STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
🌟 የምስራች ለመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች 🌟

🔔 ለመውጫ ፈተና በብቃት የሚያዘጋጅዎ
       Mock እና Model  Exam
       Online ይለማመዱ!

አድቫንስድ የትምህርት ማማከር አገልግሎት ማዕከል ከአተርቴክ የቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ጋር በመተባበር ፦

➭ በዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮችና መምህራን የተዘጋጀ፣
➭ የትምህርት ሚኒስቴርን የብቃት መስፈርት መሰረት ያደረገ፣
➭ ተገቢውን ሳይንሳዊ  የምዘና ሥርዓት የተከተለ፣
➭ ለአንድ ፕሮግራም ከ1,000 በላይ መለማመጃ ጥያቄዎችን የያዘ፣
ሁሉንም የፈተና ኮርሶች ያካተተ
ለእያንዳንዱ ጥያቄ መልስና ማብራሪያ
     የያዘ

➭ በየትኛውም ቦታ በማንኛውም ሰዓት የሚያገኙት የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) መለማመጃ አቀረበልዎ!

ለሙሉ መረጃው፡-

➧ www.http://elts.com.et ይጎብኙ፣
https://t.me/aec_ethiopia ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

#AdvancedEducationalConsultingCenter
እንመረቅ እንጂ አንፈተንም አላልንም‼️

የ ደብረማርቆስ  ዩኒቨርሲቲ  ተማሪ ነኝ እኛ እንመርቅ እንጂ አንፈተንም አላልንም ሳይማሩ ያስተማሩን ቤተሰቦቻችን ልጄ ሊመርቅ ነው እያሉ ሳልመርቅ ብቀር ምንድነው የሚሰማቸው ብቻ ከባድ ነው ፡፡ለቤተሰቦቻችን እንኳን ስትሉ አስመርቁን😢

  ፍትህ ለ ተመራቂ ተማሪዎች!!!

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
እንመረቅ እንጂ አንፈተንም አላልንም‼️

የአ
ምቦ ዩኒቨርሲቲ  ተመራቂ ተማሪዎች እንመርቅ እንጂ አንፈተንም አላልንም በማለት ድምፃቸውን አሰምቷል።

ምርቃቱ ከፈተናዉ ይቅደምልን ብሏል።

ለቤተሰቦቻችን እንኳን ስትሉ አስመርቁን


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ለ 2015 ዓ.ም የማትሪክ ፈተና ብቁ መሆን አንድትችሉ የተዘጋጀው Grand Plan (መሪ እቅድ) ቪዲዮ በዚህ https://t.me/eTemariNetetemari.net ግሩፕ አንዲሁም https://t.me/edutech_plc ቴሌግራም ቻናል ላይ pin ተድርጎ ታገኙታላችሁ
ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተከለሰ የዓመቱ ትምህርት ጊዜ ሰሌዳ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ዜና " ግነት የበዛበት ነው " አለ።

ዩኒቨርሲቲው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው ፤ ከዩኒቨሲቲው እውቅና ውጪ ባልተፈቀደ ሁኔታ በቀን 03/10/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠውን የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) " አንፈተንም "በሚል በዋናው ግቢ በዉስን ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ተሞክሮ ነበር ብሏል።

" የተደረገውን ሙከራ ተከትሎ በጥቂት የማህበራዊ ሚዲያዎች የፀጥታ ችግር እንዳለና መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ላይ መስተጓጎል እንዳለ በማስመሰል ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጨ እንዳለ ለመገንዘብ ችለናል " ብሏል።

" በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨው ዜና ግነት የበዛበት " ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው " የተፈጠረውን መጠነኛ ያለመግባባት ለመፍታት የዩኒቨርሲቲው ደህንነት ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከሀዲያ ዞን ፖሊስ፣ ከሌሞ ወረዳ ፖሊስ እንዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸው የፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት በመስራት በአስተማማኝ ሁኔታ ሠላማዊ የሆነ የመማር ማስተማር ሥራ ማስቀጠል ተችሉዋል " ብሏል።

ዩኒቨርሲቲው ፤ ለተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ባስተላለፈው መልዕክት በነበረው መጠነኛ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ በተማሪዎች ላይ " ምንም ዓይነት ጉዳት " ያለመድረሱንና ዩኒቨርሲቲው ወደተለመደው መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ መመለሱን አሳውቋል።

ተቋሙ ባወጣው መግለጫ ላይ በቪድዮ እና በፎቶ ስለተያዙት ማስረጃዎች ምንም ያለው ነገር የለም።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
Tentative EXIT EXAM Schedule -Final Draft 1 (1).xls
213 KB
Tentative Exit Exam Schedule‼️

የ 2015 Exit Exam ፈተና ለሁሉም ተማሪዎች በዚህ Schedule መሰረት ይሰጣል ።

ከ ሐምሌ 3 እስከ 8 ድረስ የሚሰጥ ይሆናል ። ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ ።

Health ተማሪዎች ሰኔ 30 ላይ ማየት ትችላላችሁ ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#AddisAbaba

" የፈተና ህትመት ደህንነቱን በጠበቀ መልኩ #ከፌደራል_ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር እየተሰራ ነው " - የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚሰጠው የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በቂ ዝግጅቶች መደረጋቸውን የከተማው ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

የፈተና ህትመት ደህንነቱን በጠበቀ መልኩ ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር እየተሰራ እንዳለ ተጠቁሟል።

በዘንድሮው ከተማ አቀፍ ፈተና በ8ኛ ክፍል 75‌100 ተማሪዎች በ766 ት/ቤቶች እንዲሁም በ6ኛ ክፍል 75‌090 ተማሪዎች በ788 ትምህርት ቤቶች በመደበኛ በማታና በግል ለመፈተን ምዝገባ ማካሔዳቸውን ተነግሯል።

ከተማ አቀፍ ፈተናውን በብቃት ለመስጠት ትምህርት ቢሮው በቂ ዝግጅት ማድረጉን ያሳወቀ ሲሆን የፈተና ጣቢያ ሃላፊዎች ሱፐርቫይዘሮችና ፈታኞችም ፈተናውን በስኬት ለማጠናቀቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

በቀጣይ በከተማዋ 53,535 የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለሀገር አቀፍ ፈተና እንደሚቀርቡ ከከተማው የትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
#Update

የትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ሥራ አቁመው የነበሩ አራት ዩኒቨርሲቲዎች በመጪው መስከረም ወር 2016 ሥራ እንደሚጀምሩ አስታውቋል።

የሚኒስቴሩ የአስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሀ (ዶ/ር) ለኢፕድ የሰጡት ቃል ፦

" በመጪው ዓመት በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

ዩኒቨርሲቲዎቹን ወደ ሥራ ለማስገባት የትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲዎቹ ያሉበት ሁኔታ ከዩኒቨርሲቲዎቹ አመራሮች ጋር በመቐለ ተደጋጋሚ ውይይት አድርጓ።

ሥራ ለማስጀመር የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመስራት ወደ ተግባር ተገብቷል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የመማር ማስተማር ሂደት ከመጀመራቸው በፊት ፦
- የምግብ ፣
- የመኝታ፣
- የሕክምና አገልግሎቶች ቅድሚያ የሚያሟሉበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነው።

ራያ ዩኒቨርሲቲም ይህንን አሟልቶ በትናንትናው ዕለት የተማሪዎች ምዝገባ ጀምሯል።

መቐለና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በቀጣዮቹ ወራት ትምህርት መጀመር የሚያስችላቸውን ተግባር እንደሚጨርሱና ተማሪዎችን መቀበል እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎች በበለጠ በጦርነቱ ጉዳት በማስተናገዱ የተወሰነ ጊዜ ሊዘገይ ይችላል።

አራቱ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከጦርነቱ በፊት 45 ሺሕ ተማሪዎችን ሲያስተምሩ ነበር። ከእነዚህ ውስጥም ባለፉት ዓመታት 22 ሺሕ የሚሆኑ ተማሪዎች እንዲወጡ ተደርጎ በጊዜያዊነት ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ተደርጓል።

እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎችም አሁን ላይ ቅበላ የሚያደርጉት ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ሳይመደቡ የቆዩ 20 ሺሕ የሚሆኑ ተማሪዎችን ነው።

በመጪው አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው የሚያልፉ ተማሪዎችም የዩኒቨርሲቲዎቹ ዝግጁነት ተጠንቶና ታይቶ ተማሪዎች ሊመደቡባቸው ይችላል።

ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩና ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ሄደው ያጠናቀቁ ተማሪዎች ውጤታቸውን የሚገልጽ የትምህርት ማስረጃ ሳያገኙ መቆየታቸውን ይታወሳል ፤ አሁን ላይ ከነበሩበት ዩኒቨርሲቲ ያገኙት ውጤት ወደ ትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲላክ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ዩኒቨርሲቲዎቹም ውጤቱ ሲደርሳቸው የነበራቸውን ውጤት ደምረው ጥቅል ውጤታቸውን የሚገልጽ ጊዜያዊ ዲግሪ ማግኘት ይችላሉ። "

Via EPA

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
🌟 የምስራች ለመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች 🌟

🔔 ለመውጫ ፈተና በብቃት የሚያዘጋጅዎ
       Mock እና Model  Exam
       Online ይለማመዱ!

አድቫንስድ የትምህርት ማማከር አገልግሎት ማዕከል ከአተርቴክ የቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ጋር በመተባበር ፦

➭ በዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮችና መምህራን የተዘጋጀ፣
➭ የትምህርት ሚኒስቴርን የብቃት መስፈርት መሰረት ያደረገ፣
➭ ተገቢውን ሳይንሳዊ  የምዘና ሥርዓት የተከተለ፣
➭ ለአንድ ፕሮግራም ከ1,000 በላይ መለማመጃ ጥያቄዎችን የያዘ፣
ሁሉንም የፈተና ኮርሶች ያካተተ
ለእያንዳንዱ ጥያቄ መልስና ማብራሪያ
     የያዘ

➭ በየትኛውም ቦታ በማንኛውም ሰዓት የሚያገኙት የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) መለማመጃ አቀረበልዎ!

ለሙሉ መረጃው፡-

➧ www.http://elts.com.et ይጎብኙ፣
https://t.me/aec_ethiopia ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

#AdvancedEducationalConsultingCenter
ለ6ኛ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሞዴል ፈተና መሰጠት ጀምራል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤቶች በጋራ የተዘጋጀ  ሞዴል ፈተና በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ የ6ኛ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መሰጠት ጀምራል፡፡

ሞዴል ፈተናው ከሰኔ 7-9 /2015 ዓ.ም ድረስ በሁሉም ትምህርት ቤቶች  የሚሰጥ መሆኑን የገለጹት የፈተና አስተዳደርና ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ተማሪዎች በሞዴል መልስ መስጫው ላይ በቂ ልምምድ እንዲያደርጉ እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አያይዘውም በዘንድሮው ከተማ አቀፍ ሞዴል ፈተና በ8ኛ ክፍል 75̡100 ተማሪዎች በ766 ት/ቤቶች እንዲሁም በ6ኛ ክፍል 75̡090 ተማሪዎች በ788 ትምህርት ቤቶች በመደበኛ በማታና በግል  እንዲሁም 53 535 የሚሆኑ የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች የሞዴል ፈተናውን የሚወስድ መሆኑን  ተናግረዋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
180 ሺህ የሚጠጉ ዕጩ ተመራቂዎች በቀጣይ ወር የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና እንደሚወስዱ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በ208 የትምህርት ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና መዘጋጀቱን በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው የመውጫ ፈተና፣ ከሐምሌ 03 እስከ 08/2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለጹ ይታወቃል፡፡

"የመውጫ ፈተና የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ ይቀጥላል" ያሉት መሪ ሥራ አስፈጻሚው፤ በተቀመጠው መመሪያ መሠረት ተፈትነው 50 በመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች እንደሚያልፉ አስረድተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የሚሰጥ በመሆኑ የተማሪዎች ስም ዝርዝር ተልኮ ወደ ዳታ ማዕከል መግባቱንም ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎቻቸውን የምረቃ መርሃግብር ከመውጫ ፈተና በኋላ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎቹ ምርጫ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሲጠናቀቅ ማካሄድ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። #ኢፕድ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተከስቶ የነበረዉ የፀጥታ ችግር ተቀርፎ ሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ስራ ተጀመረ

በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠውን የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና አንፈተንም በሚል  በዋናው ግቢ በዉስጥ ተከስቶ የነበረዉ የፀጥታ ችግር ተቀርፎ ሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ስራ መጀመሩ ተገልጿል።

ከዩኒቨሲቲውም ሆነ የሚመለከታቸዉ የፀጥታ ተቋማት  እውቅና ውጪ ባልተፈቀደ ሁኔታ ሰኔ  03 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተደረገውን ሙከራ ተከትሎ በዩኒቨርሲቲዉ ሆነ በሰዉ ላይ ሊደርስ የሚችል ጉዳት ለማስቀረት የፀጥታ ኃይሉ ህግ የማስከበር ተግባሩን ማከናወኑን ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን  በጥቂት የማህበራዊ ሚዲያዎች የፀጥታ ችግር እንዳለና መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ላይ መስተጓጎል እንዳለ በማስመሰል የሚሰራጩ መረጃዎች  ሀሰተኛና ተቀባይነት የሌላቸዉ ናቸው ተብሏል።በመሆኑም የተማሪ ወላጆችና መላው ህብረተሰብ  መረዳት ያለባቸው ከተፈጠረው አነስተኛ ግጭት ውጪ በተማሪዎች ላይ ምንም የደረሰ ጉዳት የሌለ መሆኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ሀላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
15 የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በጊዜያዊነት ታገዱ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር 15 የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በጊዜያዊነት ማገዱን አሰታወቀ።

ከጥቅምት 14/2015 እስከ ታህሳስ 30/ 2015 ዓ.ም ድረስ 15 ኤጀንሲዎች ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ምንም አይነት ሪፖርት አለማድረጋቸውን ገልጿል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩ በላይ የዜጎችን መብትና ደህንነት እንዲጠበቅ በርካታ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡

በህግ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሰረት የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ዜጎችን ለሥራ ስምምነት ወደተደረሰባቸው መዳረሻ ሀገራት ለመላክ ፍቃድ በመውሰድ ወደ ሥራ እንዲገቡ ያደርጋል፡፡

ፍቃድ ወስደው የሚሰሩ የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችም በአዋጅ ቁጥር 923/08 እና በማስፈፀሚያ መመሪያ መሰረት ሊያሟሉ የሚገባቸውን አጠቃላይ እንቅስቃሴያቸውን ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡

በአዋጅ ቁጥር 923/08 መሰረት ድርጊቱ የሥራ ፈቃድ ስረዛ የሚያስከትል መሆኑን ጠቅሶ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎችን ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ አልቻሉም፡፡

ስለሆነም ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎ ከድርጊታቸው መማር እንዲችሉ ከግንቦት 11ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለመጨረሻ ጊዜ ለሦስት ወራት ታግደዋል ብሏል።

(ኢ ፕ ድ)
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot