STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#BahirDarUniversity #BGIXP

የቢ.ጂ.አይ. ኢትዮጵያ የሙያ ክህሎት ልምምድ ፕሮግራም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ይካሄዳል።

BGIXP የተሰኘው የኢንተርንሺፕ ፕሮግራሙ፤ የ2ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለማብቃትና የሙያ ክህሎት ልምምድ ለመስጠት የሚያስችል ነው።

ፕሮግራሙ የሙያ ክህሎት ተለማማጆች/Interns በውድድር የሚመረጥ ይሆናል።

መስፈርቱን የሚያሟሉ ተማሪዎች እስከሚመረቁ ድረስ በየዓመቱ ሁለት ወራትን ከአምስቱ የቢ.ጂ.አይ. ኢትዮጵያ ፋብሪካዎች በአንዱ ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ ተከታታይ የሙያ ክህሎት ልምምድ እንዲያገኙ ይደረጋል።

የፈጠራ ችሎታና ብቃት ያላቸው ተማሪዎች ከምርቃት በኋላ በቋሚነት የመቀጠር ዕድል ይሰጣቸዋል።

ዝግጅቱ ማክሰኞ መጋቢት 06/2014 ዓ.ም ጠዋት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ጊቢ ትልቁ መሰብሰብያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

ለመመዝገብ ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፦

https://docs.google.com/forms/d/1KDZD-8uwM7rfesjp66qqfiRHhMV-wsijaH-vAaEcZ7o/edit?usp=forms_home&ths=true

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#BahirdarUniversity

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ፤

የተፈጥሮ ሳይንስ/Natural Science/ ተማሪዎች በዘንዘልማ ካምፓስ፤
የማህበራዊ ሳይንስ/Social Science/ ተማሪዎች በይባብ ካምፓስ፤
የተፈጥሮ ሳይንስ በመምህርነት/Natural Science Teaching/ እና የማህበራዊ ሳይንስ በመምህርነት/Social Science Teaching/ ተማሪዎች በሰላም ካምፓስ፤
ከሚያዚያ 28 - 30 ቀን 2014 ዓ/ም ሪፖርት እንድታደርጉ ያሳውቃል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርስቲውን ሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ ማየት ይቻላል፡፡

ተማሪዎች ለምዝገባ ስትሄዱ ማሟላት ያሉባችሁን ነገሮች ከማስታወቂያው ያንብቡ ‼️

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#BahirDarUniversity

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መንግስት የዜጎችን የመኖር መብት እንዲያስከብር ጥሪ አቅርበዋል።

ተማሪዎቹ ዛሬ ሰኔ 20/2014 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ግቢዎች ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ሰሞኑን በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በሚኖሩ ንፁሃን የአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ማንነትን መሰረት ያደረገ አሰቃቂ ጅምላ ግድያ አውግዘዋል።

መንግስት የዜጎችን የመኖር መብት እንዲያስጠብቅ በተለይም በአማራ ተወላጆች ላይ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለውን ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲያስቆም ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#BahirDarUniversity

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የነባር የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎች የ2014 ዓ.ም የምዝገባ ጊዜን አሳውቋል።

• የመጀመሪያ ዲግሪ የክረምት ተማሪዎች ምዝገባ ~
ሐምሌ 25 እና 26/2014 ዓ.ም

• የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ምዝገባ ~
ነሐሴ 10 እና 11/2014 ዓ.ም

• የርቀት ተማሪዎች ቲቶሪያል የሚሰጠው ከሐምሌ 27 እስከ ነሐሴ 01/2014 ዓ.ም ፤ ፈተና የሚሰጠው ከነሐሴ 03 እስከ 07/2014 ዓ.ም

( ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል። )


ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#BahirDarUniversity

በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ #የክረምት ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

• የመጀመሪያ ዲግሪ የክረምት ተማሪዎች ምዝገባ ~
ሐምሌ 21 እና 22/2014 ዓ.ም

• የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ምዝገባ ~
ነሐሴ 09/2014 ዓ.ም

( ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል። )


ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#BahirDarUniversity

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የPGDT ተማሪዎች የክረምት ትምህርት ሐምሌ 25/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር አሳውቋል።

ተማሪዎች ምዝገባ ለማድረግ ስትሄዱ፦

• በትምህርት ሚኒስቴር ስፖንሰር የሆናችሁ መገጣጠሚያ ደብዳቤ፣

• በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ስፖንሰር ተደርጋችሁ መስሪያ ቤቱ ከዩኒቨርሲቲው ጋር የያዘውን ውል ኮፒና የ2014 ዓ.ም የትምህርት፣ የምግብና ዶርም ክፍያ የተከፈለበት ደረሰኝ መያዝ ይጠበቅባችኋል።

( ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል። )

ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#BahirDarUniversity

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2015 የትምህርት ዘመን የመደበኛ እና የኤክስቴንሽን ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን ይፋ አድርጓል።

➤ የኤክስቴንሽን ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ
     ➭ ጥቅምት 18/2015 ዓ.ም

➤ የመደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ
     ➭ ጥቅምት 24/2015 ዓ.ም

➤ የሌሎች ተማሪዎች (የ2015 አዲስ ገቢዎችን ጨምሮ) የመጀመሪያ ሴሚስተር ምዝገባ፦

➭ መደበኛ ተማሪዎች 👉🏾 ጥቅምት 21/2015 ዓ.ም
➭ ኤክስቴንሽን ተማሪዎች 👉🏾 ጥቅምት 24/2015 ዓ.ም

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የ2015 የዩኒቨርስቲወች ጥሪ ‼️

እስካሁን የምዝገባ ቀን ያሳወቁ ዩኒቨርስቲዎች ስም ዝርዝር ከታች ተገልጿል።

1ኛ- #HaramayaUniversity

➤ 2ኛ ዓመት እና ከዛ በላይ ➭ ህዳር 02

➤  1ኛ አመት - ኦንላይን ምዝገባ ኅዳር 11-12

2ኛ - #WolkiteUniversity ---Calendar ነው።
በ ከለንደሩ መሰረት ጥቅምት 28 እና 29 ብሏል።  (ማስታወቂያ እንጠብቃለን )

3ኛ- #WolloUniversity --ጥቅምት 24-25 ጠርቷል።

4ኛ- #HawassaUniversity --ጥቅምት 28-29 ጠርቷል።

5ኛ- #KotebeUniversity -- ጥቅምት 28 እና 29 ነው።

6ኛ- #Gambella University - በቀጣይ እናሳውቃለን። (የነበረው ተራዝሟል)

7ኛ- #ArbaMinchUniversity - መደበኛ ተማሪዎች

📭 ነጭ ሳር ካምፖስ --- ጥቅምት 19-20 ተብሏል።

8ኛ- #BahirdarUniversity --ጥቅምት 21 እና 22 ተብሏል።

📭BIT 4ኛ አመት Internship ላይ የነበሩ ተማሪዎች ጥቅምት 21- 22 ይገባሉ።

9ኛ- #AmboUniversity --ጥቅምት 28 እና 29 ተብሏል።

10ኛ- #AStuUniversity ----ጥቅምት 26 እና 27

11ኛ - #DebraTaborUniversity --ህዳር 1-2

12ኛ- #WolaitasoddoUniversity --ህዳር 8 እና 9

13ኛ- #OdaBultumUniversity -- ህዳር 5 እና 6

14ኛ - #SelaleUniversity --  ህዳር 1 እና 2 ( ከ 1ኛ-4ኛ አመት)

15ኛ- #JimmaUniversity --ጥቅምት 28 እና 29

16ኛ - #SamaraUniversity
     
         ➤ 1ኛ አመት  ጥቅምት 21 እና 22
        ➤የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ኅዳር 01 እና 02

17ኛ- #InjibaraUniversity -- ኅዳር 01 እና 02

18ኛ- #WachamoUniversity

       ➤ ተመራቂ ያልሆኑ ተማሪዎች ህዳር 12-13
       ➤ተመራቂ ተማሪዎች ኅዳር 2 እና 3

19ኛ - #MekdelaUniversity -ጥቅምት 25-26

20ኛ- #MaddaWolabuUniversity --ጥቅምት 30 እና ህዳር 01

21ኛ- #ArbaMinchUniversity ---ጥቅምት 30 - ኅዳር 2

22ኛ - #AASTU_University -- ጥቅምት 24 -25
        ( 4ኛ አመት--ጥቅምት 26-27)

23ኛ- #ArsiUniversity --ኅዳር 1-2

24ኛ -#WollaggaUniversity --ኅዳር 14--15

25ኛ -#DillaUniversity --
  1ኛ አመት ---ጥቅምት 28 -29
3ኛ እና ከዛ በላይ ---ኅዳር 5 እና 6

ሌሎች ዩኒቨርስቲዎችም ቀጣይ ቀናቶች ያሳውቃሉ።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#BahirDarUniversity

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ መደበኛ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው በ2015 ዓ.ም በመደበኛ መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ከየካቲት 20 እስከ 22/2015 ዓ.ም እንደሆነ መግለጹ ይታወቃል።

መንግስት ዘንድሮ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች
ምደባ ካደረገባቸው 15 ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ5 ሺህ 100 በላይ ተማሪዎች በቀዳሚነት የመረጡት ዩኒቨርሲቲ ነው።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#BahirdarUniversity

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በጊዚያዊነት ከትግራይ ክልል ዩኒቨርስቲዎች #ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ቀሪ ኮርሶችን ሲወስዱ የነበሩ ተማሪዎች ውጤታቸው ሙሉ በሙሉ #ቀድሞ ወደ ነበሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ መሆኑን በመግለጽ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ጥሪ እነኚህን ተማሪዎች የማይመለከት መሆኑን አሳስቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot