STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#Update

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ በውጭ ሀገር በሳዑዲ አረቢያ ዓለምአቀፍ ትምህርት ቤት የ2012 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ከ2013 ተፈታኞች ጋር ፈተናውን እንደሚወስዱ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አስታውቋል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሪ እንደገለፁት ፥ ፈተናውን በጊዜ መስጠት ያልተቻለው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ነው ብለዋል፤ ከሁለት ወር በኃላ የ2013 ብሄራዊ ፈተና ሲሰጥ አብረው እንዲወስዱ ይደረጋል ሲሉ ተናገርዋል።

ትክክለኛው ጊዜ ባይወሰንም ግንቦት ወይም ሰኔ ላይ ፈተናው ይሰጣል።

የ12ኛ ክፍል ፈተና በውጭ ሀገር ባሉ የኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ትምህርት ቤቶች በመጨረሻ ሰዓት መሰረዙን ተገልጾ ነበር።

ከቀናት በፊት የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ በትግራይ ክልል በፀጥታ ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተና መፈተን ካለባቸው ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱት 2,130 እንደሆኑ ገልፆ የቀሩት ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ከ2013 ተፈታኞች ጋር ከሁለት ወር በኃላ ፈተናውን እንዲፈተኑ እንደሚደረግ መግለፁ አይዘነጋም


#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ ለሆኑ የተጣሩ መረጃዎች እና ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
#ቅሬታ #NEAEA የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2012 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤትን አስመልክቶ ቅሬታ ካላቸው/አቤቱታ ካላቸው ከሰኞ መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ማቅረብ እንደሚችሉ አሳውቋል። #SHARE መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ ለተጨማሪ ተማሪ ነክ ለሆኑ የተጣሩ መረጃዎች እና ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT
የብሔራዊ ፈተና online የቅሬታ ማቅረቢያ ቅጽ ይህ ነው።

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSd2taZnPEhGPldTwTIx87tnYfEhYPkCWHnm3eRWjRhnD-FtTg/viewform

ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ከ27 ጀምሮ ቅሬታ እንዲያቀርቡ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል። ቅሬታ ያላቹህ ተማሪዎች መጠይቁን በሚገባ መሙላት አለባችሁ፡፡

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ ለሆኑ የተጣሩ መረጃዎች እና ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
አንዱን ብቻ መርጠን አመጣነው እንጂ ከኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እጅግ በጣም ተደጋጋሚ መልዕክቶች ደርሰውናል

ሰላም ሰላም እንደት ናችሁ
የኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርስቲ ስድስት የትምህርት አይነቶችን በስድስት ተከታታይ ቀን ለመፈተን ፕሮግራም አውጥቶ ክላስ ነገ ጨርሰን ከሰኞ እስከ አርብ ያለምንም ክፍተት ሊፈትኑን ነው እኛም የሰሚ ያለህ ብንል የሚሰማን አጥተናል ዛሬም ከድፓርትመንት እስከ ም/ፕሬዝዳንት ብንሄድም ፍትህ አላገኘንም እባካችሁን ይህንን ጉዳይ ጠይቁልን እባካችሁ እባካችሁ


@NATIONALEXAMSRESULT
የ2012 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት በአጭር ጊዜ ነው ይፋ የተደረገው ፥ ፈተናው እንዴት በዚህ ፍጥነት ታርሞ ይፋ ሊሆን ቻለ ?

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶ/ር ዲለሞ ኦቶሬ በትላንትና ምሽት የቢቢሲ ሬድዮ ስርጭት ላይ ቀርበው ከላይ በተነሳው ጥያቄ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እሳቸው እንዳሉት የመጀመሪያው ምክንያት በሰላም መጠናቀቁ ነው። ፈተናው በሰላም ባይጠናቀቅ ኖሮ የሚጣራ ጉዳይ፣ በፖሊስ የተያዘ ጉዳይ፣ የዝርፊያ ሁኔታ ስለሚኖር የእርማቱ ጊዜ እንዲዘገይ ያደርገዋል ብለዋል።

ሁለተኛው የሰዓት አጠቃቀም ሲሆን፥ ፈተናው ሲታረም የነበረው በፈረቃ 24 ሰዓት ነው። ተማሪዎች በፈተናው መዘግየት ስለተጎዱ ሌላው ቢቀር ውጤቱ በቶሎ ይገለፅ የሚል አቋም ተወስዶ ነው ፈተናው የታረመው ሲሉ ገልፀዋል።

ፈተናውን ለማረም ምንም አይነት አዲስ ቴክኖሎጂ በትግበራ ላይ ያልዋለ ሲሆን እንደከዚህ ቀደሙ በDRS ሲስተም (በማሽን) ነው የታረመው አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል የ2013 ፈተና በኦንላይን እንዲሰጥ ውጤቱም እዛው በኦንላይ እንዲታወቅ የሚደረግበትን ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።

ከ2013 የፈተና ዝግጅት ጋር በተያያዘ ፦

- የቀረው የታብሌት መግባት ብቻ ነው።

- ታብሌቶቹ ከሆንግኮንግ የሚመጡ ሲሆን በኮቪድ-19 ምክንያት አልገቡም።

- ወደ900 ሺህ ተማሪ ስለሚፈተን፤ 900 ሺህ ታብሌት እንዲመጣ እየተደረገ ነው።

- ለሌላ ዓመት ተማሪዎች ታብሌቱን በአግባቡ እንዲቀመጥ ተደርጎ እንዲጠቀሙበትም ማድረግ ይቻላል።

- ከታብሌት ውጭ ሌላው ዝግጅት ያለቀ ነው። ላፕቶፖች ገብተዋል፣ ኢንተርኔት የሚገኝበት ቴክኖሎጂ በየፈተና ጣቢያው ተተክሏል።

Via BBC Amharic

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ ለሆኑ የተጣሩ መረጃዎች እና ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
አንዱን ብቻ መርጠን አመጣነው እንጂ ከኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እጅግ በጣም ተደጋጋሚ መልዕክቶች ደርሰውናል ሰላም ሰላም እንደት ናችሁ የኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርስቲ ስድስት የትምህርት አይነቶችን በስድስት ተከታታይ ቀን ለመፈተን ፕሮግራም አውጥቶ ክላስ ነገ ጨርሰን ከሰኞ እስከ አርብ ያለምንም ክፍተት ሊፈትኑን ነው እኛም የሰሚ ያለህ ብንል የሚሰማን አጥተናል ዛሬም ከድፓርትመንት እስከ…
የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ……

የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፋይናል ፈተና በተከታታይ ለ7 ቀናት ልንፈተን አይገባም ሲሉ ቅሬታ ማቅረባቸውን እና ቅሬታቸውን ማቅረባችን ይታወሳል።

ይሁንና ዩኒቨርሲቲው ይባስ ብሎ ከተማሪዎቹ ቅሬታ በባሰ መልኩ ረቡዕ እና አርብ ሁለት ሁለት ትምህርቶችን ጠዋት እና ከሰአት እንዲፈተኑ ሰኞ ማክሰኞ እና ሐሙስ ደግሞ አንድ አንድ ትምህርት እንዲፈተኑ ወኖ ቁጭ ብሏል።

የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረትም ቅሬታውን ወደ አካዳሚክ ጉዳዮች እያቀረበ ይገኛል፡፡

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ ለሆኑ የተጣሩ መረጃዎች እና ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
በኤርትራ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶች ተከፈቱ❗️

በመላ ሀገሪቱ ትምህርት ቤቶቹ የተከፈቱት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችሉ ስርዓቶች በመዘርጋት መሆኑን ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የመማር ማስተማር ሂደቱ በክፍል ውስጥ መጨናነቅን መቀነስ በሚያስችል መልኩ በሶስት ፈረቃዎች እንደሚሰጡም ተገልጿል።

አካባቢያዊ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ቁጥጥር ተግባራዊ እንደሚደረግም ነው ሚኒስትሩ ያስታወቁት።

ኤርትራ ከኮሮና ቫይረስ መከሰት በኋላ አገልግሎት አቁመው የነበሩ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን ባለፈው ሳምንት ወደ ስራ ማስገባቷ የሚታወስ ነው


#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ ለሆኑ የተጣሩ መረጃዎች እና ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
በቅዱስ ፓውሎስ ሆስፒታል ሕክምና ለመማር ለምትፈልጉ ዘንድሮ ውጤታችሁን ላወቃችሁ ተፈታኝ ተማሪዎች የወጣ ማስታወቂያ

የምዝገባ መስፈርቶች

📌For Afar, Borna zone (Oromia ) Benshagnul Gumze, Gabmbella, Somali, South Omo zone (SNNP), Wagemira Zone (Amhara) and West Omo Zone ( SNNP): 525 and above

📌For Addis Ababa and other regions: For Male 575 and above and for female 550 and above

📌The transcript average mark from from 9th -12th should be 80 and above High School transcript from 9th-12th grade should be uploaded

📌EHEEE result printout that shows clear admission number should be uploaded

📌Applicants should pay 50 birr registration fee and upload the receipt.

📌Additional copy of all necessary educational documents should be uploaded

📌Application fee of 50 birr should be paid and uploaded

🧿የመወዳደሪያ ፈተናው

፨Aptitude, Situational judgment testing and accounts 55%
Multiple mini interview (20%) (only for short listed applicant’s) Academic records accounts 25% (Transcript 5 % and EHEEE result 20%)

፨The maximum intake capacity of the college is 80 students

📌Written examination will be held on Sunday April 11, 2021GC

🏦Bank Account number of the college: Commercial Bank of Ethiopia, St. Paul's Hospital Millennium Medical A/C Number 1000208431068[note: make sure you fulfil all admission requirements before you make payment]

📌Application deadline is Thursday, April 8, 2021 at 6PM (12 o’clock local time).

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ ለሆኑ የተጣሩ መረጃዎች እና ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
የስፖርት እንቅስቃሴዎች በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲስፋፉ የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈረመ



መጋቢት 25/2013 - በየደረጃው ባሉ የትምህርት ተቋማት የስፖርት እንቅስቃሴዎችን ለማስፋፋት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ዛሬ በአዳማ ከተማ ተፈርሟል።

የስምምነት ሰነዱን የተፈራረሙት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ እና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር ናቸው።

ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ምቹ መሆን እንዳለባቸው የገለጹት፣ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ንቁና ጤናማ ትውልድ ለማፍራት ስፖርት መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል።
ስፖርትና ትምህርት ተነጣጥለው መታየት የለባቸውም ሲሉም ተናግረዋል።

የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር በበኩላቸው፣ ስምምነቱ በትምህርት ቤቶች ስፖርትን ለማስፋፋት እንደሚያግዝ፣ ውጤታማ ታዳጊዎችን ለማፍራትና የማዘውተሪያ ቦታዎች በትምህርት ቤቶች በብዛት እንዲገነቡ ለማድረግ እንደሚረዳ ገልጸዋል።

Via walta

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ ለሆኑ የተጣሩ መረጃዎች እና ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
የተፋጠነ የትምህርት ፕሮግራምን ተቋማዊ በሆነ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ ነው።


የትምህርት ሚኒስቴር የተፋጠነ ትምህርት ፕሮግራምን ተቋማዊ በሆነ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው የተፋጠነ የትምህርት ፕሮግራም መደበኛ ትምህርትን በተለያየ ምክንያት ላላገኙ ዜጎች ሁለተኛ የትምህርት እድልን የሚፍጠር አማራጭ ፕሮግራም መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የተፋጠነ የትምህርት ፕሮግራም ተቋማዊ በሆነ መልኩ መተግበር ሰዎች በሁሉም ቦታና ሁኔታ የሚማሩበት እና ለትምህርት ጥሩ እሳቤ ያለው የሚማር ማህበረሰብ የመፍጠር ጉዳይ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል፡፡

የተፋጠነ የትምህርት ፕሮግራም የመደበኛ የትምህርት እድል በተለያየ ምክንያት ያላገኙ እድሜያቸው ከ9 እስከ 14 ዓመት የሆናቸው ህፃናት ተጠቃሚ የሚሆኑበት አማራጭ ፕሮግራም ነው፡፡

ፕሮግራሙ የማስተማር ስነ-ዘዴን በማሻሻል፣የተቀናጀ ስርዓተ ትምህርት በማዘጋጀት እንዲሁም የምዘና ስርዓቱን ከነባራዊ ሁኔታው ጋር ታሳቢ በማድረግ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የሚያስችል መሆኑንም በመድረኩ ተገልጿል፡፡

የተፋጠነ የትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች በሳምንት 5 ቀን ከግማሽ እንዲሁም በቀን ለ7 ሰዓት የሚማሩበት የትምህርት ፕሮግራም ነው፡፡

ፕሮግራሙ ባለፉት 4 ዓመታት በሙከራ ደረጃ በተለያዩ ክልሎች ተግባራዊ ተደርጎ ውጤታማና የተሻለ አማራጭ እንደነበር ተገልጿል።

የምክክር መድረኩን የትምህርት ሚኒስቴር ከጄኔቫ ግሎባል ጋር ያዘጋጁት ሲሆን በቀጣይ ውይይት ከተደረገበት በኋላ በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡

Via MOE

@NATIONALEXAMSRESULT
#ASTU #AASTU መግባት ለምትፈልጉ ተማሪዎች

ኢንጂነሪንግ

፨ለታዳጊ ክልሎች

415 እና ከዚያ በላይ ለወንዶች
410 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች

፨ለሌሎች ክልሎች እና ለአዲስ አበባ

420 እና ከዚያ በላይ ለወንዶች
415 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች

አፕላይድ ሳይንስ

፨ለታዳጊ ክልሎች

400 እና ከዚያ በላይ ለወንዶች
395 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች

፨ለሌሎች ክልሎች እና ለአዲስ አበባ

405 እና ከዚያ በላይ ለወንዶች
400 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች
የምዝገባ ጊዜ፡-
• ከመጋቢት 26/2013 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 02 ቀን 2013 ዓ.ም
ምዝገባው የሚጠናቀቀው፡-
• ሚያዝያ 02 ቀን 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
የምዝገባ ቦታ፡
• የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online)
www.aastu.edu.et; www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ ለሆኑ የተጣሩ መረጃዎች እና ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
የተማሪዎችን ቅበላ እና ድልደላ የሚያስተዳድርበት ሥርዓት ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል !

የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችን ቅበላና ድልደላ የሚያስተዳድርበት ሥርዓት ማዘጋጅቱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ዋና ዳይሬክተር ተሻለ በሬቻ ለኢፕድ እንደገለፁት፣ ዩንቨርሲቲው የተማሪዎችን ቅበላና ድልደላ የሚያስተዳድርበት ሥርዓት አዘጋጀቶ ለኢፊድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲፀድቅ አቅርቧል።

በዚህም በቅርቡ ፀድቆ ዩንቨርሲቲው ተማሪዎችን መቀበል እንደሚጀምር ገልጿል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ፤ ዩንቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን መቀበል የሚጀምር ሲሆን ተማሪዎቹ በኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የሚሰጥ የመግብያ ፈተናም እንደሚሰጣቸው ገልፀዋል።

በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ተቀብሎ በመጀመሪያ ዲግሪ እንደሚያስተምርም ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

Via #EPA

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ ለሆኑ የተጣሩ መረጃዎች እና ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
ከዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት የተላለፈ መልዕክት

ለዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፤ የመግቢያ ቀን በአንድ ሳምንት ስለመራዘሙ።

ውድ ተማሪዎቻችን፤ ወደ ዩኒቨርስቲያችን የመግቢያ ቀን ወደ ሚያዝያ 5 -7/2013 የተራዘመ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን።

ከሰላምታ ጋር!!!

የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ረጂስትራር
ፅ/ቤት::

የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆናችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት የሚያስተላልፋቸውን መልዕክቶች በ @adigratuniversitystudents በኩል ማግኘት ስለምትችሉ ቻናሉን መቀላቀል ትችላላችሁ፡፡

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ ለሆኑ የተጣሩ መረጃዎች እና ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
የቻናል ጥቆማ ⭕️

📚 ንባብ የምትወዱ ከሆን ምን አልባት የሚጠቅሞትን FILEs በPDF መልኩ፤ ከእኛ ሊያገኙ ይችላሉ።

📚 የአማርኛ እና በኢንግሊዘኛ ቋንቋ "International Best Sellers" ተብሎ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የተወደዱ ጨምሮ በርካታ መጽሐፍት እኛ ጋር በነጻ ያገኛሉ።

📚 በእርግጠኛነት ቻናሉን ይወዱታል፤ ቤተሰብ ይሁኑን❗️

ይሄው ሊንኩ 👇👇👇

https://t.me/joinchat/0btKCYSJmxgxYTFk
ለልደት፣ ለምርቃት እና ለማንኛውም አይነት ስጦታ🛍 #ሰዓቶችን_በሚፈልጉት_ሰው_ፎቶ ወይም በድርጅት ሎጎ እንሰራለን⌚️ በብዛት ለሚያዝ እና ለማከፋፈል ለሚፈልጉ ቅናሽ እናደርጋለን።
#ባለ_ቆዳ 300
#ባለ_ብረት 400

🔗 #በተጨማሪም_የተለያዩ_ለስጦታ_የሚሆኑ ኩባያዎች ፣ ትራስ ፣ ቲሸርት ፣ የግድግዳ ሠዓቶችን እና ሌሎችንም በፈለጉት ፎቶ አሳምረን እንሠራለን፡፡

🛍Order us via Telegram @habeshagifts1 📩
or Call 📞 0935199954
አድራሻ፡- አውቶቡስ_ተራ_መሳለሚያ ወይም ጀሙ mina mall ህንፃ ወይም ሜክሲኮ
⚠️ ወደ ክልል ከተሞች በፖስታና በሹፌር በታማኝነት እንልካለን።

For more products
#JOIN_OUR_CHANNEL👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE_-T4p_QITNQ151fA
ማስጠንቀቂያ‼️

😷 <<የመተንፈሻ ቬንትሌተሮች አልቀዋል>> የሚል መልዕክት በተንቀሳቃሽ ስልኮች እየመጣ ነው።

😷 ብዙዎች የሚወድዷቸውን አጥተዋል፤ ብዙ ሰፈሮች ውስጥ ድንኳኖች እየተተከሉ ነው።

😷ብዙ ጓደኞቻችንን፣ ወንድሞቻችንን ይሄ ክፉ በሽታ ተሰቃይተው ድነዋል። ብዙዎች ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ትግል ላይ ናቸው።

😷አሁን ላይ ሽማግሌዎቻችንን በብዛት እየነጠቀን፤ ወጣቶች እና ጎልማሶች እየሞቱ ነው።

Corona is Real!!

ለእራሳችንም፣ ለምንወዳቸውም እንጠንቀቅ፣ ማስክ በአግባቡ እንጠቀም፣ ሳኒታይዘር መጠቀም አሊያም እጃችንን መታጠባችንን አንርሳ!)
#share

Team: @NATIONALEXAMSRESULT
የኢጋድ ዩንቨርሲቲዎች ጉባኤ በጅግጅጋ ዩንቨርሲቲ ይካሄዳል
------------------------
መጋቢት 26/2013 - የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዩኒቨርሲቲዎች ጉባኤ በጅግጅጋ ዩንቨርሲቲ ይካሄዳል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቀጣይነት ላለው የሃገር እድገት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ የሚዳሰስበት እና ከኢጋድ አባል ሃገራት የተውጣጡ ዩንቨርሲቲዎች የሚሳተፉበት ጉባኤ ከሰኞ መጋቢት 27 ጀምሮ ለሁለት ቀናት በጅግጅጋ ዩንቨርሲቲ ይካሄዳል።

ከስምንቱ የኢጋድ አባል ሃገራት የተውጣጡ 20 ዩንቨርሲቲዎች የሚካፈሉበትን ጉባኤ የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ ይከፍቱታል ተብሎ ይጠበቃል።

በጉባኤው አባል ሃገራቱ ላይ እየተስተዋሉ ስለሚገኙ የዜጎች ስደት እና መፈናቀል ይመከራል። በተለያዩ ዩንቨርሲቲዎች የተሰሩና ትኩረታቸውን ፍልሰት ላይ ያደረጉ ጥናቶች ይዳሰሱበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ይኸው 20 የኢጋድ ዩንቨርሲቲዎች የሚታደሙበት ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በጅግጅጋ ዩንቨርሲቲ የሚካሄድ መሆኑም ታውቋል።

Via walta


#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ ለሆኑ የተጣሩ መረጃዎች እና ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ምገባ ከመንግሥት የሚሰጠው በጀት የወቅቱን የገበያ ሁኔታ ያገናዘበ ስላልሆነ ማስተካከያ እንዲደረግበት ተጠየቀ፡፡

ለአንድ ተማሪ በቀን 13 ብር ሒሳብ በተያዘ በጀት ዩኒቨርሲቲዎች ለዘመናት በቀን 3 ጊዜ ተማሪዎችን ሲመግቡ ቆይተዋል፡፡

ዘንድሮ ግን በጀቱ አሁን ካለው የገበያ ሁኔታ ጋር ስለማይጣጣም ሊስተካከል ይገባል የሚል ማሳሰቢያ የሰጠው በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ነው፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ማሳያ ይሆነኛል ያላቸውን 10 ዩኒቨርሲቲዎች በአካል ተገኝቶ በመመልከትና ከዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ ጋር በመነጋገር ሊስተካከሉ ይገባቸዋል ያላቸው የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየመከረ ይገኛል፡፡

በዩኒቨርሲቲዎች የምግብ አቅርቦቱ አለበት የተባለው ችግር የበጀት ማነስ ብቻ አይደለም፡፡እንደ ዘይት፣ ዱቄት፣ ሥጋ እና ሌሎችም የፍጆታ አቅርቦቶች በወቅቱ ስለማይቀርቡ የሚቸገሩ ዩኒቨርሲቲዎች ብዙ መሆናቸው ይሰማል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የወጣውን መመሪያ አተገባበር በተመለከተ በዩኒቨርሲቲዎች ታዝቤአቸዋለሁ ያላቸውን ነጥቦችም አንስቷል፡፡አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በራሳቸው ላቦራቶሪ አቋቁመው ለአካባቢው ማኅበረሰብ ጭምር የኮቪድ 19 ምርመራ የሚሰጡ አሉ ብሏል፡፡የሳኒታይዘርና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ አምርተው የሚያቀርቡ ዩኒቨርስቲዎችም እንዳሉ መስክረዋል፡፡

በሌላ በኩል ግን የውሃ አቅርቦት ችግር፣ ማስክ በአግባቡ አለመጠቀምና የመሳሰሉት በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች የታዩና ወረርሽኙን ለመግታት የሚወሰደውን እርምጃ ወደኋላ የሚመልሱ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ ብሏል ቋሚ ኮሚቴው፡፡

በተጨማሪም የኮቪድ 19 ለይቶ ማቆያ ሆነው በነበሩ ዩኒቨርስቲዎች የመኝታ በዌት መገልገያ ቁሶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ በጥገና ከተመደበላቸው በጀት በላይ ወጪ እንዲያወጡ መገደዳቸውንም ተሰምቷል፡፡

በተጠቀሱትና በሌሎችም የማስተካከያ መፍትሄ ለሚሹ ጉዳዮች መላ ለማበጀት ቋሚ ኮሚቴው ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንቶች ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የዘገበው ሸገር ኤፍ ኤም ነው፡፡

Via Sheger FM 102.1

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ ለሆኑ የተጣሩ መረጃዎች እና ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
የኢትዮጵያ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምዝገባ ጀመሩ።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሌጂ እና አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በፈተና ለመግባት ለሚፈልጉ ምዝገባው መጀመሩ ተገልጿል።

የመመዝገቢያ መስፈርቶች ፦

ተዳጊ ክልሎች (አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ) ፦

- ኢንጂነሪንግ : ወንድ 415 እና በላይ ፤ ሴት 410 እና በላይ
- አፕላይድ ሳይንስ : ወንድ 400 እና በላይ ፤ ሴት 395 እና በላይ

ሌሎች ክልሎች ፦

- ኢንጂነሪንግ : ወንድ 420 እና በላይ ፤ ሴት 415 እና በላይ
- አፕላይድ ሳይንስ : ወንድ 405 እና በላይ ፤ ሴት 400 እና በላይ

የምዝገባ ጊዜ ፡- ከመጋቢት 26/2013 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 02 ቀን 2013 ዓ.ም ሲሆን ምዝገባው ሚያዝያ 02 ቀን 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል።

ለምዝገባ የወጣውን መስፈርር የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ www.astu.edu.et / www.aastu.edu.et/ ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቀን ሚያዚያ 8 ቀን 2013 ዓ.ም (ከጠዋቱ 1፡30 እስከ 6፡00 ፣ ከሰዓት ከ8፡00 እስከ 11፡00 ድረስ ይሆናል) ተብሏል።

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ ተማሪ ነክ ለሆኑ የተጣሩ መረጃዎች እና ዜናዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
የቻናል ጥቆማ ⭕️

📚 ንባብ የምትወዱ ከሆን ምን አልባት የሚጠቅሞትን FILEs በPDF መልኩ፤ ከእኛ ሊያገኙ ይችላሉ።

📚 የአማርኛ እና በኢንግሊዘኛ ቋንቋ "International Best Sellers" ተብሎ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የተወደዱ ጨምሮ በርካታ መጽሐፍት እኛ ጋር በነጻ ያገኛሉ።

📚 በእርግጠኛነት ቻናሉን ይወዱታል፤ ቤተሰብ ይሁኑን❗️

ይሄው ሊንኩ 👇👇👇

https://t.me/joinchat/0btKCYSJmxgxYTFk