STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
#ወላይታሶዶ_ዩኒቨርሲቲ

• " ለጉልበት ሰራተኞች 4 ሚሊዮን ብር ተከፍሏል ቢባልም ገንዘብ መውጣቱን እንጂ #የት_እንደገባ ማረጋገጥ አልተቻለም " - የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲን የ2013 በጀት ዓመት የሒሳብ ህጋዊነት ኦዲት ሪፖርትን ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል።

በዚህ ግምገማ ምን ተባለ ?

- ዩኒቨርሲቲው የኦዲት ግኝቱን የማስተካከያ እርምጃ እየወሰደ ባለመሆኑ ባለፉት አራት ዓመታት ተቀባይነት የሚያሳጣ የኦዲት አስተያየት ውስጥ ያለፈ ተቋም እንደሆነና በትኩረት መስራት እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አስገንዝቧል።

- ዩኒቨርሲቲው ማስመለስ ከነበረበት የገንዘብ ምጣኔ 99.95% እንዳላስመለሰ እና የኦዲት ግኝት መስተካከል ከነበረበት 11 ጉልህ  የኦዲት ግኝቶች 1 ብቻ ምላሽ እንዳገኘ ኮሚቴው ገልጿል።

- የዩኒቨርሲቲው አመራር የፋይናንስ ህግጋትን እና አሰራሮችን ተከትሎ ከመስራት አኳያ ሰፊ ክፍተት በመኖሩ በትኩረት መስራት አለበት ተብሏል።

- ዩኒቨርሲቲው ባልተሰጠው ስልጣን አዳዲስ ደንቦችን እና መመሪያዎችን እያዘጋጀ ክፍያ ሲፈፅም የነበረ ሲሆን #ለጉልበት_ሰራተኞች አራት (4) ሚሊዮን ብር ተከፍሏል ቢባልም ገንዘብ መውጣቱን እንጂ የት እንደገባ ማረጋገጥ እንዳልተቻለ ኮሚቴው ገልጿል።

የኦዲት ግኝቶችን በተመለከተ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ክርስትያን ታደለ ምን አሉ ?

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተሻሻለ የኦዲት ግኝት ማሻሻያ መርሃ-ግብሩን እስከ መጋቢት 23/2015 ዓ.ም እንዲያቀርብ እና መርሃ-ግብሩም ፦
- ለገንዘብ ሚኒስቴር፣
- ለፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት እና ለሰው ኃብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ግልባጭ ሪፖርት ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ተቋሙ የኦዲት ግኝቶችን ትኩረት ሰጥቶ ተገቢውን የእርምት ዕርምጃዎችን እየወሰደ በየ 3 ወሩ ለቋሚ ኮሚቴው ሪፖርት ማቅረብ አለበት ብለዋል።

አያይዘውም ገንዘብ ሚኒስቴር ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባልተወጡ የዩኒቨርሲቲው #አመራሮች እና የሥራ ኃላፊዎች ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃዎችን ወስዶ ሪፖርቱን በ10 ቀናት ውስጥ ማሳወቅ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

የፍትህ ሚኒስቴር #በወንጀለኛ እና #በፍትሃብሄር ተጠያቂነት የሚያስከትሉ ጉዳዮች ካሉ መርምሮ ክስ መመስረት እንዳለበት አቶ ክርስቲያን ታደለ አስረድተዋል።

አቶ ክርስትያን የሰው ኃብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኦዲት ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ተገቢውን የቁጥጥር ስራ እንዲሰራ እና የኦዲት ግኝቶች ዩኒቨርሲቲው የእቅድ አካል አድርጎ እንዲያካትታቸው ተገቢውን አመራር  እንዲሰጥ አሳስበዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከስልጣኑ ውጪ ባወጣቸው ደንቦች እና መመሪያዎች የሚያደርጋቸውን ክፍያዎች እንዲያቆም እና በቀጣይም በመንግስት የፋይናንስ ህግጋት እና መመሪያዎች ተንተርሶ ብቻ መስራት እንዳለበት፤ ያለ አግባብ የተከፈሉ ክፍያዎችም ተመላሽ እንዲሆኑ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

#FDRE_HoPR

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ባንካችን በ2014 ዓ.ም በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ምዘና በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 በላይ እንዲሁም በማኅበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ500 በላይ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የትምህርት ወጪያችሁን እንደሚሸፍን መግለፁ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም የተጠቀሰውን ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የስም ዝርዝራችሁ ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ስለቀረበልን፣ አቅራቢያችሁ በሚገኙ የባንካችን ቅርንጫፎች የትምህርት ማስረጃችሁን እና የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ይዛችሁ በመቅረብ እንድታመለክቱ እንጠይቃለን፡፡

[አማራ ባንክ]

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የወልዲያ ዩኒቨርስቲ ኒቃብ የለበሱ ሙስሊም ተማሪዎች ካፌ መግባት የለባቸውም ብሎ መከልከሉን ተከትሎ ሁሉም ሙስሊም ተማሪ ሳያፈጥር በዚህ መልኩ ይገኛል።

ዩኒቨርስቲው በእህቶቻችን ላይ በአለባበሳቸውና በእምነታቸው ሳቢያ ከሚፈጽመው ጽንፈኝነት ባሻገር የተራዊሕ ሶላት እንዳይሰግዱ ከምሽቱ 1 ሰዓት በኋላ ወደ ግቢ መግባት አይቻልም ብሎ ከልክሏል። ሁሌም በየአመቱ ረመዿን በመጣ ቁጥር ሙስሊም ተማሪዎችን በካፌ አጠቃቀም ዙሪያ እየበደለ መሆኑን አሳውቀውኛል።


የሚመለከተው አካል ተቋሙ ተገቢውን ማስተካከያ እንዲያደርግና እየፈጸመ የሚገኘውን የሙስሊም ጠልነት ተግባር እንዲያቆም ማድረፍ አለበት።


|የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ለሚገኙ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ  ሞዴል ፈተና ተሰጠ።

በዩኒቨርሲቲው ለሚገኙ የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የመውጣ ሞዴል ፈተና የተሰጠ ሲሆን በተፈጥሮ እና ማኅበራዊ ሳይንስ ፋካሊቲዎች በሚገኙ ሁሉም ዲፓርትመንት ተመራቂ ተማሪዎች የሙከራ ፈተናው ተሰጥቷል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የሃይማኖት አባት በድንጋይ ተወግሮ የሚገደልባት ሀገር = ኢትዮጵያ

እኚህ ካህን በ14/07/15 ዓ.ም ኃይሌጋርመንት (በአዲሱ አወቃቀር ደግሞ ሸገር ሲቲ ፉሪ አካባቢ) ከምትገኘው ሆርሲሳ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን  ቅዳሴ ቀድሰው ወደቤት ሲሄዱ በድንጋይ ተወግረው ተገድለዋል።

በወቅቱ ድርጊቱን የፈጸሙትን ግለሰቦች እና ሁኔታዎች በስልካቸው የቀረጹ ሰዎችም በፖሊስ እየታደኑ መረጃው ለስልካቸው እንዲጠፋ ተደርጓል።

😔 መጨረሻችን ወደየት ነው?


@NATIONALEXAMSRESULT
#በስልካችን_ብቻ_ወንድማችንን_እንታደገው

#ከተጋገዝን_እናሸንፋለን 💪

የደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች በግቢያቸው የሁለተኛ ዓመት ተማሪ የሆነ እና በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም ኩላሊቶቹ #Fail አድርገው የህክምና እርዳታ ለማግኘት ገንዘብ በማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚገኝ ጓደኛቸውን ለመርዳት በሚል "ዶንኪ ቲዩብ" የተሰኘ የዩትዩብ ገፅ በቅርቡ ይፋ ያደረገውን ማለትም ለአሸናፊው #500ሺህ ብር የሚያሸልመውን ውድድር በመወዳደር የሽልማቱን ገቢ ለጓደኛቸው ድጋፍ ለማዋል አስበዋል።


ቻሌንጁ "Donkey Tube" የተሰኘውን የዩትዩብ ገፅ ሰብስክራይብ በማድረግ ከላይ በምስሉ በሚታየው መልኩ screenshot 👉 @legesecharitybot ላይ መላክ ብቻ ነው።

📌የውድድሩ አዘጋጆች እስከ 1.5k Subscribe ያስደረጉ አስር ሰዎችን በማወዳደር ለአሸናፊው ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚሸልሙ በመሆኑ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የበጎ አድራጎት ክበብ አባላት ለአንድ ዓላማ እድላቸውን ለማስፋት በሚል በርካታ Subscription Screenshot እንደሚያስፈልጋቸው ነግረውናል። በመሆኑም ይህንን መልዕክት የሰማቹህ በሙሉ መልካም ስራቸውን ለመጋራት ቻናሉን ሰብስክራይብ በማድረግ Screenshot --> @legesecharitybot ላኩላቸው🙏


፨ይህን መልዕክትም በብዛት #Share አድርጉት።


፨ውድድሩ የፊታችን #ሰኞ ይጠናቀቃል።

#ከተጋገዝን_እናሸንፋለን 💪


@NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
#AddisAbaba

" ከ75 ሺ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን የሚኒስትሪ ፈተና ለማስፈተን ዝግጅት እየተደረገ ነው " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ

ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠውን የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ተማሪዎችን ለማስፈተን የዝግጅት ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋቃ።

የቢሮው የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሠጡት ቃል ፦

- በአዲስ አበባ ከተማ በግል እና በመንግሥት ትምህርት ቤቶች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙ ከ75 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስፈተን ዝግጅት እየተደረገ ነው።

- ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤቶች ድረስ ተማሪዎቹን ለፈተና የማዘጋጀት ሥራ እየተሠራ ይገኛል።

- ተማሪዎች የሚኒስትሪ ፈተና ከመፈተናቸው አስቀድሞ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ ሞዴል ፈተናዎችን በማዘጋጀት በወሩ እንዲወስዱ ተደርጓል። ለፈተናው የተለያዩ አጋዥ መጽሐፍትንም አንብበው እንዲዘጋጁ እና እንዲፈተኑ እየተደረገ ነው።

- በአማርኛ ቋንቋ የሚፈተኑ አራት እንዲሁም በአፋን ኦሮሞ የሚፈተኑ አምስት የትምህርት ዓይነት ፈተናዎች የሚወስዱ ይሆናል። በዚህ መሠረትም ፦
👉 የሒሳብ፣
👉 የአካባቢ ሳይንስ፣
👉 አማርኛ፣
👉 አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶች ይሰጣሉ።

- ምዝገባው የሚካሄደው በኦንላይን ሲሆን የተመዘገቡ ተማሪዎች የተመዘገቡበትን የስም እና ዕድሜ ስህተት እንዳይኖር ማረጋገጥ እና ማስተካከል ይችላሉ።

- በየክላስተሩ ላሉ ትምህርት ቤቶች ወጥ በሆነ መልኩ ስልጠና በመስጠት ትምህርት ቤቶች ራሳቸው ፈተናዎችን እንዲያወጡ እና እንዲፈተኑ ይደርጋል።

- በአዲሱ ሥርዓት ትምህርት በየምዕራፉ ማጠናቀቂያ ላይ ለተማሪዎች ፈተና ይሰጣል። ለዚህም አንደኛ ምዕራፍ የሚባለው ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ያለው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ሲሆን ሁለተኛ ምዕራፍ የሚባለው ከሰባት እስከ ስምንተኛ ክፍል ነው።

- የመጀመሪያ ምዕራፍ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚያጠናቅቁት ስድስተኛ ክፍል ላይ ስለሆነ የሚኒስትሪ ፈተናው ተማሪዎች ከታች ጀምረው ራሳቸውን እያነጹ እንዲመጡ የሚያደርግ ነው። የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ አንጻር ከፍተኛ ጥቅም አለው።

- የመማሪያ መጽሐፍት በሚፈለገው ልክ ሀገር ውስጥ አለመገኘት እና በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ከውጭ የሚመጡ መጽሐፍት የመዘግየት ሁኔታ አለ።

- የሚኒስትሪ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት የሚወሰነው በአገር አቀፍ ደረጃ ቢሆንም እንደ ቢሮ #ከሰኔ አጋማሽ በኋላ ለመስጠት ዝግጁ ነን።

#ኢፕድ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ዩኒቨርሲቲው ደረጃውን የጠበቀ የፈተና ማዕከል እያስገነባ እንደሆነ ተገለፀ‼️

በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የሚሰጡ ማንኛውም አይነት ፈተናዎች ተማሪዎች በራሳቸው አቅም ብቻ እንዲሰሩ፣ በራስ የመተማመን አቅማቸው እንዲጎለብት እንዲሁም የትውልድ ነቀርሳ የሆነውን ኩረጃ ከዩኒቨርሲቲው ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት የሚያስችል በሲሲቲቪ ካሜራ የተደገፈ በአንድ ጊዜ በርካታ ተማሪዎችን ማስተናገድና መፈተን የሚያስችል የፈተና ማዕከል እያስገነባ ይገኛል፡፡

ይህ የፈተና ማዕከል ከዩኒቨርሲቲው አልፎ ከቅጥር ጋር ተያይዞ ለሌሎች መሰል ተቋማት ፈተናዎችን ለመስጠት የሚያገለግል እንደሆነ ከዩንቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ራያ ዩኒቨርሲቲ ስራውን በማስጀመር ዙርያ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት አደረገ‼️

የራያ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት አመታት ከተቋረጠ በኋላ የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዴት መጀመር እንዳለበት ከአካዳሚክ እና አስተዳደር ሰራተኞች ጋር በመጋቢት 12/2015 ዓ/ም ውይይት አካሄደ። የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ለሁለት አመታት ከተራዘመ ጦርነት እና አስከፊ ሁኔታ በኋላ ሰራተኞቹን በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም በአዲስ መንፈስና ጉልበት የመማር ማስተማሩን ሂደት እንዲቀጥል ጠንካራና ጠንካራ ሆነው እንዲቀጥሉ ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል። በተጨማሪም ክልሉ ከገባበት ጥልቅና ውስብስብ ችግሮች ለመዳን ዩኒቨርሲቲው እና ህብረተሰቡ ጠንካራ ቁርጠኝነት ስለሚፈልግ የሀብት አጠቃቀምን በወቅቱ አጽንኦት ሰጥቷል።
ተሳታፊዎች በበኩላቸው የመማር ማስተማር ሂደቱን በአዲስ መንፈስና ጉልበት ለመቀጠል ያላቸውን ፍላጎት እና ተነሳሽነት ገልፀዋል ።
ባለፉት ሁለት አስከፊ አመታት ህብረተሰቡ ያጋጠሙትን የተወሳሰቡ የስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ጉዳቶችን ለመቅረፍ እና ለማቋቋም በሚችሉት ሁሉ የድርሻቸውን ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ካሰለጠናቸው ተማሪዎች በተጨማሪ በልዩ ልዩ የትምህርት ዘርፎች በድህረ ምረቃ 112 ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ዩኒቨርስቲው ከቅዱስ ላሊበላ ቅርስና ጥናት ግቢ 25 ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በድህረ ምረቃ መርሀ ግብር አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት 160 ሴት አና 430 ወንድ በድምሩ 592 ተማሪዎችን አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ኘሬዝዳንት አበበ ግርማ ( ዶ.ር) ዩኒቨርሲቲው በወልድያ፣ በመርሳና በላሊበላ ግቢዎች በጤና፣ በቱሪዝም፣ በግብርናና በቴክኖሎጂ የልህቀት ማዕከላት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከ2004 ዓ ·ም ጀምሮ የምርምርና የልህቀት ሥራ እየሠራ ይገኛል።


መረጃው የአሚኮ ነው

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በደቡብ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መቀነስ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል።

በክልሉ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 2.6 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ማለፋቸው ይታወቃል።

ባለፉት ዓመታት በክልሉ የታየው የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ችግሮች ለትምህርት ውጤታማነት መቀነስ ተጠቃሽ ምክንያት እንደሆኑ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በትምህርት ዘርፍ ላጋጠመው የውጤታማነት ችግር የመምህራን፣ የተማሪዎች፣ የአመራሩ እና የህብረተሰቡ ድርሻ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚገባ ተነስቷል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot