STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#Amhara-Tigray‼️
በትግራይ የትምህርት ሁኔታ ለመምከር በሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የተመራ የፌደራል የልዑካን ቡድን መቀሌ ገብቷል።
የመቀሌ ዩንቨርስቲ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ፕሮፈሰር ክንድያና ገብረህይወት የባህርዳር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው፣የደብብርሃን ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ንጉስ ታደሰን ጨምሮ በመቀሌ ተገናኝተው እንዲህ ተቃቅፈዋል።
ከትምህርት ባሻገር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን በዚህ መልኩ ተጀምሯል

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊዎች እና የተለያዩ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮች የመቐለ ዩኒቨርሲቲን ጎብኝተዋል።

አመራሮቹ የተፈናቀሉ ዜጎች መቆያ ማዕከላትንም ጎብኝተዋል።

ጉብኝቶቹን ተከትሎ ልዑካኑ በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየው ጠቅላላ እና ከፍተኛ ትምህርት ያለበትን ሁኔታ ገምግመዋል።

የአመራሮቹ ውይይት ነገ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በአፋር ክልል ስምንት ሺህ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ሊመለሱ ነው፡፡

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው የቆዩ ስምንት ሺህ ተማሪዎች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንደሚመለሱ የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በክልሉ ሁለት ወረዳዎች (መጋሌ እና አባላ) ትምህርታቸውን አቋርጠው የቆዩ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ የትምህርት ቁሳቁሶችን የማሟላትና ሼዶችን የመገንባት ሥራ እንደተሰራ የቢሮው ኃላፊ አብዱሀሰን ያዬ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ለሴቶች፣ ልዩ ፍላጎት ላላቸውና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እየተሰራ ነው፡፡
……………………………………………

መጋቢት 28/2015ዓም.(የትምህርት ሚኒስቴር) ፡ትምህርት ሚኒስቴር ለሴቶች፣ ልዩ ፍላጎት ላላቸውና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች በመውጫ ፈተና ወቅት ምቹ ሁኔታ መፍጠር በሚቻልበት ሂደት ላይ ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከተውጣጡ የዘርፉ ኃላፊዎች ጋር ምክክር አካሂዷል፡፡

በምክክር መድረኩ የትምህርት ሚኒስቴር የሴቶች ማህበራዊ ጉዳይና አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ታምሩ የትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ያለውን የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ በርካታ የሪፎርም ስራዎችን እየሰራ እንዳለ ጠቅሰው ከዚህ ውስጥ አንደኛው የመውጫ ፈተና ነው ብለዋል፡፡

በመውጫ ፈተናው ከስርዓተ ፆታ አንፃር እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውና ልዩ ድጋፍ የሚፈልጉ ተመራቂ ተማሪዎችን እኩል እንዲሳተፉ ምቹ የፈተና አካባቢ በመፍጠር ውጤታማ እንዲሆኑ ማድረግ ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚጠበቅም ገልፀዋል።

በዝግጅት ምዕራፍ፣ ከመፈተኛ ቦታዎች፣ ከመፈተኛ ቁሳቁሶች እንዲሁም በፈተና ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ የሰርዓተ ፆታ ጉዳዮች ለይቶ ከወዲሁ መፍታት እንደሚገባም ተገልጿል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#AddisAbabaEducationBureau

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሞዴል ፈተና ለ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች እየሰጠ ነው።

ሞዴል ፈተናው ዛሬ መጋቢት 29/2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀው ሞዴል ፈተናው፤ ተማሪዎች ራሳቸውን ለዋናው ፈተና ዝግጁ እንዲያደርጉ ያስችላል ተብሏል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችንና ትምህርት ቤቶች ትምህርት ለማስጀመር ሁሉን አቀፍ ዝግጅት እየተደረገ ነው‼️

በትግራይ ክልል የሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎችን እና አጠቃላይ መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር የስርዓተ ትምህርትና የመምህራን ዝግጅት እየተደረገ ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች፣ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶችና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች በክልሉ ትምህርት ማስጀመር የሚያስችል ውይይት አድርገዋል።

መንግስትና ህወሃት በፕሪቶሪያ የደረሱትን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ከማቅረብ ጀምሮ የክልሉን ህዝብ በዘላቂነት ማቋቋም የሚያስችሉ የመልሶ ግንባታና መሰረታዊ አገልግሎቶች እየተሰጡ ነው።

መንግስት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም፣ የታጠቁ ኃይሎች ትጥቅ ፈትተው ወደ መደበኛ ህይወት እንዲመለሱ፣ መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ፣ እንዲሁም ትምህርት እንዲጀመር የሰላም ስምምነቱን እየተገበረ ነው።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በውይይቱ ላይ እንዳሉት፣ በግጭቱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የዩኒቨርሲቲዎችና አጠቃላይ መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ ነው።

በዚህም የትምህርት ተቋማት የደረሰባቸውን የጉዳት መጠን በማጥናት ትምህርት ለመጀመር የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን ለይተን ቅድመ ዝግጅት ጀምረናል ብለዋል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምሽት ግቢ መግቢያ ሰዓት ወደ 1:00 ተቀይሯል‼️

እንደሚታወቀው በቅርቡ የምሽት የበር መግቢያ ሰዓት ወደ 2:00 መሸሻሉ ይታወቃል።ይሁንና
አሁን ባለው ወቅታዊ አለመረጋጋት ምክንያት ለተማሪዎቻችን ደህንነት ሲባል የበር መግቢያ ሰዓት ለጊዜው ወደ 👉 1:00 የተቀየረ መሆኑን ከዩንቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው የትምህርት ተቋማትን ዳግም ሥራ ለማስጀመር ሁሉም አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉና እንዲተባበሩ የዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች ጥሪ አቀረቡ።

በትግራይ ክልል ሥራ ያቆሙ ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ሥራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

በዚህም መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎችን ዳግም ሥራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩን ኢዜአ ያነጋገራቸው የዩኒቨርሲቲዎች የሥራ ኃላፊዎች ገልጸዋል።

ተቋማቱን ሥራ ለማስጀመር ከትምህርት ሚኒስቴር ፈቃድ በተጨማሪ ለመማር ማስተማር አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ለማሟላት በጀት ሊመደብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በመሆኑም ሁሉም አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉና እንዲተባበሩ የዩኒቨርሲቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮቹ ጥሪ አቅርበዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🕊 ሠላም ለሀገራችን 🕊
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በክልሉ በ126 ሚሊዮን ብር ወጪ 25 ትምህርት ቤቶች ተጠግነዋል
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ጉዳት ከደረሰባቸው ተቋማት መካከል የ25ቱ ትምህርት ቤቶች ጥገና ከ126 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ መከናወኑን የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=96402

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ወደ ፊት የሚቋቋሙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች፤ ራስ ገዝ ሆነው እንደሚደራጁ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

በፌደራል መንግስት ወደ ፊት የሚቋቋሙ አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች፤ ራስ ገዝ ሆነው እንደሚደራጁ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተናገሩ። ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከሚገቡ ተማሪዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት፤ ከፍለው የሚማሩ መሆን እንዳለባቸውም ሚኒስቴር ዴኤታው አስታውቀዋል።

ዶ/ር ሳሙኤል ይህን ያሉት፤ ስለ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎችን ለመደንግግ በወጣው የአዋጅ ረቂቅ ላይ በተጠራ የአስረጂ መድረክ ላይ ነው። በተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ ዛሬ ሰኞ ሚያዚያ 2፤ 2015 የተደረገውን ይህን የአስረጂ መድረክ የጠራው፤ የፓርላማው የሰው ሃብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ነው።

የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታው ዶ/ር ሳሙኤል በዚሁ መድረክ ላይ ባቀረቡት ገለጻ፤ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ የሚሆኑበትን ሂደት አብራርተዋል። “አዋጁ ባስቀመጠው መልኩ ዩኒቨርሲቲዎች መስፈርት ሲያሟሉ፤ ደንቦቻቸው በዚህ አዋጅ መሰረት መልሶ እንዲከለስ ይደረግ እና ራስ ገዝ ሆነው መልሰው ይደራጃሉ” ብለዋል። ለፓርላማው የቀረበው የአዋጅ ረቂቅ፤ “ጠንካራ የፋይናንስ አቅም እና አካዳሚያዊ ተወዳዳሪነት” ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ከሚያበቁ መስፈርቶች መካከል እንደሚካተቱ አስፍሯል።

ይህ አዋጅ በፓርላማ ከጸደቀ በኋላ “ራስ ገዝ” የሚሆኑት፤ አሁን በትምህርት ሚኒስቴር ስር የሚተዳደሩ ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ አለመሆናቸውን ዶ/ር ሳሙኤል በዛሬው ማብራሪያቸው ጠቁመዋል። “መስፈርቱን አሟልተው የሚፈጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች ሲኖሩ፣ ወደፊት አዲስም ቢሆኑ፤ እንደራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ይደራጃሉ” ሲሉ አዋጁ ወደፊት የሚቋቋሙ ዩኒቨርሲቲዎችንም የሚመለከት መሆኑን ሚኒስቴር ዴኤታው አስረድተዋል።
Ethio Insider

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#AdigratUniversity

አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የደረሰበት ጉዳት ሦሥት ቢሊዮን ብር እንደሚደርስ አሳውቋል።

በርካታ የዩኒቨርሲቲው የማስተማሪያ ግብዓቶች ዝርፊያ እንደተፈጸመባቸው የሪፖርተር ምንጮች ተናግረዋል።

ቤተመጻሕፍትን ጨምሮ ከ20 በላይ የተቋሙ ህንፃዎች በጦርነቱ ውድመት እንደደረሰባቸው የዩኒቨርሲቲው አስተዳዳሪዎች ለሪፖርተር እንግሊዝኛ አሳውቀዋል።

በክልሉ ትምህርት በድጋሜ ለማስጀመር ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ረዳኤ ኀለፎም ገልጸዋል።

ሙሉውን ለማንበብ፦ https://www.thereporterethiopia.com/32963/

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ረቂቅ አዋጁ   ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዲያካትት ተደርጎ መዘጋጀት አለበት
፦የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ
...............................................................................

ሚያዚያ 6/2015 ዓ.ም.(የትምህርት ሚኒስቴር)፣   በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በትናንትና ውሎው የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ረቂቅ አዋጁ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዲያካትት ተደርጎ በጥንቃቄ መዘጋጀት እንዳለበት አሳስቧል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) እንዳሉት ረቂቅ አዋጁ የዩኒቨርሲቲዎችን አካዳሚክ ነፃነት የሚያጎናፅፍ ቢሆንም ከመንግሥትም ሆነ ከግል ዩኒቨርሲቲዎች የሚመረቁ ተማሪዎች ላይ ቅሬታ እንዳይፈጥር የዩኒቨርሲቲዎችን ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የኅብረተሰቡን ፍላጎትም ያካተቱ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡

የተከበሩ ዶክተር ነገሪ አክለውም የቦርድ አባላት፣ ፕሬዚዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶና ሌሎች የዩኒቨርሲቲዎቹ አመራሮች ስብጥር ፆታዊ ብቻ ሳይሆን ሕብረ-ብሔራዊነትን እንዲያካትቱም በረቂቅ አዋጁ መመላከት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

በየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚሠሩ የአስተዳደር ሠራተኞች ትኩረት እንደማይሰጣቸው በየጊዜው ቅሬታ ስለሚያነሱ ረቂቅ አዋጁ ለአካዳሚክ ሠራተኞች የሚሰጠውን ትኩረት ለአስተዳደር ሠራተኞችም መስጠት እንዳለበት ዶክተር ነገሪ አስታውሰው፤ የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የገንዘብ አቅም ያላቸውን ብቻ እንዲያስተምሩ ተደርገው የሚቋቋሙ ከሆነ የፍትሐዊነት ጥያቄ ስለሚያስነሳ ረቂቅ አዋጁ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች በፍትሐዊነት እንዲያስተናግድ ተደርጎ መዘጋጀት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ መስማት የተሳናቸውን ብቻ ሳይሆን ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ሌሎች ተማሪዎችንም እንዲያካትት ተደረጎ መዘጋጀት እንዳለበት የተከበሩ ዶክተር ነገሪ ጨምረው ጠቁመዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ዶክተር ቤተልሔም ላቀውም በበኩላቸው የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ኃብት ከማመንጨት ባሻገር ለትምህርት ጥራት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ እና የመማሪያ ሆስፒታሎች ላሏቸው ዩኒቨርሲቲዎች ረቂቅ አዋጁ ትኩረት እንዲሰጣቸው የተከበሩ ዶክተር ቤተልሔም ጨምረው አመላክተዋል፡፡

የምክር ቤት አባላትም በበኩላቸው የሚቋቋሙት ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የግዥና ንብረት የማስተዳደር ሥርዓታቸውን በግዥ ሥርዓትና የንብረት አስተዳደር ሕግ መሠረት እንዲያደርጉና የኦዲት አደራረግ ሥርዓትን እንዲያመላክት ተደርጎ በረቂቅ አዋጁ መካተት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው የሚቋቋሙት የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ምቹ የአመራርና የአስተዳደር ሥርዓት እና የአካዳሚክ ነፃነት እንዲኖራቸው በማድረግ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ከዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተወዳዳሪ ለማድረግ ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን ጠቁመው፤ ረቂቅ አዋጁም ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች በፍትሐዊነት እንዲያገልግል ተደርጎ የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መስፈርቱን ሲያሟሉ ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆኑ ጠቁመው፤ በአንፃራዊነት የረጅም ዓመታት ልምድና የተሻለ ኃብት ባለው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጀመር በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ደግሞ ስምንት ዩኒቨርሲቲዎችን የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች በምልክት ቋንቋ ትምህርት ለመስጠት በረቂቅ አዋጁ የተመላከተ ቢሆንም ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ግን በሚወጡት መመሪያዎች የሚካተቱ መሆኑን አመላክተው፤ ረቂቅ አዋጁ የሕዝብን፣ የመንግሥትንና የዩኒቨርሲቲዎችን ጥቅም አካቶ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ:- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35botr
የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ዝግጁ እንዲሆኑ አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን የመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ገለጹ‼️


የትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ዓመት የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና እንደሚሰጥ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

መውጫ ፈተናው ተማሪዎች በሰለጠኑባቸው የሙያ ዘርፎች ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ፡፡

የመውጫ ፈተና በኦንላይን ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚሰጥ ሲሆን ኢዜአ ያነጋገራቸው የመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር መውጫ ፈተናውን ለመስጠት ተዘጋጅተዋል፡፡

የጅማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ መውጫ ፈተና ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የሚጠቀሙባቸውን እውቀት ክህሎትና አመለካከት በብቃት መያዛቸውን መለኪያ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን ዩኒቨርስቲዎች በትምህርት አሰጣጥ ላይ ያሉበትን ሁኔታ በማሳየት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ሚናው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ የመውጫ ፈተናውን በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱንና አስፈላጊውን ግብዓት የማሟላት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ከዚህ ጎን ለጎንም ተፈታኞችን በእውቀትና በስነልቦና የማዘጋጀት ስራ መሰራቱንም ጠቅሰዋል፡፡

የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኝ በበኩላቸው የመውጫ ፈተና ውጤት ፍትሀዊነትን የሚመልስ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናው የመጀመሪያው እንደመሆኑ መጠን ለተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫና ድጋፍ ለሚፈልጉ ተማሪዎች ድጋፍ የማድረግ ስራ እየተሰራ ስለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፈተናው የሚሰጥባቸውን የትኩረት መስኮች በመለየት የማጠናከሪያ ፕሮግራም እየተሰጠ ነው ያሉት ደግሞ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳምጠው ደርዛ ናቸው፡፡

ጎን ለጎንም ለሴቶችና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ ተኩረት ተሰጥቶ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡

የከፍተኛ ትምህርት አገራዊ ቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የተዘጋጀው የፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ ባለፈው ዓመት ነሀሴ ወር ላይ መጽደቁ ይታወሳል፡፡ (የትምህርት ሚኒስቴር)


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ጠቅላላ የሰራተኞች የምክክር መድረክ አካሂዷል።

የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና ሠራተኞች በተቋሙ እንቅስቃሴ እና ቀጣይ ተግባራት ላይ ተወያይተዋል።

አክሱም፣ መቐለ፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎችን ዳግም ሥራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot