STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.6K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየርመንገድ አቪዬሽን ዩንቨርስቲ ከ600 በላይ በተለያዩ መስኮች ያስለጠናቸውን ተማሪዎችን በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

በዛሬው የምርቃት ፕሮግራም በአውሮፕላን አብራሪነት በአውሮፕላን ጥገና እና መስተንግዶ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

በምርቃት ስነስርዓቱ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ዋና ስር አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰውን ጨምሮ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት አቶ ካሴ ይማም የተማሪዎች ወላጆች በተገኙበት በኢትዮጵያ አየርመንገድ ውስጥ ፕሮግራሙ እየተካሄደ ይገኛል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Freshman 2016 Notes AMU.pdf
287.2 KB
የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይህን ፋይል አንብቡት


💥Students who want to be transferred from Natural Science to Social Science can submit their
written application to the main or campus registrar offices. The application should be short but
must contain the applicant’s full name, ID number and signature.

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
አዲግራት ዩኒቨርስቲ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን 832 አዲስ ተማሪዎች መቀበሉን አስታወቀ።

ዩኒቨርስቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ1 ሺሕ 500 በላይ ተማሪዎች ታህሳስ 6 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚያስመረቅም ተመላክቷል።

የዩኒቨርስቲው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ዮሐንስ ከበደ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን የተቀበለው የመመገቢያ፣ የመማሪያ፣ የመኝታ እና ሌሎች ለመማር ማስተማር ሥራው አስፈላጊ የሆኑ የዝግጅት ሥራዎችን ካጠናቀቀ በኋላ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የዩኒቨርስቲውን ቅጥር ግቢ በማስዋብና በማፅዳት ተማሪዎቹን መቀበሉን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ዩኒቨርስቲው ትምህርታቸውን በተለያዩ ምክንያቶች አቋርጠው ከነበሩ ከ5 ሺሕ በላይ ተማሪዎች መካከል ዳግም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 1 ሺሕ 500 ተማሪዎችን የፊታችን ቅዳሜ እንደሚያስመርቅም ዮሐንስ አመልክተዋል።

የመቀሌ እና የአክሱም ዩኒቨርስቲዎች በተያዘው የትምህርት ዘመን የሚያስተምሯቸውን ከ2 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ባለፈው ሳምንት መቀበላቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
"ከ51ሺ ትምህርት ቤቶች መካከል የጥራት መስፈርቶችን ያሟሉት 6ቱ ብቻ ናቸው" - የትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አሁን ላይ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስር ካሉ 51 ሺህ ትምህርት ቤቶች መካከል የተቀመጡ የጥራት ደረጃዎችን ያሟሉት 6 ትምህርት ቤቶች ብቻ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

አብዛኛው ትምህርት ቤቶች ምቹ የመማሪያ ቦታ የሌላቸው፤ የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ እና ብቁ የመምህራን እጥረት እንዳለባቸውም አመላክተዋል ፡፡

መንግስት አሁን ላይ ይህንኑ ችግር ለመቅረፍ አዲስ ስርዓተ ትምህርት ከማዘጋጀት ጀምሮ የመምህራንን አቅም ማሻሻል እንዲሁም የመንግስት ትምህርት ቤቶች ከግል የትምህርት ተቋማት ጋር የሰፋ ልዩነት እንዳይኖራቸው በትኩረት እየሰራበት እንዳለም ጠቁመዋል፡፡

እያንዳንዱ የግል የትምህርት ቤቶች 10 አቅም የሌላቸው ተማሪዎችን ተቀብለው በነፃ በማስተማር ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የሚያስችል አሰራር እየተዘረጋ ስለመሆኑም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም አለምአቀፍ ትምህርት ቤቶችም ለአቅም ደካማ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል እንዲሰጡ እንደሚደረግም ነው የተናገሩት፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የአጠቃላይ_ትምህርት_የተማሪዎች_ምዘና_እና_የክፍል_ክፍል_ዝውውር_መመሪያ_16_1_2016_2.pdf
712.7 KB
ለሁሉም ትምህርት ቤቶች
የተማሪዎች ምዘናን ይመለከታል
ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች ምዘናን አስመልክቶ ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቶ የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ (ቴሌግራም) ቻናሎች ላይ ተለጥፎ ይታያል፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግ አንድ አንድ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ማድረግ መጀመራቸዉን መረጃዉ ደርሶናል፡፡ ይሁንና ይህ መመሪያ ረቂቅና ከተማ አስተዳደሩ ተግባራዊ እንድናደርግ በደብዳቤ ያላሳወቀን በመሆኑ ተግባራዊ ማድረግ የጀመራችሁ እንድታቆሙና በነበረዉ የተማሪዎች ተከታታይ ምዘና ሂደት መሰረት ተማሪዎችን እንድትመዝኑ አሳስባለሁኝ፡፡

Addis Ketema Education Office

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ማስታወሻ

በ2016 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሐግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በየተመደባችሁበት የዩኒቨርሲቲው ካምፓስ ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 09 እና 10/2016 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡

ለመመዝገብ ከመሔዳችሁ በፊት https://portal.aau.edu.et ላይ በመግባት ➧ Freshman ➧ Student Profile የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የግል መረጃቻችሁን ማሟላታችሁን አትዘንጉ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#FakeAnnouncementAlert

በ2016 ዓ. ም በሪሚዲያል ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ መቱ ዩኒቨርሲቲ ተመድባችሁ ጥሪ በመጠባበቅ ላይ የምትገኙ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ጥሪ #አለመደረጉን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በአንዳንድ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ዩኒቨርሲቲው ጥሪ እንዳስተላለፈ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሐሰት መሆኑንም ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የ2016 ዓ. ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪን ወደፊት እንደሚያሳውቅ ጠቁሟል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

“ኬኖ” ተብሎ ለሚጠራው የቁጥር ግመታ ጨዋታ ፈቃድ አለመሰጠቱ ተገለጸ


“ኬኖ” ተብሎ ለሚጠራው የቁጥር ግመታ ጨዋታ ፈቃድ አለመስጠቱን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት ቤቲንግ ቤቶችና ሌሎችም ቁጥር በማስገመት ለሚያጫወቱት “ኬኖ” አስተዳደሩ ፈቃድ ያልሰጠ ሲሆን፣ ይህን ጨዋታ በሚያጫውቱ ቤቶች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡

በቀጣይም ጨዋታውን ሲያጫውቱ በተገኙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

#ኢፕድ እንዳጣራው “ኬኖ” ህጻናትን ጨምሮ በርካታ ታዳጊዎች፣ ወጣቶችና አዛውንቶች እያዘወተሩት የሚገኝና በብዛት ብራቸውን የሚከስሩበት የቁማር ዓይነት ነው፡፡

(ኢ ፕ ድ)
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ከ200 ሜትር ራዲየስ በታች የቤትንግ ስፖርት ውርርድ በሚያጫውቱ ፣ በማጫወቻ ቦታዎች ጫት፣ ሺሻ እና አልኮል እንዲሁም ተመሳሳይ ነገሮችን በሚያስጠቅሙ አካላት ላይ እርምጃ መውሰድ ተጀመረ።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የህግ አግባብን ተከትለው በማይሰሩ የቤቲንግ እስፖርት አጫዋች ድርጅቶች ላይ የከተማ አስተዳደሩ ስለ ወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ በሚመለከት በዛሬው እለት ለሚዲያ አካላት ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።


ወ/ሮ ሊዲያ በመግለጫቸው በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ከ200 ሜትር ራዲየስ በታች የቤትንግ እስፖርት ውርርድ ማጫወት፣ በማጫወቻ ቦታዎች ጫት፣ ሺሻ እና አልኮል እንዲሁም ተመሳሳይ ነገሮችን ማስጠቀም፤ ካለህጋዊ ፈቃድ እስፖርታዊ ውርርዱን ማካሄድ ፤ በስፍራው የሚደረጉ የእርስ በርስ ግጭቶች ፤ የቡድን ፀብ፤ ከ21 ዓመት በታች የሆኑ ተማሪዎችና ታዳጊዎችን ማወራረድን ጨምሮ የቤቲንግ ቤቶቹ የተላለፏቸው ህጎች መሆናቸውን ጠቁመው ይህም ከህብረተሰቡ ከደረሰ ጥቆማ በተጨማሪ ቢሮው ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በቂ ጥናት አድርጓል ህዝቡንም አወያይቷል ብለዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የቤቲንግ እስፖርት ውርርድ የሚካሄድባቸው ስፍራዎች ልዩ ልዩ ወንጀሎች የሚፈጸሙባቸው ዋነኛ ማዕከላት እየሆኑ መምጣታቸውን ጨምሮ በህብረተሰቡ ላይ እየፈጠሩ ያሉትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በዝርዝር ከሚመለከታቸው የፀጥታ ተቋማት ጋር በጥናት በመለየት የተቀናጀ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ወ/ሮ ሊዲያ በመግለጫቸው ወቅት አስታውቀዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎችን ጠርተው ትምህርታቸውን እንዲያስቀጥሉ ተነግሯል ተባለ‼️

በወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት በአማራ ክልል የሚገኙ በርካታ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በወቅቱ ወደ ትምህርት ገበታቸው ሳይጠሩ እንደቆዩ ይታወቃል።

ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ የሚመለከተው የትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሃሳብ ሰጥቶበታል።

በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን ጠርተው ትምህርት እንዲያስቀጥሉ ትእዛዝ ተላልፏል ሲሉ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኤባ ሜጀና ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።

ተቋሟቱ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛዉም ነገር እገዛ እንዲደረግላቸዉ እንዲያሳውቁ መልእክት ተላልፏል ብለዋል። በውይይታቸው መሰረት በቅርቡ ተማሪዎች በየተቋሟቱ ገብተው ትምህርታቸውን እንደሚቀጥሉ ነዉ ስራ አስፈጻሚዉ የተናገሩት፡፡

ትምህርት ያልጀመሩትን ብቻ ሳይሆን በትምህርት ገበታቸው ላይ የሚገኙትንም ተማሪዎች ሁኔታ በመከታተል ላይ እንገኛለን ያሉት መሪ ስራ አስፈጻሚው ከሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ጋር በመሆን የትምህርት ሂደቱ እንዳይስተጓጎል ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸዉን አመላክተዋል፡፡

ስራ አስፈጻሚው ተማሪዎቹ መቼ ተጠርተው ትምህርት እንደሚጀምሩ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም፡፡

ምንጭ፡መናኸሪያ ሬዲዮ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ለጥናትና ምርምርዎ እገዛ ይፈልጋሉ?
    አዎ ከሆነ መልስዎ!
በመንግስትም ሆነ በግል ዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ በዲፕሎማ፣ዲግሪ እና በማስተርስ ፕሮግራም ለምትማሩ እና ትምህርታችሁን ጨርሳችሁ የምርቃት ጊዜያችሁን በጉጉት ለምትጠብቁ ሁሉ ስለ ጥናትና ምርምር በቂ እዉቀትን በመያዝ የመመረቂያ ፅሁፋችሁን ተመራጭ እና ተወዳጅ አድርጋችሁ በመስራት በጥሩ ዉጤት ትመረቁ  ዘንድ እናግዝዎታለን፡

If you need support related to:    
1 Assignment / አሳይመንት
2 Research / ሪሰርች
3 Proposal / ፕሮፖዛል
4 Term Paper /  ተረም ፔፐር
5 Case study/ ኬዝ ስተዲ
6 Article Review
7  Mini research
8  Business plan
9  Environmental impact assessment [EIA]

Any other Questions
Contact us via
@ResearcherETH
@ResearcherETH
@ResearcherETH
በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች  ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ ቢሆኑም  በክልሉ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ችግር እንደፈጠረባቸው በድጋሜ አስታወቁ

በአማራ ክልል የሚገኙ አስር ዩኒቨርሲቲዎች በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ለነባር እንዲሁም አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎቻቸው ጥሪ ሳያደርጉ አራት ወራት ተቆጥረዋል።

ተማሪዎችም ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ሌሎች አካባቢዎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመድባቸውና ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ጉትጎታ ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ግን በአማራ ክልል የሚገኙ አስሩም ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ጠርተው ትምህርት እንዲያስቀጥሉ እንደተነገራቸው እና ተቋማቱም በቅርቡ ጥሪ ለማድረግ መስማማታቸውን ይናገራል።

ይህንንም ተከትሎ ኢትዮ ኤፍ ኤም ትምህርት መቼ  ለመጀመር እንዳሰቡ   በአማራ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ጊዜያዊ  ፀሀፊ የሆኑት ዶክተር ንጉስ ታደሰን ጠይቋል ።

አስር ዩኒቨርሲቲዎችን በአባልነት የያዘው በአማራ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ጊዜያዊ  ፀሀፊ የሆኑት ዶክተር ንጉስ ታደሰ   በክልሉ  ያለው የፀጥታ ሁኔታ ተማሪዎችን መጥራት እንዳላስቻላቸው አንስተዋል።

ተቋማቱ  ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን ያነሱት ፀሐፊው በክልሉ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ግን እንቅፋት እንደሆነባቸው ገልፀዋል።

በአማራ ክልል የሚገኙ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑንና የፀጥታው ሁኔታ የበለጠ ሲሻሻል ለተማሪዎቻቸው ጥሪ እንደሚያደርጉ  በቅርቡ መናገራቸው ይታወሳል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ETA

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የትምህርት መስኮቻቸው የፈቃድ ወቅታዊ መረጃን አውጥቷል፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ ያገኙበትን የትምህርት መስክ፣ ካምፓስ እና መርሐግብር አሟልቶ የያዘና በየጊዜው ወቅታዊ የሚደረግ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፦ https://bit.ly/43Z1Rck

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቀረበው መረጃ ላይ አስተያየት እና ጥቆማ አዲስ አበባ ጉለሌ ክ/ከተማ ሽሮ ሜዳ አሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኝው የባለሥልጣን መ/ቤቱ በአካል በመገኘት ወይም በኢ-ሚይል አድራሻ hemis.info@gmail.com አማካኝነት እስከ ዓርብ ታህሳስ 19/2016 ዓ.ም ብቻ መላክ የምትችሉ መሆኑን ባለሥልጣኑ አሳስቧል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ትምህርት ይጀምራሉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል በተፈጠረው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በ2016 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያዉ ወሰነ-ትምህርት ተማሪዎቻቸውን ለመጥራትና መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸዉን ሙሉ ለሙሉ ለመጀመር አልቻሉም ነበር ብሏል ሚኒስቴሩ።

በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር ከክልሉ ኮማንድፖስት፣ የጸጥታ አደረጃጀቶችና የሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን ሲያካሂድ መቆየቱ ተገልጿል።

" የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ፣ የአስሩ ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልሉ ጸጥታ አካላት ትናንት ታህሳስ 18/2016 ዓ.ም በጉዳዩ ዙሪያ የመከሩ ሲሆን አሁን በክልሉ አንጻራዊ ሰላም የተፈጠረ በመሆኑ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን መጥራትና ማስተማር እንደሚችሉ ውሳኔ ላይ ተደርሷል። " ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

በዚህም መሰረት ከጥር 1/2016 ጀምሮ ባሉ ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን ጠርተው የመማር ማስተማር ስራቸውን ይጀምራሉ ተብሏል።

በመሆኑም በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲዎቹ የሚያደርጉትን ጥሪ እንዲከታተሉ ጥሪ ቀርቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot