STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.9K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ወልድያ‼️

ግቢውን ለቃችሁ ለወጣችሁ 2ኛ አመት የወልድያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ ዩንቨርስቲው ከላይ የተያያዘውን ማስታወቂያ አውጥቷል።

#share #ሼር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በጦርነት ምክንያት ከሶስት ጊዜ በላይ ተፈናቅላ ከፍተኛ ውጤት ያመጣችው የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ👏

ተማሪ ገሊላ አሰፋ ትባላለች፤ በአጣዬ ከተማ ተወልዳ ያደገች ሲሆን በአካባቢው በነበረው ግጭቶች ምክንያት ለብዙ ወራት ትምህርት ተቋርጦ ነበር። ወደ አጎራባች ከተሞችም ከሶስት ጊዜ በላይ ከቤተሰቧ ጋር ተፈናቅላ እንደነበርም ትናገራለች።

በዚህ ሁሉ ችግር መሃል የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ የወሰደችው ተማሪ ገሊላ 569 ማምጣቷን ለአልዐይን ተናግራለች።ተማሪ ገሊላ ለዚህ ውጤት መምጣት ከጎኗ የነበሩ ቤተሰቦቿን እና መምህራንን አመስግናለች።

ሳይንቲስት የመሆን ህልም ያላት ተማሪ ገሊላ በውጤቴ ባልረካም ወደ ዩንቨርሲቲ የሚያስገባኝ ስለሆነ አይከፋኝም ብላለች።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ማስተካከያ ‼️

ከትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ተነስቶ ለተማሪዎች ማብራሪያ በሰጠው ላይ ማስተካከያ አድርጓል።

29,909 ተማሪዎች መቼ ወደ ግቢ ይገባሉ የተባለው ገና አልተወሰነም። መግለጫው ላይ ከሰማችሁ በሚቀጥለው አመት ይባል እንጂ ገና ከውሳኔ እንዳልተደረሰ እና የነሱስ ምደባ መቼ ነው የሚለው ገና ነው።

ሌላው እነዚህ ከ 50 በላይ ያመጡ ተማሪዎች Freshman Course ይወስዳሉ ተብሏል። መቼ የሚለው ግን አልታወቀም። ስለዚህ Freshman አይኖርም የተባለው በስህተት ነው።

ለ 50% ቅርብ የሆኑት 100ሺ ተማሪዎች ገና አልተለዩም። ከተለዩ በኋላ በምን መልኩ ክለሳ ይወስዳሉ፣ የት ሆነው ይወስዳሉ፣ ለስንት ጊዜ ነው የሚወስዱት የሚሉ ጥያቄዎችም በዛው ጊዜ መልስ ያገኛሉ።

ስለ Astu, Aastu, Phawulos ውድድር ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ያስቀምጣል። አብዛኛው ተማሪ የጨነቀው ደግሞ College መግባት እችል ወይ? የሚለው ነው።

College'ን አስመልክቶ ምንም አልተባለም። መቼስ ባዶ ሆነው አይቀሩም። ስለዚህ በተስፋ መጠበቅ ነው።

በአጠቃላይ ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች ቅሬታን መልስ ከሰጣ በኋላ ትንታኔ ይሰጣል። ውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ እስከ ጥር 26 ድረስ ቅሬታ ማቅረብ ትችላላችሁ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ትምህርታቸውን አቋርጠው የቆዩ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ መሆኑ ታወቀ!

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል በነበረው ጦርነት ሳቢያ የባከነው የትምህርት ዘመን በሚካካስበት ሁኔታ ላይ የሁለተኛ አመት ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር መስማማት አልቻሉም።በጦርነቱ ሳቢያ ተቋርጦ የነበረውን የሁለት ዓመት ትምህርት በተጣበበ ፕሮግራም በአንድ ዓመት ውስጥ ተምረን መጨረስ አለብን የሚሉት ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ውሳኔ ጋር ባለመስማማታቸው ግቢውን ለቀው እየወጡ መሆናቸውን የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ አስታወቋል።

ከሁለተኛ አመት ተማሪዎች መካከል ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ከሚገኙ ከህግ፣ ከጤና፣ ከአርክቴክቸር እና ከልዩ ፍላጎት አካቶ ተማሪዎች ውጭ ያሉት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ፕሮግራም መሰረት ለመማር ፍላጎት ባለማሳየታቸው ለሁለት ሳምንታት ያክል ትምህርታቸውን አቋርጠው ቆይተዋል።ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በጦርነቱ በደረሰበት ከፍተኛ ውድመት ቤተ ሙከራዎች አገልግሎት መስጠት የማይችሉ በመሆናቸው፣ የትምህርት ሚኒስቴር የተጣበበ የትምህርት የጊዜ ሰሌዳ እንዳይኖር ለሁሉም የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በደብዳቤ በማሳወቁ የተማሪዎች ጥያቄ ተቀባይነትን ሳያገኝ ቀርቷል ተብሏል።

በቀጣይ የሚሰጠው የመውጫ ፈተናና የትምህርት ጥራት ጉዳይ በተማሪዎቹ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ እና የየትምህርቶቹ የኮርስ ባህሪ መለያየት እንዲሁም የጊዜ እጥረት ጋር ተያይዞ ጥያቄያቸው ባለመስተናገዱ መማር የሚፈልጉ እንዲቀጥሉ፣ መማር የማይፈልጉ ደግሞ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ዩኒቨርሲቲው ውሳኔ አስተላልፏል።የዩኒቨርሲቲውን ውሳኔ ተከትሎ ከሁለተኛ አመት ተማሪዎች መካከል ከፊሎቹ ትላንት ማለትም ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ግቢውን ለቀው እየወጡ ናቸው ተብሏል።

[Addis Zeybe]

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የደሴ አዳሪ ትምህርት ቤት አቅሙን ለማሳደግ ድጋፍ እንዲደረግለት ጥሪ አቀረበ!

ተማሪዎችን ለማብቃትና የቅበላ አቅሙን ለማሳደግ ድጋፍ እንዲደረግለት የደሴ አዳሪ ትምህርት ቤት ጥሪ አቅርቧል፡፡

የትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር አቶ ፍቅር በላይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ÷ ትምህርት ቤቱ በወቅታዊ ችግርና በተለያዩ ምክንያቶች ቢያልፍም ከሀገሪቱ ከፍተኛውን ውጤት በማስመዝገብና ተማሪዎችን በማብቃት ቀዳሚ መሆን ችሏል።

ሆኖም ትምህርት ቤቱ የበለጠ እንዳይንቀሳቀስ የመምህራን ዝቅተኛ የኢኮኖሚ አቅም፣ በቂ የሕክምና መገልገያዎችና ሥፍራዎች እጥረት ፣ የባለሙያ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችና የህንጻ  አገልግሎት እጥረትና  መሰል ችግሮችን ጠቅሰዋል፡፡

ወደፊት ትምህርት ቤቱን ለማሳደግና የበለጠ ተፎካካሪ እንዲሆን እንዲሁም ችግሮቹን ለመፍታት ሁሉም አካል በመተባበር መስራት እንዳለበትም ነው ያነሱት።

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ላይ ውጤታማ የሆነው የደሴ አዳሪ ትምህርት ቤት ከዚህ በላይ መስራት እንዲችልና የቅበላ አቅሙን ከፍ አድርጎ ውጤታማ ተተኪ ትውልድን ለመፍጠር ሁሉም እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

አምስት አባላትን የያዘው የትምህርት ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በመቐለ የሥራ ጉብኝት እያደረገ ነው።

በሚኒስቴሩ የአስተዳደር እና መሠረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) የተመራው ቡድን በመቐለ እና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ዳግም ማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከረ ነው፡፡

ወደ መቐለ ያቀናው ቡድን በትግራይ ክልል የከፍተኛ እና አጠቃላይ ትምህርትን ማስጀመር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፋና ሀጎስ (ዶ/ር)፣ ከዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዛይድ ነጋሽ (ዶ/ር) እና ከሌሎች የክልሉ የትምህርት አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል።

የትምህርት ዘርፍ ሰራተኞች ደሞዝ ክፍያ እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች ላይ ውይይት መደረጉን ሰምተናል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ምንድን ነው አንድ ትልቅ የትምህርት ተቋም ከተማሪዎች ጋር እንዲህ እልህ መጋባት እና ማስፈራርያ አዘል መልዕክት ማዥጎድጎድ የያዘው?

ጥፋተኛ እና ትምህርት ለማወክ የሚፈልግ ተማሪ እንዳለ ሁሉ ከዛሬ ነገ ትምህርቴን ጨርሼ፣ ከዛም ራሴን፣ ቤተሰቤንና ሀገሬን ጠቅሜ የሚለው ብዙ ነው። በዛ ላይ እነዚህ ተማሪዎች ጦርነት በነበረበት አካባቢ የነበሩ ናቸው፣ የስነልቦና ጫና ይኖርባቸዋል።

ማስፈራራቱ ቀርቶ ቁጭ ብሎ ተወያይቶ መፍትሄ ማበጀት ይሻላል። ፖለቲከኛው እንኳን በስምምነት ችግሩን እየፈታ አይደል እንዴ?

Elias Meseret

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የግብዓት እጥረት ፈተና እንደሆነባቸው የዳግማዊ ምኒሊክ ትምህርት ቤት ዓይነስውራን ተማሪዎች ተናገሩ
***
(ኢ ፕ ድ)
👉ትምህርት ቤቱ የችግሩ መንስኤ የበጀት ውስንነት ነው ሲል፤ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ ችግሩ የአመራር ነው ብሏል

የመማሪያ ግብዓት አቅርቦት እጥረት መኖሩ ተወዳዳሪ እንዳንሆን እንቅፋት ሆኖብናል ሲሉ በዳግማዊ ምኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዓይነስውራን ተማሪዎች ገለጹ።

የዳግማዊ ምኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ችግሩን ለመቅረፍ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር ብሠራም ተደራሽነቱን ማረጋገጥ አልቻልኩም ብሏል።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ ችግሩ የአመራር እንጂ በቂ በጀት መድቤያለሁ ይላል።

የዳግማዊ ምኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ዓይነ ስውር ተማሪ አብዩ ገብረሚካኤል ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጸው፤ ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች የጽሕፈት፣ የመንገድ መምሪያ መሣሪያ፣ የመቅረፀ ድምፅና የብሬል ተደራሽነት እጥረት በትምህርት ቤቱ አለ።

ትምህርት ቤቱ ማየት ለተሳናቸው ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያግዛቸውን የትምህርት ቁሳቁስ በበቂ ሁኔታ ባለመሟላቱ ከተማሪዎች ጋር በውጤት ለመፎካከር እንቅፋት ሆኖብናል ሲል አብራርቷል። በተጨማሪም በክፍል ውስጥ የሚሰጡ ትምህርቶችንና ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተማሪዎችን ብቁ ለማድረግ የሚሰጡ የተለያዩ ትምህርቶችን እንደ መደበኛ ተማሪዎች መከታተል አለመቻሉንና ፈተናውን ጥሩ ውጤት አስመዝግቦ
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=91174

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተመዘገበው ውጤት የተሻለ መሆኑ ተመላከተ፡፡

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 896,520 ተማሪዎች መካከል፡-
1. 50 ከመቶ እና በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች 3.3 በመቶ ሲሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 19.8 ፐርሰንት ተማሪዎች 50 እና በላይ ማለፊያ ውጤት ማስመዝገብ መቻላቸው፤

2. በሀገር አቀፍ ደረጃ 600 እና በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር 273 ሲሆን ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል 125 ተማሪዎች በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ውጤት ማምጣታቸው፤

3. እንደ ሀገር እጅግ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ 20 ትምህርት ቤቶች መካከል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 10 ትምህርት ቤቶች እጅግ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸው፤

በአጠቃላይ የከተማ አስተዳደሩ ተፈታኝ ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው ውጤት አንጻር በጣም አስደሳችና አበረታች ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ ይሁን እንጂ ውጤቱ ገና የሚቀረው በመሆኑ በቀጣይ ከዚህ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንዲቻል የትምህርት ባለድርሻ አካላት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ የሚናችሁን እንድትወጡ አደራ እያልን ለተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ! ለማለት እንወዳለን፡፡

©የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#TVTI

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2015 የትምህርት ዘመን የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባን ከዛሬ
ጥር 23/2015 ዓ.ም እስከ አርብ ጥር 26/2015 ዓ.ም ያከናውናል።

በተቋሙ ዋና ግቢ ለመማር ያመለከታችሁና የመግቢያ ፈተና ያለፋችሁ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ በተገለጹት ቀናት ይከናወናል።

፨መረጃው የ2014 ተፈታኝ ተማሪዎችን አይመለከትም‼️

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ASTU #AASTU

በ2014 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ውጤት ያመጣችሁና ወደ ሁለቱ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በመግባት ትምህርታችሁን መከታተል ለምትፈልጉ ተማሪዎች ስለ መግቢያ፣ምዝገባ እና ሌሎች ጉዳዮችን አስመልክቶ በቀጣይ የሚገለፅ በመሆኑን ተማሪዎች በትዕግስት ትጠብቁ ዘንድ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አሳውቋል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
“ራሴን ማየት የምፈልገው ናሳ ገብቼ ነው” ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበው ሚክያስ አዳነ

ሚክያስም ከስድስተኛ ክፍል ጀምሮ ለአስትሮኖሚ እና ፊዚክስ ልዩ ፍላጎት እንዳዳበረ ይናገራል። በብሔራዊ ፈተና ውጤቱ ፊዚክስ 100 ነው ያመጣው። የውጭ አገር የትምህርት ዕድል ካገኘ አስትሮፊዚክስ ማጥናት እንደሚፈልግ ሚክያስ ይናገራል። ከወዲሁም የትምህርት ዕድሎች እያፈላለገ ነው። “ራሴን ማየት የምፈልገው ስፔስ ኤክስ ወይም ናሳ ገብቼ ነው” ሲል የወደፊት ሕልሙን ለቢቢሲ አጋርቷል።
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚንስቴር ዴኤታው ዶክተር ሳምኡል ክፍሌ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ከተናገሩት የተወሰደ 👇

፨ከ50% በላይ ያመጡ ተማሪዎች በሙሉ በባቻቸው ፍሬሽማን ኮርስ ይጀምራል።

፨ከ50% በታች ያመጡ ተማሪዎች ሶስት አማራጭ አላቸው

1) *መንግስት የሚሰጠውን ሁለተኛ ዕድል በመጠቀም የማካካሻ ትምህርት መውሰድ እና አንድ ባች ዝቅ ብሎ ፍሬሽማን መጀመር።(መቁረጫ ነጥብ ለሚያሟሉ)

*ከመንግስት ዩንቨርሲቲ ውጭ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የማካካሻ ትምህርት ተምረው በድጋሚ የወደቁባቸውን ትምህርት በመከታተል ቀጣይ ዓመት በግል ፍሬሽማን ኮርስ መጀመር

2) ከቀጣይ ተፈታኞች ጋር በግል ድጋሚ መፈተን

3)ቴክኒክና ሙያ መሰልጠን

በመንግስት ስፖንሰርነት ማካካሻ የሚወስዱ የ#100ሺህ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ከ10-15 ቀን ጊዜ ውስጥ ይፋ ይደረጋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ተጨማሪ_ማብራሪያ ‼️

29,909 ተማሪዎች ምደባ ተደርጎላቸው ቀጣይ ወደ ዩኒቨርስቲ ገብተው Freshman ይማራሉ። ከዚሁ ውስጥ Astu, Aastu እና Phaulos መወዳደር የፈለጉም ተወዳድረው ይገባሉ።

100ሺ ተማሪዎችም ተመልምለው ዩኒቨርስቲ ገብተው የማካካሻ ትምህርት ይወስዳሉ። የማካካሻ ትምህርቱ በወደቁበት/በደከሙበት / Subject ብቻ ይሆናል። ከዛም ፈተና ወስደው ካለፉ እዛው ዩኒቨርስቲ ቀጣይ አመት Freshman ይጀምራሉ።

College ትምህርት ዘንድሮ የለም። ነገር ግን በግል ኮሌጅ ገብቼ የማካካሻ ትምህርት እማራለሁ የሚሉ ካሉም ትምህርት ሚኒስቴር ፈቅዷል። ስለዚህ የ College መግቢያ ቀጣይ ይነገራል።

ሌላው ደግሞ ቴክኒክ እና ሙያ መማር ነው። ይሄንን የማይፈልግ ደግሞ ከ 2015 ተፈታኞች ጋር በ Private መፈተን ይችላል

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው #ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን ወጪ እንደሚሸፍን አማራ ባንክ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

በዚህም ወጪያቸው የሚሸፈንላቸው ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 በላይ ውጤት እና ለማኅበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ500 በላይ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች መሆኑን ባንኩ ገልጿል፡፡

#ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው በወር 750 ብር እየከፈለ እንደሚያስተምር ባንኩ መግለፁ ይታወሳል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በመላ ሀገሪቱ #ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅናና ሽልማት እሰጣለሁ ማለቱ አይዘነጋም።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በቅርቡ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የመልቅቂያ ፈተና የተገኘውን ውጤት አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ብለዋል👇

"ከብዙ ጥናትና ሙግት በኋላ ኩረጃና ሥርቆትን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ተግባራዊ የተደረገው የተማከለ የፈተና ስልት ያስገኘው ውጤት ከፍተኛ ማኅበረሰባዊ መደናገጥን ሲፈጥር ታይቷል። ከተፈታኞቹ ሃምሳ ከመቶና ከዚያ በላይ ጥያቄዎቹን መልሰው ለማለፍ የቻሉት ተማሪዎች ቁጥር እጅግ አናሳ ናቸው። በሺህ የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች አንድ ተማሪ እንኳን ለማሳለፍ ያልቻሉበት ሁኔታ ተፈጠረ። ይህም የትምህርት ጥራት ላይ ያሉብንን ችግሮችና ያለንበትን ቀውስ ፍንትው አድርጎ አሳየን። የችግሩን ልክ በአግባቡ፣ በአሐዝ መረጃ የተገነዘበነው እና ያየነው አሁን ቢሆንም፣ ችግሩ ግን በፈተናው የተገለጠ እንጂ የተፈጠረ አይደለም። የትምህርት ሥርዓቱ ስብራት ዛሬ የተፈተኑትን ተማሪዎች የሚያስተምሩ አስተማሪዎች ከተመለመሉበት፣ ከሠለጠኑበት መንገድ፣ አጠቃላይ የትምህርት ሥርዓቱ ከተመራበት ፖሊሲና አቅጣጫ እና ከሌሎች ብዙ ጉዳዮች ጋር የተያይዘ፤ ባለፉት አሥርት አመታት የሄድንበት የተንሻፈፈ ጉዞ ውጤት ነው። ዛሬ የችግር ሰብሉን ብናጭድም ዘሩ አፈር ነክቶ መብቀል ከጀመረ ዘመናት ተቆጥረዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ አንድ እውነት ማወቅ አለብን፤ ችግሩ በአንድ ሌሊት እንዳልተፈጠረ ሁሉ መፍትሔውም በአንድ አዳር ሊመጣ አይችልም። ዛሬ ከአበባ አልፎ ፍሬውን ያየነውን የትምህርት ችግር ቀልብሶ ለማስተካከል ረጅም ጊዜና ከባድ ዋጋ ይጠይቃል። እንዲህ ያለው ስብራት በአንድ ዘርፍ ብቻ ያለ ችግር ነው ብሎ ማሰብ ስህተት ነው። "


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በጦርነት ሙሉ በሙሉ ከወደሙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 71 የሚሆኑት በ2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ወጭ በዚህ ዓመት እንደሚገነቡ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ትምህርት ሚኒስቴር ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እየሰራ መሆኑን ሚነስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ አስታወቁ።
---------------------------------------------
ጥር 25/2015ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር ) ሚኒስትሩ በጦርነት የወደሙና በልዪ ሁኔታ የሚገነቡ 71 ትምህርት ቤቶችን ስራ በይፋ አስጀምረዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በ71 ትምህርት ቤቶች ይፋዊ ስራ ማስጀመሪያ መርሀግብር ላይ እንደገለጹት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ትምህርት ቤቶች በተሻለ ዲዛይን የሚጠበቅባቸውን መሠረተ ልማት አሟልተው ይገነባሉ።

ምቹና የተሻሉ ትምህርት ቤቶችን መገንባት ለትምህርት ጥራት ወሳኝ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ትምህርት ቤቶቹ በዚህ ዓመት ተገንብተው እስከ መጪው መስከረም ወር ድረስ ለአገልግሎት እንደሚበቁ ተናግረዋል።

ከ71 ትምህርት ቤቶች መካከል 50ዎቹ በዓለም ባንክ ድጋፍና ትብብር 16ቱ በሰዎች ለሰዎች ድርጅት እንዲሁም 5ቱ በዲያስፖራ ትረስት ፈንድ እንደሚገነቡ አመልክተዋል።

በመሆኑም የስራ ተቋራጮችና አማካሪዎች የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ በተያዘላቸው ጊዜ ገንዘብና የጥራት ደረጃ ተገንብተው ለአገልግሎት እንዲበቁ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

የትምህርት ፕሮግራሞችና ጥራት መሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዩሐንስ ወጋሶ በበኩላቸው በጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን በተሻለ መንገድ ለመገንባት እየተሰራ ነው ብለዋል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot