STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ቤት በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ፤ በማታ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ መረጃዎች
1. የትምህርት መረጃ፡- ሙሉ የትምህርት መረጃ ኦርጅናልና ሁለት (2) ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ሁለት (2) ጉርድ ፎቶ ግራፍ
2. የድጋፍ ደብዳቤ፡- የአመልካቹን ጥንካሬና ባህሪ የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ከመ/ቤት ኃላፊ /ከቀድሞ መምህር/ Recommendation Letter/
3. የመመዝገቢያ ክፍያ፡- የማመልከቻ ክፊያ የ100 ብር ደረሰኝ በመያዝ የማመልከቻ ቅጽ ከቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210፣ 211 እና ከዩኒቨርሲቲው ድኀረ-ገፅ (www.amu.edu.et) ማግኘት ይችላሉ፡፡
. በመንግሥት /በድርጅት ስፖንሰርነት ለሚማሩ በመስሪያ ቤቱ/ በድርጅቱ ኃላፊ የሚፈረም /Sponsorship Form/ ከዩኒቨርሲቲው ድኀረ-ገፅ (www.amu.edu.et) ማግኘት ይችላለ፡፡
የማመልከቻ፤ የፈተና መስጫ፤ የውጤት ማሳወቂያ፤ የምዝገባ ጊዜ እና ቦታ
የማመልከቻ ጊዜ፡- ከየካቲት 15/2014 ዓ.ም እስከ የካቲት 30/2014 ዓ.ም፤
የማመልከቻ ቦታ፡- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አ/ዳ/ጽ/ቤት ቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210፣ 211 እና አዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት አራት ኪሎ ሮሚና ካፌ ጎን፤
ለፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር የሚወጣበት ቀን፡- መጋቢት 02/2014 ዓ.ም ፤ ለፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር በውስጥ ማስታወቂያ እና በዩኒቨርሲቲው ድኅረ-ገጽ (www.amu.edu.et) መከታተል ይችላሉ፡፡
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፡- መጋቢት 5/2014 ዓ.ም
ፈተና የሚሰጥበት ቦታ፡- የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ነጭ ሳር ካምፓስ
ማሳሰቢያ፡-
 ማንኛውም የመግቢያ ፈተና ያለፈ አመልካች ኦፊሻል ትራንስክሪፕት /Official Transcript/ ብቻል በምዝገባ ወቅት ካልሆነ በ60 ቀናት ውስጥ ካልቀረበ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
 በአካል ቀርባችሁ ማመልከት ለማትችሉ አመልካቾች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂ/ቁ 1000021480502 የማይመለስ ብር የ 100 ገቢ ያደረጋችበትን አንድ ኮፒና ሙለ የትምህርት ማስረጃችሁን ኮፒ በማድረግ በ Email አድራሻችን admission@amu.edu.et ማመልከት ትችላላችሁ፡፡
PhD Program - PhD in Public Health
 መደበኛ የፒ ኤች ዲ ተማሪዎች ሁሉም በተመጣጣኝ ክፊያ የዶርም አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አ/ዳ/ጽ/ቤት

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

ለወሎ ዩኒቨረሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የሁሉም መደበኛ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች (የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጨምሮ) ምዝገባ የሚከናወነው #መጋቢት 12 እና 13/2014 ዓ.ም ሲሆን ነባሩ መታወቂያ ስለተቀየረ ወደ ግቢ ስትመጡ ለመታወቂያ የሚሆን ሁለት 3×4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ እና ነባሩን መታወቂያ ይዛችሁ እንድትመጡ እያሳሰብን ከመግቢያ ቀን በፊት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግደሆናችንን እናሳውቃለን፡፡

የወሎ ዩንቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ለአዲስ የሕክምና ትምህርት አመልካቾች የምዝገባና ተያያዥ መሥፈርትን በዛሬው ዕለት ይፋ እናደርጋለን ሲል ቅዱስ ፓውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ አሳውቋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ መጋቢት 4 ቀን 2014 እንዲፈጸም ሲኖዶሱ ወሰነ።

የካቲት 25/2014 ዓ.ም

ቅዱስ ሲኖዶስ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሁድ እንዲፈጸም ውሳኔአሳልፏል፡፡

አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚከናወን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቪዥን የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ወቅታዊ ሁኔታን ስለማሳወቅ

=============================

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በጥቂት ተማሪዎች የእርስበርስ ግጭት ሐሙስ የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ረፋድ ላይ ግጭት የተቀሰቀሰ ቢሆንም ብዙም ሳይቆይ በፀጥታ ሀይሎች የጋራ ርብርብ ማረጋጋት ተችሏል።

በግጭቱ ሳቢያ እስካሁን የአንድም ተማሪ ህይወት አለማለፉንና የከፋ አደጋና የንብረት ውድመት አለመድረሱን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።

በግጭቱ ሰቢያ ጥቂት መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕሬንስቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ሌሎች ተማሪዎች ወደ ማደርያቸው ተመልሰዋል።

ከዚህ ውጪ አንዳንድ አካላት ለጊዜያዊ የፖለቲካ ፍጆታቸው ሲሉ የተዛባና የተሳሰተ መረጃ በአንዳንድ የማህበራዊ የትስስር ገፆች እያሰራጩ እንደሆነ ተደርሶበታል። ይህ የሚለቀቁ የሀሰት መረጃዎች ዩኒቨርሲቲው የሰላም አምባሳደር መሆኑ ያልተመቻቸው እና የራሳቸውን አጀንዳ ለማስረፅ የሚፈልጉ አካላት የሚነዙት የሀሰት ወሬ ነው።

በመሆኑም የሚለቀቁ መረጃዎች የተዛቡና ከእውነት የራቁ መሆናቸውን እየገለፅን በቀጣይ ያሉ መረጃዎችን ከዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ድረ-ገፅ ብቻ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን።

በዚህ መሠረት ዩኒቨርሲቲው ሰላም መሆኑን እና የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የዩኒቨርሲቲው አመራርና የሚመለከታቸው አካላት በጋራ በመሆን የተፈታ ሲሆን በቀጣይም ዘላቂ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲካሄድ በጋራ ውይይት እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን መደበኛ የመማር ማስተማር ስራ መቀጠሉን እናሳውቃለን።

ዘገባው የህዝብ ግንኙነት እና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የግል_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማትና_እውቅና_ፈቃድ_የተሰጣቸው_የትምህርት_መስኮች.pdf
6 MB
#Repost

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እስከ የካቲት 2014 ዓ.ም ድረስ ያጠናቀራቸውን አጠቃላይ የ350 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና የትምህርት መስኮቻቸውን የእውቅና ፈቃድ የሚገልጽ የተሟላ መረጃ ከላይ ተያይዟል።

ከ350ው 330ዎቹ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሆኑ 20 ተቋማት በርቀት ትምህርት እውቅና የተሰጣቸው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በክልል መንግስታት የሚተዳደሩ ተቋማት ይገኙበታል።

የእውቅና ፈቃድ ባልታደሰባቸው የትምህርት መስኮች #አዲስ_ተማሪ_መቀበል_እንዳይችሉ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡

ይህ መረጃ እስከ የካቲት ወር ድረስ ያለውን የእውቅና ፈቃድ ነው።

በሂደት ላይ ያሉ የእውቅና ፈቃድ እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት ጥያቄዎች ውሳኔ ሲያገኙ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የእውቅና ፈቃድ ሲሰረዝና በሌሎች ምክንያቶች የውሳኔ ለውጦች በሚኖሩበት ወቅት የመረጃ ለውጥ ሊኖር ይችላል።

በመሆኑም ፦
- ተማሪዎች፣
- ወላጆች፣
- ቀጣሪና የሙያ ፈቃድ የሚሰጡ ድርጅቶች ፣
- የሚዲያና ማስታወቂያ ተቋማት ፣ እንዲሁም መላው ህብረተሰብ የተቋማቱን ወቅታዊ መረጃ በመከታተል ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ተቋማት ይፋ ከተደረገው የእውቅና ፈቃድ መረጃ ውጪ ተማሪ ተቀብለው ቢያስተምሩ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

[ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና እውቅና ፈቃድ የተሰጣቸው የትምህርት መስኮች ከላይ በ #PDF ተያይዟል ]

#ሼር #Share

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት #በሳተላይት_ኮሌጆች በ2014 ዓ/ም ትምህርታችሁን ለመከታተል የመግቢያ ፈተና ለወሰዳችሁ ተማሪዎች በሙሉ

1. የምደባ ቦታችሁ በቀድሞው #የፌደራል_ቴክኒክና_ሙያ_ትምህርትና_ስልጠና_ኤጀንሲ በተመደባችሁበት ሲሆን በSurveying Technology እና በRoad Construction Technology ጀነራል ዊንጌት ተመድባችሁ የነበራችሁ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ #በባህርዳር_ካምፓስ የተመደባችሁ መሆኑን

2. በመጀመሪያው ምደባ በአዲስ አበባ ተግባረዕድ እና ጀነራል ዊንጌት ተመድባችሁ እና የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ወደ ተለያዩ ካምፓሶች ተበትናችሁ የነበራችሁ ተማሪዎች በጥያቄያችሁ መሰረት ወደ መጀመሪያው ምድብ ቦታችሁ ማለትም አዲስ አበባ ተግባረዕድ እና ጀነራል ዊንጌት እንድትመለሱ የተደረገ መሆኑን፤
ነገር ግን በየወሩ ከሚከፈለው ስድስት መቶ ብር ውጪ ምንም አይነት የመኝታም ሆነ የምግብ አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ ራሳችሁን ከወዲሁ እንድታዘጋጁ

3. በማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ በአምቦ እና አሰላ ካምፓሶች ለመማር ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች በቁጥር ማነስ ምክንያት ወደ #አዳማ_ካምፓስ የተመደባችሁ መሆኑን እንድታውቁ

4. በሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት ትምህርታችሁን ለመከታተል በዋናው ጊቢ ፈተና የወስዳችሁ ተማሪዎች ወደ #አርባምንጭ_ሳተላይት ካምፓስ የተመደባችሁ መሆኑን

5. የመመዝገቢያ ቀን ቀድሞ በየሳተላይቶቻችሁ በተገለፀው መሰረት #ከየካቲት_30_እስከ_መጋቢት_1 /2014ዓ/ም ሲሆን በቅጣት የመመዝገቢያ ቀን #መጋቢት_2 /2014 መሆኑን አውቃችሁ በእለቱ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

የሳተላይት ማዕከላት ማስተባባሪያ ዳይሬክቶሬት

@NATIONALEXAMSRESULT
4፤ ከ7 ሺህ በላይ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች ለአንድ ዓመት ያህል ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው መናገራቸውን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ለዜና ምንጩ ቃላቸውን የሰጡ የዩኒቨርሲቲው መምህራን ደመወዝ ባለማግኘታቸው ከእነ ቤተሰባቸው ከባድ ችግር ላይ እንደወደቁ ገልጸው፣ ችግራቸውን ለማቃለል መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የተቀጠሩ እና ሕወሃትን የተቀላቀሉ አንዳንድ መምህራን እንዳሉ ተናግዋል። ትምህርት ሚንስቴር በበኩሉ ከትግራይ ክልል ሸሽተው የወጡ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን በሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደመደበ እና ከክልሉ ላልወጡት ግን ማድረግ የሚችለው ነገር እንደሌለ ገልጧል።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ፦

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በግል መደበኛ መርሐ ግብር (Private Regular Program) አዳዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል።
በመሆኑም:-
¥ ቢኤስሲ ነርሲንግ (BSc Nursing)

¥ ቢኤስሲ ሚድዋይፈሪ (BSc Midwifery)

የትምህርት ዘርፎች ወደፊት በሚገለጸው የመመዝገቢያ ቀን እና መስፈርት መሰረት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ከኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የተሰጠ ማሳሰቢያ

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ መርሀ ግብር ለመማር የሚመዘገቡ ተማሪዎች የሚከተሉትን የቅበላ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

እነዚህም፡-
1. የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቁ ተማሪዎች ከሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ዘመኑ ያስቀመጠውን የመቁረጫ ነጥብ ሊያሟሉ ይገባል፡፡

2. ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም የተመረቁ ባለሙያዎች ከሆኑ ከሠለጠኑበት የሙያ መስክ ጋር ተዛማጅነት ባለው የሥልጠና መስክ በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ በደረጃ 4 (ወይም በቀድሞ 10+3 ወይም 12+2) ያጠናቀቁ ሆነው በሙያው ደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC level 4) ተፈትነው ያለፉበትን፤ እንዲሁም በሙያው ቢያንስ የሁለት ዓመት ሥራ ልምድ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች በምዝገባው እለት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

3. ከውጭ ሀገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ለዲግሪ መርሃ-ግብር መግቢያ የሚያገለግለው በባለስልጣኑ የአቻ ግምት ሲሰራለት ብቻ ይሆናል፡፡


4. በየተቋማቱ የሚዘጋጁትን የመግቢያ ፈተናዎች ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፤ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች በምዝገባው ዕለት ማቅረብ ያልቻለ ተመዝጋቢ ህጋዊ ተቀባይነት አይኖረውም።

ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎች ህጋዊ መመሪያዎችን ጥሶ የተገኘ ተቋም በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የስነ ስርዓት መመሪያ መሠረት በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን እየገለጽን፤ ከህግ ውጪ ገብተው የሚማሩ ተማሪዎችም ሊደርስባቸው የሚችለውን የጊዜ፣ የገንዘብና የስነ-ልቦና ኪሳራ አውቀው አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባለስልጣኑ ያሳስባል። #ETA


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ASTU #AASTU #ማሻሻያተደርጓል

ሁለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች (አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ) የ2014 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ ላይ ማሻሻያ አድርጓል።

የመመዝገቢያ መስፈት የሲቪክስ ትምህርትን አይጨምርም‼️

• ለአዳጊ ክልሎች (አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ)

- ኢንጂነሪንግ ~ ለወንድ 375፣ ለሴት 370
- አፕላይድ ሳይንስ ~ ለወንድ 365፣ ለሴት 360

• ለሌሎች ክልሎች

- ኢንጂነሪንግ ~ ለወንድ 380፣ ለሴት 375
- አፕላይድ ሳይንስ ~ ለወንድ 370፣ ለሴት 365

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ10 ሺህ በላይ መደበኛ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎቹን መጋቢት 12 እና 13 እንደሚቀበል አስታወቀ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሀላፊ ዶ/ር ብርሀን አሰፍ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተቋሙ ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ ለተማሪዎች ጥሪ ማድረጉን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከ1ኛ እሰከ 3ኛ ድግሪ ድረስ ያሉ ተማሪዎችን እንደሚቀበል የተገለጸ ሲሆን÷ በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሚማሩ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ለመቀበል መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ሁሉም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችም በተጠቀሰው ቀን በዩኒቨርሲቲው በመገኘት ምዝገባ ማካሄድ እንዳለባቸው አሳስቧል።

#FBC


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የካራማራ ድል 44ኛ ዓመት መታሰቢያ እየተከበረ ነው!

ኢትዮጵያውያን የዚያድባሬን ወራሪ ጦር ያሸነፉበት የካራማራ ድል 44ኛ ዓመት በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው፡፡የዚያድባሬ ጦር ኢትዮጵያን ለመውረር የሞከረበትና ድል የተደረገበት የካራማራ ድል 44ኛ ዓመት በዛሬው ዕለት እየተከበረ ነው።በዓሉ አዲስ አበባ በሚገኘው በኢትዮ ኩባ ፓርክ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።በአከባበር ስነ ስርዓቱ ላይ የቀድሞ የጦር ጄኔራሎች፣ መኮንኖች እና ወታደሮች እንዲሁም ወጣቶች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

[FBC]
መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ከ7 ሺህ በላይ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ደሞዝ ሳይቀበሉ አንድ ዓመት እንዳለፋቸው ተናገሩ።

መምህራኑ ምንም እንኳን የፌደራል መንግስቱ ቅጥረኛ ቢሆኑም "ደመወዝ ስላልተላከልን የከፋ ችግር ውስጥ እንገኛለን" ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ ከትግራይ ክልል የወጡ መምህራንን ወደ ሌላ ተቋማት ማሸጋገሩን እና በክልሉ ላሉት ግን ምንም ማድረግ እንደማይችል ገልጿል።

በዩኒቨርሲቲው የሕክምና ትምህርት ቤት ባልደረባ የሆኑ አንድ ሠራተኛ ፤ በትግራይ ክልል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ 7 ሺህ ሠራተኞች ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው እና እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ይገልጻሉ።

ያለውን ሁኔታ ለመቋቋም ልጆቻቸውን ወደ ገጠራማ የትግራይ አካባቢ የላኩ መምህራን መኖራቸውን የሚገልጹት እኚህ የአይደር ሕክምና ትምህርት ቤት ባልደረባ፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን እና የትግራይ ታጣቂ ኃይሎችን የተቀላቀሉም አሉ ይላሉ።

"የፌደራል ተቋም ብንሆንም፤ የፌደራል መንግሥቱ በጀት ሳይልክልን ቀርቷል" በማለት ቅሬታቸውን ይናገራሉ።

የትምህር ሚኒስቴር ሚኒሰትር ዲኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በትግራይ ላሉ ሠራተኞች ምንም ማድረግ አንችልም ብለዋል።

"ከክልሉ ሸሽተው የወጡ የዩኒቨርሲቲ ባልደረቦች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲች ተዘዋውረዋል፤ ተማሪዎችም እንዲሁ። በአሁኑ ወቅት በክልሉ ላሉት ግን ምንም ማድረግ አንችልም" ሲሉ ሚኒስትር ዲኤታው ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ዓመታዊ በጀታቸውን የሚያገኙት ከፋይናንስ ሚኒስቴር መሆኑም አክለው ገልጸዋል።

ቢቢሲ አማርኛ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ለትምህርት ጥራት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው በትምህርት ጥራት ዙሪያ ዋና ዋና ችግሮችን ለይቶ በትኩረት እየሠራ መሆኑን የካቲት 25/2014 ዓ/ም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ማኅበረሰብ አባላት፣ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ዘርፎች የተወጣጡ ተወካዮች በተገኙበት ባደረጉት ስብሳባ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ እንደተናገሩት ባለፉት 45 ዓመታት ውስጥ የትምህርት ሥርዓቱ በተጨባጭ ያለበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ከመሆኑ አንጻር የተለያዩ ጥናቶችንና ውይይቶችን በማካሄድ አራት ዋና ዋና ችግሮችን መለየት ተችሏል ብለዋል፡፡ ለትምህርት ሥርዓቱ መውደቅ መሠረታዊ ከሆኑ ችግሮች መካከል፡- የትምህርት ጥራት መውደቅ፣ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት፣ የትምህርትና የክልልተኝነት መያያዝ እና የሞራል ኪሣራ መሆናቸውን ሚኒስትሩ ጠቁመው በቀጣይ 5 ዓመታት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም በቀጣይ አዲስ ዩኒቨርሲቲዎችን የመክፈትና የማስፋፊያ ግንባታዎች የማካሄድ ዕቅድ የሌለ ሲሆን በሂደት ላይ ያሉ ግንባታዎችን የማስጨረስ፣ ያለውን ግብዓት የማሻሻልና ጥራት የማስጠበቅ ሥራ ላይ በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከታችኛው የክፍል ደረጃ ጀምሮ መሥራት ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ ከያዝነው የትምህርት ዘመን ጀምሮ የፈተና ደኅንነትን ለማስጠበቅ ፈተናው በታብሌት እንዲሰጥ እየተሠራ ሲሆን በከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከ50% በታች የሚያመጡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሊገቡ አይችሉም ብለዋል፡፡ እስከ አሁን ባለው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና መቁረጫ 34% መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር የቀጣዩ ትውልድ አብሮ የመኖርን፣ የመከባበርንና መተሳሰብን እንዲሁም ሀገራዊ አንድነትን ለማዳበር ይረዳ ዘንድ 50 አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በመክፈት፤ ከሁሉም ክልሎች በ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በመግቢያ ፈተና ውጤት አወዳድሮ በመቀበል እንዲማሩ የሚደረግ ሲሆን በ2016 ዓ/ም 13ቱ ትምህርት ቤቶች ተጠናቀው ሥራ ላይ እንደሚውሉ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ዩኒቨርሲቲዎች ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የእውነትና የእውቀት ምንጭ እንዲሆኑ ለማስቻል ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስተዳደር ቦርድ አወቃቀር ጀምሮ ያለው ሥርዓት ሁሉን ባማከለ መልኩ መደራጀቱን እና በቅርብም ተግባራዊ እንደሚደረግ የጠቆሙት ሚኒስትሩ ሁሉም ባለድርሻዎች በጋራ ለለውጥና የተሻለ ትውልድ ለማፍራት እንዲተጉ ጠይቀዋል፡፡

የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፈንታ ማንደፍሮ በበኩላቸው እንደገለጹት መጪው ትውልድ የተሻለ ሀገር እንዲኖረው የሚያስችለውና የሀገራችንን እጣ ፈንታ የሚወስነው ትምህርት እንደመሆኑ ትውልድን የሚቀርጹ መ/ራን የሚገባቸውን የደመወዝና የጥቅማ ጥቅም ክፍያ እንዲሁም የሙያ ክብር እንዲያገኙ ማድረግ የመንግሥት ኃላፊነት ነው፡፡ የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ለመቀየር ያሉብንን ተቋማዊ ክፍተቶችን ሞልተን አስተወጽኦ ማድረግ የምንችለው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምንሠራቸው ሥራዎች ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በቸልተኝነት ተማሪዎች የሚገባቸውን ሳያውቁና በቂ ክሂሎት ሳያገኙ እንዲመረቁ ማድረግ የትምህርት ሥርዓትን መግደል ነው ብለዋል፡፡

ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ ሁሉም የመንግሥትና የግል ከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች ተመርቀው ሲወጡ የሚሰጣቸውን የመውጫ ፈተና በማለፍ ብቻ ሥራ መቀጠር የሚችሉ ሲሆን በመጀመሪያ ዙር ፈተና ካለለፉ በስድስት ወራት ልዩነት ሁለት ጊዜ በግል መፈተን የሚችሉ እና በሦስቱም ዙሮች ፈተና ያላለፉት ደግሞ በመስኩ መቀጠር የማይችሉ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አክለው ተናግረዋል፡፡

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ እንደገለጹት አዲሱ የትምህርት ፍኖተ-ካርታ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ሆነ በአጠቃላይ ትምህርት ደረጃ ከየትኛውም የመንግሥት ሥርዓት ጋር የሚቀየርና የሚሻሻል እንዲሁም ከየትኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ ጋር የሚቃኝ ሳይሆን ሀገሪቱንና ዜጎቿን ታሳቢ ያደረገ የሰው ልጅን የመማር፣ የመላቅ አቅምን ባገናዘበ ሁኔታ ሀገሩን አውቆና ግብረ ገብነት ተላብሶ እንዲሄድ ለማድረግ ብርቱ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
''የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከተጀመረ ጀምሮ 71 ሺ በላይ ተፈታኞች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን 32 ሺ 480 የሚሆኑት የተሰጠውን ፈተና አልፈው የሙያ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ ገብተዋል።'' ጤና ሚኒስቴር

@NATIONALEXAMSRESULT
በግድቡ ዙሪያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው
*****
(ኢ..ድ)
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ነው።
የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ብርሀነመሰቀል ጠና በዚህ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ግድቡን መጀመር ቀላላል አልነበረም፤ የነበሩት አቅልለው አሰጀምረውታል ፤ ለመጨረሰ ደግሞ ትውልዱ አንድ በመሆን ታሪክ እየሠራ ነው ብለዋል።
ግድባችን ለዘመናት አስሮ ከያዘን ድህነት መውጫችን ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ወዳጅ እና ሀብት ለማፍራት ግድባችንን ማጠናቀቅ ያሥፈልገናልም ብለዋል።
ሁሉም የግድቡ አምባሣደር ነው ያሉት ዶክተር ብርሀነመስቀል፤ በተለይም ወጣቱ አመራሩ ሢዘናጋ ሊያነቃ ይገባል ብለዋል።
ግድቡን በማጠናቀቅ ድህነትን ማራገፍ እንችላለን ሲሉ የገለጹት ዶክተር ብርሀነመስቀል፤ ያሁኑ አመራርና ትውልድ የህዳሴው ግድብ አምባሳደር ነው ብለዋል።
ውይይቱን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አስተባባሪ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት እና በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርስቲ በጋራ የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል።
በሙሳ ሙሐመድ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT