STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.8K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
አዲስ አበባ በጉም ተሸፍናለች!

ፎቶ: ከኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የተላከልን

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
ከመቀለ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

Update! On Students Transportation!

1) ኩሓ መለስ ግቢ 2 ባስ የሚሆኑ ተማሪዎች ይቀራሉ ሌሎቹ ትላንትና ዛሬ ተሸኝተዋል

2)ኣሪድ -ዋና ግቢ almost ሁሉም ተማሪ ብጥሩ ሁኔታ ወጥተዋል

3) ዓዲ ሓቂ ግቢ አንድ ባስ ብቻ ነው የተንቀሳቀስው ፡፡በሂደት ላይ

4) ዓይደር ጤና ግቢ እስከኣሁን አልጀመረም ዛሬ እንደሚጀምር ነው እና ሊሎች ግቢም ጥሩ በሚባል የሽኝት መርሃ ግብር ናቸው፡፡

ፎቶ:- አሁን ከሠመራ ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ በዝግጅት ላይ

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
አዲስ አበባ በጉም ተሸፍናለች! ፎቶ: ከኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የተላከልን መረጃዎችን ለማግኘት @NATIONALEXAMSRESULT
አዲስ አበባን የሸፈናት ጉም ምንድነው?
=============
ዛሬ በጠዋቱ መዲናችን አዲስ አበባ ባልተለመደ መልኩ የተለያዩ ክፍሎቿ በጉም ተሸፍነው በቅርብ ርቀት ያሉ ህንፃዎችን ጭምር ማየት እንዲሳነን ሆነናል፡፡ ታድያ እኛም ይህን ክስተት አስታከን ጥቂት ስለ ጉም ልናጫውታችሁ ወደድን፤ አብራችሁን ሁኑ፡፡
ጉም እንደ ማንኛውም ደመና ሆኖ መሬትን የሚነካ መሆኑ ግን ለየት የሚያደርገው ነው፡፡ ይህ ጉም አንዳንዴ ስስ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወፍራም ሆኖ ሊያጋጥመን ይችላል፡፡ ታድያ ጉሙ ወፈር ብሎ ሲገኝ ነው አሻግሮ ማየትን ባስ ሲልም በቅርብ ርቀት መተያየት እስኪያስቸግር ድረስ እይታን በነጭ መጋረጃ የሚጋርደው፡፡ በዚህም ትላልቅ ህንፃዎች፣ ባለ ግርማ ሞገስ ተራሮች እና ሌሎችም ግዙፋን አካላት በቦታው የሌሉ እስኪመስል ድረስ ሙሉ በሙሉ ሊጋረዱ ይችላሉ፡፡
የጉም አፈጣጠር ተኖ ጋዝ የሆነ ውሃ ወደ ፈሳሽነት በሚለወጥበት ጊዜ (Condensation) ሞለኪውሎቹ ተጣምረው እጅግ ጥቃቅን የሆኑና በዚህም ሳብያ በአየር ላይ የሚንሳፈፉ ውሃዎችን ሲፈጥሩ ነው፡፡ ጉሙን የምናየውም በነዚህ ጥቃቅን ፈሳሽ ውሃዎች ምክንያት ነው፤ አለበለዚያ የተነነው ውሃ ጋዝ በመሆኑ ላይታየን ይችል ነበር፡፡
ይህ በእዲህ እንዳለ ግን አንድ ጉም ተፈጥሮ ዙርያችንን ለመክበብ የከባቢያችን አየር እጅጉን እርጥበት አዘል መሆንና በፍተኛ መጠን በተነነ ውሃ የተሞላ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ በተጨማሪም እንደ አቧራ አልያም ሌላ አየሩን የሚበክሉ ጥቃቅን ቁሶችም በአየሩ ውስጥ መገኘት አለባቸው፡፡ በዚህም የተነነው ውሃ በእነዚህ ጥቃቅን ቁሶች ላይ ሆኖ ወደ ፈሳሽነት ይቀየራል፡፡ በጨዋማ የውሃ አካላት አካባቢ ደግሞ የተነነው ውሃ በጨው ብናኞች ላይ ሆኖ ሲቀየር የባህር ጉም (Sea Fog) ተብሎ የሚጠራውን ጉም ይፈጥራል፡፡ ታድያ በአየር ላይ ባለው እርጥበት የሚወሰን ቢሆንም ጉሞች በድንገት ሊከሰቱና በዚያው ፍጥነት ሊሰወሩም ይችላሉ፡፡
በምድራችን የተለያዩ አይነት ጉሞች ሲከሰቱ እናያለን፡፡ እነዚህም እንደሚከተለው ቀርበዋል፤
የራዲዬሽን ጉም፤ በምሽት የሚፈጠር ሲሆን መሬት በቀን ውሎዋ ያጠራቀመችውን ሙቀት ወደ አየሩ ስትለቅ የሚከሰት ነው፡፡ ሙቀቱ ከምድር ወደ አየር በሚሸጋገርበት ጊዜ የውሃ ጠብታዎች መፈጠራቸው ለዚህ ምክንያት ይሆናል፡፡
አድቬኬሽን ጉም፤ ይህ ዓይነት ጉም ደግሞ ሞቃታማና እርጥበት አዘል አየር በቀዝቃዛ አካል ላይ ሲያልፍ የሚከሰት ነው፡፡ እርጥበታማ እና ሞቃታማ አየሩ ከቀዝቃዛው የመሬቱ አየር ጋር ሲነካካ የተነነው ውሃ መልኩን ቀይሮ ፈሳሽ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ይህ ሂደትም በሳይንሳዊ አጠራሩ አድቬክሽን ተብሎ ሲጠራ ብዙውን ጊዜ የትሮፒካል አየር ከቀዝቃዛ የውቅያኖስ ውሃ ጋር ሲነካካ የሚፈጠር ነው፡፡
የሸለቆ ጉም፤ ብዙውን ጊዜ በክረምት ወራቶች ተራራና ሸለቆዎች ውስጥ የሚፈጠር ነው፡፡ አፈጣጠሩም ተራሮች አልያም ሸለቆች ውስጥ የተጠቀጠቀውን አየር እንዳያልፍ አግደው ሲያስቀሩት የሚከሰት ነው፡፡ አንዳንዴ ሁኔታው አደገኛ ሊሆንም ይችላል፡፡ ለምሳሌ ከ90 ዓመታት በፊት በቤልጅየሙ የሚዩስ ሸለቆ ውስጥ የተነነ ውሃ በበካይ የአየር ቁሶች ላይ ሆኖ በመቀየሩ ሳብያ ከ60 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተው ነበር፡፡
የቅዝቃዜ ጉም፤ በተለምዶው ደመና በሸፈናቸው ተራሮች ላይ የሚከተው ይህ ዓይነት ጉም ፈሳሽ የደመና ጠብታዎች በአንድ ቁስ ላይ ቀዝቅዘው ሲቀሩ የሚፈጠር ነው፡፡ ይህ አይነት ቀዝቃዛ ጉም ከአካባቢው ተነስቶ ከሄደ በኋላ ምድሩም ሆነ ዛፎች እና እንደ ሸረሪት ድር ያሉ አካላት ጭምር ስስ የበረዶ ሽፋን ተነስንሶባቸው ልናገኝ እንችላለን፡፡ መሰል ጉሞች ቀዝቃዛና እርጥበታማ አየር ፀባይ ባላቸው እንደ ስካንዲኔቪያ እና አንታርክቲካ ባሉ አካባቢዎች ላይ በብዛት መመልከቱ የተለመደ ነው፡፡
ስለ ጉም ካወራን አይቀር ከጉም ላይ ውሃን ስለመሰብሰብም ጥቂት እንበልዎ፡፡ በተለያዩ ማህበረሰቦች ጉም ሲከሰት ትላልቅ የውሃ ማስቀመጫዎችን ከዛፍ ስር በማስቀመጥ በዛፉ ላይ የሚወርደውን ውሃ በመሰብሰብ ጥቂት ውሃን የማግኘት ባህል ነበር፡፡ አሁን ላይ ታድያ የዘመናችን ባለሙያዎች ውሃን ከጉም ላይ የመሰበሰብ ስልትን በዘመናዊ መንገድ ተግባራዊ አያደረጉ ይገኛል፡፡ ታድያ አንዳንድ አካባቢዎችም ዋነኛ የውሃ አቅርቦታቸውን ከጉሞች ላይ በመሰብሰብ እስከማግኘት ደርሰዋል፡፡

ምንጭ [National Geographic]

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
የ2013 ዓ.ም ኢንተራንስ ፈተና…

ኢትዮጵያ ቼክ እንደዘገበው

የዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ፈተናን የተመለከቱ ግራ መጋባቶችን እንድናጣራ የሚጠይቁ በርካታ መልእክቶችን ተቀብለናል!

ፈተናዎቹ በኦንላይን (online) ነው ወይስ በወረቀት የሚሰጡት በሚል የተፈጠረ ግርታ እንዳለ እና ይህንንም እንድናጣራ በተጠየቅነው መሰረት የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አግኝተን ነበር።

በዚህ ጊዜ ምንም የተወሰነ ነገር እንደሌለ ለኢትዮጵያ ቼክ የተናገሩት የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ረዲ ሽፋ፣ ተማሪዎች ሁለቱንም የመፈተኛ ሁኔታዎች ታሳቢ አድርገው እንዲዘጋጁ መክረዋል።

"ተማሪዎች ፈተናው በኦንላይን ወይም በወረቀት ሊሰጥ እንደሚችል ታሳቢ አድርገው መዘጋጀት ይኖርባቸዋል:: ነገር ግን የፈተናው ጊዜ እየተቃረበ ሲመጣ ይህንን እና ሌሎች ጉዳዮችን ለማጥራት መግለጫ የምንሰጥ ይሆናል" ብለዋል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ረዲ ሽፋ ፈተናዎቹ ጥቅምት አጋማሽ ላይ እንደሚሰጡ እና ፈተናዎቹ የሚሰጡበት ትክክለኛዎቹ ቀናት ጊዜው ሲቃረብ መግለጫ እንደሚሰጥ በተለይ ለኢትዮጲያ ቼክ ገልጸዋል።

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የትግራይ ክልል ተወላጅ ተማሪዎቹን በነገው ዕለት ሊሸኝ ነው

በወልድያ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ 200 ገደማ የትግራይ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች በነገው ዕለት ወደ ሰመራ ዩኒቨርስቲ ሊሸኙ ነው።

ዩኒቨርስቲው ተማሪዎቹን ለመሸኘት የወሰነው፤ ለመጀመሪያ ዓመት እና ነባር የጤና ሳይንስ ተማሪዎቹ ከትላንት ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ እረፍት መስጠቱን በይፋ ማሳወቁን ተከትሎ ነው።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አበበ ግርማ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዛሬ እንደተናገሩት፤ በአካባቢው ባለው ጦርነት የደህንነት ስጋት በመኖሩ ተማሪዎቹ ወደ የቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ከውሳኔ ላይ መደረሱን ገልጸዋል። በዚህም መሰረት በአሁኑ ወቅት በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ የቀሩትን የትግራይ ክልል ተወላጅ ተማሪዎችን፤ በሰመራ በኩል ወደ ትግራይ ለመሸኘት መወሰኑን አስታውቀዋል።

በወልድያ አካባቢ እየተባባሰ የመጣውን ውጊያ በመስጋት የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ግቢውን ለቅቀው መውጣት የጀመሩት ካለፈው ቅዳሜ ሐምሌ 17 ጀምሮ ነበር።

በርካታ ተማሪዎች በራሳቸው ውሳኔ ዩኒቨርስቲውን ለቅቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው መሄዳቸው፤ የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዳስተጓጎለው የወልዲያ ዩኒቨርስቲ አካዳሚክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን መሐመድ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስረድተዋል።

© ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
Calendar for Fresh Regular 2013 Eth Cal. Entry.pdf
415.8 KB
Debrebirehan university calendar for fresh regular 2013 students both 1st and 2nd semester

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
በአዲስ አበባ በሚገኙ አብዛኛቹ የግል ት/ቤቶች የትምህርት ክፍያ ከ40 እስከ 100 ፐርሰንት ጨምሯል።

ፊደል ፖስት ያነጋገራቸው ወላጆች መንግስትን ጣልቃ ይግባ ሲሉ ት/ቤቶቹ ደግሞ ለጭማሪው የዋጋ ንረቱ እንደምክንያት አቅርበዋል።

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የክብር ዶክትሬት ለመስጠት ዛሬ ባካሄደው የሴኔት ስብሰባ አፀደቀ፡፡

በመሆኑም ቴዎድሮስ ካሳሁን ወደ ጎንደር በመምጣት ቅዳሜ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም በተማሪዎች ምረቃ ዕለት ተገኝቶ የክብር ዶክትሬቱን የሚቀበል ይሆናል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙት ዳይሬክቶሬት
ሐምሌ 22/2013 ዓ.ም

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለተማሪዎች በሙሉ
የመደበኛ ትምህርት ይዘት እና ለመደበኛው ትምህርት አጋዥ የሆኑ ከ3 ሺ በላይ ይዘት ያላቸው መፅሃፍትን እና ቪዲዮዎችን የያዘ ኢለርኒንግ ፖርታል ተዘጋጅቷል ፡፡ኢለርኒንግ ፖርታሉ በክፍል ደረጃ ߹በትምህርት ዓይነት እንዲሁም በምዕራፍ ተከፋፍሎ ለአጠቃቀም ምቹ በሆነ መንገድ ተዘጋጅቷል፡፡ስለዚህ ማንኛውም ተማሪ ባለበት ቦታ ሆኖ በ https://elearn.moe.gov.et ድረ-ገፅ በመግባት አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
የትምህርት ቤት የመመዝገቢያ ዋጋ ፦

የትምህርት ቤት የመመዝገቢያ ዋጋ ከወርሀዊ ክፍያ ከ25 በመቶ በላይ እንዳይበልጥ የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን የትምህርትና ስልጠና ጥራት፣ ሙያ ብቃትና ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን አስታውቋል።

የትምህርትና ስልጠና ጥራት፣ ሙያ ብቃትና ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ በሰጡት መግለጫ ትምህርት ቤቶችን ለምዝገባ ከወርሀዊ ክፍያቸው በላይ እንዳያስከፍሉ የሚያስገድድ አሰራር መዘርጋቱን ተናግረዋል።

ትምህርት ቤቶች ለምዝገባ ብቻ ከክፍያቸው በላይ እያስከፈሉ በማስቸገራቸው ምክንያት አሰራሩን መፈተሽ እንዳስፈለገ የጠቆሙት ዋና ስራ አስኪያጇ አዲሱ አሰራር ግን ለዚህ መፍትሄ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

እንደ ወይዘሮ ሸዊት ገለፃ፤ የአገልግሎት ክፍያ ጭማሬን በሚመለከት ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በሚደረግ ስምምነት መሠረት እንደሚሆን ገልፀዋል። #ኢፕድ

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው።

#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 6 ሺህ 574 ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል፡፡

በ87 የመጀመሪያ እንዲሁም በ67 የድህረ ምረቃ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው የሚያስመርቀው፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የውኃ መስኖ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ተገኝተዋል፡፡

#ደብረታቦር_ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ለስምንተኛው ዙር ነው ተማሪዎቹን እያስመረቀ የሚገኘው።

#ቦንጋ_ዩኒቨርሲቲ

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ Batch ተማሪዎች በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ይገኛል።

#ደብረብርሃን_ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ13ኛ ዙር በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያስተማራቸውን በ2ኛ ዲግሪ 231 ተማሪዎችን እና በ3ኛ ዲግሪ አንድ ተማሪ እያስመረቀ ነው።

#ኮተቤ_ሜትርፓሊታን_ዩኒቨርሲቲ

የኮተቤ ሜትርፖሊታን በተለያየ የትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩንቨርሲቲው በዛሬው እለት ያስመረቃቸው በመጀመሪያና ሁለተኛ ድግሪ ወንድ 448 ሴት 135 በድምሩ 583 ተማሪዎች ናቸው።

#ቅድስተ_ማርያም_ዩኒቨርሲቲ

የቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 636 ተማሪዎችን በኦሮሞ ባህል ማዕከል አስመርቋል።

አጠቃላይ ከተመረቁት ውስጥ 322 ወንዶች 314 ደግሞ ሴቶች ናቸው።

#ሀራምቤ_ዩኒቨርሲቲ
ሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 3683 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነዉ።
ዩኒቨርሲቲው ለ18ኛ ዙር ነው ተማሪዎችን እስመረቀ የሚገኘው።

[ኢፕድ፣ ዋልታ፣ አሚኮ፣ የዩኒቨርሲቲዎች ገፅ]

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን የክብር ዶክትሬት ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የክብር ዶክትሬት ሰጠ፡፡ ዩኒቨርሲቲው ዛሬ በይፋ በተከናወነ ስነ ስርአት ለአርቲስት ቴዎድሮስ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም ለአርቲስት አስቴር አወቀ በተመሳሳይ መልኩ የክብር ዶክትሬት መስጠቱ ይታወሳል፡፡

[FBC]

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
"ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የክብር ዶክትሬት የመስጠት ምንም አይነት ሃሳብ የለንም"--- ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ እንደሆነ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች መረጃዎች እየተዘዋወሩ ይገኛሉ።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ በመረጃው ዙሪያ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የውጭ ግንኙነትና ፓርትነርሺፕ ዳይሬክተር የሆኑትን ማንእንዳንተ ሙሉጌታ (ዶ/ር) ጠይቋል።

"የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት የክብር ዶክትሬት ለመስጠት የሚያስባቸው ሰዎች አሉ። ገና በዕጩነት የቀረቡ ሰዎች አሉ፤ ይሁን እንጂ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በዕጩዎቹ ዝርዝር ውስጥ የሉም" ብለዋል። በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የሚዘዋወረው መረጃም ሐሰት መሆኑን ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ 300 በላይ ተማሪዎች ሐምሌ 10/2013 ዓ.ም ማስመረቁ ይታወሳል። ሌላ ዙር የምረቃ ስነ ስርዐት በመስከረም 2014 ዓ.ም መጨረሻ ወይም ጥቅምት 2014 ዓ.ም መጀመሪያ ሊኖር እንደሚችል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

Via Tikvah University

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን የክብር ዶክትሬት ሰጠ አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የክብር ዶክትሬት ሰጠ፡፡ ዩኒቨርሲቲው ዛሬ በይፋ በተከናወነ ስነ ስርአት ለአርቲስት ቴዎድሮስ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም ለአርቲስት አስቴር አወቀ በተመሳሳይ መልኩ የክብር ዶክትሬት መስጠቱ ይታወሳል፡፡…
ቴዲ አፍሮ በኪነ -ጥበብ ላበረከተው ሚና ዛሬ በጎንደር ዩንቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ማእረግ ተሰጥቶታል።

ይሄንንም መልእክት አስተላልፏል;

"በታሪካዊዋና በገናናው ጀግና ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የትውልድ ሃገር በሆነችው የጐንደር ከተማ በተዘጋጀው በዚህ የምረቃት መርሀ ግብር ላይ የታደማችሁ ጥሪ የተደረገላችሁ ክብሯን እንግዶች ክቡራትና ክብሯን በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ በተለይ በዛሬው እለት ከብዙ ድካምና ጥረት በኋላ ፍሬያችሁን ለማየት ለበቃችሁ ተመራቂዎችና የተመራቂ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ የሚል መልክቴን ላስተላልፍ እወዳለሁ

በመቀጠልም በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ከጉኔ ሳይለየኝ ያለ መታከት የረዳኝ ቅዱስ እግዚአብሔርን በታላቅ ትህትና ለማመስገን እወዳለሁ

እንዲሁም በተሰማራሁበት የኪነ ጥበብ ዘርፍ ይህ የክብር ሽልማት ይገባሃል ብሎ በዛሬው እለት በእናተ ፊት እንድቆም ምክንያት ለሆነኝ ለአንጋፋው የጎንደር ዩኒቨርስቲ ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ

በማስከተልም የሕይወት አጋሬ ለሆነችዉ ባለቤቴ አምለሰት ሙጬ እና ለወላጅ አባቴ አቶ ካሳሁን ግርማሞ እንዲሁም ለወላጅ እናቴ ለወ/ሮ ጥላዬ አራጌና ለመላው ኢትዮጵያዊ ወገኖቼ ከፍያለ የአክብሮት ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ

ከእዚህ በማስከተልም በማስተላልፈው አጭር መልክት ንግግሬን እቋጫለው

ሃገራችን ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ የገባችበት ከባድ አጣብቂኝና እጅግ ፈታኝ ሁኔታ በሁሉም ዘንድ የታቀወቀ ቢሆንም እንኳን ነገርግን እናት ከመጨረሻው አስጨናቂ ምጥ በኋላ አዲስ ልጇን አይታ እንደምትደሰተው ሁሉ ሃገራችንም ከገጠማትና ሊገጥማት ከሚችለው ማንኛውም ከባድ አደጋ በደል ወጥታ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አሸናፊ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም
ላለፉት ቀላል ለማይባሉ ዓመታት አገራችንን አስጨንቆ የያዛትና አሁንም ላለችበት ቀውስ የዳረጋት የጐሳ ፖለቲካ አሳብ እንደማንኛውም ፍልስፍናና ሀሳብ ተወልዶ አድጐ አርጅቶና በስብሶ ተፈጥሯዊ ሞቱን ሞቷል

ሰለዚህም ከዚህ በኋላ መላው የሃገራችን ህዝብ በተለይም በተለይም ወጣቶች በጎሳና በዘር እንዲሁም በሃይማኖት ልዩነት ሳትናወጡ ከመቼው ጊዜ በላይ በአንድነትና በፍፁም ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ ስሜት በተጠንቀቅ ፀንታችሁ መቆም ያለባችሁ ወይም ያለብን መሆኑን በአፅኖት ለማሳሰብ እወዳለሁ

እኛ የአዲስቷ የኢትዮጵያ ትንሣኤ የአባቶቻችን ልጆች ኃይላችን ጉልበታችን እና መመኪያችን ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ነው

ራዕያችንም ፍቅር ሠላምና ፍትህ የሰፈነባት
ታላቅ እና ገናና አንዲት ኢትዮጵያን ማየት ነው

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ፍቅር ያሸንፋል"


መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
“በአለት ላይ የተመሠረተው ኢትዮጵያዊነት ዛሬም ጠላቶቹን ያሸንፋል “ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ

የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ኢትዮጵያዊነት የተመሠረተው በአለት ላይ በመሆኑ ዛሬም የገጠሙንን ችግር እናሸንፋለን ብለዋል።

ሚኒስትሩ በጎንደር ዩንቨርስቲ የተማሪዎች የምርቃት መርሃ ግብር ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ለተማሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል ።

”ጠላቶቻችን ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ብለው ቢያሟርቱም እኛ ግን ጠላቶቻችንን አሳፍረንና አስደምመን ግድባችንን ሞልተናል አገራዊ ምርጫውንም በሰላም አከናውነናል ፤በቀጣይም አንድነታችንን አጠናክረን በአገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ጠላቶቻችንን ማሳፈር አለብን” ብለዋል ።

ጥራት ያለው ትምህርት አገርን በዕድገት ጎዳና ይመራል ያሉት ሚኒስትሩ ትምህርት ላይ አትኩረን በመስራት ለችግሮቻችን መፍትሄ ማምጣት ያስፈልጋል ።

ለዚህ ደግሞ ከትርክት ሴራ መውጣት እንደሚገባ ነው ኢንጂነሩ ያሳሰቡት።

ከዚህ በተጨማሪም ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ለክብር ዶክትሬት ተሸላሚው ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን የእንኳን ደስ ያለህ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ በቀጣይም በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ማዜሙን እንዲቀጥል ጠይቀዋል ።

የጎንደር ዩንቨርስቲ በዛሬው ዕለት 6 ሺህ 5መቶ 74 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

[Ethio fm]

መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT