STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.7K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ጥበቡ ሰለሞን ይባላል የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመውሰድ ዛሬ ወደ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከገቡ ተማሪዎች አንዱ ነው። ከቤቱ የቡና ዛፍ ተክል ይዞ በመምጣት አሻራውን አኑሯል።

ጂንካ ዩንቨርሲቲ ተማሪውን አመስግኖታል👍

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በመጀመሪያው ዙር ፈተና የወሰዱ ሶሻል ተማሪዎች አጋጠሙን ብለው የነገሩኝ ችግሮች 👇

*የምግብ ችግር
*የካፌ ሰልፍ ርዝመት
*የተማሪዎች ጩኸት (ለንባባ አይመችም)
*ኩረጃን እንዳላየ የሚያልፉ ፈታኞች
*በግሩፕ የተደራጁ ተማሪዎች ማስፈራሪያ
*ብጥብጥ ረብሻ (በትምህርት ቤት መጣላት)
*ስንት ሰዓት እንደሆነ ለማወቅ መቸገር
*የውሃ ችግር
*ሽንት ቤት እና ሻወር

#Atc

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በጋምቤላ ክልል ከልጃቸው ጋር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ያሉት እናት
*****

በጋምቤላ ክልል በ45 ዓመታቸው ከልጃቸው ጋር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ያሉት እናት ጋምቤላ ዮኒቨርሲቲ ገብተዋል።

የ5 ልጆች እናት መሆናቸውን የገለፁት ወይዘሮ ኛቹወል ሪክ በነበራቸው ከፍተኛ የትምህርት ፍላጎት የቤት ውስጥ የስራ ጫናን ተቋቁመው በላሬ ወረዳ ከሴት ልጃቸው ከተማሪ ኘክዋት ጋር እየተማሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመውሰድ በቂ ዝግጅት አድርገው ወደ ጋምቤላ ዮኒቨርሲቲ መግባታቸውን ለኢቲቪ ገልጸዋል።

ልጃቸው ተማሪ ኘክዋች በበኩሏ ከወላጅ እናቷ ጋር ትምህርቷን ጨርሳ ለብሄራዊ ፈተና በመብቃቷ መደሰቷን ተናግራለች።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አፈፃፀም ተገመገመ

ጥቅምት 5/2015 (ዋልታ) የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አፈፃፀም የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በተገኙበት በፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ተገምግሟል።

ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከክልል ፖሊስና ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት ጋር በመቀናጀት የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት መወጣቱን ገልጸዋል፡፡

የግምገማ መድረኩ በመጀመሪያው ዙር የፈተና አፈፃፀም ሂደት የነበሩ ውስንነቶችን ለማረምና ጠንካራ ጎኖች እንዲጠናከሩ ለማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታና ደህንነት አካላት ጋር በመሆን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ተቀናጅቶ ፈተናን በማጀብ፣ ጥብቅ ፍተሻ በማድረግ እና የፈተና ጣቢያ አካባቢ ጥበቃዎችን በማጠናከር በስኬት ማጠናቀቅ ተችሏል ብለዋል፡፡

የሁለተኛው ዙር ፈተና በመጀመሪያው ዙር ያጋጠሙንን ችግሮች በመፍታት ተፈታኞች ያለ ምንም የፀጥታ ችግር ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ እንዲያጠናቅቁ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታና ደህንነት አካላት ጋር በመሆን በቂ ዝግጅት ማድረጉንም ገልፀዋል፡፡

በመጀመሪያ ዙር የተከሰቱ ችግሮችን እንደ ትምህርት ወስደን የሁለተኛ ዙር ፈተና ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሁሉም ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር በመቀናጀት በቂ ዝግጅት አድርጎ ወደ ተግባር ገብቷል ማለታቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ዩኒቨርሲቲው 2ኛ ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ

ጥቅምት 5/2015 (ዋልታ) የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ 2ኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞችን መቀበል ጀምሯል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ከማል አብዱራሂም (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ከሁለት ቀናት በኋላ ከጥቅምት 8 ጀምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት የሚሰጠውን 2ኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ መሆኑን ተናግረዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቢንያም መንገሻ በበኩላቸው በክልሉ በመጀመሪያው ዙር የተሠጠው የማኅበራዊ ሳይንስ ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

የ2ኛውን ዙር ፈተና ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ለማሳካት አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
12ኛ ክፍል አጠናቀው በየትኛውም የትምህርት ዘርፍ ያልተመረቁ ወጣቶችን ሥራ እንዲያገኙ እየሠራሁ ነው- የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣
ጥቅምት 5፣ 2015
(ኤፍ ቢ ሲ)

በተለያየ ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡና 12ኛ ክፍል አጠናቀው በየትኛውም የትምህርት መስክ ያልተመረቁ ወጣቶች ሥራ እንዲያገኙ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ “ብቃት” በተሰኘ ፕሮጀክት እስካሁን ምንም አይነት ሥራ ያልጀመሩ ሥራ እንዲያገኙ እየሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡
ዛሬ በባሕርዳር፣ ጎንደር፣ ኮምቦልቻ፣ ሐዋሳ ፣ ጅማ፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ፣ ወላይታ ሶዶ እና ድሬዳዋ ከተሞች ለሚተገበረው የ“ብቃት” ፕሮጀክት የማስጀመሪያ መርሐግብር ተካሂዷል፡፡
የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሱ ጥለሁን በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በፕሮጀክቱ በ11 ከተሞች ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 24 ዓመት የሆኑ ከ70 ሺህ በላይ ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይሠራል ብለዋል።
“ብቃት” የተሰኘው ፕሮጀክት የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ለመተግበር የተቀረጸ ነው፡፡
ለፕሮጀክቱ ትግበራ 65 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በጀት መመደቡ ተጠቁሟል፡፡
ሥራ አጥነት በከተሞች 70 በመቶ መድረሱ እና 30 ነጥብ 4 በመቶ የሚሸፍኑት ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 24 የሚሆኑ ወጣቶች ናቸው፡፡
ይህ ፕሮጀክት በዚህ ዕድሜ ክልል ያሉ ወጣቶች በዘላቂነት ሥራ እንዲያገኙ የሚተገበር ሲሆን÷ 60 በመቶ ያህል ሥራ አጥ ሴቶችን የማቀፍ ትኩረት እንዳለው አቶ ንጉሡ ተናግረዋል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራው ባሻገር በማኅበረሰብ ተኮር ሥራዎች የበለጠ መሥራት አለበት- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2015 ኤፍ ቢ ሲ

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ሥራው ባሻገር በማኅበረሰብ ተኮር ሥራዎች የበለጠ መሥራት አለበት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም÷ ዩኒቨርሲቲው ከአካዳሚክ ሥራው ጎን ለጎን ግቢዎቹን በአትክልትና ፍራፍሬ ለማስዋብ ያደረገውን ጥረት ተመልክተዋል።

ዩኒቨርሲቲው የጀመረው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸው÷ በሚያከናውነው የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሥራ ከራሱ አልፎ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራው ባሻገር በማኅበረሰብ ተኮር ሥራዎች የበለጠ መሥራት እንዳለበት መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት “በሰመር ካምፕ” ያሰለጠናቸውን ታዳጊዎች አስመረቀ
**

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት “በሰመር ካምፕ” የሥልጠና መርሓ ግብር ያሰለጠናቸውን ታዳጊዎች በሳይንስ ሙዚየም አስመርቋል፡፡

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት በመገኘት ለተመራቂዎቹ የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል፡፡

ሚኒስትሯ በመርሓ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ተመራቂዎቹ ዓለም እየተወዳደረበት በሚገኘው ረቂቅ ቴክኖሎጂ ሥልጠና በመውሰዳቸው ሊኮሩ እንደሚገባ በመግለፅ ሀገር ወደፊት ብዙ እንደምትጠብቅባቸው አመላክተዋል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#Update

ዛሬ እና ነገ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማእከላት / ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ።

ይህ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ጥብቅ በሆነ ህግ መሰጠት ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ ፈተናቸውን ጨርሰው የወጡት " የማህበራዊ ሳይንስ " ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የተመለከቱትን እና በቀጣዩ " የተፈጥሮ ሳይንስ " ፈተና ወቅት ሊስተካከለ ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አቅርበዋል።

ፈታኝ መምህራንም ሀሳባቸውን አጋርተዋል።

#ከማህበራዊ_ሳይንስ_ተፈታኞች

- በባለፈው ፈተና ወቅት በአንዳንድ ተቋማት ውስጥ በምግብ አቅርቦት ጉዳይ ክፈትቶች የነበሩ ሲሆን ተማሪዎች በጊዜ ምግብ እንዲያገኙ እንዲሁም በግቢ ውስጥ ያሉት የአገልግሎት ሰጪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ሊያቀርቡ ይገባል። " የውሃ " አቅርቦትም ችግሮች የነበሩባቸው ተቋማት ነበሩ የሚገቡት ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያቸው እንደመሆኑን ለአምስት ቀን እንኳን ተማሪ ለማስተናገድ የሚሆን ውሃ ማቅረብ ይገባል። 

- አንዳንድ ተቋማት ውስጥ ስርዓት የጎደላቸው ተፈታኝ ተማሪዎች በሌሎች ተማሪዎች ላይ ጫና ለማሳደር ሲሞክሩ ታይቷል ፤ በየዶርሙ እየዞሩ ምግብ አምጡ፣ ብር አምጡ ሲሉ የነበሩም ተማሪዎች የነበሩ ሲሆን በቀጣዩ የፈተና ወቅት እንዲህ አይነት ባህሪ ያላቸው ተፈታኞች ካጋጠሙ የሚመለከተው አካል ለሌሎች አስተማሪ የሆነ እርምጃ መውሰድ ያስፈልገዋል።

- በባለፈው ፈተና ወቅት በአንዳንድ ተቋማት ውስጥ ሌሎች ተማሪዎችን የሚረብሹ፣ የሚጮሁ ፣ በየዶርሙ እየሄዱ ተማሪ በተኛበት ሲያንኳኩ የነበሩ ተማሪዎች ነበሩ ፤ በተጨማሪ የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች " ፈተና ደርሷቸዋል " በሚል የተሳሳተ መረጃ ተማሪዎች ላይ ጫና ለማሳደር እና ለማስፈራራት የሞከሩ ነበሩና በዚህኛው ፈተና ሁሉም ተማሪ በቂ ገለፃ እና ከመሰል ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ማስገንዘብ ይገባል።

- ተፈታኝ ተማሪዎች ፤ ስለታም ነገሮች እና የተከለከሉ የሚጬሱ ነገሮችን ለምሳሌ እንደ ሲጋራ እንዳያስገቡ ፍተሻ ላይ የሚመደቡ የፀጥታ ኃይሎች ያለመሰልቸት ፍተሻ ማድረግ ይገባቸዋል። በግቢ ውስጥ ተማሪዎች ሲረብሹ ቢገኙ ደግሞ አጥፊዎችን ለይቶ ማስወጣት ይገባል እንጂ ሁሉም ተማሪዎች ላይ በጅምላ እምርጃ መውሰድ አይገባም።

- አንዳንድ ስነ ስርዓት የሌላቸው ተፈታኝ ተማሪዎች " ሴት ተማሪዎችን ለመተንኮስ " የሞከሩም ታይተዋልና የፀጥታ ኃይሎች ተማሪዎች ሳይጨነቁ እና ምንም ሳይፈሩ ፈተናቸውን እንዲወስዱ ማድረግ አለባቸው ፤ የላላ ቁጥጥር በተማሪዎች ውጤት ላይ የሚያደርሰው ተፅእኖ ከባድ ነው።

- ከተማሪዎች ማደሪያ/ዶርም ጋር በተያያዘ ትክክለኛና ወጥ የሆነ አሰራር መዘርጋት ይኖርበታል። በአንዳንድ ተቋማት ተማሪዎች በተመደቡበት ሳይሆን እንደፈለጉ እየገቡ፣ ሌሎችን ተፈታኝ ተማሪዎች እየረበሹ የመኝታ ክፍል ለመያዝ ሲጥሩ ነበር። አንዳንድ ተማሪዎች " ተመድበንበታል " ብለው የሄዱበት ማደሪያ / ዶርም በሌሎች ተይዞ እንዳገኙ ገልፀዋል፤ በማደሪያ ክፍል ችግር የተንገላቱ ብዙ ናቸው። በቀጣይ ፈተና ወቅት ይህ ከማደሪያ ክፍል ጋር የተያያዘ ችግር መስተካከል ይኖርበታል።

- ምሽት ላይ የተማሪዎችን ደህንነት የማስጠበቅ ስራ መጠናከር አለበት፣ የሚረብሹ፣ የሚጮሁ ተማሪዎችን መቆጣጠር ይገባል። ከዚህ ባለፈ ከፍተሻ መሰላቸት ጋር በተያያዘ ሊሆን ይችላል ያልተፈቀዱ ነገሮች አልፈው ሲገቡ ታይተዋል ፤ ስልክም ደብቀው ይዘው የገቡም ነበሩና ጥብቅ የሆነ ፍተሻ እና ቁጥጥር ያስፈልጋል።

ማጠቃለያ ፦ የ2014 ተፈታኞቹ እንደመጀመሪያ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ ቆያታቸውና በእንደህ አይነት መንገድ ለፈተና መቀመጣቸው አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርከታ እክሎች የነበሩ ቢሆን በቀጣይ ላለው ፈተና እንዲስተካከል ጠቁመዋል።

#ከፈታኝ_መምህራን

- አንዳንድ ፈታኞች " ኩረጃን በሚያበረታታ " ድርጊት ሲፈፅሙ ነበር ፤ ይህ የትውልድ ጉዳይ ለመሆኑን ያለመሰላቸት የፈተናውን ሂደት መከታተል አለባቸው።

- ተማሪዎች ስልክ ይዘው ግቢ እንዳይገቡ የተደረገው ከውጭ በመደዋወል በሀሰተኛ ወሬ እንዳይረበሹ በማሰብ ነበር ነገር ግን አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፈታኝ በፈተነበት ተቋም ፀጥታ ለማስከበር የተሰማሩ አካላት ለተማሪዎች ስልክ ሲሰጡ ተመልክቷል። የፀጥታ ኃይሎች ግቢ ውስጥ ሬድዮ ብቻ ቢጠቀሙ እና ሞባይል ባይፈቀድ መልካም መሆኑን ጠቁሟል።

- አንድ የቤተሰባችን አባል የሆነ ፈተና ፈታኝ ተማሪዎች ለቀው ከወጡበት በአንዱ ተቋም እያስፈተነ የነበረ ሲሆን በፈተና ስርዓቱ ያጋጠሙ ችግሮችን በዝርዝር ገልጾልናል፡ ሱፐርቫይዘሮች እና የጣቢያ ኃላፊዎች ስራቸውን በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ እና በፈተና ክፍል ለሚስተዋሉ ችግሮች ፈጣን መፍትሄ ሊሰጡ ይገባል ብሏል።

- በፈተና ወቅት ለተፈታኞ የተሰጠው " የፈተና ሰዓት " በአግባቡ መቆጣጠር የሚገባ ሲሆን ቢቻል ቢቻል ፈተናው " ሙሉ በሙሉ " እስኪያልቅ የፈተናውን ወረቀት ይዘው እንዳይወጡ መከታተል ቢቻል ጥሩ ነው።

- "በቂ ዝግጅት"  ያላደረጉ ተማሪዎች የኩረጃ መንገዱ ሁሉ ስለተዘጋባቸው የፈተናው ስርዓት እንዲረበሽ እና ፈተናው እንዲሰረዝ ለማድረግ ሲጥሩ ነበር። እነዚህ ተማሪዎች ዓለማቸውን ለማስፈፀም ሌላ አካባቢ " ፈተና ተሰረቋል " የሚል እና ሌሎችንም ያልተረጋገጡ ወሬዎችን ነው የሚያስወሩት።

በተጨማሪ ፦

• በአንዳንድ ተቋማት ውስጥ ተማሪዎች ፈታኞችን በግልፅ " እንድንኮራረጅ ካላስደረጋችሁን " ሲሉ ነበር ፤

• ፈታኝ የሚያክብሩ እንዳሉ ሁሉ ፈታኞችንና የፈተናውን ህግ የማያከብሩ ነበሩ፣

• አንዳንድ ተማሪዎች ለፈተና መምጣታቸውን በማወቅ መዘጋጀት ሲገባቸው በግቢ ውስጥ ጥንድ ጥንድ ሆነው ሲዟዟሩ/ሲዝናኑ ነበር ፣

• አንዳንድ ተማሪዎች " ፈተናውን አናልፍም " በሚል የጥያቄ ወረቀቱን ሳይከፍቱት የመልስ ወረቀቱን ዝም ብለው ሲሞሉ ነበር ፣

• ተማሪዎች " በጭንቀት " ብቻ ለህመም ስለሚጋለጡ ትምህርት ሚኒስቴር / ዩኒቨርሲቲዎች በተማሪዎች ስነልቦና ላይ ከፍተኛ ስራ ሊሰሩ ይገባል። ተማሪዎቹ ለፈተና ሊገቡ ሲሉ ፈተናውን በራሳቸው አቅም መስራት እንደሚችሉ ተስፋ ሊሰጣቸው ይገባል።

ማጠቃለያ ፦ ክፍተቶች በቶሎ ቢታረሙና መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮች በፍጥነት ቢስተከከሉ ቀጣዩን ፈተና ካለፈው በመማር ስኬታማ ማድረግ ይቻላል።

#ለተፈጥሮ_ሳይንስ_ተማሪዎች

ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሚናፈስ ምንም ያልተረጋገጠ እና ሀሰተኛ ወሬዎች ሳትረባሹ ቀደም ብለው ወደ ግቢ ገብተው ብሔራዊ ፈተናውን ከወሰዱት " የማህበራዊ ሳይንስ " ተፈታኝ ጓደኞቻችሁ ግቢውን ለመላመድ ይረዳቹ ዘንድ በቂ መረጃ በመጠየቅ ፣ የፈተና ህጎችን ሁሉ በማክበር ፈተናችሁን በስኬት ታጠናቅቁ ዘንድ እንመኛለን። መልካሙ ሁሉ ይግጠማችሁ ፤ መልካም ፈተና !

#ለማህበራዊ_ሚዲያ_ተጠቃሚዎች

ዩኒቨርሲቲ ገብተው ፈተና የወሰዱት / በቀጣይ ቀናት የሚወስዱት ታዳጊዎች ለፈተና ስርዓቱ ብቻ ሳይሆን ለዩኒቨርሲቲ ዓለም አዲስ በመሆናቸው መደገፍ ፣ ማበረታታት  እና በራሳቸውን እንዲተማመኑ ማድረግ ፣ እንጂ በሀሰተኛ እና ባልተረጋገጠ ወሬ እንዲረበሹ እና ይህን ገና ብዙ የሚሰሩበትን እድሜ የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ ማደርግ ፣ ተስፋቸው እንደጨለመ አድርጎ ወሬ መንዛት የአይገባም።

tikvah ethiopia

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#NationalExam

የ12ኛ ክፍል " የተፈጥሮ ሳይንስ " ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባት ጀምረዋል።

ተማሪዎች ነገ ተጠቃለው የሚገቡ ሲሆን ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ (ኦሬንቴሽን) ይሰጣቸዋል።

ከጥቅምት 08 እስከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

ከዚሁ ከሁለተኛ ዙር ፈተና ጋር በተያያዘ የባለፉት ክፍተቶች መታረም ያለባቸው ሲሆን፤ ትምህርት ሚኒስቴር  ሴት ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ በቀን ሆነ በማታ ምንም አይነት ትንኮሳ እንዳይደርስ እና ፈተናውን ተረጋግተው እንዳይወስዱ የሚያደርጉ ጫናዎች እንዳይፈጠሩ እንዲሁም ምቾታቸውን ሆነ ደህንነታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል እንቅስቃሴ እንዳይኖር ጥብቅ ቁጥጥር ማደረግ ይኖርበታል።

የፀጥታ ኃይሎች የግቢ መውጫ እና መግቢያ ላይ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ዙርያ ገባው ላይ ቁጥጥራቸውን ማጠንከር እንዳለባቸው የከዚህ ቀደም ተፈታኝ ተማሪዎች ጠቁመዋል። (በአጥር የተከለከሉ ነገሮች እንዳይገቡ)

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆናችሁ የ2014  የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ ሁሉንም የፈተና ህጎችን በማክበር በመረጋጋት፣ በከፍተኛ የራስ መተማመን እንዲሁም በብሩህ ተስፋ ፈተናችሁን እንድትወስዱ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ደግሞ እነዚህ ታዳጊዎች አሁን ለተተገበረው የፈተና ስርዓት/ለዩኒቨርሲቲም  አዲስ በመሆናቸው ማበረታታ እና መደገፍ እንጂ ባልተረጋገጠ መረጃ እንዲረበሹ፣ ተስፋ እንዲቆርጡ፣ በራሳቸውን እንዳይተማመኑ ማድረግ የለባችሁምና ስለምታጋሩት መልዕክት ጥንቃቄ አድርጉ እንላለን።

ተማፅኖ፦ ተፈታኝ ተማሪዎችን ወደ ፈተና ማዕከል በማጓጓዝ ላይ አሽከርካሪዎች በእርጋታ እና በጥንቃቄ ማሸከርከር እንዳትዘነጉ እንማፀናለን።

መልካም ፈተና!

@NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
#NationalExam የ12ኛ ክፍል " የተፈጥሮ ሳይንስ " ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባት ጀምረዋል። ተማሪዎች ነገ ተጠቃለው የሚገቡ ሲሆን ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ (ኦሬንቴሽን) ይሰጣቸዋል። ከጥቅምት 08 እስከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ፈተናቸውን ይወስዳሉ። ከዚሁ ከሁለተኛ ዙር ፈተና ጋር በተያያዘ የባለፉት ክፍተቶች መታረም ያለባቸው ሲሆን፤ ትምህርት ሚኒስቴር  ሴት ተፈታኝ…
#ማስታወሻ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ " የፈተና ስርቆት እና ኩረጃ ከፍተኛ የደንብ ጥሰትና #ወንጀል " መሆኑን የሚገልፅ ሲሆን እንዲህ ያለው ድርጊት በህግ እንደሚያስጠይቅ ያስገነዝባል።

የማህበረሰብ የጋራ ሀብት በሆነው ፈተና ላይ ሚፈጸም ማንኛውንም አይነት ወንጀል በጋራ መከላከል ይገባል ይላል አገልግሎቱ።

የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የብሔራዊ ፈተና ከማክሰኞ ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከ አርብ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
ቀን 6/2/2015 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ11ዱም ክፍለ ከተማዎች ለተማሪዎች ሽኝት ተካሄደ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ወደ ሚፈተኑባቸዉ ዩኒቨርስቲዎች ከ11ዱም ክፍለ ከተማዎች ሽኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዛሬው እለት በተዘጋጀላቸው ተሽከርካሪ ወደፈተና ጣቢያዎች ገብተው በዩኒቨርሲቲዎቹ ኦረንቴሽን ተሰቷቸው የፊታችን ማክሰኞ ፈተናውን መፈተን እንደሚጀምሩ ቀደም ብሎ መገለጹ ይታወቃል።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነቡ 10 የተማሪ መመገቢያ ማዕከሎች ተመረቁ

ጥቅምት 6/2015 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነቡ 10 የተማሪ መመገቢያ ማዕከሎችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

ምክትል ከንቲባና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ጃንጥራር አባይ እንደተናገሩት የምገባ ማዕከሎች በከተማ አስተዳደሩና በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍና ልዩ ክትትል የተገነቡ ናቸው፡፡

የምገባ ማዕከሎችም መጋቢ እናቶች ንፅህናቸው ተጠብቆ ምግብ እንዲያዘጋጁ ተማሪዎች ደግሞ ንፅህናው የተጠበቀ ምግብ እንዲያገኙ ያስችላሉ ብለው ይህ ደግሞ ጤናው የተጠበቀ አምራች ትውልድ ለመፍጠር ያስችላል ሲሉ ገልፀዋል።

ምክትል ከንቲባው አክለውም በአዲስ አበባ በሚገኙ 128 ትምህርት ቤቶች የተማሪ መመገቢያ ማዕከሎች መገንባታቸውን ገልፀው ግንባታው እንዲጠናቀቅ ሲሰሩ ለነበሩ ተቋማትና ግለሰቦችም ምስጋና አቅርበዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሀይሉ ሉሌ በበኩላቸው ዛሬ የተመረቁ የምገባ ማዕከሎች ትውልድን የምንቀይርባቸው እንዲሁም የተማሪዎችንና የወላጆችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች በማቃለል የትምህርት ጥራትን የምናረጋግጥባቸው ናቸው ብለዋል።

የምገባ ማዕከሎች ለእናቶችም የስራ እድል የተፈጠረባቸው መሆናቸውን ዋና ስራ አስፈጻሚው መግለጻቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሁለተኛ ዙር ተፈታኞችን እየተቀበለ ነው

ጥቅምት 6/2015 (ዋልታ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በተዘጋጀላቸው ተሽከርካሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ በመግባት ላይ እንደሚገኙ የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በተመሳሳይ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የሁለተኛ ዙር ተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ መሆኑን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ከትምህርት ሚኒስቴር ከተመደቡለት 12 ሺሕ 265 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች መካከል 5 ሺሕ 746 ያህሉን ትላንት መቀበሉን የዩኒቨርሲቲው መረጃ አመልክቷል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot