STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.7K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በር ስለተዘጋባቸው በአጥር ለመውጣት ተገደዋል።



@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
ብዙ ቤተሰቦቻችን በ @INFONERCBOT ላይ በፎቶ አስደግፈው ያሉበትን ሁኔታ እየላኩልን ነው። ሌሎቻችሁም ላኩልን።

ድምጻችሁን እናሰማለን
Team
@NATIONALEXAMSRESULT
ሚዲያዎች የደበቁትን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተሰራ ያለው ጉድ ቤተሰቦቻችን እውነቱን እንዲህ አጋልጠውታል

ደርብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ መረጋጋት ርቋታል፡፡ ስለደብረ ታቦር የሚያወራም ድምጻቸውንም የሚያሰማላቸው ጠፍቷል፡
ተማሪዎች በቡድን ሆነው እየተደበደቡ ነው፡፡ ዛሬ ካፌ ውስጥ ችግር ነበር፡፡ class ቆሟል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ተማሪውን አረጋግቼ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ለመግባት እየጣርኩ ነው ቢልም ነገር ግን ጭራሹኑ ተማሪውን ከጊቢ አትወጡም ብሎ ይዞ በውስጥም ምንም ጥበቃ ሳያደርግ ተማሪዎች እየተደበደቡ ነው፡፡

የተማሪው ድምጽ ይሰማ!!!


@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ

ሚዲያዎች የደበቁት የዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ጉድ

ተማሪዎች በሜዳ ላይ በወታደር እየተጠበቁ ማደር ከጀመሩ 4 ቀን አለፋቸው። ቀርቦ የሚያወያያቸው እና መፍትሔ የሚሰጣቸው አቤት ባይ አካል አጥተው እየተሰቃዩ ነው።

የተማሪው ድምጽ ይሰማ!!!

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ

ሚዲያዎች የደበቁት ጉድ


በሌሎች ጊቢዎች ያለው ችግር ስጋት የፈጠረባቸው ትንሽ የማይባሉ ተማሪዎች ከጊቢ ውጪ ማደር ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ የትኛውም ሚዲያ ግን የእነዚህን ተማሪዎች ሰቆቃ ሲዘግብ አልተስተዋለም።

የተማሪው ድምጽ ይሰማ!!!

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ

ሚዲያዎች የደበቁት የዩኒቨርሲቲ ውስጥ ጉድ


ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ብታላቅ ሰቀቀን ውስጥ ናቸው፡፡ ከጊቢ እንዳይወጡ እና ወደ ቤታቸው እንዳይመጡ ከጊቢ መውጣት አትችሉም ተብሎ የጊቢው በር ተዘግቷል። ቤተሰቦቻቸው እንደተጨነቁ እና እነርሱም ወደ ቤተሰቦቻቸው መሄድ እና ከስጋት ነጻ መሆን እንደሚፈልጉ እየተናገሩ ነው።

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU)

ሚዲያዎች የደበቁት የዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ጉድ


ASTU የሚማሩ ቤተሰቦቻችን ይህንን ብለውናል።

"Astu ሳምንቱን ሙሉ ትምሮ ዝግ ነው ምክንያቱ ደግሞ በሌሎች ዩንበርሲቲ እየታየ ያለው የሰላም ችግር ወንድሞቻችን እዛ እየተሰቃዩ እዚህ እኛ በሰላም የምንማርበት ምንም ምክንያት አይኖም በማለት ነው ከነገ ወዲያ ማለትም ሰኞ እለት የሚድ ፈተና የሚሰጥበት ፕሮግራም ነበረ እስካሁንም ፈተና ይራወም አይራዘም ዩንበርሲቲው ምንም አይነት መረጃ አልሰጠም እኛም ቁርጡን ለማወቅ ነገ ግቢ እንገባለን ከገባን በኋላ የሚፈጠረውን እግዚአብሔር ይወቅ"

የተማሪው ድምጽ ይሰማ!!!


@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
ባህርዳር ዪኒቨርሲቲ

ሚዲያዎች የደበቁት የዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ጉድ

ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በተለይም ዘንዘልማ እጅግ በጣም ብዙ ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው ወጥተዋል። አሁንም ጊቢውን ለቀው መውጣት የሚፈልጉ እጅግ በጣም ብዙ ናቸው። በዛ ያሉ ቤተሰቦቻችን እንደነገሩን የክልሉ ልዩ ኃይል ጊቢው ውስጥ ከፍተኛ ቁጥጥር እና የማረጋጋት ስራ እየሰራ ቢሆንም ነገር ግን ተማሪዎቹ ይህም ስጋታቸውን አልቀነሰውም። ዛሬ ደግሞ "ምሽት ላይ እንበጠብጣለን" የሚል ማስፈራሪያ ግቢው ውስጥ ስለተናፈሰ በተማሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

የተማሪው ድምጽ ይሰማ!!!

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
ዩንቨርስቲዎቻችን እንዴት ሰነበቱ ??

#ሀዋሳ_ዩንቨርስቲ

ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ዘንድ በማን እንደተሰራጨ ለጊዜው ባልታወቀ አካል ተማሪዎች የሚያሸብር ፁሁፍ በብሄር ተከፍሎ ለሁለት ወገን ብቻ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ተማሪዎች ጠቁመዋል።

ይህ መረጃ ከተሰራጨበት ሰዐት አንስቶ ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ተማሪዎች ለየኔቲዩብ ተናግረዋል።

#ድሬደዋ_ዩንቨርስቲ

የድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ተማሪ ከፎቅ ወድቆ ሞተ የሚል ዜና ዩንቨርስቲው በፌስቡክ ገጹ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ተማሪዎች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ነግረውናል።

ከዚው ጋር በተያያዘ የዩንቨርስቲው ተማሪዎች ከግቢው ለቀን እንወጣለን ቢሉም ዩንቨርስቲው መከልከሉን ተከትሎ ተማሪዎች በአጥር ዘለው መውጣታቸውን ሰምተናል።

#ወልዲያ_ዩንቨርስቲ

ተማሪዎች ዛሬ ወደ ቤታችን መልሱን እያሉ ይገኛሉ ግቢው በመከላከያ እየተጠበቀ ይገኛል። የፊታችን ሰኞ ትምህርት እንደሚጀመር ዩንቨርስቲው ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ገልፅዋል።

#አዳማ_ዩንቨርስቲ

አዳማ ዩንቨርስቲ የፊታችን ሰኞ Mid Exam ይጀምራል ብሏል ነገር ተማሪዎች ትምህርት ካቆሙ አንድ ሳምንት አልፏቸዋል፤ ተማሪዎቹ ግን ስጋት ውስጥ ሆነን ስለ ትምህርታችን እናስብ ወይስ ስለ ህይወታችን በማለት ዩንቨርስቲ ያወጣውን የፈተና ፕሮግራም ኮንነዋል።

#ደብረብርሀን

እንደሚታወቀው ደብረብረሀን ዩንቨርስቲ ዛሬ የአንድ ተማሪ ህይወት አልፏል። ከዚህ ክስተት በኋላ ግን ዩንቨርስቲው ሰላም መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።ነገር ግን ተማሪዎች እንደነገሩን ከሆነ ነገ ምንም እንደሚከሰት መገመት አንችልም ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ነን ብለውናል።
___________________________
በዚህ መሰረት ችግር የሚታይባቸው የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል ዩንቨርስቲዎች መሆናቸው ለማወቅ ችለናል ነገር ግን ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ችግር ባይኖርም የተበተነው መረጃ ተማሪዎች ላይ ስጋት ጥሏል።
@nationalexamsresult
@nationalexamsresult
@nationalexamsresult
#HawassaUniversity

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከ08-12/2012 ዓ/ም ትምህርት አይኖርም በማለት አንድ አንድ ተማሪዎች የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ደርሼበታለሁ፤ እንዲያህ ያለ ነገር እያሰራጩ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ሲል አስጠንቅቋል። በተሰራጨው የተሳሳተ መረጃ ግቢው ለቀው እየወጡ ያሉ ተማሪዎች እንዳሉ አረጋግጠናል ብሏል ተቋሙ። የትምህርት ስርዓቱ እንደማይቋረጥ የገለፀው ዩኒቨርሲቲው ግቢውን ጥለው የሄዱ ተማሪዎችም በትምህርታቸው ላይ በሚደርስባቸው እክል ሃላፊነቱን እራሳቸው ይወስዳሉ ሲል ገልጿል።

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ

ሚዲያዎች የደበቁት የዩኒቨርሲቲዎች ጉድ


ጅማ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ቤተሰቦቻችን እንደገለጹት ጅማ ዩኒቨርሲቲ main cumpas ብዙ ተማሪዎች ጊቢውን ከቀው ወጥተዋል፡፡ ዛሬም ከሰአታት በፊት ጊቢ ውስጥ ድምጾችን እንደሰሙ እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በጊቢው አካባቢ ሲመላለሱ እንዳስተዋሉ ገልጸውልናል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ምንም እንዳልተፈጠረ እና ተማሪዎችን ወደ ጊቢ የመመለስ ስራ እየሰራሁ ነው ቢልም ተማሪዎች ግን አሁንም ወደ ጊቢ አልተመለሱም፡ በጊቢ ውስጥ ያሉትም በከፍተኛ ሰቀቀን ውስጥ ናቸው፡፡

የተማሪው ድምጽ ይሰማ!!!

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
ድሬዳዋ ዩንቨርስቲ

በዩኒቨርስቲው ትላንት ምሽት በነበረ አለመረጋጋት ቢያንስ 12 ተማሪዎች መጎዳታቸውን የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል። የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ዛሬ እንዳስታወቀው የሞተ ተማሪ እንዳለ ተማሪው የሶስተኛ ዓመት የቴክስታይል ኢንጂነሪንግ ተማሪ መሆኑን ገልጿል።

ተማሪው ከፎቅ ወድቆ መሞቱን ዩኒቨርስቲው ቢገልጽም ዝርዝር ሁኔታው ግን እየተጣራ ነው ብሏል። ተማሪው ጉዳት እንደደረሰበት ዩኒቨርስቲው አቅራቢያ ወደሚገኘው ሳቢያን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለህክምና የተወሰደ ሲሆን ብዙም ሳይቆይ ህይወቱ ማለፉን የሆስፒታሉ የተመላላሽ ህክምና ክፍል አስተባባሪ ዶ/ር አዲስ መስፍን ለዶይቼ ቨለ (DW) ገልጸዋል።

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ

ሚዲያዎች የደበቁት የዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ጉድ

መዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች ወደቤታችን መልሱን እያሉ ተንበርክከው ሲያነቡ። እጅግ በጣም ልብ የሚነካ እና የሚያሳዝን vedio ነው፡፡ ሚዲያዎቻችን ይህንን እንዳላየ አልፈውታል።

የተማሪው ድምጽ ይሰማ!!!

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
ወደቤተሰቦቻቸው ለመሄድ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ አዲስ አበባ የመጡ ተማሪዎችን አውቶቡስ ተራ የሚገኘው አዲሱ ሚካኤል ሄደን አገኘናቸው::

የደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን የመጡበትን እና የሚሄዱበትን አካባቢ እየመዘገበ እየተቀበላቸው ነው:: የአከባቢው ምእመን ሙስሊም እና ክርስቲያን ሳይለይ ከእንባ ጋር እህል ውሃ ሲያቀርብላቸው አይቻለሁ::

ዛሬ ጠዋት ብቻ 11 አውቶቡሶች ሙሉ ተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪ ተሸፍኖላቸው ከጥቂት የኪስ ፍራንክ ጋር ወደየቤተሰቦቻቸው ተሸኝተዋል:: አሁንም በርካታ ተማሪዎች በአጸደ ቤተክርስቲያኑ ተጠልለዋል:: አሁንም ሌሎች በርካቶች ተማሪዎች መንገድ ላይ መሆናቸውንም ነግረውናል::

Via:- Yohannesmekonnen


@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
ዛሬ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ስጋት እና ጥቃት ሸሽተው ወደ አዲስ አበባ የመጡ ተማሪዎች በአውቶብስ ተራ አካባቢ በሚገኘው አዲሱ ቅ፥ሚካኤል ቤተክርስቲያን የቆዩ ሲሆን በመከላከያ ሰራዊት ታጅበው ወደ አካባቢያቸው ተሸኝተዋል፡፡

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
ከላይ የምትመለከቱት ፎቶ የመጀመሪያው ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ (አሁን) ነው። ዩኒቨርሲቲዎች ምን አይነት አቅመ ቢስ ቢሆኑ ነው አንዱ በሞቀ ክፍል ውስጥ አንዱ ሜዳ ላይ በብርድ እንዲያድሩ የሚፈቅዱት? ለመሆኑን እነዚህ ምስኪን ተማሪዎች እንዲህ የሚያሰቃዩ አካላት እነማናቸው? አይጠየቁም? አይነኩም? ህግ እና ስርዓት ለነሱ አይሰራም?
ተማሪዎቻችን በዚህ መልኩ ሲሰቃዩ እና ሲንገላቱብን የፀጥታ ኃይላት እንዴት መቆጣጠር አቃታቸው? ለነዚህ ልጆች ያለሃጢያታቸው፣ ያለበደላቸው መንገላታት ማነው ተጠያቂው? መንግስት የነገ ሀገር ተረካቢ ናቸው፤ የኔም ልጆች ናቸው ካለ ያለውን አቅም ተጠቅሞ አስቸኳይ መፍትሄ ይስጥ። ህዝቡ በጋራ ሆኖ ይህ የምስኪን ተማሪዎች ስቃይ በቃ ሊል ይገባል። ለአንድ ቀን ተማሪዎች እንዲህ በማደራቸው መጠየቅ ያለበት አካል ሁሉ ከላይ እስከ ታች ሊጠይቅ ይገባል።
ሚዲያዎች፣ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶች፣ በተማሪ ስቃይ በዩትዩብ ገንዘብ የምትለቃቅሙ...ሌሎችም እባካችሁ እጃችሁን ከወንድምና እህቶቻችን ላይ አንሱልን። በስቃያቸው አትነግዱ! ከቻላችሁ እኩል ጩሁላቸውና መፍትሄ ፈልጉላቸው ካልሆነም ስቃያቸውን አታብዙት ዝም በሉ!
ተማሪዎች-እባካችሁ በማንም ቅስቀሳ ወደተሳሳተ አቅጣጫ ከመሄድ ተቆጠቡ። እናተ ውጭ ስታድሩ እነሱ በሞቀ ቤታቸው ሆነው ይፅፋሉ፤ አብረዋቹ ለአንድም ቀን እናተ ያያችሁትን ስቃይ አያዩትም። ሀገር ቢተራመስ ሳይውል ሳያድር ይኮበልላሉ እዚህ የምንቀረው እኛና እናተ ብቻ ናችሁ።
@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
"ሁላችንም ወንድማማቾች ነን!"
"ሁላችንም እህትማማቾች ነን!"

የቴሌግራም እና የፌስቡክ ፕሮፋይላችንን ምስል ከላይ ባሉት ምስሎች በመቀየር የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻውን እንቀላቀል!

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ
#Update #ባህርዳር_ዩኒቨርስቲ

ዛሬ የሚገርምህ ከለሊት ጀምሮ ወደ መጡበት አካባቢ ለመመለስ መናኸሪያ የነበሩ ተማሪዎችን ከእያንዳንዱ መኪና በመለየት ካወጡዋቸው በኃላ ወደ ግቢያቸው እንዲመለሱ አድርገዋል እንዲሁም ዛሬ በስልክ እንደሰማሁት በይባብ ካምፓስ 1 ሲኒየር ልጅ ወደ ግቢ ከተመለሰ በኃላ ግቢ ውስጥ ሜዳ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት ነፍሱን እየሮጠ አስመልጦ ሆስፒታል እንደሆነ ነው ማውቀው ።

ደሀ ሁሌም እንደሚጎዳ ያየሁት ማለት ነው የሀብታም ልጆች አሁን በ ፕሌን flight እያደረጉ ነው አየህ አይደል ወንድ ከሆኑ ለምን እንደመናኸሪያው Airportunm አይከለክሉም፡፡
@nationalexamsresult
Via Natnael (info et)
@nationalexamsresult
@nationalexamsresult
መቱ ዩኒቨርሲቲ

ሚዲያዎች የደበቁት የዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ጉድ


"ሰላም ናቹ እኛ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ነን ግቢ ውስጥ ረብሻ ከተነሳ ሳምንት ሆነን በየቦታው ተበትነናል ልብስ ሳንቀይር በብርድ ውጪ ነው ያለነው እስካሁን መፍትሔ የሚሰጠን አካል አላገኘንም"

@NATIONALEXAMSRESULT
https://t.me/joinchat/AAAAAFOUbJV0CPRu9x45bQ

ከመቱ ዩኒቨርሲቲ
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ሳምንት ምንድን ነው የተፈጠረው??
በቪዲዮ የተደገፈ ማስረጃ ደርሶናል👇

@NATIONALEXAMSRESULT