STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#MoE

" የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቅድሚያ የመዘገቧቸውን ተማሪዎች ለትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ማሳወቅ ይኖርባቸዋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መስጠት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁን አሀዱ ዘግቧል።

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ95 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች ከ50 በመቶ በታች ውጤት ማምጣታቸው ይታወቃል፡፡

ከሀምሳ በመቶ በታች ካመጡት ተማሪዎች መካከል በልዩ ሁኔታ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለአንድ አመት የአቅም ማሻሻያ ትምህርት ሪሜዲያል እንዲወስዱ የተወሰነ ሲሆን ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተጨማሪ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መውሰድ እንደሚችሉ የትምህርት ሚንስቴር የህዝብ ግንኙት ሃላፊ ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ገልፀዋል፡፡

ትምህርት ሚንስቴር ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ያደረገ ሲሆን ይህን የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መስጠት የሚፈልጉ የግል ከፍትኛ የትምህርት ተቋማትም በዚሁ መሰረት ተማሪዎች ተቀብለው ማስተማር የሚችሉ ሲሆን በቅድሚያ ግን የመዘገቧቸውን ተማሪዎች ለትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ማሳወቅ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የልህቀት ማእከል ተብለው በተለዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በኩል የተዘጋጀ የአቅም ማሻሻያ ሪሜዲያል ትምህርት ማስተማሪያ ተዘጋጅቶ ለሁሉም የመንግስት እና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መላኩን ጠቁመዋል፡፡

አያይዘውም የማስተማሪያ ሰነዱ ለተማሪዎቹ ከ 9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ትምህርት አጠቃሎ የያዘ ሲሆን ሁሉም የትምህርት ተቋማት ማስተማር የሚችሉት ይሄንን በመጠቀም መሆን እንዳለበት ለአሀዱ በሰጡት ቃል አመላክተዋል፡፡

Credit : #Ahadu

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot