STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
4_5940274679032842609 (2).docx
3.4 MB
#HawassaUniversity

በ2014 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የተመደቡ አዲስ የመጀመሪያ ድግሪ መደበኛ ተማሪዎች የOnline ምዝገባ አካሄድ፤
ሙሉ stepu በዚክ pdf አለ ተከተሉት አንድ በአንድ Hawassa University
ድረ-ገጽ
https://sis.hu.edu.et

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#JigjigaUniversity

በ2014 ዓ.ም በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ከግንቦት 01 እስከ 03/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

• ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው
• ጉርድ ፎቶግራፍ (8)
• ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርሲቲውን ድረ-ገጽ www.regi@jju.edu.et መጎብኘት ትችላላችሁ፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#SelaleUniversity

በ2014 ዓም የትምህርት ዘመን በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው 👉 ግንቦት 8 እና 9 ቀን 2014 ዓ/ም መሆኑን እናሳውቃለን።

ለምዝገባ ስትመጡ
• የ8ኛ ብሔራዊ ፈተና ውጤት
• የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት • የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል የተማራችሁበት ትራንስክሪፕት ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ
• ስምንት 3×4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ
• አንሶላ ፣ ብርድ ልብስ፣ የስፖርት ልብስ እና የትራስ ልብስ ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችዋል፡፡

ማሳሰቢያ
• የምዝገባ ቦታ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ጀነራል ታደሰ ብሩ ካምፓስ
. ከተጠቀሰው የምዝገባ ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ክፍያ

የአዲስ አበባ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በቀጣይ የትምህርት ዘመን (2015 ዓ/ም) ክፍያ መጨመር የሚችሉት የግል ትምህርት ቤቶች መለየታቸውን እና ጭማሪውም ከወላጆች ጋር መክረው የሚያደርጉት መሆኑን አስታውቋል።

ጭማሪ ማድረግ የሚችሉ ት/ቤቶች በ2014 ዓ/ም ምንም አይነት የክፍያ ጭማሪ ያላደረጉ ናቸው።

የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ህይወት ጉግሳ ጉዳዩን ከተመለከተ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ በሰጡት ቃል፥ " ጭማሪ ማድረግ የሚችሉት በ2014 ምንም አይነት ጭማሪ ያላደረጉ ብቻ ናቸው። ጭማር ማድረግ ይችላሉ ሲባል ደግሞ ቀጥታ ይጨምራሉ ማለት ሳይሆን ከወላጆች ጋር መክረው / ከወላጅ ኮሚቴ ጋር መክረው ሲተማመኑ ነው " ብለዋል።

ወ/ሮ ህይወት ጭማሪ የሚደረገው ክፍያ ተፈፃሚ የሚሆነው ወላጆች እና የወልጅ ኮሚቴ ያመነበት ብቻ እንደሆነም አክለዋል።

ወላጆችና ትምህርት ቤቶች ባይስማሙ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ጣልቃ ገብቶ ሁለቱን አካላት የማግባባት ስራ የሚሰራ ሲሆን መንግስት ያስቀመጠውን መመሪያ ሳይከተል ወላጆች ያልተስማሙበት ወርሃዊ ክፍያ እጨምራለሁ የሚል ትምህርት ቤት ካለ እውቅና ፍቃዱ ይሰረዛል ፤ ትምህርት ቤቱ ይታሸጋል ለዚህም የተዘጋጀ በቂ መመሪያ መኖሩን የአዲስ አበባ ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል።

በሌላ በኩል፤ ነገ እና ከነገ በስቲያ በአዲስ አበባ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከተማሪ ወላጆች ጋር ምክክር ለማድረግ ቀድመው ቀጠሮ የያዙ ሲሆን ሁሉም ወላጆች በት/ቤት ተገኝተው የተማሪዎች መመዝገቢያ እና የወርሃዊ ክፍያ ላይ በንቃት ተሳትፈው የጋራ ውሰኔ እንዲያሳልፉ የከተማው ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ጥሪ ማቅረቡን ሸገር ኤፍ ኤም
ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት አምጥተው በየዩኒቨርሲቲው የተመደቡ ተማሪዎች ምደባውን እና የተለያዩ ጉዳዮችን ተከትሎ ያላቸውን ቅሬታ በኦንላይን ሲቀበል መቆየቱን ገልጾ ለቀረቡት ቅሬታዎች በሙሉ ተገቢውን ምላሽ ሰጥቶ መጨረሱን ዛሬ አሳውቋል።

ይህን ተከትሎ ወደ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች በሙሉ ዩኒቨርሲቲዎቹ በሚያደርጉት የጥሪ መርሃ-ግብር መሰረት በየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ አስፈላጊውን መረጃ አሟልተው እንዲገኙ አሳስቧል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከሳምንታት በፊት የተማሪዎችን ምደባ ይፋ ማድረጉ ፤ ይህንን ተከትሎም ቅሬታ ያላቸው ቅሬታቸውን እንዲያቀርቡ ጥሪ ማቅርቡ ይታወሳል።
ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update

መግቢያ / ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ፦

👉 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ማድረጊያ ሚያዚያ 24 እና 25/2014 ዓ/ም ፤ በረመዷን በዓል ምክንያት መድረስ ለማይችሉ እስከ አርብ ሚያዚያ 28 /2014 ዓ/ም ድረስ

👉 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የኦንላይን ምዝገባ ግንቦት 01 እስከ 05/2014 ዓ/ም ፤ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ግንቦት 8 እና 9/2014 ዓ/ም

👉 ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም

👉 ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 27 እና 28/2014 ዓ/ም

👉 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2 /2014 ዓ/ም

👉 መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 01 እና 02/2014 ዓ/ም

👉 ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 29 እና 30 /2014 ዓ/ም

👉 ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እስከ 30 /2014 ዓ/ም

👉 ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እና 29/2014 ዓ/ም

👉 ASTU / AASTU ሚያዚያ 28 እና 29 /2014 ዓ/ም በቅጣት ግንቦት 1 /2014 ዓ/ም

👉 ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 8 እና 9 ፤ ምዝገባ ግንቦት 10 እና 11

👉 መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 01 እና 02 /2014 ዓ/ም

👉 ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ግንቦት 12፣ 13 እና 14

👉 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2/2014 ዓ/ም

👉 ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2/2014 ዓ/ም

👉 መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 10 እና 11 /2014 ዓ/ም

👉 ጅማ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 4 እና 5 /2014 ዓ/ም

👉 ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 4 እና 5 /2014 ዓ/ም

👉 ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከሚያዚያ 28 እስከ 30/2014 ዓ.ም

👉 ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 3 እና 4 /2014 ዓ/ም

👉 መቱ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 3 እና 4/2014 ዓ/ም

👉 እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከግንቦት 9 እስከ 11/2014 ዓ/ም

👉 ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 09 እና 10/2014 ዓ.ም

👉 ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከግንቦት 01 እስከ 03/2014 ዓ.ም

👉 ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
📚 አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነጭ ሳር ግቢ ዶርም ምደባ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ሰላም እንዴት ናቸው የመደወላቡ ዩኒቨርስቲ የአንደኛ አመት ወይም የመጀመሪያ አመት አዲስ ተማሪዎች እንዴት ናችሁ ? ዝግጅት እንዴት ነው?

ግቢያችን ለአዲስ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች መግቢያ ጊዜ ግንቦት 1 እና 2 መሆኑን ማሳወቁ አይዘነጋም ። አነሆ መምጫችሁ ደርሶ ወደ ግቢያሁ ስትመጡ በትራንስፖርት መጨናነቅ እንዳይፈጠርባችሁ በማሰብ እስከ ግቢ ድረስ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መኪናዎችን ያዘጋጀን ሲሆን መኪናዎቹም ከ አዲስ አበባ አራቱም መንሀሪያዎች ማለትም
አየር ጤና መንሀሪያ
አውቶቡስ ተራ መንሀሪያ (መርካቶ)
አስኮ መንሀሪያ
ቃሊቲ መንሀሪያ
እንዲሁም በአዳማ በኩል ለምትመጡ ልጆች አዳማ መንሀሪያ መኪናዎችን ያዘጋጀን ሲሆን ሰኞ ማለትም 01/09/2014 አ.ም ከጡኣቱ አንድ ሰአት ጀምሮ መኪናዎቹ መጫን ስለ ሚጀምሩ በሰአቱ ተገኙ እንላለን ።
የመደወላቡ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አገልግሎት

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ድሬዳዋ_ዩኒቨርሲቲ

በ2014 ዓ/ም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ግንቦት 8-9/2014 ዓ/ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ስለሆነም ተማሪዎች በአካል ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ማሰስቢያ ተላልፏል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
በዛሬው ዕለት የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህታቸዉን እና ፈተናቸዉን በወጣላቸዉ ፕሮግራም መሠረት እየወሠዱ ይገኛሉ።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT