STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#Update

የጤና ሚኒስቴር ከነሐሴ 23/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት ለጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑ ይታወቃል።

የብቃት ምዘና ፈተናው የሚሰጥበት የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው መሆኑ ተገልጿል፦

• ፋርማሲ፣ አንስቴዥያ እና ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ | ነሐሴ 23/2014 ዓ.ም

• ነርሲንግ | ነሐሴ 24/2014 ዓ.ም

• ህክምና እና ጤና መኮንን | ነሐሴ 25/2014 ዓ.ም

• ሚድዋይፈሪ፣ ዴንታል ሜዲስን እና ኢንቫይሮመንታል ሄልዝ | ነሐሴ 26/2014 ዓ.ም

• ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ፣ ፔዲያትሪክ ነርሲንግ እና ሳይካትሪ ነርሲንግ | ነሐሴ 27/2014 ዓ.ም

(ወደ ፈተናው ለመግባት የሚያስፈልጉ እና ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ከትምህርት ሚኒስቴርና ጤና ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት በግጭት የወደሙ ቋማትን መልሶ መገንባት የሚያስችል ሀብት ለመሰብሰብ የሚረዳ የመግባቢያ ሰነድ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ጤና ሚኒስቴር ጋር ተፈራረመ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት፤ በጦርነቱ ከአራት ሺ በላይ ትምህርት ተቋማት ላይ ጉዳት ደርሷል። ከዚህ ውስጥ ከአንድ ሺ 300 በላይ የሆኑት ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ገልጸዋል።
የወደሙትን የትምህርት ተቋማት በተሻለ ደረጃ መልሶ ለመገንባት ስራዎች ተጀምረዋል ያሉት ፕሮፌሰሩ ብርሃኑ፤ በተለያየ መልኩ ሀብት ለማሰባስብ እየተሥራም ነው፤ ስምምነቱም ዳያስፖራዎች በተደራጀ መልኩ ድጋፍ ለማሰባሰብ ያግዛል።
ዳያስፖራዎች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው፤ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በተከሰተው ግጭት የጤና ተቋማት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ጉዳት የደረሰባቸውን ጤና ተቋማት መልሶ ለመገንባት በተሰራ ስራ ብዙ ጤና ተቋማትን ወደ አገልግሎት መመለስ ተችሏል።
አሁንም ወደ አገልግሎት ያልተመለሱ ጤና ተቋማት ስላሉ በውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሚኒስትሯ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሐመድ እንድሪስ፤ ዳያስፖራው በተለያየ መልኩ ለአገሩ ድጋፍ እያደረግ ይገኛል።
ዛሬው ዕለት የተፈረመው ስምምነትም ዳያስፖራው በተበታተነ መልኩ ለመልሶ ግንባታ ሲያደርግ የቆየውን ድጋፍ በተደራጀ አሰራር አጠናክሮ እንዲቀጥል ያግዛል ብለዋል።
በፋንታነሽ ክንዴ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ማስታወቂያ
**
ለ2015 ዓ.ም የድህረ ምረቃ (ለ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ) ፕሮግራም አመልካቾች በሙሉ

ለ2015 ዓ.ም የድህረ ምረቃ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው ነሐሴ 23/2014 ዓ.ም (August 29,2022) ሲሆን የመፈተኛ ሰዓትና ቦታ ፕሮግራሙ በሚሰጥበት ካምፓስ በሚገኙ ት/ክፍሎችና ት/ቤቶች የሚገለጽ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰብያ፡-ተፈታኞች ለፈተና በሚቀርቡበት ሰዓት ማንነታቸውን የሚገልጽ የመታወቂያ ደብተር መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ሬጅስትራርና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ለትምህርት ወደ ውጭ ሀገር ለሚሄዱት አቶ ላቀ አያሌው ሽኝት ተደረገ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለትምህርት ወደ ውጭ ሀገር የሚሄዱትን አቶ ላቀ አያሌውን ዛሬ በክብር ሸኝቷቸዋል።

በሽኝት መርሐ-ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የትምህርት ሚኒሰቴሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለአቶ ላቀ አያሌው ቀጣይ ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆንላቸው ተመኝቷል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#የ12ኛ_ክፍል_ብሔራዊ_ፈተና

የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ምክክር ሲካሄድ ውሏል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሀገሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንቶች እና ከየክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች እና የፈተና ጉዳይ አስፈጻሚዎችና ከትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ባለሙያዎች ጋር በፈተናው አሰጣጥ ላይ ምክክር ማካሄዱን አሳውቋል።

በውይይቱ ላይ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የውይይት መነሻ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሠነዱ ዙርያ የተለያዩ አስተያቶች እና ጥያቄዎች ተነስተው ግልጽነትና የጋራ መግባባት ተፈጥሯል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ ፈተናውን ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ሁሉ ከሚመለከታቸው ባለሚና አካላት ጋር በመሆን እየተከናወነ እንደሚገኝ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ExitExam

የትምህርት ጥራት #ፈተና_በመስጠት ብቻ ይረጋገጣል ?

ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀመር ይታወቃል።

ለመሆኑ ፈተና በመፈተን ብቻ የትምህርት ጥራት ማምጣት ይቻላል ? ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ ምላሽ አለው።

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቲቪ) የተናገሩት ፦

" የትምህርት ጥራት ፈተና ብቻ በመስጠት የሚሳካ ፤ የሚረጋገጥ ነገር አይደለም።

በአጠቃላይ ግን በትምህርት እና ስልጠና ዘርፉ በተለይም በትምህርቱ ዋና ችግር አለ ተብሎ የተለየው ዋና የትምህርት ሴክተሩ ስብራት ነው ተብሎ የተለየው ትምህርታችን ጥራትም ተገቢነትም ጎሎታል።

ስለዚህ አስመርቀን የምናስወጣው በሙሉ ባይባልም የጥራት ፣ የብቃት ችግር አለበት ይሄንን መፍታት ያስፈልጋል።

ለዚህ የሚሆን በሁሉም ደረጃ ከግብዓትም ጋር ከሂደቱም ጋር የሚያያዝ እንደዚሁም ውጤቱን ከማረጋገጥ ጋር የሚያያዝ ስራዎች መሰራት አለባቸው ተብሎ በመንግስት ቁልፍ የሪፎርሞች ተጀምረዋል አንደኛው ከመውጫ ፈተና ጋር የሚያያዝ ነው።

ይሄ የመውጫ ፈተና በዋናነት የሚመለከተው የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃንን ነው ሁለተኛ ዲግሪ እና ሌሎችን አይመለከትም የሚጀምረው በ2015 ሰፋ ብሎ ነው እንጂ ከዚህ በፊትም የተጀማመሩ ስራዎች አሉ የተጀመሩ ፕሮግራሞች አሉ።

ዋናው ቁም ነገሩ በግብአት ደረጃ ጥራቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል የምሩቁን ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን የመማር ማስተማር ሂደቱ ጥራትን በሚያረጋግጥ መልኩ መምራት እና መስጠት ያስፈልጋል።

በጥሩ ግብዓት ከተደገፈ እና ጥሩ ሂደት ካለው በውጤቱ ማረጋገጥ ይገባል ከሚል መነሻ የተጀመረ የሪፎርም ስራ ነው "

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
Finland Scholarships 2023 (Study in Finland)

Details: https://tinyurl.com/yc354wp7

The Finland Scholarships for 2022 to 2024 are open for Bachelors, Masters and PhD Programs.

The Scholarship is Funded by the Ministry of Education, Finland

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ጥቆማ

የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከGIZ-QEP ጋር በመተባበር ከ2011 ጀምሮ በአጭር የስልጠና መርሀ ግብር የተግባር እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና በማሰልጠን ላይ ይገኛል።

በ2014 ዓ.ም የስልጠና ዘመንም የ6ኛ ዙር የስልጠና ፕሮግራም ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጅት መጨረሱን አስታውቋል።

በዚህም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የሙያ ዘርፎች የመመዝገቢያ መስፈርቶችን የምታሟሉ ሰልጣኞች እንድትመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።

የሙያ ዘርፎች፦

1. Automotive (አውቶሞቲቭ)
2. Food Preparation and Bakery(ምግብ ዝግጅት እና ዳቦ እና ኬክ ስራ)
3. Electrical installation and Sanitary የኤሌክትሪክ እና ሳኒተሪ መስመር ዝርጋታ)
4. Garment (ልብስ ስፌት)
5. Leather Products(የቆዳ ስራ)

ስልጠናው ከመስከረም 05 እስከ የካቲት 30 2015 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን ተመዝጋቢዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት (ነሐሴ 9/2014) ባሉ ተከታታይ 6 የስራ ቀናት ውስጥ በኮሌጁ ሬጅስትራር ፅ/ቤት በአካል በመገኘት መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ኮሌጁ ያለው ቦታ ውስን በመሆኑ የተመዝጋቢ ቁጥሩን አይቶ የመግቢያ ፈተና ካለ እንደየአስፈላጊነቱ በውስጥ ማስታወቂያ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

* ተጨማሪ መረጃ ከላይ ከተያያዘው ማስታወቂያ ማግኘት ይችላሉ።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ከ350 በሚበልጡ የግል የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን ባለስልጣኑ አስታወቀ
===== ===== =====

👉 ጥናት ካካሄደባቸው 10 ሺ የትምህርት ማስረጃዎች 505ቱ ሀሰተኛ ናቸው።

አዲስ አበባ፡- የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በ2014 በጀት አመት የስነ ስርዓት ጥሰት በፈጸሙ ከ350 በላይ የግል የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡ ባለስልጣኑ በበጀት አመቱ ከአረጋገጣቸው 10 ሺ የትምህርት ማስረጃዎች 505 ቱ ሀሰተኛ ናቸው ብሏል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳሬክተር ዶክተር አንዷለም አድማሴ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ በ2014 በጀት አመት ከየትኛውም በጀት አመት የበለጠ የትምህርት ጥራትን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን የማጽዳት ስራ ተከናውኗል፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ ገምግሞ አቅጣጫ ካስቀመጠ ጊዜ ጀምሮ ከ350 በላይ በሚሆኑ የግል የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ ወስዷል፡፡

መንግሥት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እየወሰዳቸው ካሉ ተጨባጭ እርምጃዎች ውስጥ ሕገ ወጥ የትምህርት ተቋማትን መቆጣጠር አንዱ ተግባር ነው ያሉት ዶክተር አንዷለም፤ አሁን ላይ የትምህርት ጥራት በኢትዮጵያ ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ ኃላፊነት የማይሰማቸውና ትርፍን ብቻ አላማ ያደረጉ ሕገ ወጥ የግል የትምህርት ተቋማት መስፋፋት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ተቋምና ፕሮግራም መዝጋት አማራጭ አይደለም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ነገር ግን የእውቅና ፈቃድ ሳይሰጣቸው በትውልድ ህይወት የሚነግዱ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል ነው ያሉት፡፡

እንደ ዶክተር አንዷለም ገለጻ፤ በርካታ ዜጎች እውቅና በሌለው የግል የከፍተኛ የትምህርት ተቋም ገንዘባቸውን ከፍለው ከተማሩ በኋላ ባለስልጣኑ ማረጋገጫ ሲሰራላቸው ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ሲሆንባቸው ለተመሰቃቀለ ህይወት እየተዳረጉ ነው፡፡ በተቋማት ላይ ድንገተኛ ፍተሻ በማድረግ በ355 የግል የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ከፕሮግራም መዝጋት እስከ ተቋሙን ሙሉ በሙሉ እስከ መዝጋት የደረሰ የማስተካከያ እርምጃ ተወስዷል፡፡ ለዚህም መገናኛ ብዙሃን የነበራቸው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡

የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ ስራ በበጀት አመቱ በትኩረት ከተሰራባቸው መካከል መሆኑን ያስታወሱት ዶክተር አንዷለም፤ በዘርፉ የጤና ሚኒስቴርና ጉምሩክ ኮሚሽን ለሚቀጥሯቸው ሰራተኞች ቅጥር ከመፈጸማቸው በፊት የትምህርት ማስረጃቸው በባለስልጣኑ እንዲረጋገጥ የሚያደርጉበት አግባብ ለህገ ወጥ የትምህርት ማስረጃ ቁጥጥር ጉልህ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል፡፡ዕድገትና ቅጥር ሲያከናውኑም በሙሉ ሳያስፈትሹ እንደማያከናውኑ ተናግረዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ፤ የትምህርት ማስረጃ ሲረጋገጥ በቀጣሪ መስሪያ ቤቶች ተገደው የሚመጡ አካላትን የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥና ከውጭ አገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃን አቻ ግምት በመስጠት በሁለት መልኩ የሚረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡ የማረጋገጥ ስራ የሚጀምረው ከአገር አቀፍ ፈተናዎች እንደሆነና በወቅቱ ከነበረው የመቁረጫ ነጥብ በመጀመር እያንዳንዱ የትምህርት ማስረጃ ተፈትሾ እስከ ዲፕሎማና ዲግሪ እንደሚረጋገጥም ጠቁመዋል፡፡

በ2014 በጀት አመት የጤና ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽንን ሳያካትት ተገደው ከመጡ ከ10 ሺ በላይ የትምህርት ማስረጃዎችን ማረጋገጥ ተችሏል ያሉት ዶክተር አንዷለም፤ ከተረጋገጡት የትምህርት ማስረጃዎች 505 የሚሆኑት ትክክለኛ ያልሆኑ የትምህርት ማስረጃዎች እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡

ፈቃድ ሳያገኙ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ክፉኛ እየጎዱ ያሉ ትውልድን እያቀጨጩ የሚገኙ ሕገ ወጥ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ለመቆጣጠር በሚደረገው ሂደት ህብረተሰቡ ጥቆማ በመስጠት ድጋፍ እንዲያደርግም ዶክተር አንዷለም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የቦረና ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የሁለተኛ ሴሚስተር ምዝገባ ነሐሴ 18 እና 19/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በተጠቀሱት ቀናት ብቻ በአካል በመቅረብ ምዝገባ እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
*Full Ride USA Scholarships 2023 (Fully Funded)*

Details: https://tinyurl.com/bdksxrje

American Full Ride Scholarship for Bachelors Masters and PhD Students. The Scholarship that will Cover Full Tuition Fee, Monthly Stipend, Accommodation, Room, Travel Allowance.



ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ብርሃን ኮሌጅ በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 402 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በኤክስቴንሽን ፕሮግራም በሁለት የትምሕርት ዘርፎች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ኮሌጁ ከ1 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ እንደሚገኝ የተቋሙ ዲን ሲሳይ ሙላቴ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

  ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ አምስት ቅርንጫፎች ይከፍታል።

ለዓመታት ሲሰራው የቆየው ሪፎርም የፀደቀለት ባለስልጣኑ፤ አዲስ መዋቅር ገቢራዊ ማድረግ ጀምሯል።

ባለስልጣኑ ከከፍተኛ ትምህርት እና አጠቃላይ ትምህርት በተጨማሪ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትንም እንዲቆጣጠር ተደርጓል።

ከወራት በፊት ወደ ባለስልጣን መስሪያቤትነት የተሸጋገረው ተቋሙ፤ ሦሥት ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች እንዲኖሩት መደረጉ ይታወሳል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያጸደቀው የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ደንብ ከግንቦት 26/2014 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ መዋሉ ይታወቃል።

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ሰባት አባላት ባሉት ቦርድ የሚመራ ሲሆን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የቦርድ ሰብሳቢ መሆናቸው አይዘነጋም።



  ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት የድህረ ምረቃ ተማሪዎች የ2014 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ሴሚስተር ምዝገባ ከነሐሴ 26 እስከ 28/2014 ዓ.ም #በኦንላይን ብቻ የሚከናወን መሆኑን ገልጿል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)




  ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT