STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.7K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
በትግራይ ክልል ወደ ት/ት የተመለሱ ሕጻናት ከፍተኛ የስሜት ቀውስ ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ

ሐሙስ የካቲት 30 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የሰሜኑ ኢትዮጵያ ጦርነት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ከቆመ በኋላ፣ በትግራይ ክልል ከፍተኛ የስሜት ቀውስ ወይም ትራኦማ መኖሩ ተሰምቷል፡፡

ቮይስ ኦፍ አሜሪካ(ቪኦኤ) ወደ አካባቢው አቅንቶ በሰራው ዘገባ፣ ወደ ትምህርት ቤት የተመለሱ ሕጻናት ትምህርታቸውን ከመከታተል ይልቅ በጦርነቱ ወቅት የነበሩ ሁነቶችን ማስታወስ ላይ ትኩረት አድርገዋል ተብሏል፡፡

ቪኦኤ በሰራው ዘገባ፣ ያነገገራቸው መምህራን ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ጦርነቱ መቆሙን ተከትሎ ወደ ትምህርት የተመሰሉ ተማሪዎች አዕምሮ በግጭቱ ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ጸጋ ፍፁም የተባለች በትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና መቀሌ የሚገኘው ማይ ወይኒ ትምህርት ቤት መምህርት፣ የሕጻናቱን ሁኔታ ስትገልጽ “ፊደልና ቁጥር ከመጻፍ ይልቅ ሽጉጥ ወደ መሳል ያዘነብላሉ" ስትል ተናግራለች፡፡

ወደ ትምህርት ቤት የተመለሱ ሕጻናት አሁን ላይ ጦርነት እንደሌለና ሰላም እንደሆነ በመምህራኖቻቸው ሲነገራቸው፣ መሳሪያ ከመሳል ወደ ትምህርት ሀሳብ የመመለስ አዝማሚያ ማሳየታቸው ተገልጿል፡፡ ምንም አንኳን አዎንታዊ ምልክቶች ቢታዩም፣ ጦርነቱ የሚያስከትላቸው የስነ ልቦና መዋዠቆች ለዓመታት ሊዘልቁ እንደሚችሉ ተመላክቷል፡፡

በተማሪዎች ላይ ታይቷል የተባለው የስሜት ጉዳት፣ ጦርነቱ ከቆመ በኋላ መደበኛ ባይሆንም በአንዳንድ አካባቢዎች በበጎ ፈቃደኛ መምህራን ትምህርት መስጠት መጀመሩን ተከትሎ ነው፡፡ በክልሉ በጦርነቱ ምክንያት የተቋረጠው መደበኛ ትምህት በይፋ ስለመጀመሩ እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም፡፡ ይሁን እንጂ የተቋረጠውን ትምህርት ለማስጀመር ትምህርት ሚኒስቴርና የሚመለከታቸው አካላት እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የጦርነቱ አካል በነበሩ የአፋር እና የአማራ ክልል አካባቢዎች ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሲመለሱ ተመሳሳይ የስሜት መጎዳት አጋጥሟቸዋል መባሉ የሚታወስ ነው፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Photo
የሬሚዳል ፕሮግራምን ለመከታተል የመመዝገቢያ ነጥብ በመንግስት እና በግል ዩኒቨርሲቲዎች ይለያያል?

March 9, 2023

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆኖ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን እየተቀበሉ ነው
በኮሮና ቫይረስ እና ሌሎች ተጽዕኖዎች ምክንያት ዘግይቶ የተሰጠው የ2014 ዓ. ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉ ይታወሳል።
ጥቂት ተማሪዎች እንዳለፉበት የተገለጸው ይህ የፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን ተከትሎም ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን. በተለያዩ ፕሮግራሞች በመቀበል ላይ ይገኛሉ።
አል ዓይን አማርኛ ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ ያደረገውን የመመዝገቢያ ውጤት ዩኒቨርሲቲዎች ምን ያህል እየተገበሩ ነው? ሲል ምልከታ አድርጓል።

በአዲስ አበባ በአካል እንዲሁም ከአዲስ አበባ ውጪ በስልክ ባደረግነው ማጣራት በተለይም የግል ዩኒቨርስቲዎች እና ኮሌጆች ትምህርት ሚንስቴር ባስቀመጠው ፕሮግራም እና የመመዝገቢያ ነጥብ መሰረት ተማሪዎችን እየመዘገቡ መሆኑን ታዝበናል።

ይሁንና በትምህርት ሚኒስቴር ከተቀመጠው የአቅም ማሻሻያ ወይም ሬሚዳል ስልጠና ፕሮግራም መመዝገቢያ ነጥብ በታች ያመጡ ተማሪዎችን እየመዘገቡ ያሉ ዩኒቨርስቲዎች እና ኮሌጆች መኖራቸውን ተመልክተናል።

ከ50 በመቶ በታች ላመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች 'የአቅም ማሻሻያ' የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ
በዚህ የሬሚዳል መቁረጫ ነጥብ መሰረት ባደረግነው ምልከታ ከተቀመጠው ነጥብ በታች ያመጡ ተማሪዎችን የሚመዘግቡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መሆራቸውን አይተናል።

ምዝገባውን እያከናወነ ላለው ዩኒቨርሲቲ እና ኮሎጁ ትምህርት ሚኒስቴር ካስቀመጠው ነጥብ በታች ያመጡ ተማሪዎችን ለምን መዘገባችሁ? በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄ መንግሥት ይፋ ያደረገው ለመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች እንጂ ለግል ተቋማት አይደለም ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል።

አል ዓይን ይህን ጥያቄ ይዞ ትምህርት ሚኒስቴርን የጠየቀ ሲሆን የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙንኬሽን ሀላፊ ወይዘሮ አመለወርቅ እዝቅኤል፥ "ለሬሚዳል ፕሮግራምም ይሁን ከ50 በመቶ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች መመዝገቢያ ነጥብ ለመንግሥትም ይሁን ለግል ዩኒቨርሲቲ ተመሳሳይ ነው" ሲሉ ተናግረዋል ።

ከዚህ በፊት የነበረው ለግል እና ለመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የተማሪዎች መመዝገቢያ ነጥብ ይለያይ ነበር ያሉት ሀላፊዋ፥ ከ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በኋላ ተመሳሳይ እንዲሆን መወሰኑን አክለዋል።

በዚህም መሰረት ትምህርት ሚኒስቴር ካስቀመጠው የሬሚዳል ፕሮግራም መመዝገቢያ ነጥብ ውጪ የሚመዘግቡ ዩኒቨርስቲዎች እና ኮሌጆች ህግ እየጣሱ መሆኑንና እርምጃም እንደሚወሰድባቸው ነው ያብራሩት።

[Al Ain]

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በመቀሌ ከተማ አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ትምህርት መጀመራቸዉ ተሰማ

በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ትምህርት መጀመራቸዉን ብስራት ራዲዮ ከነዋሪዎች አረጋግጧል። በስልክ አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ለጣቢያችን እንደተናገሩት ፤ አንዳንድ የመዋዕለ ህጻናት ትምህርት ቤቶች ትምህርት መጀመሩን እና ህጻናት ወደ ትምህርት ቤቶች መሄድ መጀመራቸዉን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ትምህርት ጀምረዋል ሲሉ ተናግረዋል። ሆኖም የመንግስት የትምህርት ተቋማት እስካሁን አመለመጀመራቸዉን ነዋሪዎቹ አክለዋል።

በክልሉ የትምህርት መጀመሩን ለማረጋገጥ ብስራት ራዲዮ የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሯን ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤልን ጠይቆ ባገኘዉ ምላሽ ፤ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ዳግም በክልሉ ትምህርት ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የክልሉ ነዋሪዎችም በቅርቡ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ትምህርት ይጀመራሉ መባሉን ለጣቢያችን ተናግረዋል።

በክልሉ የኮቪድ 19 በኢትዮጵያ መከሰትን ተከትሎ ትምህትርት ተዘግቶ የቆየ ሲሆን በግዜያት በኋላ በተቀሰቀሰው ግጭትም ተማሪዎች ለሶስት አመታት ገደማ ከትምህርት ገበታቸዉ ርቀዉ ቆይተዋል።

ብስራት ራዲዮ ከዚህ ቀደም በሰራዉ ዘገባ ፤ በጦርነቱ ወቅት የቄስ ትምህርት መደበኛዉን የትምህርት ስርዓት ተክቶ ህጻናት ፊደል እንዲቆጥሩ እና መሰረታዊ እዉቀት እንዲያገኙ የራሱን አስተዋጽኦ ሲወጣ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።

#ዳጉ_ጆርናል

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በሀረሪ ክልል የተማሪዎች ምገባ ተጀምሯል።

በሀረሪ ክልል የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።

ፕሮግራሙ በክልሉ በሚገኙ ገጠርና ከተማ በሚገኙ 67 ትምህርት ቤቶች የተጀመረ ሲሆን፤ በምገባ ፕሮግራሙ በአጠቃላይ 37 ሺህ 194 ተማሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ነው የተነገረው።

በምገባ መርሃግብሩም ከቅድመ መደበኛ እስከ አራተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።

መረጃው የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በአካል በመገኘት መጋቢት 8 እና 9 /2015ዓ.ም. እንድትመዝገቡ እንገልፃለን።

፨ምዝገባ የምታካሂዱባቸው ግቢዎች

1ኛ. በማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) የትምህርት መስክ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሚዛን አማን ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ ፣

2ኛ. በተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ትምህርት መስክ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ደግሞ ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ

፨ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎች እና የግል መገልገያ ቁሳቁሶች

1ኛ. የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት እንዲሁም ከ9ኛ --12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ ፣

2ኛ. አምስት የቅርብ ጊዜ ሦስት በአራት (3*4) ጉርድ ፎቶ ፣

3ኛ. ብርድልብስ፣አንሶላና የትራስ ጨርቅ መያዝ እንደሚጠበቅባችሁ እናሳውቃለን።

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በአማራ ክልል166 አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ እየተሠራ መኾኑን ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ገለጹ።

በአማራ ክልል በ2015 በጀት ዓመት 166 አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ እየተሠራ መኾኑን ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በምክር ቤቱ ጉባዔ ላይ ገልጸዋል።

አጠቃላይ በዓመቱ ለመገንባት ከታቀዱት 166 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 84 የሚኾኑት በግማሽ ዓመቱ የሚጠናቀቁ ናቸው ብለዋል። ከ84ቱ ውስጥ 45 የሚኾኑት እስከ ሩብ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።

በ2015 ዓ.ም ለመገንባት የታቀደው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ደግሞ 27 መኾኑንም ነው የገለጹት። ከዚህ ውስጥ በግማሽ ዓመቱ 14 ትምህርት ቤቶችን ለማጠናቀቅ ታቅዶ 13ቱን በሩብ ዓመቱ ለማጠናቀቅ መቻሉንም ለምክር ቤቱ ገልጸዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ እነዚህ ትምህርት ቤቶች የሚገነቡት በመንግሥት እንዲሁም በኅብረተሰቡ እና በአጋር አካላት ትብብር እንደኾነም አስረድተዋል።

ዘገባው የአሚኮ ነው

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WoldiaUniversity

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡለትን የሪሚዲያል ተማሪዎች እየተቀበለ ነው፡፡

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም 2,500 ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

ዩኒቨርሲቲው የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ የካቲት 30 እና መጋቢት 1/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን መግለጹ ይታወቃል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የውጪ ሀገር የትምህርት ዕድል /Scholarship/ ስለተሰጣቸው ተማሪዎች ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 3.3 በመቶ ተማሪዎች ብቻ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባቸውን ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው ይታወቃል፡፡

ከነዚህም መካከል 263 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት (ከ700) እንዲሁም 10 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት (ከ600) በማምጣት የላቀ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

መንግሥት ለእነዚህ 273 ተማሪዎች የካቲት 21/2015 ዓ.ም የእዉቅና ሽልማት መስጠቱ ይታወሳል፡፡ በዕለቱ ለእነዚህ ተማሪዎች በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የትምህርት ዕድል /Scholarship/ እንደተሰጣቸውም ተገልጿል፡፡

ተማሪዎቹ ከመስከረም 2016 ዓ.ም ጀምሮ የትምህርት ዕድሉን በመጠቀም እንዲማሩ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውም ተመላክቷል፡፡ ወደ ዉጪ እስከሚሄዱ ድረስ ባሉት ግዜያትም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ትምህርት ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡

የተፈጠረዉ የትምህርት ዕድል አስገዳጅ አለመሆኑ የተገለጸ ሲሆን ሀገር ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች የሚገደዱበት ሁኔታ እንደሌለ ተገልጿል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:- https://www.facebook.com/fdremoe

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በ2015 የትምህርት ዘመን 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ እና ሀገራቀፍ ፈተና ተፈታኝ ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ

ቀደም ሲል በቀጥታ / ኦላይን መመዝገባችሁ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጋርም በተያያዘ የተመዘገባችሁበትን መረጃ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንዲቻል
👉ለ6ኛ ክፍል https://aa6.ministry.et እና

👉ለ8ኛ ክፍል https://aa.ministry.et ሊንኮችን በመጫን View Result የሚለውን በመጫን የመለያ ቁጥራችሁን እና ስም / Registration Number and First Name በማስገባት ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ስህተት ካለበት ለትምህርት ቤታችሁ በስቸኳይ እንድታሳውቁ እናሳስባለን፡፡

©የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
"የኑሮ ውድነት የእኛ ኃላፊነት አይደለም" የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

🤔🤔🤔

የተጣሩ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
"የ14 ዓመት ሕጻን ሴት ተማሪዋን ልብሷን አስወልቀው ርቃኗን ፈትሸዋታል ፥ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞባታል"

ሀለባ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ተማሪ የሆነችው ተማሪ ልድያ በየካቲት 22/2015 ዓ.ም እንደማንኛውም ጊዜ ት/ቤት ለመማር ክፍሏ ተገኝታለች። ሁሉም ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሠላም እየተከታተሉ ሳለ አንዲት የክፍላቸው ተማሪ ትወድቃለች።

ይህንን ተከትሎም "ተማሪዋ ላይ ድግምት አሰርተሻል" በሚል ግራ በሚያጋባ ሁኔታ በክፍሉ ተማሪ የሆነችውን ተማሪ ልድያን ከነለበሰችው ዩኒፎርም ያለ ፖሊስ እና ፍርድ ቤት መጥሪያ ወደ ሀላባ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ይወስዷታል። በነገሩ የደነገጡት ወላጅ አባትም በሁኔታው ደንግጠው ሊጠይቋት ሲሄዱ እርሳቸውንም ያስሯቸዋል ነገር ግን ቆይተው ይፈቷቸዋል።

ሕጻን ተማሪ ሊድያ በፖሊስ ከተያዘች 5 ቀን በኋላ በ5ኛው ቀን 27/06/2015 ፍ/ቤት
ያቀርቧታል 'ፖሊስም ድግምት ሙስሊም ተማሪዎች ላይ በመስራት ወንጀል ጠርጥረናታል የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠን በማለቱ 11 ቀን ተፈቅዶላቸው የ14 ዓመት ታዳጊዋን ከፖሊስ ጣቢያ ወደ ሃላባ ማረሚያ ተቋም ውሰዷት እየማቀቀች ትገኛለች።

ተማሪ ሊድያ በምርመራ ወቅት "በንቅሳት ድግምት አሰርተሻል" በሚል ልብሷን ሙሉ ለሙሉ አስወልቀው እርቃኗን እንደፈተሿት እና ሊነገር የማይችል የመብት እና የሥነልቦና ጥቃት እንደደረሰባት ትናግራለች።

የትኛው ህግ ነው ድግምት አሰርተሻል ብሎ የ14 ቀን ቀጠሮ የሚያስጠይቀው ለዚያውም 15 ዓመት እንኳን ላልሞላት ሕጻን ልጅ?

Law የሚያስተምሩ ዩኒቨርሲቲዎቻችን ደህና ናቸው🤔

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program ) የተመደቡ 5 ሺህ ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ለአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም የተመደቡ ተማሪዎችን ዛሬ መቀበል ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው በነገው ዕለትም ከትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡትን ተማሪዎችን መቀበል ይቀጥላል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በ2015 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርሲቲያችን በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ለምትገቡ ተማሪዎች በሙሉ ከመጋቢት 05-06 2015 ዓ/ም ጥሪ የተደረገላችሁ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ስለሆነም በተጠቀሰው ቀን ጎንደር ከተማ አዘዞ አይራ መገንጠያና መስቀል አደባባይ ላይ ሰርቪስ ስለተዘጋጀ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እንገልፃለን።
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ቀን 1/7/2015 ዓ.ም

ወደ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ለሚገቡ አዲስ ስልጣኞች የተማሪ ቅበላ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮዎች በ2015 የትምህርት ዘመን ወደ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ለሚገቡ አዲስ ስልጣኞች የተማሪ ቅበላ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በጋራ አካሄደዋል፡፡

የተማሪ ቅበላ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ የተካሄደ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ምትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊዎች ፣ የየማስልጠኛ ኮሌጁ ሀላፊዎች ፣ የአሰልጣኞች ሙያ ማህበራት ፣ አስልጣኝ መምህራን፣ ተማሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና በተጨባጭ ተግባር የታገዘ በቴክኒክ ትምህርት መስልጠን ለሚፈልጉ እንዲሁም በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አዳዲስ ክህሎቶችን ማዳበር ለሚፈልጉ ስዎች የሚሰጥ የፈጠራ ክህሎትን ለማስተማር የሚያስችል ተመራጭ የትምህርት ዘርፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አክለውም ተማሪዎች በሚፈልጉት የሙያ ዘርፍ እና ደረጃ ላይ መማር የሚችሉ መሆኑን አመላከተዋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot