STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.1K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሩሲያ ትምህርት ቤቶች መሰጠት መጀመሩን የሞስኮ ትምህርት ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ‼️
የአማርኛ ቋንቋ መሰጠት መጀመሩ በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያ፣ ባህላዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያጠናክራል ነው የተባለው፡፡

ተማሪዎቹ በበኩላቸው አማርኛ ቋንቋ ከማወቅ በተጨማሪ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ህዝቡን እና የኢትዮጵያን ባህል ማየት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡

ተጨማሪ የአፍሪካ ቋንቋዎችን የመማር ፍላጎት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡

ከአማርኛ በተጨማሪ በአፍሪካ ከፍተኛ ተናጋሪ ያለው የስዋሂሊ ቋንቋ በሞስኮ ትምህርት ቤቶች መሰጠት መጀመሩን ስፑትኒክ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

#የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

በአማራ ክልል የ2016 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም 11/2016 ዓ.ም ተራዝሟል፡፡

በክልሉ የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 23/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል። እስካሁን 2.5 ሚሊዮን ተማሪዎች መመዝባቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

የተማሪዎች ምዝገባ ከሌሎች ዓመታት አንጻር ሲታይ የተጓተተ መኾኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነትና ጽ/ቤት ኃላፊ ጌታቸው ቢያዝን ተናግረዋል።

በአማራ ክልል በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ምዝገባው በተፈለገው ልክ መሔድ አለመቻሉን የገለፁት ኃላፊው፤ ከባለፉት ዓመታት የምዝገባ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የዘንድሮው ዝቅተኛ መኾኑንም ጠቁመዋል፡፡

በክልሉ ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመዝገብ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መኾኑን የተናገሩት ኃላፊው፤ የጸጥታ ችግር በሌለባቸው አካባቢዎች ምዝገባው መቀጠሉንም ገልጸዋል፡፡

በዚህም የተማሪዎች ምዝገባ በተፈገው ልክ ባለመኾኑ እስከ መስከረም 11/2016 ዓ.ም መራዘሙን ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎች እንዲመዘገቡና መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራው መስከረም 14/2016 ዓ.ም እንዲጀመር ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ #አሚኮ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

በፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያልወሰዱ ከ11,500 በላይ ተማሪዎች ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ መግባታቸው ተሰምቷል፡፡

ፈተናቸውን ለማጠናቀቅ በድጋሚ ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የገቡትን ተማሪዎች በተረጋጋ መልኩ ለማስፈተን ዝግጅት ማድረጉን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ተማሪዎቹ በሦስት ዞኖች እና በጎንደር ከተማ የመጡ መሆናቸውን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ልጅዓለም ጋሻው ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎቹ ያቋረጧቸውን የኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እንዲሁም የሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር የትምህርት አይነቶች ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል። #አሚኮ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም. ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር እንደሚቀጥል ተገለፀ


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ የአስራር ለውጦች እያደረገ ቢሆንም በተያዘው ዓመት የተማሪዎች ቅበላ በምደባ እንደሚሆን አስታወቀ።

የዩኒቨርስቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ የተቋሙን ሽግግር በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሲሰጡ፤ በ2016 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ቅበላን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር መሰረት እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው እስከ አንድ ዓመት ተኩል ይፈጃል ተብሎ በሚጠበቅ የሽግግር ሂደት ላይ እንዳለ የተናገሩት ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ ሳሙኤል ሙሉ በሙሉ ራስ ገዝ መሆን ሲችል አዳዲስ ተማሪዎችን በዩኒቨርስቲው መስፈርት መሰረት አወዳድሮ እንደሚቀበልም ጠቁመዋል።

የተቋሙ ራስ ገዝ መሆን ከፍለው መማር የማይችሉ ተማሪዎችን አይቀበልም ማለት አይደለም ያሉት ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ፤ የዩኒቨርስቲውን መግቢያ የሚያሟሉ ብቁ ተማሪዎች በመንግስት ድጋፍ ዩኒቨርስቲውን መቀላቀል እንደሚችሉ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወደራስ ገዝነት የሚያደርገውን ሽግግር ለማገዝ ቻንስለር ጨምሮ የቦርድ አመራሮችና ፕሬዝዳንቶች መሾማቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ሙሉ በሙሉ ሂደቱ ሲጠናቀቅ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በዓለም አቀፍ መስፈርቶች ተወዳድረው እንደሚቀጠሩ ተጠቁሟል።

ተቋሙ ከዚህ ቀደም ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ ተማሪዎችን በምደባ እንደማይቀበል አስታውቆ ነበር።

ምንጭ፡አዲስ ዘይቤ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ECSU

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ፦

የማታ እንዲሁም የቅዳሜና እሁድ ተማሪዎች ምዝገባ፦ መስከረም 18 እና 19/2016 ዓ.ም

የመደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ፦ መስከረም 24/2016 ዓ.ም

ዘግይተው ለሚመጡ የሁሉም መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ፦ መስከረም 28/2016 ዓ.ም

አዲስ ገቢ የማታ እንዲሁም የቅዳሜና እሁድ ተማሪዎች ምዝገባ፦ መስከረም 25 እና 26/2016 ዓ.ም

አዲስ ገቢ የመደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ፦ መስከረም 28/2016 ዓ.ም

(የዩኒቨርሲቲው የ2016 ትምህርት ዘመን ካላንደር ከላይ ተያይዟል።)

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ትግራይ ክልል

በትግራይ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራትና ምዘና ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዳይሬክቶሬት አቶ ክንፈ ፍስሃ  ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 98.6 ከመቶ ወደ ቀጣዩ ክፍል ተዛውረዋል ሲሉ ገልጠዋል።

በክልሉ ትምህርት ቢሮና የፌደራል መንግስት ቅንጅት ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑንና አገር አቀፍ ፈተና ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም እንደሚወስዱ ከትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#AAU

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሽግግር ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ በነባሩ አሰራር እንደሚቀጥል ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ተናግረዋል።

በዚህም የ2016 የትምህርት ዘመን ተማሪ ቅበላ ከዚህ ቀደም በነበረው ነባሩ ስርአት የሚከናወን ሲሆን ፤ አዲስ አሰራሮች ከመጡ በየጊዜው ይፋ እንደሚደረግ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
#MoE

የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና ከመስከረም 21 - መስከረም 23 ድረስ በኦንላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ትምህርት ሚኒስቴር ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት በ2016 ትምህርት ዘመን የድኅረ ምረቃ ትምህርት ለመከታተል ተፈታኞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው Graduate Admission Testing (GAT) የመመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aau.edu.et ከዛሬ መስከረም 11 ጀምሮ እስከ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ማመልከት ይገባቸዋል።

ይህ ተከትሎ የመግቢያ ፈተና ከመስከረም 21 እስከ 23/2016 ዓ.ም በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በበይነ-መረብ ይሰጣል።

የማለፊያ ነጥብ የሚወሰነው በትምህርት ሚኒስቴር ሲሆን ተፈታኞች ፈተናቸውን ሲጨርሱ ወዲያውኑ ማየት ይችላሉ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ማስታወቂያ ለግል ትምህርት ቤቶች!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ2016 የትምህርት ዘመን ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ የመማር ማስተማር ስራው በከተማ አስተዳደሩ ከመስከረም 7/2016 ዓ.ም ጀምሮ አንዲካሄድ እያደረገ ይገኛል፡፡


በቅድመ ዝግጅት ስራው ውስጥ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው ለትምህርት ዘመኑ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ማሟላት ሲሆን ከነዚህ ግብዓቶች መካከል በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የታተሙ የተማሪ መማሪያ መጻሕፍትና የመምህሩ መምሪያዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በመሆኑም ግብአቶቹ እንዲሟሉ በማድረግ ለመንግስት ትምህርት ተቋማት የተሰራጨ ሲሆን ለግል ትምህርት ተቋማትም በሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሰራጭ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡


የግል ትምህርት ተቋማት ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምጣት በፎቶ ላይ የተዘረዘሩትን የመማሪያ መጻሕፍትንና የመምህር መምሪያን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን በምትመጡበት ጊዜ ከዚህ ቀደም ለክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ያስገባችሁትን ፍላጎት ዝርዝር በመያዝና በክፍለ ከተማው ት/ጽ/ቤት ማህተም በማረጋገጥ ሊሆን ይገባል፡፡


ከዚህም በተጨማሪ የተቀሩ መጻሕትን ስርጭት በተመለከተ በቀጣይ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡


መሳሰቢያ ፡- በመሰራጨት ላይ የሚገኙ መጻሕፍት ዝርዝር በፎቶ ላይ ተመላክቷል፡፡


©የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ለዲላ ዩኒቨርሲቲ አራተኛ አመትና ከዚያ በላይ ያላችሁ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ!
................
የምዝገባ ቀን መስከረም 24 እና 25 ቀን 2016 ዓ.ም
ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን ዝርዝሩን ከዚህ በተያያዘው ማስታወቂያ ተመልከቱ።

#ማሳሰቢያ፦ ሁሉም የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ተማሪዎች ምዝገባችሁ የሚከናወነው በሀሴዴላ ግቢ ስለሆነ ይህንኑ አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት በሀሴዴላ ግቢ ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን!

       ሬጅስትራርና አሉምናይ ጽ/ቤት

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ExitExam

ሁለተኛው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ( Exit Exam ) ጥር ወር ላይ ይሰጣል‼️

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በዛሬው ዕለት #ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ ላይ ተቋማት የመደበኛ ተማሪዎቻቸውን እንዲሁም 2015 ላይ የመውጫ ፈተና ወስደው #ያላለፉ ተማሪዎችን መረጃ እስከ ጥቅምት 10/2016 ድረስ ይልኩ ዘንድ አሳስቧል።

ባለስልጣኑ ለግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ ላይ ቀጣዩ ማለትም ሁለተኛው የመውጫ ፈተና ጥር ወር ላይ በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚሰጥ ጠቁሟል።

፨ የመውጫ ፈተና በየ ስድስት ወሩ የሚሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚንስቴር መግለፁ ይታወሳል።


( ከላይ የተያያዘውን ደብዳቤ ይመልከቱ ‼️ )

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot