STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.6K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#Update

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከ50 በላይ ያመጡት ከተፈታኞች ውስጥ 3.3 በመቶ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፈተናውን በትክክል ከወሰዱት 896,520 ተማሪዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ ያመጡት፤ 29,909 መሆኑን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በትላንትናው ዕለት ይፋ የተደረገውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

ተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
#Update የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከ50 በላይ ያመጡት ከተፈታኞች ውስጥ 3.3 በመቶ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። ፈተናውን በትክክል ከወሰዱት 896,520 ተማሪዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ ያመጡት፤ 29,909 መሆኑን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በትላንትናው ዕለት ይፋ የተደረገውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ዛሬ…
የትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ሪፖርት ዋና ዋና ግኝቶችን ይፋ አድርጓል ።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2014 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች በአዲስ መልክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርስቲዎች  መሰጠቱን አስታውሰው ይህ አዲስ አካሄድ ቀጣይ እርምጃዎቻችንን የሚለኩ ነበሩ ብለዋል።

ሀቀኛ እና ትክክለኛ የተማሪዎችን የትምህርት ክህሎት በመለካት  የፈተና ሂደቱ ከኩረጃ፣ የፈተና ስርቆት የፀዳ ነው ተብሏል።

በዚህ ፈተና ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ የሚኮሩበት ነው ተብሏል።

በ2014 ዓም የትምህርት ዘመን ለፈተና የተመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላላ 985ሺ 3354 ተማሪዎች ሲሆኑ ለፈተና የቀረቡት 92.2 % 908ሺ ሺህ 256 ተማሪዎቹ ሲሆኑ 77ሺህ 98 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም ተብሏል።

በደንብ  ጥሰት ፣ለመኮራረጅ በመፈለግ እና በሌሎች ምክንያቶች 50ሺህ 170 ተማሪዎች ሳይፈተኑ ቀርተዋል።

በ2014 የትምህርት ዘመን 899ሺህ 520 ተማሪዎች ተፈትነዋል ።

በፆታ ማዕከልነት የአማካይ ውጤት በወንዶች 30.2 እንዲሁም ሴቶች 28.09 % አማካይ ውጤት አስመዝግበዋል።

በትምህርት ዘርፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ በተሻለ ውጤት ያስመዘገቢ ሲሆን  የተፈጥሮ ሳይንስ 31.63 ከመቶ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ 27.79 ከመቶ በአማካኝ አስመዝግበዋል።

በከሰልል ደረጃ ይህየ ነው የሚባል የውጤት ልዮነት እንደሌለ የተገለፀ ሲሆን አዲስ አበባ፣ሀረሪ እና ድሬደዋ የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል።

ከተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወንድ ከ 700፤  666 ያስመዘገበ ሲሆን 650 ሴት ተማሪ አስመዝግባለች ።

በማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ወንድ 524 አስመዝግቧል።

እነዚህ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎይ በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና እና ሽልማት ይሰጣቸዋል ተብሏል።

የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ ‼️

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
❗️❗️ወልድያ ዩኒቨርሲቲ እንደወረደ
የወልድያ ዩኒቨርስቲ 2013 ባች አደጋ ውስጥ ነን
ከነገ ጀምሮ ምግብ አትበሉም ተብለናል
በጦርነት ምክኒያት የባከነውን ጊዜ በአመት 3 ሴሚስተር አድርጋችሁ አስተምሩን የሚለውን አግባብ ያለው ጥያቂያችንን አልተቀበሉትም
የ2013 ባች ተማሪዎች አድማ ከጀመርን 2 ሳምንት አልፎናል መማር የምትፈልጉ ሪፖርት አድርጉ ቢባልም በአቅማችን ፀንተን አንድ ሆነናል
❗️ተሪዎች በፌደራል እየተወሰዱ ነው ችግራችንን ከመፍታት ይልቅ ጉልበት እየተጠቀሙ ነው ከነገጀምሮ ምግብ አትበሉም ተብለናል
❗️እስካሁን 3ኛ አመትን መጨረስ ቢገባንም ነገር ግን ሁለኛ አመትን ከጀመርን  ወር አልሆነንም
❗️ወደቤት እንዳንሄድ አጣዬ መንገድ ተዘግቷል ቤተሰባችንም እኛም ስጋት ላይ ነን ድምፅ ሁኑልን
ጊቢው ለተማሪዎቹ አስቦ አያውቅም በጦርነቱ ምክኒያት በእግራችን እስከመርሳ እና ውጫሌ ስንሄድ መጥቶ ያረጋጋን ሰው አልነበረም ጊቢ ውስጥ እንድንቆይ የሚያደርግ ማስታወቂያ ሳይወጣ አመራሮች በመኪናቸው ሲሸሹ መንገድ ላይ ተገናኝተናል
ተማሪዎቹ ድምፃቸውን አሰምተዋል


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ቅሬታ ማቅረብ ተጀምሯል ‼️

👉ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።




የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደማይቀላቀሉ የተገለጸ ሲሆን ነገር ግን የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት በውጤታቸው መሰረት ተጨማሪ ተማሪዎችን በመቀበል ለቀጣይ ዓመት ዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት እንዲያገኙ ይሰራል ተብሏል።

እስከ 100 ሺሕ የሚደርሱ ከ50 ከመቶ በታች ያስመዘገቡ ተማሪዎች፣ በውጤት ተለይተው ማካካሻ ትምህርት ወስደው በቀጣይ ዓመት የፈተና ዕድል ያገኛሉ ተብሏል። ማካካሻውን የሚወሰዱ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ ገብተው ማካካሻውን ከወሰዱ በኋላ ማለፊያ ውጤት ካስመገቡ በዚያው የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን እንደሚቀጥሉም ተገልጿል።



የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
“ለዚህ ውድቀት መንግስት ተጠያቂ ነው”- ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ


የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት በተመለከተ ዛሬ በሰጡት መግለጫ “ለዚህ ውድቀት መንግስት ተጠያቂ ነው፣ የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግስታት ኃላፊነታቸው አልተወጡም” ሲሉ ወቀሱ።

በጣም የሚያስደነግጥ ውጤት መሆኑ ማወቅ አለብን ያሉት የትምህርት ሚኒስትሩ “የወደቅነው እንደ ሀገር ነው” ብለዋል። የዘንድሮ የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱ 896 ሺህ 520 ተማሪዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች 3.3 በመቶ ወይም 29 ሺህ 909 ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን ተከትሎ ነው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይህን የተናገሩት።

ይህ በመሆኑም ዩኒቨርስቲዎች ያላቸው የመቀበል አቅም በመገምገም እሰከ 100 ሺህ የሚደርሱ ከ50 በመቶ በታች ያስመዘገቡ ተማሪዎች ውጤታቸው ዝቅ ባሉባቸው የትምህርት አይነቶች ትምህርት ወስደው በመጪው ዓመት የፈተና ዕድል ያገኛሉ ብለዋል። ሚኒስትሩ አክለውም ይህ የማካካሻ ትምህርት የሚወስዱ ተማሪዎች ባመጡት ውጤት ይለያሉ ሲሉ ተናግሯል።

“የዘንድሮው የ12ኛ ብሔራዊ ፈተና አሰጣጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ንፁህ የሆነ፣ ከኩረጃ የፀዳ እንዲሁም በእውነት ላይ የተመሰረተ ውጤት እንዲመጣ ያደረገ ነውም” ብለዋል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
🏷ከተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች

ወንድ 666/700
ሴት 600/700

🏷በማህበራዊ ሳይንስ

ሴት 524/600
ወንድ 516/600

እነዚህ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና እና ሽልማት ይሰጣቸዋል ተብሏል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አሰራር ለመከተል ማቀዱን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት ከግማሽ በላይ ያመጡት 30 ሺህ ገደማዎቹ ተማሪዎች በሚቀጥለው ዓመት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲ ገብተው የአንደኛ ዓመት ተማሪ ይሆናሉ።

ቀሪዎቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም መሰረት በማድረግ፤ የተሻለ ያመጡት ተመርጠው ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ እንደሚደረግ አስረድተዋል።

ይሁንና እነዚህ ተማሪዎች በቀጥታ የዩኒቨርስቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንደማይሆኑ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቁመዋል።

ተማሪዎቹ " የደከሙባቸው ትምህርቶችን” ለአንድ ዓመት በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እየተማሩ ከቆዩ በኋላ፤ በዓመቱ መጨረሻ ፈተና ወስደው ካለፉ በዩኒቨርስቲዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪ ሆነው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል።

Credit : ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ቅሬታ ማቅረብ ለምትፈልጉ ‼️

👉ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት

1. https://eaes.edu.et/

2. result.neaea.gov.et

ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ቀን 19/5/2015 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተመዘገበው ውጤት የተሻለ መሆኑ ተመላከተ፡፡

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 896,520 ተማሪዎች መካከል፡-
1. 50 ከመቶ እና በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች 3.3 በመቶ ሲሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 19.8 ፐርሰንት ተማሪዎች 50 እና በላይ ማለፊያ ውጤት ማስመዝገብ መቻላቸው፤

2. በሀገር አቀፍ ደረጃ 600 እና በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር 273 ሲሆን ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል 125 ተማሪዎች በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ውጤት ማምጣታቸው፤

3. እንደ ሀገር እጅግ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ 20 ትምህርት ቤቶች መካከል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 10 ትምህርት ቤቶች እጅግ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸው፤

በአጠቃላይ የከተማ አስተዳደሩ ተፈታኝ ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው ውጤት አንጻር በጣም አስደሳችና አበረታች ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ ይሁን እንጂ ውጤቱ ገና የሚቀረው በመሆኑ በቀጣይ ከዚህ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንዲቻል የትምህርት ባለድርሻ አካላት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ የሚናችሁን እንድትወጡ አደራ እያልን ለተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ! ለማለት እንወዳለን፡፡

[Adiss ababa education office ]

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
መግለጫውን በአንድ ፎቶ

(AlAin)

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ከ800ሺ በላይ የሚሆኑትን ተማሪዎች ጉዳይ በተመለከተ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመግለጫቸው በብዛት ወደ #TVET (ቴክኒክና ሙያ) ለማስገባት እንደታሰበ ተናግረዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ግቢ የሚገቡት 100ሺ ተማሪዎች ጉዳይን በተመለከተ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመግለጫቸው ለአንድ ዓመት የዩንቨርሲቲ ተማሪ ሳይሆን በዩንቨርሲቲዎች የማካካሻ ትምህርት ተምረው የዓመቱ መጨረሻ ላይ ተፈትነው የሚያልፉት ከ#29ሺዎቹ ጋር ፍሬሽማን ኮርሶችን ይወስዳሉ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በ1ሺህ 161 መደበኛ ትምህርት ቤቶች አንድም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ አላለፈም!

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ በመግለጫቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ካስፈተኑ 2 ሺህ 959 የመደበኛ ትምህርት ቤቶች መካከል 1 ሺህ 161 የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪዎችን እንዳላሰለፉ አስታውቀዋል፡፡

በውጤቱ መሰረት ከአጠቃላይ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 798 ትምህርት ቤቶች ቢያንስ አንድ ተማሪ ያሳለፉ መሆኑ ታውቋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
በ1ሺህ 161 መደበኛ ትምህርት ቤቶች አንድም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ አላለፈም! በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል። ሚኒስትሩ በመግለጫቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ካስፈተኑ 2 ሺህ 959 የመደበኛ ትምህርት ቤቶች መካከል 1 ሺህ 161 የሚሆኑት…
- 7 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች በሙሉ ያሳለፉ ሲሆን እነዚህም ትምህርት ቤቶች ፦

👉 ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ ቤት፣
👉 ኦዳ አዳሪ ልዩ ት/ቤት ፣
👉 ባህርዳር ስቴም ት/ቤት  ፣
👉 ወላይታ ሊቃ ት/ቤት፤
👉 የጎንደር ማህበረሰብ አቀፍ ት/ቤት እና ከግል ትምህርት ቤት ደግሞ ለባዊ ት/ቤት ናቸው።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
አጠቃላይ መረጃ‼️‼️
1. የተማሪዎች አማካይ ውጤት በየትምህርት አይነቱ፤

አጠቃላይ መረጃ፡-  ፈተና የተፈተኑ ብዛት-----908,256 ናቸው፡፡
  አማራ………..30.37%
  ኦሮሚያ…..…27.96%
  ደቡብ………..28.17%
  ሀረሪ…………32.88%
  አዲስ አበባ----38.46%
  ደሬደዋ--------31.42%
  ሲዳማ---------28.34%

2. ከ50% እና በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት ከተፈተኑ መካከል
(እንደ ሀገር ያለፉ 29909 (3.3%) ናቸው
  አማራ………ከ246,675 መካከል 8,810 ((3.6%)
  ኦሮሚያ…..…327,737 መካከል 6,407 (2.0%)
  ደቡብ………..ከ127,345 መካል 2,533 (2.0%)
  ሀረሪ…………ከ1,849 መካከል 194 (10.5%)
  አዲስ አበባ----ከ47,980 መካከል 9,491 (19.8%)
  ደሬደዋ-------- ከ3,726 መካከል 250 (6.7%)
  ሲዳማ---------ከ53,478 መካከል 1247 (2.3%)

3. ተፈጥሮ ሳይንስ  ከ600 እና በላይ እንደ ሀገር 263 ተማሪዎች ያስመዘገቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ
  አማራ………70 ተማሪዎች
  ኦሮሚያ…..…51 ተማሪዎች
  ደቡብ………..10 ተማሪዎች
  ሀረሪ…………1 ተማሪዎች
  አዲስ አበባ----117 ተማሪዎች
  ደሬደዋ-------- 2 ተማሪዎች
  ሲዳማ---------8 ተማሪዎች

4. ማህበራዊ ሳይንስ  ከ500 እና በላይ እንደሀገር 10 ተማሪዎች ያስመዘገቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ
  አማራ………1ተማሪ
  አዲስ አበባ----8 ተማሪዎች
  ደሬደዋ-------- 1 ተማሪ

5. ሁሉንም ተማሪዎች 100% ያሳለፉ ት/ቤቶች 7 ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ
  ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት
  ባሕር ዳር ስቲም ት/ቤት
  ጎንደር ኮሙኒቲ ስኩል
  ወላይታ ሶዶ ሊቃ ት/ ቤት
  አዳማ ኦዳ አዳሪ ት/ ቤት
ናቸው።
6. ከፍተኛ ውጤት (የዓመቱ ሰቃይ)
 ከአማራ ክልል ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ተማሪ ሚኪያስ አዳነ 666 አስመዝግቧል። በትምህርት ስርዓቱ እንደ ሀገር ወድቀናል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ክልሎች ከ350 በላይ ወይም ከ50% በላይ ያመጡ ደረጃ በመቶኛ!

▪️1ኛ. አዲስአበባ ከተማ.......19.8
▪️2ኛ. ሀረር ከተማ...............10.5
▪️3ኛ. ድሬድዋ ከተማ...........6.7
▪️4ኛ. አማራ ክልል..............3.6
▪️5ኛ. ሲዳማ ክልል.............2.3
▪️6ኛ. ትግራይ ክልል...........2.2
▪️7ኛ. ደቡብ ክልል..............2.0
▪️8ኛ. ኦሮሞ ክልል...............2.0
▪️9ኛ. ቤሻንጉል ጉምዝ.........1.5
▪️10ኛ ጋምቤላ ክልል...........1.2
▪️11ኛ. ደቡብ ምዕራብ...........1.0
▪️12ኛ. ሶማሌ ክልል...............0.7
▪️13ኛ. አፋር ክልል ................0.6


ምንጭ:- የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነው!

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ከሁለተኛ ዓመት ተማሪዎቻችን ጋር የነበረው መጠነኛ አለመግባባት በውይይት ተፈትቷል።

የወልድያ ከተማ የሃይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎችና የፀጥታ አካላት በተለያዩ መድረኮች ከተማሪዎችና ከተቋሙ ሴኔት ጋር ባደረጉት ውይይት ስምምነት ላይ በመደረሱ አለመግባባቱ ተፈትቷል። ቅሬታ የነበራቸው ተማሪዎቻችንም ዩኒቨርሲቲው ባስቀመጠው ካሌንደር መሠረት ለመስተናገድ ዛሬ 1400 ወደ ግቢያቸው የይቅርታ ፎርሙን እየሞሉ ገብተዋል። ቀሪዎቹ ተማሪዎች በተቀመጠው ጊዜ ገደብ መሠረት እስከ ነገ እኩለ ቀን ድረስ መመለስ እንደሚችሉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በዚህ አጋጣሚ የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት ጥረት ያደረጋችሁ የወልድያ ከተማ የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣የወልድያ ሪጂዮ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር በተለይም የፀጥታ አካላቱ የተማሪዎቹን ደህንነት በመጠበቅ በኩል ለነበራችሁ አበርክቶ በዩኒቨርሲቲያችን ስም እናመሠግናችኋለን።

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot