STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.8K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ዩኒቨርሲቲዎች ራሳቸውን ችለው እንዲሰሩ ማስቻል ላይ እየተሰራ እንደሚገኝ እንዲሁም ከዚህ በኃላ የሚሰጡ ድግሪዎች የመውጫ ፈተና እንደሚያስፈልጋቸውና በትምህርት ስርዓቱ ላይ ስር ነቀል ለውጥ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ሁሉም የለውጡ አካል በመሆን ትብብራችሁን እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

እንዲሁም በት/ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚ/ር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የትምህርት ሴክተር ሰፊ በመሆኑ ቅደም ተከተል በማበጀት በትምህርት ፖሊሲዎች ላይ፣ ተቋማዊ ነፃነት እና አወቃቀር ላይ፣ የመምህራን መብትና ግዴታዎች እንዲሁም የመምህራን ምዘና ስርዓታችን ልምድንና የተመዘገበ ስኬትን ያማከለ ዕድገት እንዲኖረው እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡

በት/ሚኒስትር የአጠቃላይ ትምርት ዘርፍ ሚ/ር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ በበኩላቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሀገሪቱ የገጠሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና ችግሮችን በመፍታት ሀገርን በማሻገር ሂደት ላይ የራሱን አሻራ ያሳረፈ መሆኑን ገልፀው ሁላችሁም የእኛ ልጆች ወደፊት ምን ይሉናል ብላችሁ በትምህርት ስርዓቱ ላይ የራሳችሁን ድርሻ እንድትወጡ አደራ እላለሁኝ ብለዋል፡፡

በውይይት መድረኩ የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱና ገንቢ አስተያየቶችን የሰነዘሩ ሲሆን ክቡር ሚንስትሩም ከተሳታፊዎች ጋር በመወያየት እና ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሾችን በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የጥሪ ማስታወቂያ!
***
በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ.ም ትምህርት ጀምራችሁ የነበራችሁ የአንደኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም የ3ኛ እና 4ኛ ዓመት ፔዳጎጅካል ሳይንስ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው መጋቢት 5 እና 6/2014 ዓ.ም ሲሆን በቅጣት ደግሞ መጋቢት 7/2014 ዓ.ም ስለሆነ በተጠቀሱት ቀናት በአካል ተገኝታችሁ ምዝገባ እንድታደርጉ እያሳወቅን ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ቤት ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 72 ተማሪዎች 42ቱ ከ600 በላይ ጠቅላላ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው አረጋግጧል።

ቀሪዎቹ 36 ተማሪዎች ደግሞ ከ529 እስከ 600 ድምር ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጿል።

በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነውን 659 ውጤት ያመጣው ተማሪ አላዛር ተካም የዚሁ ትምህርት ቤት ተማሪ መሆኑንም ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

"Science Shared Campus" በመባል የሚጠራው ትምህርት ቤቱ ፤ ከ6 ዓመት በፊት በSTEMpower Ethiopia ተቋቁሞ ለተወሰነ ጊዜ ድጋፍ ሲደረግለት ቆይቶ በመጨረሻ ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ተላልፎ ተሰጥቷል።

ትምህርት ቤቱ ለሳይንስና ሂሳብ ትምህርቶች ትኩረት ሰጥቶ እንደሚያስተምር ተገልጿል።



ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
በክልሉ በትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ

የካቲት 23/2014 (ዋልታ) በደቡብ ክልል በትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በልዩ ትኩረት መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

በክልሉ የ2014 ዓ.ም የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም የትምህርት ጉባኤ በጂንካ ከተማ እየተካሔደ ነው፡፡

በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) በክልሉ በትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በልዩ ትኩረት መሥራት ይገባል ብለዋል።

በክልሉ በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እየራቁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዘርፉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ተንቀሳቃሽ ትምህርት ቤቶችን ማዘጋጀት መቻሉንም ጠቁመዋል።

የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተደራሽነት ላይ ትኩረት በመስጠት መሰራት አለበት ያሉት ኃላፊው በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራምን ማጠናከር እንደሚገባም አብራርተዋል።

በክልሉ የትምህርት ጥራት ችግር መኖሩን ለኅብረተሰቡ በግልጽ ማሳወቅ ይገባል ሲሉም ጠቁመዋል።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የትምህርት ጥራት ችግርን ለመቅረፍ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ባለድርሻ አካላት መረባረብ እንዳለባቸው ተገለጸ
የካቲት 23/2014
(ዋልታ)
በአገር ዐቀፍ ደረጃ የሚስተዋለውን የትምህርት ጥራት ችግር ለመቅረፍ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ባለድርሻ አካላት መረባረብ እንዳለባቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ካውንስል አባላትና ከመምህራን ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡

ለትምህርት ሥርዓቱ መውደቅ ጥራትን ያላማከለ የትምህርት ማስፋፊያና ተደራሽነት፣ የትምህርትና የፖለቲካ ሥርዓት መጣመር፣ የፖለቲካና ከባባዊነት መደባለቅ እንዲሁም በአገር ደረጃ ላይ የደረሰ የሞራል ክስረት በዋናነት ተጠቃሽ መሆናቸውን ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የዕውቀት ማበልፀጊያ ሆነው ሳለ ከተልዕኳቸው ውጪ የፖለቲካ አስተሳሰብ ማራመጃ መሆናቸው አግባብ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ያገኘነው መረጃ👇

ወሎ ዩኒቨርሲት ተማሪዎቹን ከ #የካቲት 30 ጀምሮ በሁለት ዙር እንደሚያስገባ አሳስቦ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እኛም(ህብረቱ) ተማሪዎች የሚገቡበት ቀን እየደረሰ መሆኑን በመግለጽ የመግቢያ ቀንን በማስታወቂያ ሊገለፅ ይገባል በማለት ለዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንትና ለሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት በተደጋጋሚ ጠይቀናል።

የማኔጅመንት አካላት ተማሪዎችን በማስታወቂያ እንደሚገልፁ የነገሩን ቢሆንም #የካቲት21 ቀን በነበራቸው ስብሰባ እንደ ዩኒቨርሲቲ በቴሌቬዥን እንደሚያስነግሩና ከተባለው ቀን #አንድ_ሳምንት በመጨመር(👉መጋቢት 07 አካባቢ) እንደሚያስገቡ ገልፀውልናል‼️

፨ይህ የሆነበት ምክንያት ምንድነው?

ተማሪዎች ባልተዘጋጀ ዶርምና ካፌ መተው እንዳይንገላቱብን አስቀድመን መጨረስ ያለብንን ነገር መጨረስና ማረጋገጥ ስላለብን እንዲሁም መብራት በማይኖርበት ጊዜ ተማሪዎችን በዳቦ አቅርቦትና በጥናት ጊዜ እንዳይጉላሉ ጀነሬተሮች በህውሓት ሃይሎች ስለተበላሹ ይሄንንም ለማሰራት ጊዜ ስለሚፈልግ ነው የሚል ምላሽ እንደተሰጠው ህብረቱ ገልጿል።

፨ተማሪዎች ቀደም ብላችሁ እንደገለፃችሁት በሁለት ዙር ወይስ አንድ ላይ ትጠራላቹህ ብለን የጠየቅን ሲሆን ፡ የተማሪዎች ጉዳይ ዳይሬክተር እንደ ተማሪዎች አገልግሎት በቂ የመኝታ በሮች ስለተገጠሙልኝ በተጨማሪም የምግብ ቤት ግብዓቶች ስለተሟሉ በአንድ ላይ ቢገቡ ተማሪዎችን ማስተናገድ ይቻላል ያለ ሲሆን የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ተማሪዎች በሁለት ዙር እንደሚጠሩ ገልፀው በቅድሚያ አንደኛ ዓመት እና ሁለተኛ ዓመት የነበሩትን ጠርቶ አንድ ሳምንት ባልሞላ ልዩነት ቀሪዎችን የሚጠራ ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

📌የደሴ ካምፓስ ዳይሬክተሮችን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ባይሳካልንም እንደ ዩኒቨርሲቲ በአንድ ላይ ስለሚጠራ ልዩነት እንደማይኖረው አረጋግጠናል፡፡

በአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲው እስከ #መጋቢት15 ባሉት ቀናት ሁሉንም ተማሪዎች የሚያስገባ ስለሆነ ተማሪዎች ማስታወቂያ እንድትከታተሉ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት አሳስቧል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዩክሬን ለሚገኙና ከዩክሬን ወደ ፖላንድና ሌሎች አጎራባች አገሮች በመሄድ ላይ ላሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ማግኘት የሚችሉበት ሊንክ ይፋ አድርጓል፡፡
ኤምባሲው በሩስያ እና ዩክሬን መካከል በተፈጠረው ጦርነት ምከንያት ዜጎች ወደ አጎራባች አገራት ለመግባት በሚያደርጉት ጥረት ከአገራቶቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስርያ ቤቶች ጋር በመተባበር በተቻለ መጠን ያለችግር ማቋረጥ እንዲችሉ ሲሰራ መቆየቱን አንስቷል፡፡

አሁንም ከዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስርያ ቤት ጋር በጉዳዩ ላይ በመነጋገር ከዚህ ጋር በተያያዘው አጭር ሊንክ https://cutt.ly/qAi9vBJ በመግባት ዜጎች መረጃዎቻቸውን የት እንደሚገኙና ወደ የትኛው ድንበር ለማቋረጥ እየሄዱ እንደሆነ በማሳወቅ የዩከሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስርያ ቤት የኮንሱላር ጉዳዮች ክፍል ድጋፍ ማድረግ እንደሚፈልግ ያሳወቀ በመሆኑ ሊንኩን በመጠቀም ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ሚኒስቴሩ በትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ዙሪያ በጂንካ ከተማ እየመከረ ነው

የካቲት 24/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከደቡብ ክልል የትምህርት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ዙሪያ በጂንካ ከተማ ምክክር እያካሄዱ ነው፡፡

ሚኒስትሩ በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ከደቡብ ክልል ከሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ከተውጣጡ የትምህርት ዘርፍ አካላት ጋር ነው እየመከሩ የሚገኙት፡፡

ሚኒስትሩ ከውይይቱ በሻገር በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በመርኃ ግብሩ የደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የተዘጋጀው የትምህርት ቤት ምገባ ፖሊሲና ስትራቴጂ በቅርቡ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ተገለጸ
******
(ኢ ፕ ድ)
በቅመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ለመስጠት የተዘጋጀው የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብር የፖሊሲ ማዕቀፍና ስትራቴጂ በቅርቡ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤቶች መሻሻል ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ዮሐንስ ወጋሶ እንደገለጹት፤ ከአራት ዓመታት ወዲህ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ይሰጥ የነበረውን የምገባ ፕሮግራም በቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ እንዲሰጥ ለማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤት ምገባ መርሀ ግብር የፖሊሲ ማዕቀፍና ስትራቴጂ ሰነድ አዘጋጅቷል።
ይህ ሰነድ በቀጣይ በየደረጃው ባለው የትምህርት መዋቅር በጀትን ጨምሮ በማስፋት እና የተጠቃሚ ተማሪዎችን ቁጥር ለመጨመር ሚኒስቴሩ እቅድ ይዟል።
ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
በአሸባሪው ወራሪ ቡድን የወደሙ ትምሕርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ኹሉም ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ፡፡

የካቲት 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ)

በአማራ ክልል በአሸባሪው ወራሪ ቡድን የወደሙ ትምሕርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የኹሉም ትብብር እንደሚያስፈልግ የአማራ ክልል ትምሕርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት እና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን ተናግረዋል፡፡

እንደ አቶ ጌታቸው ቢያዝን መረጃ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ፡-

• 4 ሺህ 107 ያህል ትምሕርት ቤቶች ወድመዋል፤ ከእነዚህም ውስጥ፡- 1 ሺህ 25 ትምሕርት ቤቶች ሕንፃቸውን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ የወደሙ ናቸው፤

•3 ሺህ 82 ትምሕርት ቤቶች ደግሞ በከፊል የወደሙ ናቸው፤

• 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምሕርት ገበታ ውጭ ኾነዋል፡፡

• 116 ሺህ መምሕራን ከሥራ ገበታቸው ተፈናቅለው ቆይተዋል፤

• በትምሕርት ተቋማት ላይ ብቻ የደረሰው ውድመት በገንዘብ ሲተመን 20 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ደርሷል፡፡

• የወደሙ ትምሕርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ከ21 ቢሊየን ብር በላይ ያስፈልጋል፡፡

አቶ ጌታቸው የወደሙ ትምሕርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት እና ተማሪዎችን ወደ ትምሕርት ገበታቸው ለመመለስ ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ መኾኑን አስታውቀዋል፡፡

ትምሕርት ቤቶቹን ሙሉ በሙሉ መልሶ ለማቋቋም የኹሉም አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

በትምሕርት ቢሮው በኩል ሲከናወኑ የቆዩ ካሏቸው ተግባራት መካከልም፡-

•በመጀመሪያ መረጃ ጉዳት የደረሰባቸውን ትምሕርት ቤቶች እና የጉዳቱን መጠን የመለየት ሥራ ተሠርቷል፤

•ትምሕርት ቢሮው እና ሌሎች አጋር አካላት ምን ምን ተግባራትን ማከናወን እንዳለባቸው ለማመላከት የአደጋ ምላሽ ዕቅድ ተዘጋጅቷል፤

•ተማሪዎች ከትምሕርት ገበታቸው ውጭ እንዳይቆዩ ለማድረግ ትምሕርት ቤቶች እንዲፀዱ ተደርጎ ከመልሶ ግንባታ ሥራው ጎን ለጎን ባለው ግብዓት ልክ ትምሕርት እንዲጀመር ተደርጓል።

አቶ ጌታቸው በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች ደብተርና እስክርቢቶ አንገብጋቢ ችግር እንደነበረ ገልጸው በዚህም ከተለያዩ ተቋማት ከ19 ሺህ በላይ ደብተር አሰባስበን ድጋፍ አድርገናል ብለዋል፡፡

ጉዳት ለደረሰባቸው ዞኖች ትምሕርት እንዲጀምሩ ለማድረግ የተማሪ ቁጥራቸውን ግምት ውስጥ ያስገባ የትምሕርት ማስጀመሪያ የድጎማ በጀት መሰጠቱንም ገልጸዋል፡፡

ረጂ ድርጅቶች እና አጋር አካላት ለተማሪዎች ደብተርና ዩኒፎርም እንዲያሟሉ ጥረት መደረጉንም ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ትምሕርት ሚኒስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር 9222 አጭር የጽሑፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ በመክፈት ‹‹ ኑ የፈረሰውን የትውልድ ማፍሪያ ተቋም መልሰን እንገንባ ›› በሚል መሪ ሐሳብ የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ እየተከናወነ እንደሆነም አንስተዋል፡፡ ይህ ወቅት ለኛ ለኢትዮጵያውያን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የምንረዳዳበትና የምንደጋገፍበት ወቅት መኾኑን በመግለጽ እያንዳንዱ ዜጋ የፈረሱ የትምሕርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ርብርብ የበኩሉን ድርሻ እንዲያበረክት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የወደሙ የትምሕርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባትም ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ ግለሰቦች፣ ድርጅቶች፣ ባለሃብቶች እና በውጭ ሀገራት ያሉ ዳያስፖራዎች ለትውልድ የመድረስ ታሪካዊ ኀላፊነት ተጥሎባችኋል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የትምሕርት ቁሳቁስ ለማቅረብ የሚፈልግ አካል በክልል ደረጃ በአማራ ክልል ትምሕርት ቢሮ ወይም በፌዴራል ደረጃ ትምሕርት ሚኒስቴር ዋናው ተቋም በመምጣት ድጋፍ ማድረግ እንደሚችልም ገልጸዋል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#YANETCOLLEGE

፨ያኔት ኮሌጅ በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የሚያስተምራቸው የትምህርት መስኮች

📌BSC ነርስ
📌በሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ
📌በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ

፨ያኔት ኮሌጅ በደረጃ 4(level 4)

📌በነርስ
📌በአዋላጅ ነርስ
📌በላቦራቶሪ ቴክኒሺያን
📌በፋርማሲ
📌በአካውንቲንግ ስልጠና ይሰጣል….

ያኔት ኮሌጅ በድህረ ምረቃ (በሁለተኛ ዲግሪ)
ማስተር ኦፍ ፐብሊክ ሄልዝ (MPH) እና ማስተር ኦፍ ቢዝነስ አድሚንስትሬሽን (MBA) ያስተምራል።

አድራሻ
🏷ያኔት ኮሌጅ መሳለሚያ ካምፓስ (ሰፈረ ሰላም ንጉሴ ቱሩፌ ህንፃ)
🏷ያኔት ኮሌጅ 6 ኪሎ ካምፓስ (ያሬድ ሙዚቃ ት/ት ቤት አጠገብ)

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ለመማር ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ማምጣት እንደሚያስፈልግ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ማሳወቁ ይታወሳል።

(ሌሎች የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የምታስተምሯቸውን የትምህርት መስኮች ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች ማስተዋወቅ ትችላላቹህ)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#MekaneYesusCollege

፨መካነ እየሱስ ኮሌጅ በቅድመ ምረቃ (በመጀመሪያ ዲግሪ) ፕሮግራም የሚያስተምራቸው የትምህርት መስኮች

*በአዲስ አበባ በሚገኘው ካምፓሱ👇
📌Management
📌Gender and Development Studies
📌Accounting and Finance

*ቢሾፍቱ በሚገኘው ካምፓሱ 👇
📌Management
📌Accounting and Finance

፨በድህረ ምረቃ (ሁለተኛ ዲግሪ) ፕሮግራም
📌Business Administration
📌Organizational Leadership

🏷የመካነ እየሱስ ኮሌጅ አድራሻ እና ኮሌጁን ተመራጭ የሚያደርጉትን ነጥቦች ከላይ ካለው ምስል ይመልከቱ።

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ለመማር ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ማምጣት እንደሚያስፈልግ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ማሳወቁ ይታወሳል።

(ሌሎች የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የምታስተምሯቸውን የትምህርት መስኮች ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች ማስተዋወቅ ትችላላቹህ)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#እንድታውቁት

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ፤ የአቃቂ ክፍል 2 (New CT) የውሃ ግፊት መስጫ የሀይል አስተላላፊ መስመር ፖሎች መውደቃቸውን አሳውቋል።

ባለስልጣኑ የሀይል አስተላላፊ ፖሎቹ ትላንት መውደቃቸውን ገልፆ ተተክለው ስራ እስከሚጀምሩ የውሃ ስርጭት ከታች በተዘረዘሩት አካባቢዎች በከፊል እና በሙሉ መቋረጡን አሳውቋል።

አካባቢዎቹ ፦

• ቦሌ ክፍለ ከተማ፡- ወረዳ 1፣ 2፣ 3፣ 12፣ 13
• ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፡- ወረዳ 1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 5፣ 6፣ 7፣ 8፣ 9፣ 10፣ 11
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፡- ወረዳ 4፣ 5፣ 6፣ 7፣ 8፣ 9፣ 10፣ 11፣ 12
• አቃቂ ክፍለ ከተማ፦ ወረዳ 4፣ 5፣ 6፣ 7፣ 8
• ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8

ችግሩ ስፋት እንዳለው የገለፀው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአዲስ አበባ ኤሌትሪክ አገልግሎት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጠይቋል።

መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
በቦረና እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች 61 እንዲሁም በሶማሌ ክልል 316 ትምህርት ቤቶች በድርቅ ምክንያት ተዘጉ

ሐሙስ የካቲት 24 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በኦሮሚያ ክልል ቦረና እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች ብቻ 61እንዲሁም በሶማሌ ክልል ደግሞ 316 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መዘጋታቸው ተነገረ።

በሁለቱ ክልሎች በአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ለፍተኛ ጉዳት ተጋልጠዋል ።

በኦሮሚያ በምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ፣ ምስራቅ ባሌ ዝቅተኛ ቦታዎች፣ በቦረና፣ በምእራብ ጉጂ ዞኖች በርካቶች ለከፋ ችግር እና ለምግብ እጥረት ተጋልጠዋል።

በክልሉ በአምስት ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 40 ወረዳዎች 8 ነጥብ 4 ሚሊዮን እንስሳት ተጠቅተዋል ፣ 257 ሺህ አቅም አንሷቸዋል ሲል የብሔራዊ አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ለዶይቼ ቬለ ተናግራል።

የኮኒሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ደበበ ዘውዴ እንዳሉት በምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ፣ በቦረና ፣ በምዕራብ ጉጂ ፣ በምዕራብ አርሲ እና ባሌ ዞኖች በሚገኙ 70 ወረዳዎች ውስጥ በ605 ቀበሌዎች 2.8 ሚሊዮን ሕዝብ የመጠጥ ውኃ ይፈልጋል።

ድርቁ በቦረና እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች ባሉ 14 ወረዳዎች ብቻ 61 ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ማድረጉንም ገልፀዋል።

በእነዚህ አካባቢዎች ከ 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ድጋፍ ይሻሉ የተባለ ሲሆን፤ ከነዚህ ውስጥ 8 ሺህ 244ቱ በአዲሱ ድርቅ ተጠቂ የሆኑ ናቸው ሲሉ ደበበ ዘውዴ ተናግረዋል።

ለሁለቱ ዞኖች 254 ሺህ ኩንታል እህል ለ853 ዜጎች መላኩንም በመግለፅ፤ ለተቀሩት የድርቅ ተጠቂ አካባቢዎች ደግሞ በመደበኛው የሥርጭት መርሃ ግብር እንዲደርሳቸው እየተደረገ ነው ብለዋል።

የተከሰተውን የውኃ ችግር ለማቃለልልም 100 ውኃ ጫኝ ቦቴዎች ውኃ እያሰራጩ እንደሚገኝም ተገልጿል።

በተመሳሳይ በሶማሌ ክልል በ83 ወረዳዎች 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሕዝብ ለውኃ እጥረት መጋለጡ ተሰምቷል። በዚሁ ክልል ከሀምሌ እስከ የካቲት ባለው የድርቅ ጊዜ 864 ሺህ 43 እንስሳት መሞታቸውን ኃላፊው ለራዲዎ ጣቢያው ተናግረዋል።

በሶማሌ ክልል 58 ሺህ 305 ሰዎች በድርቁ እንደተጠቁ የገለጹት ደበበ እነዚህ ሰዎች ወደ ሌሎች ድርቅ ወዳልተከሰተባቸው አካባቢዎች እንዲሄዱ ተደርጓል ብለዋል።

በክልሉ በድርቁ ምክንያት 915 ትምህርት ቤቶች ከትምህርት ሥራቸው ተስተጓጉለዋል ከነዚህም 316ቱ ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል።

በክልሉ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሕዝብ ለምግብ እጥረት መጋለጡን ከእነዚህም እና አጠቃላይ 3 ሚሊዮን 360 ሺህ ሕዝብ የምግብ ድጋፍ እንደሚሻም ተናግረዋል።

መንግሥት በክልሉ ከመስከረም እስከ ጥር ድረስ ለ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሰዎች 530 ሺህ ኩንታል እህል እንዲከፋፈል ተደርጓልም ብለዋል።

በተጨማሪም በ15 ወረዳዎች ለ311 ሺህ ተጠቃሚዎች 255 ሚሊዮን ብር እንዲደራጭ መደረጉንና በአሁኑ ወቅት 159 የውኃ መጫኛ ቦቴዎች ለ 81 ወረዳዎች ውኃ እንዲያሰራጩ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT