STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#ETA

የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እስከ የካቲት 2014 ዓ.ም ድረስ ያጠናቀራቸውን የ350 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና የትምህርት መስኮቻቸውን የእውቅና ፈቃድ የሚገልጽ የተሟላ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡

ይፋ የተደረገው መረጃ እስከ የካቲት ወር 2014 ዓ.ም ድረስ ያለውን የእውቅና ፈቃድ መሆኑን ያሳወቀው ባለሥልኑ በሂደት ላይ ያሉ የእውቅና ፈቃድ እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት ጥያቄዎች ውሳኔ ሲያገኙ፣ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የእውቅና ፈቃድ ሲሰረዝ እና በሌሎች ምክንያቶች ውሳኔዎች ምክንያት ለውጦች በሚኖሩበት ወቅት የመረጃ ለውጥ ሊኖር እንደሚችል ገልጿል፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ ቀጣሪና የሙያ ፈቃድ የሚሰጡ ድርጅቶች፣ የሚዲያና ማስታወቂያ ተቋማት፣ እንዲሁም መላው ህብረተሰብ የተቋማቱን ወቅታዊ መረጃ በመከታተል ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባለሥልጣኑ በጥብቅ አሳስቧል።ተቋማትም ይፋ ከተደረገው የእውቅና ፈቃድ መረጃ ውጪ ተማሪ ተቀብለው ቢያስተምሩ ህጋዊና አስተዳደራዊ #እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ባለስልጣኑ አሳውቋል፡፡

ተጨማሪ ማሳሰቢያ(ለተቋማት)፡- ይፋ በተደረገው መረጃ የማስተካከያ ጥቆማ የሚኖራቸው ተቋማት በህጋዊ ተወካዮቻቸው በኩል ለባለስልጣኑ ማሳወቅ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#እርምጃ

ከባድ የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው በተገኙ 24 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ 108 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና 147 ካምፓሶቻቸው ላይ ሚያዚያ 10 እና 11/2014 ዓ.ም ድንገተኛ ፍተሻ ማካሄዱን ባለስልጣኑ ገልጿል።

በዚህም ከባድ የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው በተገኙ 24 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ካምፓሶች ላይ የፕሮግራም፣ የካምፓስ እና የተቋም መዝጋት እርምጃ ተወስዷል፡፡

በተጨማሪም በ82 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ቀላል የማስጠንቀቂያ እርምጃ መስጠቱን ባለስልጣኑ ገልጿል።

ተቋማቱ በቀጣይ የተገኝባቸው ክፍተቶች በማስተካከል በአስር የሥራ ቀናት ውስጥ ለባለሥልጣኑ ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

የፕሮግራም፣ የካምፓስ እና የተቋም መዝጋት እርምጃ የተወሰደባቸው 24 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT