STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ለመሆን የሚያስችል ዝግጅት እያደረገ ነው!

ራስ ገዝ ለመሆን የሚያስችል ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ። የዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ መሆኑ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን እንደሚያሳድገው ተገልጿል።የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል ዩሱፍ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሟት ራስ ገዝ እንዲሆኑ የተጀመረውን ጥረት ታሳቢ በማድረግ ዩኒቨርሲቲው የራሱን ዝግጅት እያከናወነ ይገኛል።

Via EPA

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
Students News Channel.zip
30.1 MB
#blueprint for national exit exam


ለዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ከትምህርት ሚኒስቴር ለእያንዳንዱ ዲፓርትመንት ለመውጫ ፈተና የተዘጋጀ Blueprint

ከላይ  የተያያዘው  ፋይል  በትምህርት ሚኔስተር በ2015 የመውጫ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች የተዘጋጀ ንድፈ ሀሳብ( Blueprint) ሲሆን ጥያቄው እንዴት እንደሚዘጋጅ ማለትም  ከአላማው  ጀምሮ  የተመራቂዎችን እውቀት ፣ ክህሎት፣ቴክኒካል ችሎታ ፣  አመላካከት  እንዲሁም   የትኛው  የትምህርት አይነት ( course theme /  tittle )  በንፅፅር ስንት ጥያቄ እንደሚይዝ እና አጠቃላይ የጥያቄ ብዛት  በዝርዝር እንዲሁም መሰል ነገሮችን  የሚገልጽ ነው።


ተመራቂ ተማሪዎች በዚህ ንድፍ መሰረት ራሳችሁን ለመውጫ ፈተና ከወዲሁ እንድታዘጋጁ  እናሳስባለን‼️

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ በማደግ በኤሮስፔስ እና በተለያዩ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፎች በቅድመ ምረቃ እና ድሕረ ምረቃ ፕሮግራሞች ማስተማር ጀመረ።


አካዳሚው ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ካደገ በኋላ በኤሮኖቲካል ኢንጂነሪንግ በቢኤስሲ ዲግሪ፣ በአውሮፕላን ጥገና ኢንጂነሪንግ በቢኤስሲ ዲግሪ፣ በአቪዬሽን ማኔጅመንት ቢኤስሲ ዲግሪ፣ በቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ ማኔጅመንት ቢኤ ዲግሪ እና ኤምቢኤ በአቪዬሽን ማኔጅመንት የመሳሰሉ የዲግሪ መርሃ ግብሮችን ጀምሯል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር መስፍን ጣሰው እንደተናገሩት "ከቀጣይ እድገትና ኢንቨስትመንት በኋላ 65 ዓመት ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማደጉ በአየር መንገዳችን ረጅም እና ስኬታማ ጉዞ ውስጥ ሌላው ምዕራፍ ነው። እና በኢንዱስትሪው ውስጥ ያለውን አመራር ይጠብቃል።" ብለዋል።

አክለውም፤ "ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ እና በድህረ ምረቃ የአቪዬሽን ፕሮግራሞችን በመስጠት የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ቁርጠኛ ነው።" ያሉ ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲው እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እና ሌሎች አየር መንገዶችን በአካባቢው ያለውን የሰው ሃይል ፍላጎት የሚያሟሉ የአቪዬሽን ባለሙያዎችን እና አመራሮችን ያፈራል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።

የቀድሞው ኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ የአሁኑ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ካሴ ይማም በበኩላቸው፤ ዩንቨርስቲው በፍጥነት እያደገ ላለው የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ዘርፍ እና በአጠቃላይ ለአህጉሪቱ የሚያደርገውን አስተዋፅኦ ይቀጥላል ብለዋል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የምዝገባ ጥሪ ማስታወቂያ ለሬሚድያል ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ:

በ2015ዓ/ም ለሬሚዲያል ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ከመጋቢት 2-3/2015 ዓ/ም ስለሆነ በአካል ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን።

ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ይሁን ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እየገለፅን ማንኛዉም ተማሪ ሲመጣ የትራስ ጨርቅ እና አንሶላ ይዞ መምጣት እንዳለበት እናሳስባለን።

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት

👉 ለበለጠ መረጃ ከዛሬ ጀምሮ ምሽት ሁለት ሰዐት ዜና በኋላ በኢቲቪ ዜና ቻናል ለተከታታይ ቀናት የሚተላለፈውን የጥሪ ማስታወቂያ እንድትከታተሉ እናሳውቃለን!!


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
Update‼️
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ የጥሪ ማስተካከያ አድርጓል። ዩኒቨርሲቲው በሪሚዳል ፕሮግራም የተደመደቡ ተማሪዎችለ መጋቢት 12&13 የጠራ ቢሆንም በፕሮግራም መደራረብ ምክንያት ጥሪውን ለመጋቢት 16&17 አድርጓል።
የካቲት 28/2015 ዓ.ም
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#AxumUniversity

አክሱም ዩኒቨርስቲ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሳቢያ የደረሰበት ጉዳት 15 ቢሊዮን ብር እንደሚገመት ማስታወቁን " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።

ላለፉት 19 ወራት ትምህርት መስጠት አቁሞ የቆየው ዩኒቨርስቲው፤  ሊያከናውነው ላቀደው ዳግም ግንባታ የድጋፍ ጥሪ አቅርቧል።

የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ገብረእየሱስ ብርሃነ የሰጡት ቃል ፦

- ዩኒቨርስቲው በጦርነቱ ሳቢያ በደረሰበት #ውድመት እና #ዘረፋ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የሚያስችሉት ቁሳቁሶች እና መሳሪያዎች አጥቷል።

- ሙሉ ለሙሉ የተዘረፉ እና ከወደሙ የዩኒቨርስቲው ንብረቶች ውስጥ ኮምፒውተሮች፣ የላብራቶሪ መሳሪያዎች፣ ሰርቨሮች እና የቢሮ በሮች ይገኙበታል።

- ዩኒቨርስቲው ከጦርነቱ በፊት የነበሩት 60 ገደማ ተሽከርካሪዎች ተዘርፈው እና ተቃጥለው አሁን በስራ ላይ የሚገኘው #አንድ_መኪና ብቻ ነው።

- በጥር ወር ላይ በተደረገ ዳሰሳ የደረሰው ውድመት 15 ቢሊዮን ብር ይደርሳል።

- ጉዳት የደረሰባቸውን ንብረቶች በተወሰነ መልኩ በመተካት ወደ ስራ ለመግባት ታቅዷል።

- ለሚያከናውነው ዳግም ግንባታ እና ጥገና ስራ የገንዘብ እና የማቴሪያል ድጋፍ እንዲደረግልን  ጠይቀናል። የድጋፍ ጥሪው ለዓለም አቀፍ እና ለሀገር በቀል አጋር ድርጅቶች፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ነው።

- ዩኒቨርስቲው የሚያገኘውን ድጋፍ በፌደራል መንግስት ከሚመደበለት በጀት ጋር በማጣመር በአጭር ጊዜ ውስጥ የመማር ማስተማር አገልግሎቱን ለመስጠት ታቅዷል። 

- ቁሳቁሶችን በተወሰነ መልክ ቅድሚያ እየሰጠን ካስገባን፤ የግዢ ሂደቱ ፈጣን ከሆነ፤ ተማሪዎችን #በሶስት_ወር ውስጥ ማስገባት እንችላለን። በትግራይ ክልል የሚኖሩ እና ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት ያቋረጡ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን ትምህርት ማስጨረስ ላይ ትኩረት ይደረጋል።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ከፌደራል መንግስት በጀት ባይለቀቅለትም፤ በስሩ ለሚገኘው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 43 መምህራንን ለመቅጠር ከ2 ሳምንት በፊት ማስታወቂያ አውጥቷል።

የቅጥር ሂደቱ የሚፈጸመው በትምህርት ሚኒስቴር ተፈቅዶ፣ በጀት ሲለቀቅ መሆኑ ተገልጿል።

ከፌደራል መንግስት የሚለቀቀው በጀት፤ ለዩኒቨርስቲው ሰራተኞች ደመወዝ ለመክፈል እና ትምህርት ለማስጀመር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

#አራት_ሺህ ገደማ የሚሆኑት የዩኒቨርስቲው መምህራን እና ሰራተኞች ከሐምሌ 2013  ዓ.ም. ወር ጀምሮ #ደመወዝ_አለማግኘታቸውን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።

Credit : www.ethiopianInsider.com

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙት ሃላፊ ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ትላንት ለአሀዱ በሰጡት ቃለ ምልልስ ወቅት የአቅም ማሻሻያ ትምህርት " ለአንድ ዓመት " በሚል የተገለፀው ስህተት እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀው እንዲታረም ብለዋል።

የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) የሚሰጠው ከዚህ በፊት እንደተገለፀው ለአራት ወራት እንደሆነ አመልክተዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከግማሽ በታች የሆኑትን በቅድመ መደበኛ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ጉድለታቸውን እንዲሞሉ ኮርስ እንደሚወስዱ ከዚህ ቀደም መግለፁ ይታወሳል።

እነኚህ ተማሪዎች ያለባቸውን ጉድለት የሚሞላው የሬሜዲያል ፕሮግራም ይከታተላሉ፤  ዋና ዋና ይዘቶች እና መታወቅ ያለባቸውን እስከ #አራት_ወር ተወስዶ ተማሪዎቹ አቅማቸውን የሚሞላ ትምህርቶችን እንዲማሩና እንዲከልሱ ይደረጋል።

የሬሚዲያል ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ተማሪዎች ተከታታይ ምዘና እንዲኖራቸው ተደርጎ በየተቋማት የሚሰጠው ምዘና 30 % እና በማዕከል የሚዘጋጀው ፈተና 70% ተመዝነድ በድምሩ አማካይና ከዚያ በላይ (50 ከመቶና በላይ) የሚያመጡት በመንግስት ተቋማት ሲከታተሉ የቆዩት በዚያው ተቋም መቀጠል የሚችሉ ሲሆን በራሳቸው ወጪ ሸፍነው ወደ ግል ተቋማት ሄደው መማር ቢፈልጉ መብታቸው የተጠበቀ ይሆናል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ከአብዛኛው የአማራ ክልል የደረሱኝ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ህገወጥ የሰዎች ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ገልፀውልኛል። በተለይ የ12ኛ ከፍል ውጤት ያልመጣላቸው ወጣቶች የዚህ ሰለባ እንደሆኑ ገልፀውልኛል። የክልሉ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራበት ይገባል።
©አዩ ዘሀበሻ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ማስታወቂያ

የአቅም ማሻሻያ (REMEDIAL) ትምህርት ለመማር ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች የማደሪያ ክፍል ድልደላ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የመኝታ ክፍል ድልደላ ቦት {WKU Dormitory Placement(@WKUDormitoryBot)} ማግኘት የምትችሉ ሲሆን የብሄራዊ ፈተና የመለያ ቁጥር (Admission Number) በማስገባት የተመደባችሁበትን ዶርም ቁጥር እና ህንፃ ቁጥር ማወቅ የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ማስታወሻ

የብሄራዊ ፈተና የመለያ ቁጥራችሁ (Admission Number) ከዜሮ(0) የሚጀምር ካለ ዜሮን በማስወገድ በመቁጠሪያ ቁጥር ብቻ ጀምራችሁ እንድትጠቀሙ እንጠይቃለን።
ለምሳሌ 067801 => 67801


የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#አምቦዩኒቨርሲቲ

አምቦ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የተመደቡ የሪሜዲያል (የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም) ተማሪዎችን የሚቀበልበት የመግቢያ ቀን መጋቢት 07 እና 08 2015 ዓ.ም በመሆኑ በተጠቀሰው ቀናት ብቻ በማህበራዊ ሳይንስ መስክ የተመደባችሁ በዋና ካምፓስ ፤ በተፈጥሮ ሳይንስ የተመደባችሁ አምቦ ከተማ ሃጫሉ ሁንደሳ ካምፓስ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ ጥሪ እያደረገ ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞ ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨረሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
ሁሉም ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-
- ከ8 –12ኛ ክፍል ያሉ የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒ፡
- የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሳርትፍኬት ዋናውና ኮፒ፡
- 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ ብዛት 8:
- አንሶላ፡ ብርድልብስ፡ ትራስልብስ እና የስፖርት ትጥቅ::

ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
አክሱም ዩኒቨርስቲ፤ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ሳቢያ 15 ቢሊዮን ብር የሚገመት ጉዳት እንደደረሰበት አስታወቀ

በትግራይ ክልል ውስጥ ከሚገኙ አራት ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ አንዱ የሆነው አክሱም ዩኒቨርስቲ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሳቢያ የደረሰበት ጉዳት 15 ቢሊዮን ብር እንደሚገመት አስታወቀ። ላለፉት 19 ወራት ትምህርት መስጠት አቁሞ የቆየው ዩኒቨርስቲው፤ ሊያከናውነው ላቀደው “ዳግም ግንባታ” የድጋፍ ጥሪ አቅርቧል።

በ2006 ዓ.ም የተመሰረተው አክሱም ዩኒቨርስቲ በስሩ ባሉት ስድስት ኮሌጆች እና ሁለት ኢንስቲትዩቶች ተማሪዎችን ከመላው ሀገሪቱ ሲቀበል ቆይቷል። አክሱም ዩኒቨርስቲ የመጨረሻ ተማሪዎቹን ያስመረቀው ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መጀመር በኋላ በየካቲት 2013 ዓ.ም ሲሆን፤ በዚያው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ ትምህርት መስጠት ማቋረጡን የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ገብረእየሱስ ብርሃነ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ዩኒቨርስቲው በጦርነቱ ሳቢያ በደረሰበት “ውድመት እና ዘረፋ” የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የሚያስችሉት ቁሳቁሶች እና መሳሪያዎች ማጣቱን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል። ፕሮፌሰር ገብረእየሱስ ሙሉ ለሙሉ እንደተዘረፉ እና እንደወደሙ ከጠቀሷቸው የዩኒቨርስቲው ንብረቶች ውስጥ፤ ኮምፒውተሮች፣ የላብራቶሪ መሳሪያዎች፣ ሰርቨሮች እና የቢሮ በሮች ይገኙበታል። ዩኒቨርስቲው ከጦርነቱ በፊት የነበሩት 60 ገደማ ተሽከርካሪዎች “ተዘርፈው እና ተቃጥለው”፤ አሁን በስራ ላይ የሚገኘው “አንድ መኪና ብቻ” መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ አክለዋል።

/የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ ሪሚዲያል የትምህርት ፕሮግራም በተቋሙ ለተመደቡ ተማሪዎች በቅርቡ ጥሪ እንደሚያደርግ ግልጿል፡፡

ተቋሙ እያደረገ ያለውን ዝግጅት በቅርቡ እንዳጠናቀቀ በይፋ በመገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ የሚዲያ ገጾቹ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ድረ ገጽ www.du.edu.et ጥሪ የሚያደርግ መሆኑን አመልክቷል፡፡

ጥሪ እስከሚደረግ ድረስ በተቋሙ የተመደባችሁ ተማሪዎች በትዕግስት እንድትጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#UniversityofGonder

ጎንደር ዩኒቨርስቲ ለተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች እና አቅም ማሻሻያ ተማሪዎች በሙሉ ወደ ግቢ መግቢያ ቀን👉 መጋቢት11 እና 12 መሆኑን እናሳውቃለን፡

1.የአቅም ማሻሻያ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፋሲል ግቢ

2.የተፈትሮ ሳይንስ መደበኛ ተማሪዎች ቴድሮስ ግቢ

3.የማህበራዊ ሳይንስ ሁሉም ማራኪ ግቢ የተመደባችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡መረጃ ስትፈልጉ የህብረቱን ቴሌግራም ቻናል በመቀላቀል ፤በቀጥታ በመደወል እና በቅርቡ የምትገኙ ቢሮ ድረስ በአካል በመምጣት መጠየቅ የምችሉ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ሩሲያኛ ቋንቋ አይችሉም?

ምዕራባውያን ሚዲያዎች ብቻ የሚዘግቧቸውን ሚዛን የሳቱ መረጃዎች ብቻ ነው እያገኙ ያሉት?

ስለሩሲያ የዩክሬን ልዩ ተልዕኮ የጦር ሜዳ ላይ ዘገባዎችን ማግኘት ይሻሉ?

እንግዲያውስ እነዚህን ዘገባዎች በአማርኛ ከኛ ዘንድ ያግኙ📰

ቻናላችንን ይቀላቀሉን 👉 @Rtnews_amharic