STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በካሜራ በመታገዝ ክትትልና ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል።
-------------
የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንትና ከፍተኛ አመራሮች በአካል ተገኝተዉና ተንቀሳቅሰዉ የፈተናዉን ሂደት ከመከታተል በተጨማሪ ቴክኖሎጂን መሰረት በማድረግ፣ የደህንነት ካሜራ በመታገዝና ከካሜራ መቆጣጠሪያ ክፍል በመገኘት ፈተናዉን በተመለከተ፣ መፈተኛ ክፍሎችን፣ የግቢውን መውጫና መግቢያ፣ አጠቃላይ እንቅስቃሴዉን እንዲሁም አጠቃላይ የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን በተመለከተ በካሜራ በመታገዝ ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
2015 E.C (2022-23 G.C) Academic Calendar (1).pdf
259 KB
✳️ Arbaminch University Calendar.


ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
WOLKITE UNIVERSITY 2015 EC ACADEMIC CALENDAR.pdf
189.2 KB
Wolkite University academic calendar

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
2015 E.C Academic Calander Revised.pdf
251.2 KB
Check out the revised calander of ASTU

አዲሱ የ 2015 የ ትምርህት ክለንደር


ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት የሀገርን ጥሪ የተቀበሉት የ60 ዓመት አዛውንት የ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየወሰዱ እንደሚገኝ ተነገ

በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት የሀገርን ጥሪ ተቀብለው መከላከያ ሰራዊትን በመቀላቀል ለሰባት አመት ያገለገሉት የ60 ዓመቱ አዛውንት የ12 ክፍል ፈተና  እየወሰዱ እንደሚገኝ የአምሓራ ሳይንት ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ገለፀ።

የ60 ዓመቱ ተማሪ አ/ቶ በላይ እሸቴ በደቡብ ወሎ ዞን አምሓራ ሳይንት ወረዳ አጅባር በሚባል ቀበሌ እንደተወለዱ ተገልጿል። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በማቋረጥ ወደ ትዳር ገብተው በነበረበት ወቅት ለኢትዮ -ኤርትራ ጦርነት በቀረበላቸው ጥሪ መሰረት የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በመቀላቀል ለሰባት አመት ያክል እንዳገለገሉ ተነግሯል። የአቋረጡትን ትምህርት በመደበኛ የትምህርት ጊዜ በመቀጠል በአሁኑ ሰዓት በወሎ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቂያ ፈተና እየወሰዱ እንደሚገኝ የአምሓራ ሳይንት ወረዳ ትምሀርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አ/ቶ ክንዱ ጥላሁን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ተማሪ አቶ በላይ በአሁኑ ጊዜ የ6 ልጆች አባት እና ስምንት የቤተሰብ አባላትን እንደሚያስተዳድሩ ተገልጿል። በቀጣይ ዩንቨርሲቲ በመግባት ትምህርታቸውን ተከታትለው በማጠናቀቅ የተሻለ ኑሮ ለመኖር ህልም እንዳላቸው መናገራቸውን አ/ቶ ክንዱ ተናግረዋል። ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች እየተሰጠ ይገኛል ።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ግኝትን መነሻ በማድረግ የክትትል እና ቁጥጥር ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

የኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ ከዋና ኦዲተር የተሰጠውን አስተያየት መሰረት በማድረግ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ፤በትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች እና በዴሞክራሲ ተቋማት የክትትል እና ቁጥጥር ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት ያላቸውን ክህሎት እና የካበተ የአማራር ልምዳቸውን በሙሉ አቅማቸው በመጠቀም የሕዝብን እና የመንግስትን ሃብት ከብክነት ለማዳን በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው የተከበሩ አቶ ክርስቲያን አስገንዝበዋል፡፡

ከዋና ኦዲተርና ከተቋማት የሚመጡ ሪፖርቶችን በጥልቀት ማንበብና መረዳት ጥያቄዎችን ለማውጣትና ግብረ መልሶችን ለማዘጋጀት ስለሚረዳ የቋሚ ኮሚቴው አባላት ይህንኑ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ማስገንዘባቸዉን ብስራት ራዲዮ ከም/ቤቱ ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው ፤ በባለፈው ዓመት የታዩ ክፍተቶችን በማረም የተሻለ ሥራ ለመስራት በተቋማት ኃላፊዎች የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን ለማረም የሚመለከተው አካል አስተማሪ የሆነ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

በክዋኔ ኦዲት እና በፋይናንስ ሕጋዊነት ይፋዊ የሕዝብ ውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ከባለድረሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ መስራት የበጀት ዓመቱ አንዱ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚሆንም የቋሚ ኮሚቴው አባላት ጠቅሰዋል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
4_5891108753876455692.pdf
1.1 MB
#Calander 2022/2015 Jijiga U
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 2015

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#HaramayaUniversity

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር የምዝገባ ጊዜን አሳውቋል።

➤ የመግቢያ ጊዜ ➭ ህዳር 02/2015 ዓ.ም

➤ የኦንላይን ምዝገባ ጊዜ ➭ ህዳር 03 እና 04/2015 ዓ.ም

➤ በአካል መመዝገቢያ ጊዜ ➭ ህዳር 05/2015 ዓ.ም

➤ ትምህርት የሚጀምረው ➭ ህዳር 06/2015 ዓ.ም

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
Wollo university

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ እና ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም የቅድመ-ምረቃ እንዲሁም የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የ2015 ዓ.ም አመታዊ የትምህርት የጊዜ ሰሌዳ (Academic Calendar) ከዚህ በታች የተገለፀ ሲሆን በፕሮግራሙ መሰረት ተገቢውን ዝግጅት ከወዲሁ እንድታደርጉ እያሳወቅን የመደበኛ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀመረው ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም ሲሆን የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት 28 እና 29/2015 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በየኮሌጃችሁ ሬጅስትራር በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ በጥብቅ እናሳስባለን።


የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት
━━━━━━━━━━━━━━━━━
ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የ2014ዓም 12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች የሁለተኛ ቀን ፈተና በሰላም ተጠናቋል ።

ጥቅምት 09/2015 ዓም.፣ (ትምህርት ሚኒስቴር ) የ2014ዓም 12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች የሁለተኛ ቀን ፈተና በሰላም የተጠናቀቀ ሲሆን በነገው እለትም የሚቀጥል ይሆናል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
"አማራ ክልል ላይ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተናቸውን አቋርጠው እንዲወጡ የሚያደርጉ አካላት የአማራ ጠላቶች ናቸው" ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ርዕሰ መስተዳደሩ ይሄን ያሉት የ2014 ዓ.ም የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያና የእውቅና አሰጣጥ መርሃግብር ላይ ነው።

መንግስት የትምህርት ሥርዓቱን ጥራት ለማሻሻል እና በፈተና ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት አዲስ የአፈታተን ስርዓት መንደፉ የሚደገፍ መኾኑን ነው የተናገሩት።

ኾኖም ግን በመጀመሪያው ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች በተለየ ሁኔታ አማራ ክልል ላይ 12ሺህ በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተናቸውን አቋርጠው መውጣታቸው የሚያሳዝን ነው ብለዋል።

ተማሪወች ልዩ ተልዕኮ ባላቸው የአማራ ጠላቶች መጠቀሚያ ሁነዋል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ።
የክልሉ ወጣት ራሱን በራሱ እንዲያጠፋ ፣የተሳሰሰተ አቅጣጫ እንዲይዝ፣የወጣቶችን ስነልቦና የሚሰልቡ በተለያየ መገናኛ አውታሮች የሚሰብኩ አካላት አሉ ነው ያሉት።

ለራሱም፣ ለወላጅም፣ ለሀገር የሚያኮራ ዜጋ ለመፍጠር የሚደረገውን ተግባር የሚያከሽፉ የአማራ ጠላቶች ናቸው ብለዋል።

ራሱን እያጠፋ፣ ራሱን እያከሰረ መልማትና ማደግ የለምና ይሄን ማህበራዊ ቀውስ የፈጠረው ማነው የሚለውን ወጣቱ መመርመር እንደሚገባውም አሳስበዋል።

ወጣቶች ለመኖር እንዳይጓጉ፣ ለሕዝባቸው ፣ ለሀገራቸው እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን እንዳይጠቀሙ የሚያደርጉ አካላት የአማራ ጠላት መኾናቸውን መረዳት ይገባል ብለዋል።

ችግር አለ ከተባለ ኀላፊነትን እየተወጡ መጠየቅ እንጂ ራስን አስቀድሞ ለኪሳራ ዳርጎ ሌላውን ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ።

መምህራን ወላጆች፣ ወጣቶችና ማንኛውም ሰው እሄን ነገር መመርመር ፣እኩይ ዓላማ አንግበው ለጥፋት የሚዳርጉ አካላትን ለህግ ማቅረብ ይገባልም ብለዋል።

በየትኛውም መመዘኛ በአማራ ክልል ተማሪዎች ተፈትነው ማለፍ ባህል ኾኖ እያለ በጠላት ማደናገሪያዎችን ተማሪዎች ፈተናቸውን አቋርጠው መውጣት እንዳሳዘናቸው ነው የተናገሩት። በዚህ ጉዳይ መንግስት ተገቢውን ምርመራ እንደሚያደርግና እርምጃ እንደሚወስድም ገልጸዋል።

አሚኮ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ማተብ ታፈረ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ እየተፈተኑ የሚገኙ የሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና አሰጣጥ ሁኔታን ጎበኙ።
***
በጉብኝታቸውም የፈተና አሰጣጥ ሁኔታው በተረጋጋ መንፈስ ሕግና ሥርዓቱን ጠብቆ እየተሰጠ እንደሚገኝ መገምገማቸውን ገልጸዋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot