STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.7K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
እስከ ሚያዚያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም እንድታቀርቡ

ለሁሉም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት !

በ2015 ዓ.ም ከሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመራቂ ተማሪዎቻችሁን መረጃ በተላከላችሁ የመረጃ መላኪያ ቅጽ መሠረት እስከ ሚያዚያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ለኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እንድታቀርቡ እያሳሰብን እስከ ተጠቀሰው ቀን መረጃውን የማያቀርብ ተቋም ኃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ለሚካሄደው የመውጫ ፈተና 30 ሺህ ኮምፒውተሮች ዝግጁ ሆነዋል

በመጪው ሀምሌ ወር በዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ለሚካሄደው የመውጫ ፈተና 30 ሺህ ኮምፒውተሮች ዝግጁ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።
ከ 240 ሺህ በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቋል።
በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ድግሪ የማይሰጣቸው በመሆኑ ተማሪዎች ለሚሰጠው ፈተና ራሳቸውን አንዲያዘጋጁ ኃላፊው አሳስበዋል።

በሀምሌ ወር ከሚሰጠው ፈተና በፊት በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ የሙከራ ፈተና እንደሚሰጥም ነው የተገለጸው።
በኦንላይን ፈተናው መሰጠቱ ኩረጃን ለማስቀረት፣ የወረቀት ወጪና ማጓጓዣን ለመቀነስ ይረዳል ብለዋል ኃላፊው።
ለፈተናው በአጠቃላይ ከ15 በላይ ኮርሶች በየትምህርት መስኩ ተወጣጥተው ዝግጁ መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ሰይድ ፤ የፈተናው ውጤት በኦንላይን ይፋ የሚደረግና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች ያለገደብ በተደጋጋሚ የመፈተን እድል እንደሚኖራቸው በመመሪያ መቀመጡን ነው ኃላፊው የገለጹት።
የመውጫ ፈተናው የተለየ ዓላማ የሌለው እና የተማሩትን ብቻ የሚመዝን በመሆኑ ሳይደናገጡ እንዲዘጋጁ ለተማሪዎች ጥሪ አቅርበዋል።
ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመፈተኛ ጣቢያ እንደሚሆኑም ኃላፊው ገልፀዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን አሰልጥኖ ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለማሰማራት እንቅስቃሴ መጀመሩን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ

የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን አሰልጥኖ ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለማሰማራት እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታወቀ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 85 ሺህ ዜጎችን ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለማሰማራት አቅዶ ማከናወን የቻለው 66 በመቶ ብቻ ነው ብሏል።
በዚህ ጊዜ ውስጥ ስድስት ሚሊዮን ዜጎች በስራ ፈላጊነት መመዘገባቸውንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Tigray

ከዓመታት በኃላ በትግራይ ያሉ #ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ምዝገበ እየተካሄደ ይገኛል።

የትግራይ ትምህርት ቢሮ  ለዓመታት በኮቪድ-19 እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር ከሚያዚያ 18 ጀምሮ ምዝገባ እንደሚከናወን እና ሚያዚያ 23 ትምህርት እንደሚጀመር ማሳወቁ የሚዘነጋ አይደለም።

ተማሪዎች ያለፋቸውን ጊዜ ለማካካስ በሳምንት 3 የትምህርት ፕሮግራሞች የነበሩትን ወደ 5 እና 6 በመቀየር አንድ ሴሚስተር የሚጨርሰውን ጊዜ ለማሳጠር እንደሚሰራ መነገሩም ይታወሳል።

በትግራይ ጦርነት ምክንያት ክፉኛ ከተጎዱት መካከል #ተማሪዎች ዋነኛዎቹ ሲሆኑ ተማሪዎች ለበርካታ ወራት ከትምህርት ርቀው ይገኛሉ።

እንደ ህፃናት አድን ድርጅት (Save the Children) መረጃ በትግራይ 2.3 ሚሊዮን ሕጻናት ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም።

ፎቶ ፦ ድምፂ ወያነ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
University of Miami Stamps Scholarship in USA 2023 | Fully Funded

Link: https://scholarshipscorner.website/university-of-miami-stamps-scholarship/

Benefits:

1) Tuition and fees
2) On-campus housing
3) A meal plan
4) University health insurance
5) Textbooks
6) A laptop allowance
7) Access to a $12,000 enrichment fund.

Deadline: November 1.
የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎቹ በስልክ ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳሰበ

በሰሜኑ ጦርነት ውድመት የደረሰበትና ከ35 ሺ በላይ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ የነበረው መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ከጦርነቱ በኋላ ስራ ለማስጀመር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል በነበረው ጦርነት ሳቢያ ለዓመታት የመማር ማስተማር ስራውን ያቋረጠው መቀሌ ዩኒቨርሲቲ አሁን የጥገና እና የመረጃ ማጣራት ስራዎችን እየሰራሁ ነው ብሏል።

በጥር ወር 2013 ዓ.ም መከላከያ ሰራዊት መቀሌ መግባቱን ተከትሎ በጊዜያዊ አስተዳደር አማካኝነት መደበኛ ትምህርት ማስተማር ጀምሮ የነበረው ዩኒቨርሲቲው የጦርነቱን ማገርሸት ተክትሎ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲቋረጥ የግድ ሆኗል።

የዩኒቨርሲቲው የትምህርት ክፍል ምክትል ኃላፊ ሳሙኤል ክፋሌ (ዶ/ር) ትምህርት ከመጀመሩ በፊት የጥገና፣ የበጀት ማስተካከል እና የአእምሮ ማነቃቂያ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል።

ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/mekelle/current-affairs-am/mekele-university-urged-its-former-students-to-report-by-phone

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከሚያስተምሩ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ለአራት ቀን የሚቆይ ውይይት በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ።

ውይይቱ በዛሬው እለት በ77 ክላስተሮች 63,470 መምህራን እና የትምህርት አመራሮችን ተሳታፊ በማድረግ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በዛሬው እለት ውይይቱን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸው በውይይቱ 1,368 ቡድኖች ከመደራጀታቸው ባሻገር 2,736 አወያዮች መመደባቸውን አስታውቀዋል።

ውይይቱ በዋናነት ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አመታት ያስመዘገበቻቸውን ውጤቶችና በሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መሰረት በማድረግ የሚካሄድ መሆኑን ዶክተር ዘላለም ገልጸው ለትምህርት ልማት ስራው ውጤታማነት መምህራንም ሆኑ የትምህርት አመራሮች የአንበሳውን ድርሻ እንደመውሰዳቸው የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የተማሪዎችን ውጤት እና ስነምግባር ለማሻሻል ውይይቱ የጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት መሆኑንም አስረድተዋል።

ውይይቱ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀን በክላስተር ደረጃ ተካሂዶ እሁድ እለት ከየትምህርት ቤቱ ከተውጣጡ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ጋር በየክፍለከተማው ተመሳሳይ ውይይት ከመካሄዱ ባሻገር እሁድ 500 የሚሆኑ መምህራን በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ ታላላቅ የልማት ስራዎችን የሚጎበኙበት መርሀ ግብር መዘጋጀቱን ኃላፊው ጠቁመው ሰኞ ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም በከተማ ደረጃ የአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት 5,000 ከሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
#ማሳሰቢያ

ለሁሉም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት !
በ2015 ዓ.ም ከሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exite Exame) የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመራቂ ተማሪዎቻችሁን መረጃ በተላከላችሁ የመረጃ መላኪያ ቅጽ መሠረት እስከ ሚያዚያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ለኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እንድታቀርቡ እያሳሰብን እስከ ተጠቀሰው ቀን መረጃውን የማያቀርብ ተቋም ኃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡


የኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoH

ጤና ሚኒስቴር በግንቦት 2015 ዓ.ም ለሚሰጠው የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ምዝገባው እስከ ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም ብቻ ይከናወናል።

የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ተቋማት ተመዛኞች hple.moh.gov.et ላይ በመግባት በኦንላይን እንድትመዘገቡ ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ከተጠቀሰው ጊዜ ውጪ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ #የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

የግል ትምህርት ተቋማት አዲስ ተመዛኞች ከምዝገባ በፊት የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በማረጋገጥ ስማችሁን ወደ ጤና ሚኒስቴር ማስላክ ይጠበቅባችኋል፡፡

ማንኛውም ተመዛኝ ምዝገባ ሲያደርግ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር የያዘ ወረቀት (ስሊፕ) print አድርጎ መያዝ ይጠበቅበታል። #ጤና_ሚኒስቴር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ትምህርት ቤቶችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በማሳደግ የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትን ለማስጠበቅ እየተሰራ ነው
-----------------------------
ሚያዚያ 20,2015ዓ.ም ( የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን አስመልክቶ ከክልልና ከተማ መስተዳደር ለተውጣጡ የትምህርት ባለሙዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።

የአቅም ግንባታ ስልጠናው ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኔስኮ-ሁዋዊ (UNESCO - Huawei) ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ነው የተሰጠው።

በስልጠናው ላይ የተገኙት የዩኔስኮ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዳይሬክተር ሪታ ቢሶናዝ (ዶ/ር) ስልጠናው ለትምህርት ባለሙያዎች በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ያላቸውን ክፍተት ለመሙላት አጋዥ መሆኑን ገልፀዋል።

በትምህርት ቴክኖሎጂ በቂ እውቀት ያላቸውን የትምህርት ባለሙያዎችን በማፍራት እና ት/ቤቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመገንባት የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትን ለማስጠበቅ የሚደረገውን ርብርብ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ከድር ኡርጂ በበኩላቸው የትምህርት ስርአቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በተጠናከረ መልኩ ለመደገፍ የሚያስችሉ ስራዎችን በትኩረት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር እያከናወናቸው ካሉ የለውጥ ስራዎች መካከል አንዱ ዲጂታላይዜሽን ሲሆን በዘርፉም በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የኢንተርኔት አገልግሎት ላለፉት ሁለት ሳምንታት መቋረጡ በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው እንደሚገኝ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ፡፡

አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ከመምህራን የሚሰጣቸውን የቤት ሥራም ሆነ በግላቸው የሚፈልጉትን ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት መቸገራቸውን ተማሪዎቹ ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳን ከየካቲት ወር ጀምሮ በመላ አገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠ ቢሆንም፤ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ግን አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በወልድያ፣ በቆቦ እና በአላማጣ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ #ሪፖርተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot