STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.7K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
መቱ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን የሪሚዲያል መርሐግብር ተማሪዎች መቀበል ጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ2016 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደቡ ተማሪዎች ጥር 20 እና 21/2016 ዓ.ም ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ማስተላልፉ ይታወቃል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
🎉Good News for Ethiopian Undergraduate Program Students !

Study in USA! 🇺🇸

⭐️ከፍተኛ ትምህርቶን በአሜሪካ ሀገር እየተከታተሉ የሚሰሩበት ትልቅ ዕድል !

No Prepayment !



Bachelor Degree ✈️

Fast Process

Quality Service

High Visa Ratio

Limited Spot ! Take your spot early live your dream !

🟡🟡Contact us :

🔵 @Gossa07

☎️ +251935343325 / +393444355194

ቴሌግራም ገፅዓችንን መቀላቀል እንዳይረሱ 👇👇👇:

@Ethiogenuine1
@Ethiogenuine1

📍 Address : Addis Ababa, 22, Tsega Business Center, 7th Floor, Office No - H04 .

🌐 Www.Ethio-Genuine-Consultancy.com
እስከ የካቲት 30/2016 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንዲልኩ

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት የተማሪዎቻቸውን ዝርዝር መረጃ እንዲልኩ ጠይቋል፡፡

ፈቃድ በተሰጣቸው የትምህርት መስኮች በ2016 ዓ.ም ተመዝግብው እየተማሩ ያሉ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ እና በ2015 ዓ.ም የተመረቁ ተማሪዎች (የመውጫ ፈተና ያለፉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች) ዝርዝር መረጃን እስከ የካቲት 30/2016 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንዲልኩ ባለሥልጣኑ አሳስቧል፡፡

ይህም የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማስጠብቅ እንዲሁም የተመረቁ ተማሪዎች መጉላላት እንዳይገጥማቸው ባለሥልጣኑ ለሚያከናውናቸው ተግባራት አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል፡፡ #ETA

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ወለጋ_ዩኒቨርሲቲ

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ነቀምት ካምፓስ ከትላንት ጀምሮ የመማር ማስተማር ሂደት ሙሉ ለሙሉ መቋረጡን ዋዜማ ራዲዮ ከምንጮቼ አረጋግጫልምሁ ብላለች። ዩኒቨርሲቲው ሦስት ካምፓሶች ያሉት ሲኾን፣ ከዋናው ግቢ ነቀምት ካምፓስ በስተቀር በሻምቡና ጊምቢ ካምፓሶች መደበኛው የመማር ማስተማር ሂደት እየተካሄደ እንደኾነና በነቀምት ካምፓስ ግን የመማር ማስተማር ሂደቱ መቋረጡን ዘግባለች።

የመማር ማስተማር ሂደቱ የተቋረጠው፣ ሰሞኑን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በመላው ኦሮሚያ ጠርቶታል የተባለውን የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ የማስቆም አድማን ተከትሎ ተማሪዎች አንማርም ብለው በማመጻቸው እንደኾነም ዋዜማ ጨምራ ዘግባለች።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህከምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኮምፐሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለተለያዩ የትምህርት ከፍሎች በህከምና ሙያና ለሌሎች ትምህርት ከፍሎች መምህራንን ምስሉ ላይ ለተዘረዘሩት ከፍት የስራ ቦታ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ የሚያሟሉ ስራ ፈላጊዎችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።

፨ ለተዘረዘሩ የሥራ መደቦች የምታሟሉ የትምህርት ማስረችሁን ይዛችሁ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የኮሌጁ ሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ቡድን በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ማሳሰቢያ :- ተመዝጋቢዎች የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃዎቻችሁን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር አብሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የተሰረዙ ወይንም የተደለዙ ማስረጃዎች ተቀባይነት የላቸውም።

1. ለሥራ መደቡ የተጠየቀው ተፈላጊ ችሎታ ለሥራ መደቡ ተመሳሳይ መሆን አለበት።

2. የፈተና ጊዜ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ ባሉ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ይገለፃል።

3. የስራ ቦታ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሬሚዲያል ፈተና መዘጋጀቱ ተማሪዎቹን ሊያዘናጋ እንደሚችል ተገለጸ።

የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈታናን ማለፍ ላልቻሉ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሬሚዲያል ፈተና መዘጋጀቱ ተማሪዎች አማራጭ እንዳላቸው እንዲያስቡ እንደሚያደርጋቸው እና እንደሚያዘናጋቸው የትምህርት ባለሙያዎች ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቀዋል፡፡

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈታናን ወስደው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ማምጣት ላልቻሉ ተማሪዎች በዩንቨርስቲዎቹ ውስጥ የሬሚዲያል ፈተና መዘጋጀቱ ተማሪዎቹን እንደሚያዘናጋቸው የትምህርት ባለሙያው አቶ ቢኒያም ገ/እየሱስ ተናግረዋል፡፡

ሌላኛው የትምህርት ባለሙያ ዶ/ር አለማየሁ ከበደ የአቶ ቢንያምን ሃሳብ በማጠናከር ተማሪዎቹ አሁን ላይ #ባናልፍም ሬሚዲያል እንወስዳለን በሚል ተስፋ ትምህርታቸው ላይ ትኩረት አያደርጉም ብለዋል፡፡

በድጋሚ ለመፈተን በዩንቨርስቲዎች ውስጥ የሚቆዩት አንድ አመት ቢሆንም መንግስትን ላልተገባ ወጪ የሚዳርግ በመሆኑ ትኩረት ተደርጎበት ከስር ከመሰረቱ ሊሰራ እንደሚገባ ባለሞያዎቹ አመላክተዋል፡፡


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
መቱ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ፕሬዝዳንት ተመድቦለታል።

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት በድሉ ተካ (ዶ/ር) ከጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከያዙት ኃላፊነት በተጨማሪ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሠሩ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) መመደባቸው ታውቋል።

ዩኒቨርሲቲውን ላለፉት አምስት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የቆዩት እንደገና አበበ (ዶ/ር) በፌደራል ደረጃ ለአመራርነት መመረጣቸውን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘ መረጃ ያሳያል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
🎉Good News for Ethiopian Undergraduate Program Students !

Study in USA! 🇺🇸

⭐️ከፍተኛ ትምህርቶን በአሜሪካ ሀገር እየተከታተሉ የሚሰሩበት ትልቅ ዕድል !

No Prepayment !



Bachelor Degree ✈️

Fast Process

Quality Service

High Visa Ratio

Limited Spot ! Take your spot early live your dream !

🟡🟡Contact us :

🔵 @Gossa07

☎️ +251935343325 / +393444355194

ቴሌግራም ገፅዓችንን መቀላቀል እንዳይረሱ 👇👇👇:

@Ethiogenuine1
@Ethiogenuine1

📍 Address : Addis Ababa, 22, Tsega Business Center, 7th Floor, Office No - H04 .

🌐 Www.Ethio-Genuine-Consultancy.com
#Update

የ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ተራዝሟል።

የመውጫ ፈተናው ከጥር 27 እስከ የካቲት 01/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሎ እንደነበር አይዘነጋም።

ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ይፋ ባደረገው መርሐግብር ፈተናው ከየካቲት 06 እስከ 09/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ታውቋል።

ለአዲስ ተፈታኞች ሞዴል ፈተና ከጥር 27 እስከ 30/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ቲክቫህ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያሳያል።

የተፈታኞች ዝርዝር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚላክም ተገልጿል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ማስታወቂያ

ለድጋሚ (Re-exam) ተፈታኞች በሙሉ

የካቲት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና  ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የ ድጋሚ (Re-exam) ተፈታኞች በሙሉ የመፈታኛ የይለፍቃል (Password) ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. በምዝገባ ወቅት በሞላችሁት email በኩል

2.  https://exam.ethernet.edu.et  ላይ በመግባት የከፈላችሁበትን Transaction Number በማስገባት እንዲሁም

3. ከተመደባብችሁብት የመፈተኛ ተቋም ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ
• ለመጀመሪያ ጊዜ የመዉጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች የይለፍቃል (Password) የምታገኙት ከምትማሩበት ወይም ከተመደባብችሁበት የመፈተኛ ተቋም ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን።

• ሁሉም ተፈታኞች የሞዴል ፈተናን እስከ  የካቲት 5/2016 ዓ.ም መውሰድ ይኖርባቸዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርቁ የሆኑት ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

ዶ/ር መቅደስ ከነርሰሪ እስከ 12ኛ ክፍል በአዲስ አበባ ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት ተምረዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ የህክምና ትምህርታቸውን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተከታተሉ ሲሆን የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሰርተዋል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ሆነው በማስተማር እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የህክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡

ዶ/ር መቅደስ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በጽንስና ማህጸን ትምህርት ክፍል ውስጥ የሠሩ ሲሆን የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት ሆነውም ሠርተዋል፡፡

ዶ/ር መቅደስ ዳባ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ በኃላፊነት ያገለገሉ ሲሆን ላለፉት 18 ወራት በዓለም ጤና ድርጅት ዋና መ/ቤት ከፍተኛ አማካሪ በመሆን አገልግለዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የካቲት 4/2016 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

(ቀን ጥር 30/2016 ዓ.ም)

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የካቲት 4/2016 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
REVISED EXIT EXAM SCHEDULE for the 2016 E.C Mid Year.xls
222 KB
#ExitExam

የ2016 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ከረቡዕ የካቲት 6 ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።

ቲክቫህ ፤ ከዩኒቨርሲቲዎች ያገኘው የተሻሻለ የፈተናው መርሀ ግብር ከላይ ባለው ፋይል አያይዞታል።

መርሀ ግብሩ እንደሚያሳየው ከሆነ በመጀመሪያው የፈተና ቀን የጤና ተማሪዎች ፈታናቸውን ይወስዳሉ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
#repost

የመውጫ ፈተና ከረቡዕ ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።

በዚህ ፈተና ወቅት ከተማሪዎች እና ከፈታኞች ምን እጠበቃል ?

[ ከተፈታኞች የሚጠበቅ ]

- ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍላቸው ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው።  (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል)

- ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው።

- ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው።

- ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም።

- ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው።

- ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት።

- በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገርም ሆነ ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም።

- ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም።

- ተፈታኞች በምንም አይነት ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

- ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተናው ፈታኝ መምህራን እና ለአስተባባሪዎች መታዘዝ ያለባቸው ሲሆን የፈተናው ደንብና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

NB. ሁሉም ተፈታኞች ወደ ፈተና መፈተኛ ክፍል ተፈትሸው እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ እንዲገለል ተደርጎ በቀጣዩ የመውጫ ፈተና መስጫ ወቅት እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል።

[ ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ ]

- የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል።

- ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

- ፈታኝ መምራህን የተፈታኝ ተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ።

- በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው።

- የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው።

- በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከመተኛ ክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ።

- ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ኮምፒውተር እንዳይመለከቱ መቆጣጠር አለባቸው።

- ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል።

- ሲኮርጅ ወይም ሲያስኮርጅ የተገኘ ማንኛውም ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

- ፈተናው ከጀመረ ከ15 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም።

- የፈተና አፈጻጸም ሪፖርት ለሱፐርቨዘር ማቅረብ ይጠብቅባቸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነው የሰበሰበው።

ለመላው ተፈታኞች መልካም ፈተና ይሆን ዘንድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይመኛል !

(መልዕክቱ በባለፈው ዓመት የፈተና ወቅት የተዘጋጀ እና በቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ላይ የተለጠፈ ነው)

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የነባር የ1ኛ ዓመት 2ኛ ሴሚስተር ተማሪዎች እንዲሁም የ3ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ተማሪዎች የመጨረሻ ምዝገባ ቀን ዓርብ የካቲት 08/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ምዝገባ ኦንደማይኖር ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ትናንትና ማታ ከንግድ ባንክ የሌላችሁን ብር ለወሰዳችሁ ተማሪዎች በሙሉ😁

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT