STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
በአዲስአበባ አንዳንድ ት/ት ቤቶች ስለተፈጠረው ችግር ኢዜማ ለአዲስ አበባ ት/ት ቢሮ ማብራራያ እንዲሰጠዉ በደብዳቤ ጥያቄ ባቀርብም ምላሽ አልተሰጠኝም አለ

👉🏽 ፓርቲዉ ህገወጥ ያለዉ ተግባር ካልቆም ጉዳዩን ወደ ህግ እንደሚወስደዉ አስጠንቅቋል


በአዲስ በአበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልልን አርማ መሰቀልና መዝሙር መዘመርን አስመልክቶ ህዳር 29/2015 ዓ.ም. ፓርቲዉ ባወጣው መግለጫ ይህ ህገ ወጥ ተግባር በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል ብሎ እንደሚያምን አጽንኦት ሰጥቶ አሳስቧል ሲል ፓርቲዉ አስታዉሷል። የሚመለከተው አካልም ለከተማው ነዋሪዎች ግልፅ የሆነ መረጃ እንዲሰጥ ፓርቲዉ ጥሪውን አቅርቤያለሁ ብሏል፡፡

ሆኖም አሁንም በትምህርት ቤቶች እየተነሳ ያለው ሁከት ቀጥሎ መዝሙሩም ይዘመራል አርማውንም እንሰቅላለን የሚለው ግብ ግብ እንደቀጠለ ነው ሲል ኢዜማ አስታውቋል፡፡

ፓርቲዉ ይህን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተልኩት ነዉ ያለ ሲሆን ለሚመለከታቸው አካላትም በጉዳዩ ላይ ማብራርያ እንዲሰጡና እና ይህ ሕገወጥ ተግባር እንዲቆም የሚጠይቅ ደብዳቤዎችን አስገብቻለሁ ብሏል።

ነገር ግን የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽ/ቤት ሁለት ጊዜ ፓርቲዉ የላከውን ደብዳቤ አልቀበልም በማለት ለህግ እንደማይገዛና በማናለብኝነት አንደሚንቀሳቀስ በገሀድ አስመስክሯል ሲል ከሷል፡፡

አሁንም በድጋሚ ብጥብጡን እየፈጠረው ያለውን አርማ የመስቀልና መዝሙር ዘምሩ የማለት ግዳጅ እንዲቆም ኢዜማ እየጠየቀ ፤ በቀጣይነትም ጉዳዩን ወደ ህግ አግባብ ወስደን እልባት እንዲያገኝ ከማድረግ ወደኃላ እንደማንል ለማረጋገጥ እንወዳለን ብሏል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቅሬታ

ትምህርት ሚኒስቴር የ2014/15 የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በስኬት ማጠናቀቁን በማስመልከት በነበረው መግለጫ ላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚኒስትር የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በፀጥታ ችግር እና ባጋጠሙ ድንገተኛ አደጋዎች ምክንያት ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ በሁለተኛ ዙር ፈተና ፕሮግራም እንደሚፈተኑና ውጤትም እንደ አጠቃላይ ከአንድ ወር ተኩል ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማለትም ከሁለተኛው ዙር ፈተና በኋላ በ15 ቀናት ውስጥ ይፋ እንደሚደረግ መግለፃቸው ይታወሳል።

ፈተናው ከተሰጠ እነሆ ከአንድ ወር ተኩል በላይ ጊዜ የተቆጠረ ቢሆንም ዛሬም የሁለተኛው ዙር ፈተና የሚሰጥበት ቀን በይፋ አልተነገረም።በመጀመሪያው ዙር ፈተና የወሰዱ ቁጥራቸው ከዘጠኝ መቶ ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች "ትምህርት ሚኒስቴር ቃሉን የሚያከብረው መቼ ነው?" በማለት ጠይቀዋል።

፨ትምህርት ሚኒስቴር ግን ቃሉን የሚያከብረው መቼ ይሆን 🤔

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ “ለህግ እንደማይገዛና በማናለብኝነት አንደሚንቀሳቀስ በገሀድ አስመስክሯል” ሲል ኢዜማ ወቀሰ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ “ለህግ እንደማይገዛና በማናለብኝነት አንደሚንቀሳቀስ በገሀድ አስመስክሯል” ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ወቀሰ።

ፓርቲው በአዲስ በአበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልልን ባንዲራ መሰቀልና መዝሙር መዘመር ጋር በተያያዘ “ይህ ህገ ወጥ ተግባር እንዲቆም እና ማብራሪያ እንዲሰጥበት” የትምህርት ቢሮውን በደብዳቤ ቢጠይቅም ሁለት ጊዜ የተላከ ደብዳቤ “አልቀበልም ብሏል” ሲል ቢሮውን ወቅሶታል።

ኢዜማ በጉዳዩ ላይ ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ “ይህ ህገ ወጥ ተግባር በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል” በማለት አሳስቦ ነበር። ዛሬ ባወጣው መግለጫም በትምህርት ቤቶች ውስጥ ሁከቶች ቀጥለዋል ብሏል።

ፓርቲው ለሚመለከታቸው አካላት ልኬዋለሁ ባለው ደብዳቤ “ብጥብጡን እየፈጠረው ያለውን አርማ የመስቀልና መዝሙር ዘምሩ የማለት ግዳጅ እንዲቆም” ጠይቆ በቀጣይነትም ጉዳዩን ወደ ህግ አግባብ እንደሚወስና እልባት እንዲያገኝ ከማድረግ ወደኃላ እንደማይል አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በአዲስ አበባ በትምህርት ቤቶች አካባቢ ሁከት ለመፍጠር የሞከሩ 72 ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቆ ነበር።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ETA

የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ሁሉም የግል የከፍተኛ  ትምህርት ተቋማት አሁን በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ እንዲልኩ አሳሰበ።

ባለሥልጣኑ አሁን በግል የከፍተኛ ትምህርት ቋማት በመማር ላይ የሚገኙ  ተማሪዎች የተመዘገቡበትን አግባብ ማየት አስፈላጊ ሆኖ በማግኝቱ እውቅና በሰጣቸው የትምህርት መስኮች በትምህርት ላይ የሚገኙ የተማሪዎችን  የስም ዝርዝር የያዘ መረጃ በሶፍትና በሀርድ ኮፒ በማጠናቀር በ30 ቀናት ውስጥ እንዲልኩ አሳስቧል፡፡

የሚላከው የተማሪዎች መረጃ  #በፕሬዝዳንት ወይም #በበላይ_ኃላፊ ተፈርሞ መውጣት እንዳለበት ከዚህ ውጪ ፈራሚ አካል ካለ  ስምና  ኃላፊነት የሚገልጽ ደብዳቤ  በነዚሁ የበላይ ኃላፊዎች እንዲገለጽ  እና  የተማሪዎችን መረጃ  በተናጥል በሚልኩ  ተቋማት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በአዲስ አበባ የትምህርት ቤቶች ጉዳይ የከተማው አስተዳደር፣ ትምህርት ቢሮ ፣ ፖሊስ ፣ ወላጆች ምን ይላሉ ?

የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፦

" ሲጀመር አዲስ አበባ አፋን ኦሮሞ የምታስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልነበራትም መምህራኖች ታውቃላችሁ ይሄንን እውነት።

ያኔ ቀርቶ እስካሁንም አፋን ኦሮሞ ወይም ቋንቋዎች የምናስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልጨረስንም አላፀደቅንም።

ስርዓተ ትምህርት ከኦሮሚያ ተዋስን አፋን ኦሮሞ የሚሰጠው ኦሮሚያ ነው ይህ በዘመነ ኢህአዴግ ነው።

እዛ ላይ ስርዓተ ትምህርቱ ላይ ምን አለ ትምህርት ክፍል ከመጀመሩ በፊት የክልሉ መዝሙር ይዘመራል፤ የክልሉ ባንዲራ ይሰቀላል የሚል አለ።

ይህን ሙሉ ስርዓተ ትምህርቱን በመተግበር ነው 4 ትምህርት ቤቶች (አ/አ ያሉ) የጀመሩት። በውቅቱ አጀንዳ ያደረገውም የለም። በዚህ ምክንያት በተለየ ሁኔታ ኦሮሞ ይጠቀማል ተብሎ የታሰበ ነገር አልነበረም።

ከዛ ተማሪዎች እያደር እየሰፉ መጡ ፣ ከየአካባቢው ፍላጎት ያላቸው ፣ በየአካባቢው ተመዝጋቢ እየበዛ መጣ ኦሮሞም የሆነ ያልሆነ መማር የሚፈልግ እየተመዘገበ መጣ።

እና እንዴት አድርገን ነው የካ ላይ የተመዘገበን ሄደህ ኮልፌ ላይ ነው የምትማረው የምንለው ? ለምን በአካባቢው ላይ ባለ ት/ቤት ክፍል የማንከፍትለት ?

በአካባቢው ትም/ቤት ላይ ፤ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማር እንዲችሉ ትምህርት ቤት እየተከፈተ (በ403 ትምህርት ቤት ውስጥ) በአፋን ኦሮሞ መማር ተጀመረ ሲጀመር ይኸው ካሪኩለም / ስርዓተ ትምህርት ነው አብሮ እየሄደ ያለው።

መማህራኖች፣ ትምህርት ቤቶች እጃቸው ላይ ያለው ስርዓተ ትምህርት እሱ ነው ስርዓተ ትምህርቱን ተግብሩ ተብሎ ስለተሰጣቸው ስርዓተ ትምህርቱ ላይ ያለውን ሙሉ ነገር እየተገበሩ መጡ ይኸው ነው። "

የአ/አ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፦

" የሆኑ ት/ቤቶች ላይ ይሄንን ቋንቋ አንሰማም የሚል ይህ መዝሙር መዘመር የለበትም የሚል ጥያቄ ያነሳ አለ። ሌላ ትምህርት ቤቶች ላይ በተለይ አፋን ኦሮሞ ተማሪዎች የሚበዙበት ላይ ሌላ ጥያቄ።

በአማርኛ የሚማሩ/ የአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች ቁጥር ባነሰበት በባንዲራ መዝሙር አላማው አንድ ያደረገ ግን በተለያየ ስትራቴጂ መጥቶ የከተማውን ሰላማዊ መማር ማስተማር ማደፍረስ ነው። "

ወላጆች እና ተማሪዎች የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ምን ይላሉ ?

ደስ ታቲሌስ ፦

" ... ትምህርት በ ' #አፍ_መፍቻ_ቋንቋ ' መማር እና የአንድ ክልልን ባንዲራን መስቀልና መዝሙር ማዘመር በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው። 

ለምሳሌ ያህል ፦ አብዛኛዎችን የትምህርት አይነቶች የምንማረው በእንግሊዘኛ ነው። ነገር ግን የእንግሊዝን መዝሙር አልዘመርንም ፣ ባንዲራቸውም በትምህርት ቤቶቻችን ላይ አልተሰቀለም።

ይህንን ያልኩት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወይንም በመንግስት የተገነቡት ትምህርት ቤቶች ላይ ነው።

የግል ትም/ቤትን አይጨምርም። አሁን ግን የኦሮሚያ ክልል መዝሙር እየተዘመረ እና ባንዲራው እየተሰቀለ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በራሱ ወጪ በሰራቸው ትምህርት ቤቶች ላይ ነው።

ሲቀጥል ቋንቋውን ማስተማርም ካስፈለገ የሌላውን ክልል መዝሙር እንዲዘምሩ በማስደረግ መሆን የለበትም።

በከተማው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲማሩ እኮ የአማራ ክልል ባንዲራ አልተሰቀለም ፤ የአማራ ክልልን መዝሙር አልተዘመረም።

አሁን ላይ እየታየ ያለው ነገር እና ለድርጊቱ የከተማ አስተዳደር እየሰጠ ያለው መልስ ፍፁም የተለያየ ነው። "

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/ADDIS-ABABA-12-13

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ሀሰተኛ የትምህርት መረጃ ...

(በዳውሮ ዞን)

በዳውሮ ዞን ፤  ከጪ በተባለው ወረዳ ለመጀመሪያ ዙር በተደረገ ማጣራት ከ264 የትምህርት መረጃ 127 #ሀሰተኛ ሆኖ መገኘቱ ተሰምቷል።

ሀሰተኛ ሆኖ ከተገኘው የትምህርት መረጃ መካከል 6ቱ #የአመራርና ቀሪው #የመንግስት_ሰራተኞች ነው።

የሁለተኛ ዙሪ የማጥራት ስራ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በዚሁ ዞን ፤ ቶጫ በተባለው ወረዳ በመጀመሪያ ዙር ከተደረገው ማጣራት ከ565 የትምህርት መረጃ የ218 ሰዎች #ሀሰተኛ ሆኖ ተገኝቷል።

መረጃቸው ወደ ግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኮ ከተጣራው ከ565 የመንግስት ሰራተኞች መካካል የ210 ባለሙያዎችና የ8 #አመራሮች የትምህርት መረጃ ነው ሀሰተኛ ሆኖ የተገኘው።

ይኸው የማጣራት ስራ ይቀጥላል ተብሏል።

መረጃው ከዳውሮ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
በአዲስ አበባ የትምህርት ቤቶች ጉዳይ የከተማው አስተዳደር፣ ትምህርት ቢሮ ፣ ፖሊስ ፣ ወላጆች ምን ይላሉ ? የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፦ " ሲጀመር አዲስ አበባ አፋን ኦሮሞ የምታስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልነበራትም መምህራኖች ታውቃላችሁ ይሄንን እውነት። ያኔ ቀርቶ እስካሁንም አፋን ኦሮሞ ወይም ቋንቋዎች የምናስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልጨረስንም አላፀደቅንም። ስርዓተ…
አዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በህጋዊ ሽፋን የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንንት በሚያውኩ ልዩ ልዩ ህገወጥ ተግባር ላይ ይሳተፋሉ ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ቡድኖችና ግለሰቦችን አስጠነቀቀ።

ፖሊስ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፤ ዛሬ ታህሳስ 4 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማሩ ተግባር በሰላም ሲካሄድ መዋሉን ገልጿል።

ፖሊስ በመግለጫው ፤ በህጋዊ ሽፋን የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንንት በሚያውኩ ልዩ ልዩ ህገወጥ ተግባር ላይ ይሳተፋሉ ያላቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ቡድኖችና ግለሰቦች " አጥፊ " ሲል ከጠራው ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቋል።

አዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በአዲስ አበባ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን የረብሻ እና የጥፋት ብሎም የውድመት መድረክ ለማድረገው በታቀደ ህገወጥ ተግባር ላይ አንዳንድ የባልደራስ ለእውነተኛዲሞክራሲ አባላት ቀጥታኛ ተሳትፎ ማድረጋቸውን በማስረጃ  እንደተረጋገጠ ገልጿል።

በጥፋት ድርጊቱ ላይ ቀጥተኛ ተሣትፎ የነበራቸው አንዳንድ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ከትምህርት ቤት ውጭ ሆነው  ችግሩን በማቀጣጠል እና ወደ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ሰብረው በመግባት በትምህርት ቤት ሀብት ላይ ከፍተኛ ውድመት እንዲደርስ ያደረጉ የጥፋት አጀንዳ የተቀበሉ ሌሎች ግለሰቦችም እጅ ከፍንጅ ተይዘው ጉዳያቸው እየተጣራ ነው ብሏል።

" የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንንት በማረገገጥ የከተማዋን ፀጥታ የማስጠበቅ ኃላፊነት ተጥሎብኛል ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ የከተማዋን ሰላም ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ገልጾ ይህን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

የተማሪ ቤተሠቦችና ህብረተሰቡ እውነታውን በመረዳት ልጆቹን በመምከር ሃላፊነቱን እንዲወጣ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።
@NATIONALEXAMSRESULT
@studentsnewsadv35bot
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ከተቋሙ ከተመርቃችሁ ሁለት ዓመት ያለፋችሁና ዋናውን የትምህርት ማስረጃ (Original Degree) ያልወሰዳችሁ ምሩቃን በዩኒቨርሲቲው ሬጂስትራርና አሉምናይ ጽ/ቤት በመገኘት ዋናውን የትምህርት ማስረጃችሁን መውሰድ እንደምትችሉ አሳውቋል።


@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
#ASTU

ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች "ሞት ይቁም" የሚል መፈክር ይዘው ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ብዙም ሳይቆይ ሰልፉ በአድማ በታኞች እንዲበተን ተደርጎ እንደነበር እና ትምህርትም በከፊል መቋረጡን መዘገባችን ይታወሳል።

ከቀናት በፊት የተቋረጠው ትምህርት እስከዛሬ አለመጀመሩንና ተማሪዎችም ከግቢ መውጣት እንደተከለከሉ ዛሬ ከግቢው ተማሪዎች ሰምተናል።

ዩንቨርሲቲው ተማሪዎች ወደ ክፍል ገብተው ትምህርታቸውን ይከታተሉ ዘንድ ቢያሳስብም ከዚያም አልፎ ቢያስጠነቅቅም ተማሪዎች ክላስ እየገቡ እንዳልሆነም አረጋግጠናል።

፨ተማሪዎች ለምን አንማርም አሉ?

ለ#ATC መረጃ ካደረሱ ተማሪዎች እንደተረዳነው ከሆነ ሰላማዊ ሰልፉ በመበተኑ ድምፃችን ታፍኗል ስለሆነም አንማርም የሚሉ ተማሪዎች በሌሎች ተማሪዎች ላይ በፈጠሩት ጫና መሰረት ትምህርት ሙሉ በሙሉ ሊቆም ችሏል።

በዛሬው ዕለት ግቢው ውስጥ የሚገኙ ፌደራል ፖሊሶች ተማሪዎችን ከዶርም እያስወጡ ወደ ክፍል እንዲገቡ ለማስገደድ ቢሞክሩም አለመሳካቱን ከተማሪዎቹ ያሰባሰብነው መረጃ ያሳያል።

ዩንቨርሲቲው ከተማሪዎቹ ጋር ውይይት በማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱ ይመለስ ዘንድ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጠይቀዋል።


 [ATC]

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በከፍተኛ 12 ትምህርት ቤት ባለፈው ሳምንት በተፈጠረ ግጭት አንድ ተማሪ መሞቱን አረጋግጫለሁ ሲል #አሰመጉ አስታወቀ

በከፍተኛ 12 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለፈው ሳምንት ህዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም. በተፈጠረ ሁከት የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉን አረጋግጫለሁ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አስታወቀ።

ኢሰመጉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በየካ ክፍለ ከተማ ስር በሚገኘው ከፈተኛ 12 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለፈው ሳምንት ከኦሮሚያ ክልል ባንዲራ እና መዝሙር ጋር ተያይዞ በተፈጠረ ሁከት የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉን በቦታው ተገኝቶ ማረጋገጡን ገልጿል።

ይህን መረጃ ባለፈው ሳምንት የአዲስ አበባ ፖሊስ “ሀሰተኛ መረጃ ነው” ማለቱ ይታወሳል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
UPG Sustainability Leadership Program 2023 in the USA | Fully Funded

Duration and Location: 1 Week, Hurricane Island

Link: https://scholarshipscorner.website/upg-sustainability-leadership-program/

#Benefits:

Participants selected for the 1-week immersive excursion will have the costs of the program covered – training material, accommodation, subsistence, local transportation, international flights (a round trip flight from the participant’s hometown to the US)

No. of Participants: 500 for the free online program and 60 participants will be attending a fully-funded event in the USA.

Deadline: 31 December 2022.

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot