሚ ሀዘን ስለደረሰበት ይሄኛው ሲጨመር በከፍተኛ ጉዳት ላይ ይገኛል።

እባካችሁ ከታች ስማቸውን የተዘረዘሩት ካያችሁ ስለሴት ልጅ ጥቃት ብላችሁ ያሉበትን ካወቃችሁ እንድትጠቁሙን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ሌሎቻችሁም share እያደረጋችሁ ለሁሉም እንዲደርስ እንድታደርጉልን በትህትና እንጠይቃለን። በተለይ መርካቶ አካባቢ የምትኖሩ የጉራጌ ተወላጆች መረጃው ሊደረሳችሁ ስለሚችል የበኩላችሁን እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

ተፈላጊዎች

👉 1,ያለው በለጠ ጠላፊ
👉2,ለገሰ ጥላሁን ዋና አስተባበሪ
👉3,ዮሴፍ ጥላሁን
👉4,አዲሱ ጥላሁን
👉5,ማሙሽ ተስፋዬ
👉6,ቻለው አዳነ
👉7,ማረኝ ፀጋዬ
👉8,ዳንኤል ሰለሞን

ሌሎቹ ከቀጫ፣ አሞጎፍ፣ የከቶኒ፣ አጨበር  ከሚባሉ ቦታወች  የመጡ ሲሆን ማንነታቸው ለጊዜው አልታወቀም።

ስልክ 0938415351
         0915554039
         0703326230
         0911663067
         0926378205

ስለምታደርጉልን ትብብር ከወዲሁ እናመሰግናለን🙏🙏🙏

@NATIONALEXAMSRESULT
ነጻ የትምህርት ዕድል!

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ት/ቤት በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ በሚገኙ የመንግሥት እና የግል ት/ቤቶች በመማር ላይ ከሚገኙ በትምህርታቸው፣ በመልካም ምግባራቸው እና በልዩ ተሰጥኦዋቸው የተመሰከረላቸውን ተማሪዎች አወዳድሮ ነጻ የትምህርት ዕድል ለመሥጠት መዘጋጀቱን ገልጾልናል።

ተወዳዳሪ ተማሪዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልተው መምጣት ይጠበቅባቸዋል፦

1. ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ የሆነ፣

2. የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ት/ቤቱ በሚከተለው ሥርዓተ ትምህርት በኬምብሪጅ ኢንተርናሽናል አይ.ጂ.ሲኤስ.ሲ እና በኬምብሪጅ ኢንተርናሽናል አድቫንስድ (Cambridge International IGCSC and Cambridge International Advanced) ለመማር እና በዚሁ ሥርዓተ ትምህርት ለመፈተን ፈቃደኛ የሆኑ፣

3. የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት መግለጫ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፣

4. በ2015 ዓ.ም መጨረሻ የክፍል ውጤታቸው ከ90% በላይ የሆነ እንዲሁም የ8 ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አማካይ ውጤታቸው ከ95% በላይ የሆነ፣

5. ስለመልካም ምግባራቸው እና ልዩ ተሰጥኦዋቸው ከሚማሩበት ት/ቤት የጽሑፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

6. ት/ቤቱ የሚሰጠውን የመግቢያና ቃለመጠይቅ ፈተናዎችን የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ማለፍ የሚችሉ፣

7. የልደት የምሥክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

8. የወላጅ/አሳዳጊ ሙሉ ፈቃድ ማግኘት የሚችሉ፣

በመሆኑም መስፈርቱን የሚያሟሉ እና ፍላጎቱ ያላቸው ተማሪዎች እስከ ነሐሴ 19/2015 ዓ.ም ሰሚት ፍርድ ቤት አካባቢ በሚገኘው ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።

#Tikvah

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Budapest 🇪🇹 እንኳን ደስ አለን 🇪🇹
ታሪክ ተደገመ

በ2023ቱ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ10,000 ሜትር ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለሀገራችን የመጀመሪያ ሜዳልያ ተከታትለው በመግባት ማስመዝገብ ችለዋል።

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ውድድሩን በበላይነት ስታጠናቅቅ ለተሰንበት ግደይ ሁለተኛ እጅጋየሁ ታዬ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል።

🥇ጉዳፍ ፀጋዬ 🇪🇹🇪🇹
🥈ለተሰንበት ግደይ 🇪🇹🇪🇹
🥉እጅጋየሁ ታዬ 🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹 እንኳን ደስ አለን 🇪🇹🇪🇹

@NATIONALEXAMSRESULT
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያወጣቸውን ስራዎች ONLINE እንድንመዘግባችሁ የምትፈልጉ ዶክመንታችሁን ማለትም የ8,10,12 ፣ መታወቂያ ፊትና ጀርባ አንድ ፓስፖርት ሳይዝ ፎቶ ለልደት ሰርተፍኬት ካላችሁ እና ተጨማሪ በሚጠይቁት ዘርፍ ያላችሁን ዶክመንት አያይዛችሁ @JobsET19
ላይ መላክ ትችላላችሁ የምትልኩት ስካን የተደረገ ፎቶ አንስታቹ ከሆነ ደግሞ ጥርት ያለ መሆን አለበት
ማሳሰቢያ ምዝገባው መጠነኛ ክፍያ አለው

@JobsET19
@JobsET19
@JobsET19
የገላን የወንዶች 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት የ7ኛ ክፍል ቅበላ ማስታወቂያ!

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላወጣው ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ በጋምቤላ ክልል ምዝገባ በሁለት ስፍራዎች እንደሚከናወን የክልሉ መንግሥት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አሳውቋል፡፡

በዚህም ምዝገባው ከዛሬ ነሐሴ 15/2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አርብ ነሐሴ 19/2015 ዓ.ም በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ እና በክልሉ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ይከናወናል፡፡

✓ ነሐሴ 15/2015 ዓ.ም በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣
✓ ነሐሴ 16/2015 ዓ.ም በክልሉ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት፣
✓ ነሐሴ 17/2015 ዓ.ም በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣
✓ ነሐሴ 18/2019 ዓ.ም በክልሉ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት፣
✓ ነሐሴ 19/2015 ዓ/ም ግማሽ ቀን በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣
✓ ነሐሴ 19/2015 ዓ.ም ግማሽ ቀን በክልሉ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት፡፡

(የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያወጣው ሙሉ የምዝገባ መርሐግብር ከላይ ተያይዟ፡፡)

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያወጣቸውን ስራዎች ONLINE እንድንመዘግባችሁ የምትፈልጉ ዶክመንታችሁን ማለትም የ8,10,12 ፣ መታወቂያ ፊትና ጀርባ አንድ ፓስፖርት ሳይዝ ፎቶ ለልደት ሰርተፍኬት ካላችሁ እና ተጨማሪ በሚጠይቁት ዘርፍ ያላችሁን ዶክመንት አያይዛችሁ @JobsET19
ላይ መላክ ትችላላችሁ የምትልኩት ስካን የተደረገ ፎቶ አንስታቹ ከሆነ ደግሞ ጥርት ያለ መሆን አለበት
ማሳሰቢያ ምዝገባው መጠነኛ ክፍያ አለው

@JobsET19
@JobsET19
@JobsET19