STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
2.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል አሁንም ከትምህርት ገበታ ውጪ እንደሆኑ "ሴቭ ዘ ችልድረን" የተባለው ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ተቋም ገለጸ፡፡

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍሎች የመልሶ ግንባታ ሥራዎች ባለመጀመራቸው ምክንያት 2.3 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ተማሪዎች አሁንም ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን ድርጅቱ ገልጿል፡፡

የመማሪያ ክፍሎች እንደገና ተከፍተው ተማሪዎችን ያስተናግዱ ዘንድ አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል ተቋሙ።

በመላ ሀገሪቱ ከ 3.5 ሚሊዮን በላይ ህጻናት (ከ16 ህጻናት አንድ) ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ድርጅቱ አመልክቷል።

ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑት ህጻናቱ፤ ለጉልበት ብዝበዛ፣ ለጾታዊ ጥቃት እና ላልተፈለገ ጋብቻ ተጋላጭ እንደሚሆኑ ድርጅቱ ስጋቱን ገልጿል።

በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ውድመት አስተናግደዋል።

በትግራይ ክልል 85 በመቶ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የተጎዱ ሲሆኑ የመንግስት ትምህርት ቤቶች አሁንም ዝግ መሆናቸውን የድርጅቱ መረጃ ያሳያል።

22, ሺህ 500 መምህራን ከሁለት ዓመት በላይ ደመወዝ ሳይከፈላቸው እንደቆዩም ድርጅቱ አስታውሷል።

ምንጭ፦ Save the Children

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoH

የጤና ሚኒስቴር በ10ኛ ዙር የሰጠውን የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከወሰዱ ውስጥ 45.7 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ማለፋቸው ተገለጸ።

ሚኒስቴሩ በ2015 ዓ.ም ጥር ወር የሰጠውን የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ውጤት ይፋ አድርጓል።

ለፈተና ከተቀመጡቱ 19,681 ውስጥ 8,993 ተፈታኞች ፈተናውን ያለፉ ሲሆን ይህም 45.7 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ማለፋቸውን ያሳያል፡፡

የብቃት ምዘና ፈተናውን ከወሰዱ የመንግስት ተማሪዎች ውስጥ 60.7 በመቶ የሚሆኑት ያለፉ ሲሆን በግል ከተፈተኑ ተማሪዎች ደግሞ 34.5 በመቶ የሚሆኑት ማለፋቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

በአጠቃላይ 21 ሺ ባለሙያዎች ለፈተና የተመዘገቡ ሲሆን 19,681 ተመዛኞች ፈተናውን መውሰዳቸው ታውቋል።

ሞባይል ስልክ እና ለሌላ ሰው ለመፈተን የሞከሩ 40 ተፈታኞች ከፈተናው እንዲታገዱ መደረጉም ተገልጿል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ የመጀመሪያ መደበኛ ጉባኤውን አድርጓል።

ካውንስሉ ወቅታዊና አግባብነት ባላላቸው ጉዳዮች ላይ መክሯል።

ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከፌደራል ተቋማት ጋር እስካሁን የተደረጉ ውይይቶች ያሉበት ሁኔታ ላይ ገለጻ ተደርጓል።

የተማሪ አገልግሎት መስጫ አቅርቦቶች፣ ሀብት የማሰባሰብ ጥረቶች፣ ደመወዝ ያልተከፈላቸው ሰራተኞች ጉዳይ ሌሎች ውይይት የተደረገባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ለተቋሙ ሰራተኞች የስነ-ልቦና ቴራፒ አስፈላጊነት ላይ አፅንሆት የሰጠው ውይይቱ፤ ተማሪዎች ዳግም ለመቀበል ያለውን ዝግጁነት አረጋግጧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ETA

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የስነ-ስርዓት ጥሰት በሚፈጽሙ ተቋማት ላይ አስተማሪ ቅጣት ለማሳለፍ የሚያስችለውን የስነ-ስርዓት መመሪያ አሻሽሏል።

መመሪያው በቅርቡ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ በባለሥልጣኑ የፈቃድ እና ጥራት ኦዲት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ውብሸት ታደለ በተለይ ለቲክቫህ ተናግረዋል።

አዲሱ መመሪያ የስነ-ስርዓት ጥሰት በሚፈጽሙ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ጠንካራ፣ ተመጣጣኝ እና የሚያስተምር እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

ተደጋጋሚ ጥፋት በሚፈጽሙ ተቋማት ላይ ፈቃድ መሰረዝ እና ማዘጋት እርምጃዎችም ይወሰዳሉ ብለዋል።

ተቋማቱ ከሚነሱባቸው የስነ-ስርዓት ጥሰቶች መካከል
ፈቃድ ባልተሰጣቸው የትምህርት መስኮችና ካምፓሶች ማስተማርን ጨምሮ ከተፈቀደላቸው ቁጥር በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይገኙበታል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
እንኳን አደረሳችሁ !

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ አባላት በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

Team :@NATIONALEXAMSRESULT
ዶ/ር ታዘባቸው "ትምህርቱን ከአራተኛ ዓመት እንዲቀጥል" ተወስኖለታል፡፡

ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በህክምና የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው ዶ/ር ታዘባቸው ውዴ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማህፀንና ፅንስ ሬዚደንትነት ትምህርቱን ሲከታተል ቆይቷል፡፡

ዶ/ር ታዘባቸው ስፔሻላይዜሽን ትምህርቱን ለማጠናቀቅ ሁለት ወራት ሲቀረው በአንደኛው አይኑ ላይ ባለበት መሸዋረር ምክንያት ትምህርቱን እንዲያቆም መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡ ወደሌላ የትምህርት ክፍል ተዘዋውሮ ከአንደኛ ዓመት እንዲጀምር መወሰኑም አይዘነጋም፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ እና የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የባለሙያዎች ቡድን በማቋቋም የዶ/ር ታዘባቸውን ቅሬታ ሲመረምር ቆይቷል፡፡

የባለሙያዎች ቡድን የቀረቡለትን መረጃና ማስረጃዎች ከመረመሩና እንደገና የማጣራት ሥራ ካከናወኑ በኋላ ዶ/ር ታዘባቸው ወደ ትምህርቱ እንዲመለስ የውሳኔ ምክረ ሃሳባቸውን ለዩኒቨርሲቲው ቦርድ አቅርበዋል።

የዩኒቨርስቲው ቦርድም የባለሙያዎቹን ውሳኔ መሰረት በማድረግ ዶ/ር ታዘባቸው ትምህርቱን ከአራተኛ ዓመት እንዲቀጥል ወስኗል፡፡

ዶ/ር ታዘባቸው ትምህርቱን አቋርጦ በቆየበት ወቅት ድጋፍ ላደረጉለትና ውሳኔውን በመቃወም ለተሟገቱለት አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡ #Hakim

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎችን የሚያቋቁመው ረቂቅ አዋጅ በርካታ አደረጃጀቶችን ይዞ መምጣቱ ጥያቄ አስነስቷል።

የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎችን ለማደራጀት በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ፤ ቻንስለር፣ የሥራ አመራር ቦርድ፣ ፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ ሴኔት፣ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል፣ ማኔጂንግ ካውንስል እና ሌሎችም መዋቅሮችም እንደሚኖሩ ተብራርቷል፡፡

በትምህርት ተቋማቱ ይዋቀራሉ ተብለው የታሰቡት አደረጃጀቶች መብዛት በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሥራ መጠላለፍና መደራረብ ይፈጥራል የሚል ስጋት እንዳለባቸው ምሁራን ገለጹ፡፡

በረቂቅ አዋጁ ላይ ግብዓት ለመሰብሰብ ከዩኒቨርሲቲ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከትምህርት ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

የአደረጃጀቶች መብዛት የኃላፊነት መጣረስ እንዳያመጣ
እና ለውሳኔ አሰጣጥ ክፍተት እንዳይፈጥር ተሳታፊዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አደረጃጀቶቹ የተለያየ ኃላፊነት እንደሚኖራቸው ተናግረዋል፡፡

የቦርድ አወቃቀሩም ጠንካራ የሆኑና የዩኒቨርሲቲን ሥራ የሚያውቁ ሰዎች በያዘ መልኩ እንደሚደራጅ ጠቁመዋል። #ሪፖርተር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ቦንጋ

ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ ትምህርት መስክ የተማሩ ተማሪዎች ሊመረቁ ነው።

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፤ በ2015 የትምህርት ዘመን መጨረሻ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ 37 ተማሪዎችን በ " ቡና ሳይንስ " የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን ተማሪዎች እንደሚያስመርቅ አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው የቡና ምርት ኢትዮጵያ ትልቁ የውጭ ምንዛሬ የምታገኝበት ሸቀጥ በመሆኑ በ2015 ዓ.ም መጨረሻ 37 ተማሪዎችን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ የትምህርት መስክ ይመረቃሉ ብሏል።

ኢትዮጵያ ቡናን ለዓለም ያበረከተች ሀገር ብትሆንም እስካሁን ድረስ የቡና ትምህርት መስክ ብቁ ባለሙያዎችን ማፍራት አዳጋች ሆኖ ነበር ያለው ተቋሙ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቡና ሳይንስ ትምህርት ክፍል እራሱን ችሎ በ2012 ዓ.ም እንዲከፈት ማድረጉን አስታውሷል ።

በቡና ምርት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመመርመር ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን ቡናን በትምህርትና ምርምር አስደግፎ ለመምራት ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ የቡና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል በማቋቋም ነው ተማሪዎችን እያስተማረ የሚገኘው።

በሚቀጥለው ዓመት በሁለተኛ ዲግሪ በቡና ሳይንስ ተማሪዎች የሚመረቁ ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ጊዜትም የቡና ሳይንስ ትምህርት መስክን በዶክትሬት ዲግሪ ደረጃ ማስተማር እንደሚጀምር ዶክተር ጴጥሮስ ጠቁመዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ካለው 200 ሄክታር መሬት ውስጥ በ150 ሄክታሩ ላይ የግብርና ምርቶችን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።

#ኢፕድ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ማስታወቂያ

የተባበሩት ኤምሬትስ የሰጠውን ስኮላርሽፕ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ ተማሪዎች ሁሉ
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ለመስጠት በፈቀደው መሰረት ቀደም ሲል በተማሪዎች ቃል የተገባላችሁ ተማሪዎችና በዕድሉ ለመጠቀም ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች Application Form link:
http://survey.ethernet.edu.et/index.php/518562?lang=en --
በመግባት ከዛሬ 09/08/15 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 ቀናት ከላይ በተቀመጠው ሊንክ በመግባት፡-
1. የ12ኛ ክፍል የማትሪክ ውጤት ኮፒ (Grade 12 Result) copy
2. ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኮፒ (Grade 9-12 transcript) copy
3. CV/ Curriculum Vitae copy
4. የልደት የምስክር ወረቀት ኮፒ (Birth Certificate) copy እና ሌሎች በሊንኩ የተጠቀሱ መረጃዎችን እንድትሞሉ እናሳስባለን ።
መረጃዎች ተጣርተው ለፈተና የሚቀረቡ ተማሪዎችን ስም ዝርዝር በቀጣይ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የምናሳውቅ መሆናችንን እንገልጻለን።
የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር
አዲስ አበባ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ETA

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በርቀት መርሐ ግብር በ2ኛ ዲግሪ ፕሮግራም በሚያስተምሩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ዕርምጃ ይወስዳል።

በርቀት መርሐ ግብር በ2ኛ ዲግሪ ፕሮግራም ማስተማር የማይቻል መሆኑን የገለጸው ባለሥልጣኑ፤ ተማተማሪዎች ሲመዘግቡም ሆነ ሲያስተምሩ በሚገኙ ተቋማት ላይ ጠበቅ ያለ ዕርምጃ ይወሰዳል ብሏል።

በተመሳሳይ በየትኛውም መርሐ ግብር በሕግ፣ በግብርና እና በመምህራን ትምህርት ስልጠና መስጠት እንደማይቻል ባለሥልጣኑ አስታውሷል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በትግራይ ክልል ትምህርት ሊጀመር ነው

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የክልሉ ትምህርት ቢሮ በመጭው ሚያዝያ 23 የመማር ማስተማር ሥራ ይጀምራሉ ማለቱን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

በዕለቱ ትምህርት የሚጀምሩት፣ በክልሉ የሚገኙ ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍሎች የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች በሙሉ እንደኾኑ ዘገባው አመልክቷል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#RayaUniversity

በራያ ዩንቨርሲቲ መደበኛ ትምህርት ስትከታተሉ ቆይታቹህ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ትምህርታችሁን ላቋረጣቹህ ተማሪዎች በሙሉ፣

በራያ ዩንቨርሲቲ በመደበኛ ፕሮግራም ከ2ኛ እስከ 5ኛ ዓመት ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁና ወደ ሌሎች ዩንቨርሲቲዎች ተመድባቹህ የመማር ዕድል #ያላገኛቹህ ተማሪዎች በስራ ሰዓት ብቻ ከ09-13/2015 ድረስ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች እየደወላቹህ ተመዝገቡ።
👇👇👇👇👇
# Raya University registration
የራያ ዩኒቨርስቲ ምዝገባ ከ 09-13/08/2015
via 1.0970140000
2.0970240000
3.0970230000
N.b-በስራ ቀንና በስራ ሰዓት ብቻ‼️

ዩንቨርሲቲው ሙሉ ዝግጅቱን ሲያጠናቅቅ የግቢ መግቢያ ቀንን በመገናኛ ብዙሃን እንደሚያሳውቅ ገልጿል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
አራት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በፌስቡክ ማንነቱን ቀይሮ በመተዋወቅ ‘‘ካናዳ እና እንግሊዝ እወስዳችኋለው’’ በማለት ጾታዊ ግንኙነት እንዲፈጽሙ አድርጓል የተባለው ግለሰብ በጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ።

ግለሰቡ ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ እና 20 ግራም ወርቅ ተቀብሎ የማታለል ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ ነው በጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ የተወሰነው። የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 2ኛ አርቲዲ ወንጀል ችሎት ሲሆን÷ተከሳሹ ታዲዮስ ዘላለም በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ነዋሪ ነው።

ተማሪዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጽ “ናቲ መላኩ” ብሎ ማንነቱን ቀይሮ በካናዳ ነዋሪ በመምሰል ከተዋወቃቸው በኋላ ‘’ካናዳና እንግሊዝ እወስዳችኋለው’’ ብሎ የማታለል ተግባር መፈጸሙ በክሱ ተመላክቷል። ከዚህም በኋላ ተከሳሹ ከካናዳ ወደ አዲስ አበባ እንደመጣ በማስመሰል በግንቦትና በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም በተለያዩ ቀናቶች ለ4 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የግል ተበዳዮች ስልክ ይደውላል፡፡ በዚህም'' ከእንግሊዝ ኤምባሲ ጉዳይ የሚፈጽምላችሁ ሰው ይመጣል፤ አሻራ የሚወሰደው ከዘር ፈሳሽ እና ከወርቅ ስለሆነ አልጋ ይዛችሁ ጠብቁ በማለት'' የግል ተበዳዮች በተለያየ ቀናቶች በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አልጋ ይዘው እንዲጠብቁ ማድረጉ በክሱ ተጠቅሷል።

አልጋ እንዲይዙ ካደረገ በኋላ ማንነቱን ቀይሮ ወደ አልጋ ቤት በመሄድ የግብረስጋ ግንኙነት እንዲፈጽሙ ማድረጉም በክሱ ተመላክቷል።

በተጨማሪም ተከሳሹ ከግል ተበዳይ ተማሪዎች ከእያንዳንዳቸው የተለያየ መጠን ያለው በአጠቃላይ 20 ነጥብ 7 ግራም ወርቅ ለአሻራ ምርመራ ያስፈልጋል ብሎ መውሰዱ በክሱ ተገልጿል፡፡ ለጉዳይ ማስፈጸሚያ በሚል ከእያንዳንዳቸው ግማሽ ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ መቀበሉም በክሱ ተዘርዝሯል።

ተከሳሹ ከግል ተበዳዮች መካከል ከአንደኛዋ ተማሪ ጉዳይ ለማስፈጸም "አይፎን "ሞባይል ስልክ ያስፈልጋል በማለት እንድታመጣ በማዘዝ የስልክ ቀፎውን ለመቀበል በቀጠራት ዕለት ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ በኦፕሬሽን ክትትል በቁጥጥር ስር መዋሉ  በክሱ ተመላክቷል። በዚህም ተከሳሹ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 692/1 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በማታለል ወንጀል ተደራራቢ አራት ክሶች ቀርቦበታል።

ተከሳሹ ክሱ ከደረሰውና በችሎት በንባብ ከተሰማ በኋላ ወንጀሉን አልፈጸምኩም ሲል የዕምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል። የፍትህ ሚኒስቴር የቦሌ ምድብ ዓቃቤ ሕግ ለወንጀሉ መፈጸም ያስረዳሉ ያላቸውን የግል ተበዳዮችን ጨምሮ 6 ምስክሮችን በችሎት አቅርቦ የምስክርነት ቃላቸውን አሰምቷል።

ፍርድ ቤቱ የምስክር ቃል መርምሮ ተከሳሹ ወንጀሉን መፈጸሙ በዐቃቤ ሕግ ምስክር ቃል ማረጋገጡን በመግለጽ ተከሳሹ በተከሰሰበት አንቀጽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ ነበር። ይሁንና ተከሳሹ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መከላከል ባለመቻሉ በመጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተከሰሰበት በአራት ክሶች በአንቀጽ 692 (1) ስር የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎበታል።

ተከሳሹ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጉን ለህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዢ መፈጸሙን እንዲሁም ለማህበራዊ በጎ አድራጎት  ያበረከተውን አስተዋጾን የሚገልጽ   ከቦሌ ክ/ከ ወረዳ 13  ጽዳት አስተዳደርና ከዚሁ ወረዳ ከሴቶችና ሕጻናት ቢሮ የተሰጠውን ማስረጃ ጨምሮ  አራት የቅጣት ማቅለያ አስተያየት አቅርቦ በፍርድ ቤቱ ተይዞለታል።

በዐቃቤ ሕግ በኩል ግን የቅጣት ማክበጃ አስተያየት አለመቅረቡን የችሎቱ ዳኛ ገልጸዋል።

በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት በደረጃ ስድስት በዕርከን 25 መነሻ በ7 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነ ሲሆን÷በዕርከን 3 መሰረት ደግሞ በ3 ሺህ ብር የገንዘብ እንዲቀጣ ተወስኗል። ቅጣቱን የአዲስ አበባ  ማረሚያ ቤት እንዲያስፈጽም የታዘዘ ሲሆን÷የቅጣት ውሳኔ ሲወሰን የግል ተበዳይ ከሆኑት ተማሪዎች መካከል ሁለቱ በችሎት ተገኝተው ቅጣቱን ተከታትለዋል።(በታሪክ አዱኛ)

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም በዓል ❤️


Team : @NATIONALEXAMSRESULT
የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ዝግጁ እንዲሆኑ አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን የመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ገለጹ

የትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ዓመት የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና እንደሚሰጥ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

መውጫ ፈተናው ተማሪዎች በሰለጠኑባቸው የሙያ ዘርፎች ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ፡፡

የመውጫ ፈተና በኦንላይን ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚሰጥ ሲሆን ኢዜአ ያነጋገራቸው የመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር መውጫ ፈተናውን ለመስጠት ተዘጋጅተዋል፡፡

የጅማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ መውጫ ፈተና ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የሚጠቀሙባቸውን እውቀት ክህሎትና አመለካከት በብቃት መያዛቸውን መለኪያ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን ዩኒቨርስቲዎች በትምህርት አሰጣጥ ላይ ያሉበትን ሁኔታ በማሳየት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ሚናው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ የመውጫ ፈተናውን በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱንና አስፈላጊውን ግብዓት የማሟላት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ከዚህ ጎን ለጎንም ተፈታኞችን በእውቀትና በስነልቦና የማዘጋጀት ስራ መሰራቱንም ጠቅሰዋል፡፡

የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኝ በበኩላቸው የመውጫ ፈተና ውጤት ፍትሀዊነትን የሚመልስ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናው የመጀመሪያው እንደመሆኑ መጠን ለተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫና ድጋፍ ለሚፈልጉ ተማሪዎች ድጋፍ የማድረግ ስራ እየተሰራ ስለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፈተናው የሚሰጥባቸውን የትኩረት መስኮች በመለየት የማጠናከሪያ ፕሮግራም እየተሰጠ ነው ያሉት ደግሞ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳምጠው ደርዛ ናቸው፡፡

ጎን ለጎንም ለሴቶችና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ ተኩረት ተሰጥቶ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡

የከፍተኛ ትምህርት አገራዊ ቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የተዘጋጀው የፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ ባለፈው ዓመት ነሀሴ ወር ላይ መጽደቁ ይታወሳል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ተማሪዎች ቅሬታ

በወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ መብራት ከጠፋ #40 አካባቢ ማለፉን ተከትሎ በግቢው ውስጥ የሚገኙ ከ1500 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ባለፉት ቀናት ተደጋጋሚ ቅሬታዎችን ሲያሰሙ ቆይተዋል። በርካታ ተማሪዎች ጨለማ ላይ እንደሚገኙና ትምህርታቸውን ለመከታተልም እያዳገታቸው እንደሆነ ለATC ሲገልፁ ሰንብተዋል።

ይህ የመብራት ለበርካታ ሳምንታት መቋረጥ ያስመረራቸው የግቢው ተማሪዎች በትላንትናው ዕለት ሻንጣቸውን በመያዝ ከግቢ ለመውጣት የሞከሩ ቢሆንም የፌደራል የፀጥታ ኃይሎች ከግቢ እንዳይወጡ እይዳደረጓቸው ገልፀውልናል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአንድ ወር በላይ በዞኑ ተቋርጦ የነበረው የመብራት አገልግሎት ከሰዓታት በኋላ እንደሚለቀቅ የዞኑ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot