STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.7K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#MOE

ሚንስቴር መስሪያቤቱ የ12 ክፍል ውጤት ከሁለተኛው ዙር ፈተና በኋላ ተጠቃሎ እንደሚገለጽ በይፋዊ ፌስቡክ ገጹ አስነብቧል

በሁለተኛው ዙር በ ኦሮሚያ ክልል በጸጥታ ስጋት ያልተፈተኑ ከ 56000 በላይ እና በአሁኑ ዙር መፈተን ኖሮባቸው ከአቅም በላይ በሆነ ችግር መፈተን ያልቻሉ ከ 1300 በላይ ተፈታኞች እንደሚፈተኑ ተገልጿል

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የሸገር የተማሪዎች ሰርቪስ አውቶቡስ አገልግሎት ላይ ከታኅሳስ ወር ጀምሮ የዋጋ ጭማሪ ይደረጋል መባሉ ወላጆችን አስቆጣ፡፡ የሸገር የብዙኃን ትራንስፖርት የተማሪ ሰርቪስ ተጠቃሚ ወላጆች ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ ከታኅሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ አዲስ የታሪፍ ጭማሪ እንደሚደረግ፣ ከኅዳር 1 እስከ 15 ቀን 2015 ዓ.ም. በተመዘገቡበት ዴፖ ቀርበው ውል እንዲያድሱ የሚገልጽ  የታሪፍ ዝርዝር እንደተላከላቸው ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም እስከ ሰባት ኪሎ ሜትር ለሚደርስ ርቀት በወር 250 ብር የነበረው ታሪፍ 730 ብር እንደሚሆን የሚያሳይ ሲሆን፣ 12 ኪሎ ሜትር ለሚደርስ ጉዞ 350 ብር የነበረው ክፍያ ደግሞ 1,240 ብር ይሆናል የሚል ነው፡፡ከዚህ ቀደም እስከ 15 ኪሎ ሜትር ለሚሸፍን ርቀት ይጠየቅ የነበረው 400 ብር ወደ 1,550፣ እስከ 21 ኪሎ ሜትር 450 ብር የነበረው ታሪፍ 1,870 ብር እንደሚሆን ለወላጆች የተላከው ማስታወሻ ያሳያል፡፡

የሸገር ብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ፍሰሐ ለሪፖርተር በሰጡት ምላሽ ታሪፍ የመወሰን፣ የማውጣት፣ መስመር አውጥቶ አገልግሎት የመስጠት ኃላፊነት የሸገር ትራንስፖርት ሳይሆን ተጠሪ የሆነለት የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ነው ብለዋል፡፡ የታሪፍ ማሻሻያው ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ወላጆች ተጠርተው ውይይት ተደርጎበት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶና ለትራንስፖርት ቢሮ ተልኮ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የአ.አ ትራንስፖርት ቢሮ በበኩሉ ወላጆች ሳይመክሩበት ይፋ የሚደረግ ውሳኔ አይኖርም ብሏል

Via - Reporter

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#JigjigaUniversity #ድህረምረቃ

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ እና የቅዳሜና እሁድ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች (የአንደኛ ዓመት ተማሪዎችን ጨምሮ) ምዝገባ ከጥቅምት 16 እስከ 18/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን ገልጿል።

ከምዝገባው ቀን አስቀድሞ Official Transcript ለጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት ፖ.ሳ.ቁ. 1020 ጅግጅጋ ማስላክ ያስፈልጋል።

የምዝገባ እና የትምህርት ክፍያ በንግድ ባንክ በኩል መፈጸም እና የምዝገባ ስሊፕ ለየትምህርት ክፍሎች መላክ እንደሚገባም ተገልጿል።

የቅዳሜና እሁድ ተማሪዎች ትምህርት ጥቅምት 19 እንዲሁም የመደበኛ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ጥቅምት 21/2015 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በርካታ ትምህርቶች የተገኙበት እንደሆነ ተገለፀ፡፡


የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ በርካታ ትምህርቶች የተገኙበት እንደነበር የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአግባቡ ከተመሩ፣ ከቆረጡና ጥረት ካደረጉ የትኛውንም ተልዕኮ መወጣት እንደሚችሉ ያየንበት ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም መላው ህዝባችንም ሲያማርርባቸው የነበሩ ጉዳዮችን መንግስት ለማረም ሲነሳና ጥረት ሲያደርግ ድጋፍ እንደሚሰጡ በተጨባጭ የተረጋገጠበት መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

አክለውም በቀጣይ እንደ ሀገር ህዝቡ በሚያማርርባቸው የተደራጀ ሌብነት፣መልካም አስተዳደር እጦት፣ለመንግስት አገልግሎት እጅ መንሻ መጠየቅ ላይ እንዲሁም በትምህርት ሴክተሩ ሃሰተኛ ትምህርት ማስረጃ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለማስተካከል ህዝቡን ከጎናችን ካሰለፍን ትርጉም ባለው መልኩ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል ትምህርት ተወስዶበታል ብለዋል፡፡

የፈተና አስፈፃሚዎች ከተወለዱበትና ከሚያስተምሩበት ውጪ መመደባቸው ኢትዮጵያውያን አሁንም የተሳሰርንበትና የተጋመድንበት ጠንካራ ማህበራዊ ትስርስር ያለን መሆኑን የተረዳንበት ነበርም ብለዋል ፕሮፌሰር ብርሃኑ፡፡

አጠቃላይ ሂደቱ የሚኒስቴር መስሪያቤቱን ቅቡልነት መልሶ ለመገንባት እድል የተፈጠረበት መሆኑን ጠቅሰው በትምህርት ሴክተሩ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ መተግባርና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና አፈፃፀም ዙሪያ መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
📢Maddawalabu University

ለመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ 1ኛ አመት እና ነባር መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ፦
የ2015ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚካሄደው  ጥቅምት 30 እና ኀዳር 01/2015 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በተመለከተ በትላንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ ምን አሉ ?

- "የፈተና ዝግጅት እና ህትመት" ከቀድሞው እንዲለይ በኮድ ብዛት እና በገፅ አወቃቀር በመለየት በሁለቱም የትምህርት መስኮች " 12 ኮድ " እንዲኖር እና የመለያ ኮዱ ከሚታወቅበት 2 ኮድ ወደ 3 ተቀይሮ ፈተናው ተሰጥቷል።

- #ስልክ እና ማንኛውም #ኤሌክትሮኒክ_መሳሪዎችን ተፈታኞች ይዘው እንዳይመጡ መልዕክት ቢተላለፍም በ33 የፈተና ጣቢያዎች 59 ተፈታኞች #ስልክ_ይዘው ገብተው ለመጠቀም ሙከራ አድርገው ተይዘዋል።
👉 ጫት፣
👉 አደንዛዥ ዕፅ፣
👉 ሲጋራ፣
👉 ስለታማ ነገሮች፣
👉 ጥይት፣
👉 አልኮል ..... ወዘተ ተፈታኞች ይዘው በመምጣት በተለያየ መልክ ለማስገባትና በአንዳንድ ቦታዎችም ለመጠቀም ሙከራ አድርገዋል።

- በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፤ " ከዋናው ግቢ ወደ ቴክኖሎጂ ግቢ " የሚወስደው ድልድይ በመደርመሱ ምክንያት 451 ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል ፤ 1 ተማሪ ህይወቱ ሲያልፍ 232 ተማሪዎች ቀላል የአካል ጉዳት ፣ 201 ተማሪዎች መካከለኛ ጉዳት ፣ 13 ተማሪዎች ከፍተኛ ጉዳት ፣ 5 ተማሪዎች በጣም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ሁከት የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ ፤ 5 የፀጥታ ኃይሎች እና 2 ፈተና አስፈፃሚዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- " በሶስት ዩኒቨርሲቲዎች " ቀደም ሲል በነበር የጤና እክል ምክንያት 3 ተማሪዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ በጉዞ ወቅት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ የተወሰኑ ተማሪዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው የድልድይ መደርመስ አደጋ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ፈተና መውሰድ ያልቻሉና በከፊል የተፈተኑ በአንድ ወር ጊዜ የሚዘጋጀውን ፈተና እንዲወስዱ ይደረጋል። ተፈታኞቹ የጤና ሁኔታቸው ለፈተናው የማያበቃቸው ካሉ ከ2015 ዓ/ም ተፈታኞች ጋር በመደበኛነት እንዳፈተኑ ይደረጋል።

- " ፈተና አንፈተንም " ብለው ጥለው የወጡ ዳግም በመደበኛ ተማሪነት የመፈተን እንድል አይሰጣቸውም፤ በግል በ2015 ዓ.ም የመፈተን መብታቸው የተጠበቀ ነው።

በ " ማህበራዊ ሳይንስ " ፈተና ወቅት ፈተና ሳይፈተኑ የወጡ ተማሪዎች ፦

👉 ከመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነ ሰላም ካምፓስ (1,700 ተማሪዎች)
👉 ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (1,226 ተማሪዎች)
👉 ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (2,711 ተማሪዎች)
👉 ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ (7,356 ተማሪዎች) በድምሩ 12,993 ተማሪዎች ሲሆኑ ፈተና ሳይጀምሩና የአንድ ቀን ሁለት ፈተና ከወሰዱ እንዲሁም የሁለት ቀን 4 ፈተናዎች ከወሰዱ በኃላ " አንፈተንም " ብለው ጥለው የወጡ ናቸው።

እነዚህ ተማሪዎች ከዚህ በኃላ በ " መደበኛ ተማሪነት " መፈተን #የማይችሉ ሲሆን በ2015 በግል መፈተን ይችላሉ።

- በታወቁ የጤናና ሌሎችም እክሎች ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተናን ያልወሰዱ ተማሪዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፈተናሉ።

- " የፈተናው ዉጤት " በተለያዩ ምክንያቶች ያልተፈተኑ ተማሪዎች በወጣላቸዉ ፕሮግራም መሰረት ከተፈተኑ በኋላ የሁለቱንም ዉጤት ተጠቃሎ ይፋ ይደረጋል።
[TIKVAH]
ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#HaramayaUniversity

ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የ2015 የትምህርት ዘመን መደበኛ የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን ይፋ አድርጓል።

➤ የሁሉም ነባር ሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች እንዲሁም የድኀረ ምረቃ ተማሪዎች
የ2015 ዓ.ም የአንደኛ ሴሚስተር ምዝገባ፦

➭ ኦንላይን ምዝገባ ~ ኅዳር 03 እና 04/2015 ዓ.ም
➭ በአካል ምዝገባ ~ ኅዳር 05/2015 ዓ.ም
➭ ትምህርት የሚጀምረው ~ ኅዳር 06/2015 ዓ.ም

➤ የነባር አንደኛ ዓመት ተማሪዎች የ2014 ዓ.ም የሁለተኛ ሴሚስተር ምዝገባ፦

➭ ኦንላይን ምዝገባ ~ ኅዳር 11 እና 12/2015 ዓ.ም
➭ በአካል ምዝገባ ~ ኅዳር 13/2015 ዓ.ም
➭ ትምህርት የሚጀምረው ~ ኅዳር 14/2015 ዓ.ም

➤ አዲስ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የ2015 ዓ.ም የአንደኛ ሴሚስተር ምዝገባ ኅዳር 12 እና 13/2015 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን ትምህርት ኅዳር 14/2015 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ArbaminchUniversity

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሁሉም መደበኛ እና መደበኛ ባልሆኑ የቅድመ-ምረቃና የድኅረ-ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች የተማሪዎች ቅበላ፣ ምዝገባ እና ትምህርት የሚጀመርበትን ቀን የተወሰነ ሲሆን በሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች የ2015 ትምህርት ዘመን አዲስ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ፕሮግራም አመልካቾችን ጨምሮ ፦

1ኛ. የቅበላ ቀን፦ ረቡዕ ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም

2ኛ. የምዝገባ ቀን፦ ኅዳር 1 - 2/2015 ዓ.ም ብቻ

3ኛ. ትምህርት የሚጀምረው - ሰኞ ኅዳር 5/2015 ዓ.ም

መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ማሳሰቢያ፦

1ኛ. ምዝገባ የሚፈፀመው በአካል በመገኘት ብቻ ይሆናል ተብሏል።

2ኛ. ከተጠቀሱ ቀናት ቀድመውም ሆነ ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው የማይቀበል መሆኑን አሳውቋል።

ምንጭ፦ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#AASTU

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ፦

➤ የመጀሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች
     ➭ ጥቅምት 24 እና 25/2015 ዓ.ም

➤ 4ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የማታ ተማሪዎች
     ➭ ጥቅምት 26 እና 27/2015 ዓ.ም

➤ ነባር የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች
     ➭ ጥቅምት 28 እና 29/2015 ዓ.ም

➤ አዲስ የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች
     ➭ ጥቅምት 30 እና ህዳር 01/2015 ዓ.ም

➤ ሁሉም የድኅረ ምረቃ የማታ ተማሪዎች
     ➭ ህዳር 3 እና 4/2015 ዓ.ም

አዲስ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ለምዝገባ መያዝ የሚያስፈልጋቸው፦

• ፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶግራፍ (3)

• በመንግስትና በግል ድርጅት ስፖሰርነት የምትማሩ ተማሪዎች የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ

• የግል ተማሪዎች የከፈላችሁበት ደረሰኝ

• የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው

• የሦሥተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው

የአንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ትምህርት ጥቅምት 24/ 2015 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ArsiUniversity

የአርሲ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች የ2015 ዓ.ም ትምህርት ምዝገባ ህዳር 1-2/2015 ዓ.ም ስሆን የምዝገባ ቦታ ቀደም ሲል በነበራችሁበት ካምፓስ መሆኑን ከወዲሁ እየገለፅን በቅጣት ምዝገባ ቀን ህዳር 3/2015 ዓ.ም ብቻ መሆኑን እያሳወቅን ስትመጡ አንሶላ ! ብርድልብስ | የትራስ ጨርቅ እና የእስፖርት ትጥቅ መያዝ አለባችሁ፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WollaggaUniversity

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች የ2015 የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው ህዳር 14-15 መሆኑን እናሳውቃለን።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ከ8ኛ ክፍል ተፈታኞች ገንዘብ በመሰብሰብ የፈተና መልስ ሰጥተዋል የተባሉ ርዕሰ መምህሩን ጨምሮ 5 መምህራን ተከሰሱ፡፡

ክስ የተመሰረተው አንደኛ ርዕሰ መምህር አብዱ ሸኩር ጀማል፣ ሁለተኛ ተከሳሽ የድሬዳዋ ፖሊስ ዋና ሳጅን አብዲ ዩያ ፣ ሶስተኛ መምህር መሃመድ ጠሃ አብዱላሂ እና አራተኛ መምህር ማሙሽ አካሉ ተክሌ፣ እንዲሁም አምስተኛ መምህር ሲሳይ ደስታ ሚጆና ላይ ነው ተብሏል፡፡

ለተማሪዎቹ የባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ የህብረተሰብ ሳይንስ እና የስነ-ዜጋ የትምህርት አይነቶችን ፈተና መልስ በማለት 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች እየዞሩ ተማሪዎቹ እንዲሞሉ ያደረጉ ሲሆን ዉጤት ይፋ ሲደረግ ሁሉም ተማሪዎች ከማለፊያ ነጥብ በታች ማምጣታቸው ተረጋግጧል፡፡

በመሆኑ ተከሳሾች በፈፀሙት ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡ክሱ ለተከሳሾች የደረሳቸው ሲሆን የድሬዳዋ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ተከሳሾች ከጠበቃ ጋር ተማክረዉ ለመቅረብ በጠየቁት መሰረት ለጥቅምት 22/2015 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ትምህርት ዘመን የመደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ፦

➤የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች የ2ኛ ሴሚስተር ምዝገባ
    ➭ ጥቅምት 28 እና 29/2015 ዓ.ም

➤የ3ኛ፣ 4ኛ እና 5ኛ ዓመት ተማሪዎች ምዝገባ
    ➭ ኅዳር 05 እና 06/2015 ዓ.ም

➤ የጤና እና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች (ከ2ኛ ዓመት ጀምሮ) ሪፖርት ማድረጊያ
    ➭ ጥቅምት 17/2015 ዓ.ም

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#SemeraUniversity

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ መርሃ ግብር ለቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው

የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ጥቅምት 21-22/2015 ፤

ሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ህዳር 01-02/2015 መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የ2015 የዩኒቨርስቲወች ጥሪ ‼️

እስካሁን የምዝገባ ቀን ያሳወቁ ዩኒቨርስቲዎች ስም ዝርዝር ከታች ተገልጿል።

1ኛ- #HaramayaUniversity

➤ 2ኛ ዓመት እና ከዛ በላይ ➭ ህዳር 02

➤  1ኛ አመት - ኦንላይን ምዝገባ ኅዳር 11-12

2ኛ - #WolkiteUniversity ---Calendar ነው።
በ ከለንደሩ መሰረት ጥቅምት 28 እና 29 ብሏል።  (ማስታወቂያ እንጠብቃለን )

3ኛ- #WolloUniversity --ጥቅምት 24-25 ጠርቷል።

4ኛ- #HawassaUniversity --ጥቅምት 28-29 ጠርቷል።

5ኛ- #KotebeUniversity -- ጥቅምት 28 እና 29 ነው።

6ኛ- #Gambella University - በቀጣይ እናሳውቃለን። (የነበረው ተራዝሟል)

7ኛ- #ArbaMinchUniversity - መደበኛ ተማሪዎች

📭 ነጭ ሳር ካምፖስ --- ጥቅምት 19-20 ተብሏል።

8ኛ- #BahirdarUniversity --ጥቅምት 21 እና 22 ተብሏል።

📭BIT 4ኛ አመት Internship ላይ የነበሩ ተማሪዎች ጥቅምት 21- 22 ይገባሉ።

9ኛ- #AmboUniversity --ጥቅምት 28 እና 29 ተብሏል።

10ኛ- #AStuUniversity ----ጥቅምት 26 እና 27

11ኛ - #DebraTaborUniversity --ህዳር 1-2

12ኛ- #WolaitasoddoUniversity --ህዳር 8 እና 9

13ኛ- #OdaBultumUniversity -- ህዳር 5 እና 6

14ኛ - #SelaleUniversity --  ህዳር 1 እና 2 ( ከ 1ኛ-4ኛ አመት)

15ኛ- #JimmaUniversity --ጥቅምት 28 እና 29

16ኛ - #SamaraUniversity
     
         ➤ 1ኛ አመት  ጥቅምት 21 እና 22
        ➤የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ኅዳር 01 እና 02

17ኛ- #InjibaraUniversity -- ኅዳር 01 እና 02

18ኛ- #WachamoUniversity

       ➤ ተመራቂ ያልሆኑ ተማሪዎች ህዳር 12-13
       ➤ተመራቂ ተማሪዎች ኅዳር 2 እና 3

19ኛ - #MekdelaUniversity -ጥቅምት 25-26

20ኛ- #MaddaWolabuUniversity --ጥቅምት 30 እና ህዳር 01

21ኛ- #ArbaMinchUniversity ---ጥቅምት 30 - ኅዳር 2

22ኛ - #AASTU_University -- ጥቅምት 24 -25
        ( 4ኛ አመት--ጥቅምት 26-27)

23ኛ- #ArsiUniversity --ኅዳር 1-2

24ኛ -#WollaggaUniversity --ኅዳር 14--15

25ኛ -#DillaUniversity --
  1ኛ አመት ---ጥቅምት 28 -29
3ኛ እና ከዛ በላይ ---ኅዳር 5 እና 6

ሌሎች ዩኒቨርስቲዎችም ቀጣይ ቀናቶች ያሳውቃሉ።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ህጻን ሳሙኤል ዩሀንስ ከ 11 ቀናት በኋላ ተገኘ!!!

በቤት ሰራተኛ ተሰርቆ የጠፋው የሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወር ህጻን ከአዲስ አበባ ክልል ውጪ ፖሊስ ባደረገው ብርቱ ክትትል መገኘቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቋል።

ጥቅምት 6 ቀን 2015 ዓም በለሚ ኩራ ክ ከተማ ልዩ ቦታው አያት ከሚባል አካባቢ ከቀኑ 10:30 ሰዓት በቤት ሰራተኛዋ ተሠርቆ የጠፋው ህጻን ሳሙኤል ዮሀንስ ከ11 ቀናት ብርቱ ክትትል በኋላ የተገኘ ሲሆን ከተጠርጣሪዋ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ጨምሮ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ መግለጹን ብስራት ራዲዮ ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ፖሊስ ህጻን ሳሙኤል ዮሀንስ መጥፋት ሪፖርት ከደረሰው ጀምሮ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ባደረገው የሌት ተቀን አድካሚ ክትትል በደብረ ማርቆስ በአዲስ አለም ገጠራማና አስቸጋሪ ቦታዎች ፍለጋውን በማጠናከር እንዲሁም ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በአዲስ አበባ በተደረጉ አድካሚ ፖሊሳዊ ስራዎች ከፍተኛ ገንዘብ ካላመጣችሁ ህፃኑን አታገኙም እያለ ሲደራደር የነበረውም ግለሰብ ጭምር ሊያዝ ችሏል።

ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በተገናኘ ቀሪ የምርመራ ውጤቶች በቀጣይ ይፋ የሚደረጉ ሲሆን ህብረተሰቡም የቤት ሰራተኞች ሲቀጥር ማንነትና ህጋዊነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

ዳጉ_ጆርናል

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የኢዜማው አቶ የሸዋሰው አሰፋ ፈተናቸውን ጥለው በወጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ጉዳይ ላይ ይሄን ብለዋል!

“የተማሪዎችን ጉዳይ..መንግሥት የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩንቨርሲቲዎች እንዲሰጥ እና ተማሪዎች ከኩረጃ ተላቀው በጥረታቸው እንዲያልፉ ያደረገው ጥረት መልካም ርምጃ ነው። የመጀመሪያ ጥረት እንደመሆኑ ሰውሰራሽ እና ተፈጥሯዊ እንከኖች ቢያጋጥሙት አይገርምም። በቀጣይ ዓመታት እየተሻሻለ እንደሚሄድ ተስፋ እናደርጋለን።

በዘንድሮው ፈተና አንፈተንም ብለው የወጡ ተማሪዎችን በተመለከተ ድርጊታቸው ጥፋት መሆኑን ሁሉም የተስማማበት ነው። ሆኖም ልጆች እንደመሆናቸው ከተግሳፅ የዘለለ እልህ መጋባት የመንግስትና የመንግስታዊ ተቋም ባህሪ ሊሆን አይገባውም። በድርጊታቸው ተፀፅተው ያለቀሱ፣ የታመሙ እና ህይወታቸውም አደጋ ላይ የወደቀ ተማሪዎች መኖራቸውን ስንሰማ ከዚህ በላይ መቅጣት ትንሽ የበዛ ይመስለኛል።

ስለሆነም ይቅርታ ጠይቀው፣ ካስፈለገም ለራሳቸውም ሆነ ለሌላው መማሪያ በሚሆን መልኩ ፈርመውም ቢሆን በመደበኛ እንዲፈተኑ ማድርግ ይገባል፣ እንጂ ከዚህ በላይ ህይወታቸው እንዲመሰቃቀል ማድረግ ተገቢ አይደለምና ቆም ብላችሁ እንድታስቡበት እና መፍትሄ እንድትሰጡት አደራ እላለሁ።”

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WerabeUniversity

ለማታ እና ሳምንት መጨረሻ የ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች የወጣ ማስታወቂያ ነው።

ወራቤ ዩኒቨርስቲ ለመደበኛ ተማሪዎች እስካሁን ማስታወቂያ አላወጣም። አዲስነገር ካለ ይጠብቁን👏👏

N.B:- የቀሩት ዩኒቨርስቲዎች ዛሬ እና ቀጣይ ቀናት ይጠራሉ። በፍጥነት እናደርሳችሁዋለን።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
Study in UK

British Scholarships 2023 for International Students(Fully Funded)
Details: https://tinyurl.com/bdmn6468

5000 Scholarships are offered for international students in different institution of UK to pursue Bachelors, Masters, PhD programs

The expenses will be covered by UK(British) Government.

#British
#Scholarships
#allclassnote

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ውጤት ከአንድ ወር ተኩል በኋላ ይለቀቃል ሲሉ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልፀዋል።

ይህ ማለት ከሁለተኛው ዙር ፈተና መጠናቀቅ  በኋላ ከሁለት ሳምንት  በኋላ  ህዳር መጨረሻ  ወይም  ታህሳስ  መጀመሪያ  ዉጤት ይገለጻል ማለት ነዉ



ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot