STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ከEBS ጋር ባደረጉት ቆይታ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎችን በተመለከተ የመንግስትን ሦሥት ውሳኔዎች አብራርተዋል። 1. 50 በመቶ ባያመጡም መቶ ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች በመንግስት እና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለአንድ ሴሚስተር የማብቂያ ትምህርት ተከታትለው በቀጣይ ዓመት የመጀመሪያ…
የ 100,000 ተማሪዎች  ማለፊያ ከግማሽ በታች ቢሆንም በጣም እንደማይወርድ ፍንጭ ተሰቷል የፈተናዎች  አገልግሎት  ጸሀፊ ከተማሪዎች  ቁጥር አንጻር እና የመስክ ልይታ አንጻር ማለፊያውን እንናገራለን  ነገር ግን በጣም ውጤት የወረደባቸው  ልጆች  ዘንድሮ  ዳግም  ሚፈተኑበትን እድል ስላላቸው  ይህን መጠበቅ  ቀርቶባቸው ለፈተና ቢዘጋጁ ብለዋል።

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ለዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ

የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና በመጪው ሀምሌ ወር በሁሉም የትምህርት መስኮች እና መርሀግብሮች በግልና በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ይሰጣል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በመውጫ ፈተና ዙሪያ ከተማሪዎች ህብረት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱም የመውጫ ፈተና በመጪው ሀምሌ ወር በኦንላይን ለሁሉም የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ብቁ ለመሆንም ተማሪዎች በየዩኒቨርስቲዎቹ የሚሰጠውን የመጨረሻውን ሰሚስተር ፈተና መውሰድና ኮርሶችን ማጠናቀቅ እንደሚገባም ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል፡፡

ለፈተናው በሁሉም የትምህርት መስኮች ላይ የተመረጡ ኮርሶች የብቃት ልየታ ተደርጎላቸው ዩኒቨርስቲዎች እንዲያውቁት መደረጉን የጠቆሙት ዶክተር ሳሙኤል በአሁኑ ወቅትም የፈተና ንድፈ ማሳያና / Blueprint / የፈተና ዝግጅት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች በቀሪዎቹ አምስት ወራት ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ራሳቸውን ለፈተናው ብቁ ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙ የተማሪዎች ህብረት ተወካዮችም ወደ ዩኒቨርስቲዎቻቸው ሲመለሱ ተማሪዎች ለፈተናው በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

በውይይቱም ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንቶች ተገኝተዋል፡፡(MoE)

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በ2015 የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ዉጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዩኒቨርሲቲያችን መማር ለምትፈልጉ ዩኒቨርሲቲያችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት ለማሟላት በመንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል ፡፡ ይህንንም እውን ለማድረግ ልዩ ተልዕኮ የተሰጠው ዩኒቨርሲቲያችን የትምህርት ጥራት ማዕከላት ለማድረግ (“We are dedicated to innovative knowledge”) በሚል መርህ ቃል በዘርፉ ብቃት ያላቸውን ሙያተኞችን እያፈራ ይገኛል፡፡

በመሆኑም በ2015 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲተያችን ገብተው በአፕላድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱና የመግቢያ ፈተና ውጤት በማምጣት ያለፉትን መቀበል ይፈልጋል ፡፡

✏️ልዩነታችን
• ለተማሪዎቻችን ለቀጣይ የትምህርት ስኮላርሽፕ መስጠት
• ተማሪዎች የራሳቸው ካሪኩለም (Curriculum ) እንዲቀርፁ ማስቻሉ
• Dual-major/minor degree ማግኘታቸው
• Fast track ተጠቃሚ መሆናቸው
• ያሉን ፕሮግራሞች በሙሉ አለማአቀፍ እውቅና ያላቸው ካሪኩለም Accreditation መሆኑን እየገለፅን ፡-

💢በመጀመሪያ ዲግሪ የሚሰጡ ፕሮግራሞች

1) School of Applied Natural Sciences (SoANS)
• Applied Biology
• Applied Chemistry
• Applied Mathematics
• Applied Physics
• Applied Geology
• Industrial Chemistry
• Pharmacy

2) School of Civil Engineering & Architecture (SoCEA)
• Architecture
• Civil Engineering
• Water Resources Engineering

3) School of Electrical Engineering & Computing (SoEEC)
• Computer Science & Engineering
• Electronics & Communication Engineering
• Electrical Power & Control Engineering
• Software Engineering

4) School of Mechanical, Chemical & Materials Science & Engineering (SoMCME)
• Chemical Engineering
• Materials Science & Engineering
• Mechanical Engineering
ማንኛውንም የዩኒቨርሲቲ መረጃ በዩኒቨርሲቲው ድህረ ገፅ ላይ ማግኘት ይችላሉ ፡፡
http://www.astu.edu.et/ Facebook-


ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ETA

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በሁለት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ካምፓሶች ላይ የእርምት እርምጃ ወስዷል፡፡

ባለሥልጣኑ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባደረገው ድንገተኛ የፍተሻ ጉብኝት የስነ ስርዓት ጥሰት ፈጽመው በተገኙ ሁለት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን አሳውቋል፡፡

ባለስልጣኑ ግሬት ኮሌጅ መገናኛ፣ ቦሌ ሚካኤል እና ቡልቡላ ካምፓሶች እንዲሁም ሮያል ኮሌጅ አዲስ አበባ ሰሜን ካምፓስ ላይ የማስተካከያ እርምጃ ወስዷል፡፡

ከተፈቀደለት የተማሪዎች ቁጥር በላይ መዝግቦ ማስተማር፣ ፈቃድ ሳያገኝ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር፣ ከባለስልጣኑ ባልተሰጠው ፈቃድ ትምህርት መስጠት፤ ተቋማቱ ከፈጸሟቸው ጥሰቶች መካከል ይጠቀሳሉ።

ተቋማቱ ጥሰት በፈጸሙባቸው የትምህርት መስኮች ያሉ ተማሪዎችን እንዲያሰናብቱ እንዲሁም በመስኮቹ ለተከታታይ ከሁለት እስከ ሦሥት ዓመታት ፈቃድ እንዳይጠይቁ እግድ ተጥሎባቸዋል፡፡

በተፈፀመው የህግ ጥሰት ግኝት የተቋሙ ባለሀብቶች እና የበላይ አመራሮች በፍትሐ ብሄር እና በወንጀል ህግ የሚያስጠይቅ ተግባር ካለ በሚመለከታቸው የፍትህ አላካት ተጠያቂ የሚያደረግ መሆኑን ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#አማራ

የክልሉ ትምህርት ቢሮ እየተተገበረ ላለው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ማስተማሪያነት የሚያገለግሉ 2 ነጥብ 7 ሚሊየን መጻሕፍት ማሰራጨቱን አስታውቋል፡፡

አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ ለማድረስ ከ31 ሚሊየን 668 ሺህ 812 በላይ መጻሕፍት ያስፈልጋል የተባለ ሲሆን መጻሕፍቱን በአንድ ጊዜ ለማሳተም ከፍተኛ ወጪ ስለሚጠይቅ ቢያንስ አንድ መፅሐፍ ለሦስት ተማሪዎች እንዲሆን እና በዙር እንዲታተም እየተሠራ ነው ተብሏል፡፡

ከ5 ሚሊየን በላይ መጻሕፍት በውጭ ሀገር የታተሙ ቢኖሩም በውጭ ምንዛሬ እጥረት መረከብ እንዳልተቻለም ተነግሯል፡፡

በውጭ ሀገር ከታተሙት 8 ሚሊየን 888 ሺህ 169 መጻሕፍት ውስጥ እስካሁን 1 ሚሊየን 425 ሺህ 502 መጻሕፍት መሰራጨታቸው የተገለጸ ሲሆን በተጨማሪም በሀገር ውስጥ የታተሙ 944 ሺህ 882 መጻሕፍት መሠራጨታቸውን ነው የተነገረው።

#ኦሮሚያ

በኦሮሚያ ክልል 7 ሚሊየን 35 ሺህ በላይ አዳዲስ የመማሪያ መጽሐፍት ታትመው ለተማሪዎች እየተሰራጩ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
 
በኦሮሚያ ክልል ለተዘጋጀው የቅድመ መደበኛ እና ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል አዲስ ስርዓተ ትምህርት የመማሪያ መጽሐፍት በፍጥነት አሳትሞ ለተማሪዎች ለማሰራጨት በቅንጅት ሲሰራ ቆይቷል ተብሏል።
 
በዚህ መሰረት የመምህራን መምሪያ መጽሐፍትን በቅድሚያ በማሳተም ለሁሉም ትምህርት ቤቶች እንዲሰራጩ መደረጉም ተነግሯል።
 
አሁን ላይም ከ7 ሚሊየን 35 ሺህ በላይ የመማሪያ መጽሐፍት መታተማቸው የተገለጸ ሲሆን ከታተሙት መጽሐፍት ውስጥም 5 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት በክልሉ ለሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች መሰራጨታቸውን ተገልጿል።

ምንጭ፦ FBC

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ተራዝሟል

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርስቲ ምርጫ ማስተካከያ ቀን እስከ የካቲት 03/2013 ዓም. መራዘሙን አሳውቋል።

በ2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ እንዲሁም በመንግስት ተቋማት ገብተው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን እስከ የካቲት 03/2015 ዓ.ም 12፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያስተካክሉ ቀኑ የተራዘመ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደማህበራዊ ሳይንስ ቀይረው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች መቀየር የሚችሉት ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኋላ መሆኑን ገልጾ ይህም የሚሆነው ዩኒቨርስቲዎቹ ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆኑ ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል። ስለዚህ ተማሪዎች የምርጫ ማስተካከያቸውን በጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

ከዚህ ባለፈ ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የትምህርት የልህቀት ማዕከል ሆኖ መደራጀቱን ግንዛቤ አንዲወሰድ ብሏል።

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ሰበር ዜና!

በነገው እለት በየትኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ት/ቤቶች ትምህርት እንዳይኖር ለሁሉም ክፍላተ ከተሞች ትምህርት ጽ/ቤቶች አመሻሹ ላይ ከደቂቃዎች በፊት መልዕክት ተላልፏል።

በየትኛውም የመንግስት ት/ቤቶችም የተማሪዎች ምገባ እንዳይኖር መመሪያ የተላለፈ ሲሆን ወረዳዎች እና ሲፐርቫይዘሮች ክትትል እንዲያደርጉ ትዕዛዝ ወርዷል።

እንደ ምክንያትነት የተጠቀሰውም "በተማሪዎች ውጤት ላይ ውይይት ይደረግ" የሚል መመሪያ ነው።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን እናቀርባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.free.vpn.super.hotspot.open

ቴሌግራም እና facebook አገልግሎት ተቆርጧል ይህንን VPN አውርዳችሁ መጠቀም ትችላላችሁ

@NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
PSIPHON PRO V370 [SUBSCRIBED] [MOD EXTRA].apk
እነዚህን VPNኦች በማውረድ የተቋረጡ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን መጠቀም ትችላላችሁ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን እናቀርባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
መንግሥት የማኅበራዊ ሚዲያዎችን አገልግሎት አቋርጧል‼️

መንግሥት የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎቶችን በኢትዮጵያ የገደበው፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ወቅታዊ ችግር ጋር በተገናኘ መሆኑን “ኔት ብሎክስ” የተሰኘ የኢንተርኔት ግንኙነት አጥኚ ድርጅት ይፋ አድርጓል፡፡

አገልግሎቱ የተቋረጠባቸው የማኅበራዊ ሚዲያዎች ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክ እና ሜሴንጀር ሲሆኑ፣ አገልገሎቱ መቋረጥ የጀመረው ትናንት ምሽት ላይ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መከፋፈል ምክንያት በጸረ-መንግሥት ተቃውሞ በቀጠለበት ወቅት፣ የማኅበራዊ ሚዲያ እና የመልዕክት መላላኪያ መድረኮች ፌስቡክ፣ ሜሴንጀር፣ ቲክቶክ እና ቴሌግራም መዘጋታቸውን የኔትወርክ መለኪያዎች ያሳያሉ።

እንደ “ኔት ብሎክስ” ሪፖርት፣ በእነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ መንግሥት የአገልግሎት ዕቀባ የጣለው በመንግሥት በሚተዳደረውና የኢንተርመኔት አገልግሎት አቅራቢ በሆነው በኢትዮ ቴሌኮም በኩል ነው ተብሏል፡፡

ይሁን እንጂ መንግሥት ያቋረጠውን አገልግሎት፣ የመንግሥት የኢንተርኔት ሳንሱር እርምጃዎችና ገደቦችን ማለፍ በሚችሉ ቨርቹዋል ፕራይቬት ኔትዎርክ (ቪፒኤን) አገልግሎቶችን መጠቅም እንደሚቻል ድርጀቱ ጠቁሟል፡፡ አሁን ላይ ብዙዎች ይህንኑ አግልገሎት ተጠቅመው የማኅበራዊ ሚዲያዎችን አገለግሎት እየተጠቀሙ መሆኑን የሚያመላክቱ መረጃዎች አሉ፡፡

መረጃዎችን እናቀርባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
በአዲሰ አበባ የመንግሥት ትምርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ወደ ቤታቸው መልሰዋል

👉የመንግሥት ሰራተኞች ለስብሰባ ተጠርተዋል


አርብ የካቲት 3 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች፣ ተማሪዎቻቸውን ወደ ቤታቸውን እንዲመለሱ አድርገዋል፡፡

ዛሬ ጥዋት ወደ ትምህርት ቤት ያቀኑ ተማሪዎች ዛሬ ትምህርት የለም ተብለው ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን አዲስ ማለዳ ሰምታለች፡፡ በዛሬው ዕለት ትምህርት እንደማይኖር ትናንትና ማታ ለአንዳንድ የትምህርት ማኅበረሰብ የተገለጸ ሲሆን፣ ዛሬ ማለዳ ለሁሉም እንዲደርስ ተደርጓል፡፡

የዕለቱ ትምህርት የተዘጋው፣ በየትምህርት ቤቱ የሚገኙ መምህራንና በወቅታዊ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ ስብሰባ መጠራታቸውን ተከትሎ መሆኑን አዲስ ማለዳ አረጋግጣለች፡፡ መምህራን ዛሬ ማለዳ በደረሳቸው ትዕዛዝ መሰረት በዛሬው ዕለት በሚካሄውን ወቅታዊ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ በእጅ ስልካቸው እየተደወለ ተነግሯቸዋል፡፡

መምህራኑ በድንገት ስብሰባ መጠራታቸውን ተከትሎ፣ ወደየ ትምህርት ቤታቸውን ማቅናታቸውን ተስምቷል፡፡ የስብሰባው አጀንዳ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ይባል እንጂ ስለ ስብሰባው ምንነት ለመምህራኑ የተገለጸላቸው ነገር የለም፡፡

በሌላ በኩል የፌደራል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት፣ ሰራተኞቻችውን ለስብሰባ መጥራታቸውን አዲስ ማለዳ ከደረሳት የስብሰባ ጥሪ ማስታወቂያ ተመልከታለች፡፡

የስብሰባ አጀንዳው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ባገጠመው ወቅታዊ ችግር መሆኑን ተሰምቷል፡፡ "በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለመወያየት" ተብሎ በየተቋመቱ የተጠራው ሰብሰባ፣ በስብሰባው ላይ ለአስቸኳይ ሥራ ለአዲስ አበባ ከወጡ እና ስብሰባው ከመጠራቱ አስቅድሞ በሕመም ወይም በወሊድ ፈቃድ ከወጡ ውጪ ሁሉም ሰራተኛ በስብሰባው ላይ እንዲገኝ ጥብቅ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡

በትላንትናው ዕለት አንዳንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሰራተኞቻቸውን በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማወያየታቸውና አቅጣጫ መስጠታቸው የሚታወስ ነው፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን እናቀርባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ማስታወሻ

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ያመጣችሁ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን የማስተካከያ ጊዜ ዛሬ የካቲት 03/2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እንድታስተካክሉ በትምህርት ሚኒስቴር #የተራዘመው የጊዜ ገደብ ዛሬ 12፡00 ሰዓት ይጠናቀቃል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁንና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በቀጣዩ ሊንክ ብቻ መላክ አትዘንጉ 👉
https://student.ethernet.edu.et

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot