STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ጎንደር ፣ደብረብርሃን እና ደባርቅ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች አስመረቁ።

ጎንደር ዩኒቨርስቲ በዛሬው እለት በመደበኛ እና በተከታታይ ትምህርት መርሐ ግብር በመጀመሪያ ድግሪ፣ በሁለተኛ ድግሪ እና በፒ.ኤች.ዲ ድግሪ መርሃ ግብሮቾ 3,927 ወንድ 1,600 ሴት በድምሩ 5,527 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን በአጠቃላይ በ2014ዓ.ም በሁለት ዘር 11 ሽህ 493 ተማሪዎችን አስመርቋል።

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን (ፒ.ኤች.ዲ) በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት የዛሬ ተመራቂዎች ቀደም ካሉ አመታት ተመራቂዎች ልዩ የሚያደርጋቸው አካባቢ፣  ሃገራዊ እና አለም አቀፋዊ የሆኑ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮዊ  ጫናዎችን ተቋቁመው ለዚህ በመቃታቸው ነው ብለዋል።

ተመራቂ ተማሪዎች ባገኛችሁት እውቀትና ክህሎት ተጠቅማችሁ ለዚህ ላበቃችሁ ህዝብ ትርጉም ያለው አስተዋፆ ለማበርከት የተግባር ሰው መሆን ይጠበቅባቸዋል ያሉት ዶ/ር አስራት  ዛሬ የገባችሁትን ቃል ኪዳን አክብራችሁ የሃገር እድገት፣ ሁለንተናዊ ስላም ፣ሉአላዊነት እና ህልውና እንዲረጋገጥ ከምንም በላይ ሃገራችን በእናንተ  ዘመን አንድነቷ ተጠብቆ ወደ ከፍታ ማማ እንድትወጣ ታሪካዊ አሻራችሁን እንድታስቀምጡ  ሲሉ አደራ ብለዋል።

በተመሳሳይ ደብረብርሃን እና ደባርቅ ዩኒቨርስቲዎችም በዛሬው ዕለት አስመርቀዋል።

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 928 ተማሪዎች አስመርቋል።

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 326 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በተከታታይ፣ በክረምት እና በማታ መርሃ ግብሮች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ  ናቸው።

ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
#New

መስከረም መጨረሻ ላይ የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ተማሪዎች ከመስከረም 03/2015 ጀምሮ በየትምህርት ቤታቸው ተመልሰው የማጠናከሪያ ትምህርት ይወስዱ ዘንድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለሁሉም ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤቶች ከላከው ደብዳቤ ለማየት ችለናል።

ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የ2015 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስከረም 3 ቀን 2015 እንዲሁም የቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም የመማር ማስተማሩ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ነገር ግን በከተማ ደረጃ ወጥ አድርጎ ማስጀምር በማስፈለጉ ፤ ከመስከረም 2 እስከ 6 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች ለአጀማመሩ ሙሉ ዝግጅታቸውን ያጠናቅቃሉ ተብሏል።

መስከረም 3 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን የ2014 ዓ.ም የ12 ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች #ማጠናከሪያ_ትምህርታቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጿል።

በሁሉም የትምህርት ተቋማት መስከረም 9 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማሩ ሃደት እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለሁሉም ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
Times Higher Education የተሰኘ ተቋም በሰራው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረጃ በአፍሪቃ ምርጥ 6ኛ ዩኒቨርስቲ ወይም ምረጥ አስር የአፍሪቃ ዩኒቨርስቲዎች ወስጥ የኢትዮጵያ አንጋፋ የትምህርት ተቋም የሆነውን አዲስአበባ ዩንቨርስቲ አካቷል።

የአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ከዚህ በፊትም በአፍሪካ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች የምርጥ አስር ደረጃ ይዞ እንደነበር ይታወሳል።

ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
#GoldMedalistStudent

ተማሪ ታምራት ደንቢ ዛሬ ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 4.00 በማስመዝገብ በነርሲንግ ከተመረቀ በኋላ፤ ሜዳሊያውን ለእናቱ አበርክቷል።

ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
በዓለም ላይ እድሜያቸው 10 አመት ከሆናቸው ህፃናት ውስጥ ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት ቀላል ፅሁፍ እንኳ ማንበብና መረዳት አይችሉም:- ዩኒሴፍ

-------------------- --------------------

ከ10 አመት ህጻናት መካከል ወደ ሁለት ሶስተኛ የሚጠጉት ቀላል ጽሑፍ እንኳ ማንበብ እና መረዳት እንደማይችሉ ፣ አስቸኳይ እርምጃ ካልተወሰደ አለም አቀፋዊ የትምህርት ኪሳራና የትውልድ ጥፋት ሊከተል እንደሚችል ዩኒሴፍ አስታውቋል።

ቀድሞውንም የተዳከመውን የትምህርት ስርዓት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰት ችግሩን በአለም አቀፍ ደረጃ አባብሶታል ብሏል።

ህፃናት መሰረታዊ የማንበብ እና የሂሳብ ክህሎቶች እንዲኖራቸውና አቅማቸውን እንዲጠቀሙ ለማድረግ ዓለም አቀፍ ጥረት እንዲደረግ ዩኒሴፍ በ "Let me learn "መማር እፈልጋለሁ" ቅስቀሳው ጥሪ አቅርቧል።

ሁሉም ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዲገቡ ማድረግ፣ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ ማድረግ፣ የመማር ማስተማር ስራዎችን በመደበኛነት መገምገም፣ ለትምህርት ቅድሚያ መስጠት፣ ህፃናት ለመማር ዝግጁ እንዲሆኑ የስነ-ልቦናና ማህበራዊ ጤና ደህንነትን ማዳበር የሚሉ እርምጃዎችን መንግስታት እንዲወስዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ንቅናቄ እየተደረገ ይገኛል ።

በአለም አቀፍ ደረጃ ከአስር ስድስት የሚጠጉ ህጻናት በድህነት ምክንያት በትምህርት ተጎጂ እንደሆኑና በአስር አመት እድሜያቸው ቀላል ፅሁፍ ማንበብ እና መረዳት አይችሉም ብሏል።

በፈረንጆቹ መስከረም 19/2022 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት "የትምህርት ለውጥ ሰብሰባ" የጠራ ሲሆን ጉባኤው ትምህርት የሰላም፣ የመቻቻልና የዘላቂ ልማት መሰረት ነው በሚል ጉዳዩን በልዩ ትኩረት ይመለከተዋል ተብሏል።

https://www.unicef.org/learning-crisis

ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
አሳዛኝ ዜና!

የወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪው ፋዓድ ወንድወሰን ዳንኤል ዶርም ውስጥ እራሱን ሰቅሎ ገደለ!

ተማሪያችን ፋዓድ ወንድወሰን ዳንኤልን አጥተናል፡፡ ተማሪ ፋዓድ ወንድወሰን ዳንኤል በጤና ኮሌጅ የ2ኛ ዓመት የፋርማሲ/ Pharmacy /ተማሪ የነበረ ሲሆን በ26/12/2014 ዓ.ም ምክኒያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከማደሪያ ቤቱ/ዶርሙ/ውስጥ እራሱን በመስቀል ህይወቱ አልፏል፡፡

ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለክፍል ጓደኞቹ መጽናናትን እንመኛለን፡፡



ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
|  አሥራት አፀደወይን (ዶ/ር) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት

👉 ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመቀጠል በራሳቸው ገቢ እንዲተዳደሩ ከተለዩ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ነው።

👉 ለዚህም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደተግባር ለመግባት የሚያስችለውን ዝግጅት እያደረገ ነው።

👉 ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ ግብሮችን በሂደት እየቀነሰ የሁለተኛ እና የሦሥተኛ ዲግሪ መርሃ ግብሮችን ለማስፋት እየሰራ ነው።

👉 የውጪ ሀገራት ተማሪዎችን ለመሳብ እየሰራ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት 50 ዓለም አቀፍ ተማሪዎች አሉት።

👉 ዩኒቨርሲቲው አሁን ላይ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦሥተኛ ዲግሪ እንዲሁም በስፔሻሊቲ እና በሰብ ስፔሻሊቲ መርሃ ግብሮች ከ48 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል።

ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
ጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በ2014 ዓ.ም በማስተርስ, በዲግሪ እና በቴክኒክና ሙያ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በሚሌኒየም አዳራሽ ነሐሴ 21, 2014 ዓ.ም በድምቀት አስመረቀ።

ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

የወሎ ዩኒቨርስቲ የጤና ኮሌጅ የ2ኛ ዓመት የፋርማሲ/ Pharmacy /ተማሪ የነበረው ተማሪ ፋዓድ ወንድወሰን ዳንኤል በ26/12/2014 ዓ.ም ምክኒያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከማደሪያ ቤቱ/ዶርሙ/ውስጥ እራሱን በመስቀል ህይወቱ ማለፉን ዩኒቨርስቲው ገልጿል።

ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
ዶ/ር ውብሸት ዠቅያለ የዓመቱ የበጎ ሰው ሽልማት በመምህርነት ዘርፍ ተሸላሚ ሆኑ

ነሐሴ 29/2014 (ዋልታ) በ10ኛው የዓመቱ የበጎ ሰው ሽልማት በመምህርነት ዘርፍ ከቀረቡ ሶስት እጩዎች መካከል ዶ/ር ውብሸት ዠቅያለ ተሸላሚ ሆነዋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት አካባቢ ያካሄደውን የምርምር ስራ የሰነደ መጽሐፍ አስመረቀ

ነሐሴ 30/2014 (ዋልታ) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት አካባቢ ያካሄደውን የምርምር ስራ "ወረራና መዋቅራዊ ዘር ማጥፋት በወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት" በሚል ርዕስ ለህትመት የበቃውን መጽሐፍ አስመረቀ።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) በወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት አካባቢ ከ18 ወራት በላይ የወሰደ የምርምር ስራ ለህትመት መብቃቱን ገልፀው ይህም የምርምር ውጤት በ21 የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው መጽሐፉን ለማዘጋጀት ያስፈለገው መነሻ ምክንያት አካባቢው ከ1984 ጀምሮ ሕወሓት ወደ ትግራይ እንዲካለል በማድረግ የህዝቡን ማንነት በመግፋት መጠነ ሰፊ ግፎችን ሲፈፅም በመቆየቱ መሆኑን አንስተዋል፡፡

እንዲሁም የወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት ህዝብ እኛ ጎንደሬዎች አማራ እንጂ ትግራዋይ አይደለንም በማለታቸው ከሚደርስባቸውን መዋቅራዊ የዘር ማጥፋት ግፍ ለመቀልበስ በርካታ ዓመታትን የትጥቅ ትግል ሲያካሂዱ በመቆየታቸው መሆኑንም አመላክተዋል።

የማንነት ጥያቄው ለፌደሬሽን ምክር ቤት የቀረበ ሲሆን የማንነት ጥያቄው በወቅቱ ባለመመለሱ ተጨማሪ የጥናትና የምርምር ጽሑፍ ማቅረብ በማስፈለጉ እንደሆነም ተገልጿል።

መጽሐፉ በ7 ምዕራፎችና በ380 ገፆች ተጽፎ የቀረበ ሲሆን ከ5 ሺሕ በላይ ቅጅዎች በመጀመሪያው እትም ቀርበዋል።

በመጽሐፉ መረቃ መረኃ ግብር ላይ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ጀምበር እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተገኝተዋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎች ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT