#WoldiaUniversity
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከ7 ሺህ በላይ የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።
ዩኒቨርሲቲው በኮቪድ-19 እና በፀጥታ ችግር ምክንያት የክረምት ትምህርት መርሃ ግብርን ለሁለት ተከታታይ ዓመታት አቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል።
ዛሬ ከተቀበላቸው ነባር እና አዲስ የክረምት ተማሪዎች በተጨማሪ፤ አሁን ላይ 6 ሺህ መደበኛ ተማሪዎች በግቢው በትምህርት ላይ ይገኛሉ።
የ2014 ዓ.ም የክረምት መርሃ ግብር የትምህርት ጊዜ እስከ ጥቅምት 2015 ዓ.ም ድረስ ሊቆይ እንደሚችል ተገልጿል።
ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT

#AASTU
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ምዝገባ ሊጀምር ነው።
ስርዓቱ በመንግስት እና የግሉ ዘርፍ አገልግሎቶች ላይ ግልጽነት እና የተጠያቂነት አሰራርን እንደሚያበረታታ ታምኖበታል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማከናወን የሚጠበቅባቸውን ዝርዝር አሳውቋል፦
~ ሁሉም ተማሪዎች (የቅድመ እና ድህረ-ምረቃ)፣
~ መምህራን (በሥራ ላይ እና በሀገር ውስጥ
ትምህርት ላይ የሚገኙ) እና
~ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች (ቋሚ ቅጥር፣ ኮንትራት ቅጥር ወይም ጊዚያዊ ቅጥር ሰራተኞች)
የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ የዲጂታል ምዝገባ የሚያደርጉበት የጊዜ ሰሌዳን በቀጣይ ይገለጻል ተብሏል።
ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የተመደቡ ባለሙያዎች የዲጂታል መታወቂያውን እንደሚያዘጋጁ ታውቋል።
መንግስት በ2014 ዓ.ም በተመረጡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ለማካሄድ እቅድ መያዙ ይታወሳል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዘመን መጽሔት ሀምሌ 2014ዓም. ልዩ እትም በትምህርት ዘርፋ ዋና ዋና የለውጥ ተግባራት ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
በኦሮሚያ ክልል ካሉ 9 አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ መምህራን የሚሰጠው የውጭ ቋንቋ ስልጠና
በኢትዮጵያ የቻይና ኢንባሲ ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር የቻይንኛ ቋንቋን በኢፋ ቦሩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚያስተምሩ መምህራን ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል።
በቅርቡም የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በትምህርት ቤቶቹ የፈረንሳይኛ ቋንቋን ለሚያስተምሩ መምህራን ስልጠና ለመስጠትና የተለያዩ መማሪያ ግብዓቶችን ለማቅረብ ተስማምቷል።
ስልጠናውን የሚወስዱት መምህራን በክልሉ ካሉ ዘጠኝ የልኅቀት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ መሆናቸው ተጠቅሷል።
ክልሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ''ኢፋ ቦሩ'' አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ ለአገልግሎት በማብቃት ላይ ይገኛል። በአንድ አመት ውስጥ 100 ኢፋ ቦሩ እና 7 ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን መገንባት መቻሉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
የፕሮጀክቶቹ ግንባታ 16.7 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ከዚህ ውስጥ የኦሮሚያ ክልል 6 ቢሊዮን ብር የመደበ ሲሆን፣ ቀሪው በህዝቡ ተሳትፎ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ድጋፍ የተሸፈነ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ቶላ ይህን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ላይ ጠቅሰው ነበር፡፡

Study in Korea without IELTS 2023
Visit: https://tinyurl.com/mvawnxud
Now International students can Apply for study programs in top 10 universities of South Korea
Programs: Bachelor, Masters & PhD. No need of IELTS for admission
ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
Visit: https://tinyurl.com/mvawnxud
Now International students can Apply for study programs in top 10 universities of South Korea
Programs: Bachelor, Masters & PhD. No need of IELTS for admission
ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
JP Morgan Internship 2022 (Fully Funded)
Details: https://tinyurl.com/yc47m636
Paid Internship for Bachelors, Masters, PhD, and MBA Students in more than 60 Locations.
JP Morgan Internship will Lead to On boarding Job Career.
ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
Details: https://tinyurl.com/yc47m636
Paid Internship for Bachelors, Masters, PhD, and MBA Students in more than 60 Locations.
JP Morgan Internship will Lead to On boarding Job Career.
ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ትምህርት_ሚኒስቴር
" ፈተናው የሚቀር አይደለም " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ
* ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ተማሪዎቻችሁን አዘጋጁ !
የመውጫ ፈተና በ2015 ዓ/ም መሰጠት ይጀምራል። ይህን በተመለከተ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢፕድ ከሰጡት ማብራሪያ ፦
" ... በሙሉ አቅማችን እየተዘጋጀን ነው። የሚቀር ነገር አይደለም ፤ 2015 ትምህርት ዘመን ማብቂያ ላይ ፤ ከዚህ በፊት እንደነበረው ዝም ብሎ ዲግሪ የሚሰጥበት ነገር ሀገሪቱን በጣም ክፉኛ ጎድቷታል የሚል እምነት አለን።
ይሄንንም ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንቶች ጋር፣ ከግል ኮሌጆች ፕሬዜዳንቶች እና ኃላፊዎች ባለቤቶች ጋር ፣ ከዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ተማሪዎች ጋር ሰፊ ውይይት ያደረግንበት ነው።
ይሄ አዲስ ሀሳብ አይደለም አተገባበሩ ነው አዲስ የሆነው። ከዚህ በፊት ተሞክሮ ተቃውሞ ስለንበር ነው የተተወው።
የህግና የህክምና ትምህርቶችን ብቻ እንዲሰጡት አድርጎ አሁንም እየተሰጡ ሌሎች በሙሉ ተትተው ነበር።
አሁን ግን በአጠቃላይ ከከፍተኛ ትምህርት ጥራት ችግር ጋር በተገናኘ ምንም ልንወጣው የማንችለው እና ያን ጥራት ለማስተካከል ዩኒቨርሲቲዎቹ በራሳቸው ባስተማሩበት እና እራሳቸው በሰጡት ፈተና ብቻ የሚለኩበት ሁኔታ ከጀርባው ያለ ጠንካራ የሞራል መሰረት ይጠይቃል።
ዩኒቨርሲቲዎቹ እራሳቸው ድግሪ ስንሰጥ ለማህበረሰቡ ይሄ ሰው እንዲህ እንዲህ አይነት ትምህርቶችን፣ እውቀቶችና ክህሎቶች አሉት ብለን ነው እየነገርን ያለነው።
... ከዚህ በፊት አንዱ የነበረው ችግር ማሳለፍ የሚባል ነገር አለ። ዝም ብሎ ማሳለፍ ምክንያቱም ተማሪዎች ከወደቁ የትምህርት ክፍሉን ድክመት ያሳያል እየተባለ ሲሳራበት የነበረው ነገር ምን ያህል ሀገሪቱን እንደጎዳት አሁን ለውይይትም የሚቀርብ አይደለም።
እኔ በዚህ ጉዳይ ባለፉት ሰባት (7) ወራት በትምህርት ዘርፍ ከሚሰሩ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንቶች የግል ኮሌጆች ባለቤቶች እንደዚህ አይን ያወጣ የለም መሆን የለበትም የሚል ክርክር አልሰማሁም። ሁሌ የሚሰማው ለምን በኛ ጊዜ ? ለምን ባንተ ጊዜ ለምን በሌላውስ ሰው ጊዜ የሚለውን ልትመልስ አትችልም ይሄ ዝም ብሎ ደረቅ ክርክር ነው።
በአንድ በሆነ ጊዜ መጀመር አለበት ምክንያቱም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራት ላይ እየደረሳ ያለው ጉዳት ሀገሪቱን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት ነው። ይሄንን ዝም ብለን ማለፍ አንችልም ብለን እየሄድንበት ነው።
ለተማሪዎችም ፣ ለወላጆችም፣ ለቤተሰብም አንድ (1) ዓመት የመዘጋጃ ጊዜ ሰጥተናል። ለኮሌጆችም ተማሪዎቻቸውን እንዲያዘጋጁበት ጊዜ ሰጥተናል ይሄን ጊዜ በደንብ ተጠቅመው ስራቸውን መስራት አለባቸው።
ይሄ የመውጫ ፈተና የተማሪዎች ፈተና ብቻ አይደለም። ከተማሪዎች በላይ የትምህርት ክፍሎች፣ የኮሌጆች ፣ የዩኒቨርሲቲዎች ፈተና ነው። ምን እያደረጉ ነው ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚለውን እንደትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ የምናገኘው ፤ እነዚህ ኮሌጆች ፣ ዩኒቨርሲቲዎች በእርግጥም ተማሪዎችን እያበቁ ነው ? ወይስ የዲግሪ ወፍጮ ቤት እንደሚሏቸው ዝም ብሎ ጊዜ እያስቆጠሩ ድግሪ የሚሰጡ ናቸው የሚለውን የምንለይበት ነው።
ስለዚህ የሚቀር አይደለም። ሁሉም እንደማይቀር አውቆ የተሰጠውን የመዘጋጃ ጊዜ በደንብ ተጠቅሞ ትምህርትን በደንብ አስተምሮ በደንብ አስጠንቶ ቢያዘጋጅ ነው የሚሻለው "
©ኢፕድ/ቲክቫህ

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ
የ2014 ዓ.ም የላቀ ውጤት ተመራቂው አቤል ጌታሁን የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
የኮሌጁ ፋርማሲ ትምህርት ክፍል ተመራቂው አቤል ጌታሁን 3.98 አጠቃላይ ውጤት በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ በመሆን ነበር የተመረቀው።
የኢትዮጵያ ፋርማሲ ማህበር ዛሬ ባካሄደው 42ኛ ዓመታዊ ጉባኤው፤ ተመራቂ አቤል ጌታሁን ከጤና ሚኒስቴር ሌላ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶለታል።
ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የ2014 ዓ.ም የላቀ ውጤት ተመራቂው አቤል ጌታሁን የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
የኮሌጁ ፋርማሲ ትምህርት ክፍል ተመራቂው አቤል ጌታሁን 3.98 አጠቃላይ ውጤት በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ በመሆን ነበር የተመረቀው።
የኢትዮጵያ ፋርማሲ ማህበር ዛሬ ባካሄደው 42ኛ ዓመታዊ ጉባኤው፤ ተመራቂ አቤል ጌታሁን ከጤና ሚኒስቴር ሌላ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶለታል።
ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም በክረምት መርሃ ግብር የሳይንስ ትምህርት መስኮች የሚሰለጥኑ ተማሪዎች መግቢያ ሐምሌ 25 እና 26/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።
በመሆኑም አመልካቾች የመገጣጠሚያ ደብዳቤ እና ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ በመያዝ በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመቅረብ ምዝገባ አድርጉ ተብሏል።

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 985 ተማሪዎች ነገ ያስመርቃል።
ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በማታ እና በክረምት መርሃ ግብር በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።
ተማሪዎቹ በጸጥታ ችግር ምክንያት ለአንድ ሴሚስተር በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የተማሩ እና ቀሪ ትምህርታቸውን በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ማጠናቀቃቸውን የዩኒቨርሲቲው የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ተፈራ አስናቀ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።
የተማሪዎቹ የምረቃ ስነ-ስርዓት ነገ ሐምሌ 23/2014 ዓ.ም በወልድያ ከተማ ሼህ ሙሃመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲየም ይከናወናል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#BREAKING #ሰበር_ዜና❗️
#ቻይና #አሜሪካ
አሁን|-
ቻይና በታይዋን አቅራቢያ የቀጥታ ሮኬት ተኩስ ወታደራዊ ልምምድ ማካሄድ ጀመረች።
የቻይና ሕዝባዊ ነፃ አውጪ ጦር ልምምዱን በሀገሪቱ ምስራቃዊ የፉጂያን ግዛት - ከደሴቱ ወጣ ብሎ በሚገኘው ውሃ ውስጥ ልምምዱን እያካሄደ ነው።
ልምምዱ በታይዋን፣ በቻይና እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ከፍተኛ ውጥረት በነገሰበት ወቅት ነው።
የአሜሪካ ምክር ቤት ሃላፊዋን የጫነው አውሎፕራን ወደ ታይዋን የሚያደርገውን ጉዞ መጀመሩን ተለትሎ ነው ቻይና ወታደራዊ ልምምዱን በታይዋን ድንበር ቀጥታ የጀመረችው።
ትናንትና ማታ ላይ የቻይና ሠራዊት 80ኛ ልፍለ ጦር በይፋዊ ገጹ ላይ " ለጦርነት ዝግጁ ነን" የሚል መልዕክት ማስተላለፉ ይታወሳል።
📹 RT,Sputnic
መረጃ እንዘግባለን

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1 ሺህ ተማሪዎች አስመርቋል።
ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በማታ እና በክረምት መርሃ ግብር በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።
ተማሪዎቹ በጸጥታ ችግር ምክንያት ለአንድ ሴሚስተር በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በጊዚያዊነት ተመድበው ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።
በ2004 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሥራን የጀመረው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ፤ ዛሬ 9ኛ ዙር ሰልጣኞቹን ነው ያስመረቀው።

‹‹የመውጫ ፈተና በትምህርት ጥራት ያለውን ችግር አንዱ የመፍቻ አማራጭ እንጂ ብቸኛ ርምጃ አይደለም›› – ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ
የዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና በትምህርት ጥራት ላይ የሚስተዋለውን ችግር ለመፍታት ከሚወሰዱ ስትራቴጂያዊ ርምጃዎች ውስጥ አንዱ እንጂ ብቸኛና የመጨረሻ ርምጃ አለመሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ገለጹ፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል በ2015 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ እንደሚተገበር በሚጠበቀው የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዙሪያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፤ የመውጫ ፈተና የትምህርት ጥራትን ማስጠበቂያ የመጨረሻና ብቸኛው ርምጃ አይደለም፡፡ ብቁ የሰው ሃይል በማዘጋጀት ወደ ኢኮኖሚ መግባቱን ማረጋገጫው አንደኛው መንገድ እንጂ ብቻውን የትምህርት ጥራት ሊያመጣ አይችልም፡፡
የመውጫ ፈተናው ተመራቂዎች በተማሩበት ሙያ፤ ዘመኑ የሚጠይቀውን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ገንብተው ስለመውጣታቸው የሚመዝን መሆኑንም ነው ዶክተር ሳሙኤል የተናገሩት፡፡
ባለዲግሪ ዋጋው አይታወቅም፡፡ ገበያው የሚለይበት አካሄድ የለውም፡፡ ዲግሪ በያዙ ተመራቂዎች መካከል በብቃት የሙያውን ምሉዕነት ተላብሶ የተመረቀው የትኛው እንደሆነ መመዘኛው የሚያረጋግጥ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡
‹‹ሁሉም ዲግሪ አንድ አይነት ሆኖ አይታሰብም፡፡ ራሱ ለሚማረውም፣ የቤት ስራ እየተሰራለት የሚመረቀውም ባለዲግሪ ነው፡፡ ለሁሉም እኩል ዋጋ ሰጥቶ ወደ ገበያው መቀላቀል ተገቢ አይደለም›› ሲሉ ዶክተር ሳሙኤል ተናግረዋል፡፡ በተለመደው አሰራር ቢቀጥል ከትምህርት ጥራት በላይ በኢኮኖሚው ኢ-ፍትሃዊነት እንዲነግስ ዕድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡
ምዘናው የሚሰጠው በመጀመሪያ ዲግሪ ላይ ብቻ መሆኑን፣ ትግበራው አገራዊ ፖሊሲ እንደመሆኑ በግል፣ በመንግስትም በየትኛውም ተቋም የሚማር ዲግሪውን የሚያገኘው ምዘናውን ካለፈ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ፈተናው የሚዘጋጅበት፣ የሚያዝበትና የሚሰራጭበት ስርዓት ከሰው ንክኪ ነጻ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት ዴኤታው፤ ለምዘናው የመጀመሪያ ዲግሪ የሚመረቁትን በዓመት ከ150 እስከ 180 ሺ ማስተናገድ የሚችል አቅም መኖሩን ተናግረዋል፡፡
የሙያ ማሕበራት አቅማቸው ሲጎለብት የሙያ ፈተና ይሰጣሉ፣ የመውጫ ፈተና ስራን ከመንግስት ላይ እንደሚወስዱም ነው የጠቆሙት፡፡
ሂደቱን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ግልጸኝነቱ የተጠበቀ ለማድረግ እየተሰራበት መሆኑን ጠቁመው፤ ትምህርቶቹን የሚያዘጋጁ ተቋማትና መምህራን ዝግጅት ስራዎች እስከ ግንቦት 2015 ዓ.ም ይሰራሉ ብለዋል፡፡
መምህራንን በተለያዩ አማራጮች የትምህርት ደረጃቸውንና የመመራመር አቅማቸውን እንዲያሳድጉና የተለያዩ የማስተማር ሥነ ዘዴዎችንና ክህሎት ስልጠና እንዲወስዱ እንደሚደረግም ጠቁመዋል፡፡
ተማሪዎቹ ብቁ ሆነው መውጣታቸውን ግብ አድርገው መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተልዕኮና በትኩረት እንዲለዩ ተደርጓል፡፡
የመጀመሪያ ዲግሪ ቆይታ ዘመን ወደ አራት ዓመታት እንዲያድግ ተደርጓል፡፡ ሂደቱ ተማሪዎቹ የከፍተኛ ትምህርት አውድን ተገንዝበው የሚፈልጉትን፣ መክሊታቸውንና አቅማቸውን ለይተው ማሳካት የሚችሉትን የትምህርት መርሃ ግብር መርጠው እንዲገቡ እንደሚያስችላቸውም አብራርተዋል፡፡
ተማሪዎች ሲገቡ እንጂ ለምን ወውጫ ላይ ይፈተናሉ የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ቢሆንም ወደ ዩኒቨርሲቲ እያስገባን ያለነው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ተፈትነው መሆኑን መዘንጋት እንደማይገባ ገልጸው፤የመውጫ ፈተናውም ቢሆን፤ ዩኒቨርሲቲ ተምሮ ብቁ ሆኗል የሚለውን እንደማይገልጽም ነው ዶክተር ሳሙኤል የተናገሩት፡፡
የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ 1152/2011 የመውጫ ፈተና ሊሰጥ እንደሚችል በግልጽ አስቀምጧል፡፡ የሪፎም አካል ነው፣ የሪፎም አጀንዳን መንግስት የሚመራው እንደመሆኑ ሂደቱን ትምህርት ሚኒስቴር መንግስትን ወክሎ መስራቱ የስልጣን ሽሚያም፣ መጣረስም እንደሌለውም አመልክተዋል፡፡

የባሕር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 325 ሰልጣኞች አስመርቋል።
ኮሌጁ በነርሲንግ፣ በፋርማሲ፣ በኅብረተሰብ ጤና ሳይንስ፣ በላቦራቶሪ፣ በራዲዮግራፊ እና በጤና ኤክስቴንሽን በደረጃ አራት ያሰለጠናቸውን 325 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡
በ1964 ዓ.ም ማስተማር የጀመረው የባሕር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፤ ዘንድሮ ለ50ኛ ጊዜ ነው ሰልጣኞቹን ያስመረቀው፡፡
ተቋሙ እስካሁን ከ9 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ማስመረቁን የኮሌጁ አካዳሚክ ምክትል ዲን ምንይችል ገነት ገልጸዋል።
ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ኮሌጁ በነርሲንግ፣ በፋርማሲ፣ በኅብረተሰብ ጤና ሳይንስ፣ በላቦራቶሪ፣ በራዲዮግራፊ እና በጤና ኤክስቴንሽን በደረጃ አራት ያሰለጠናቸውን 325 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡
በ1964 ዓ.ም ማስተማር የጀመረው የባሕር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፤ ዘንድሮ ለ50ኛ ጊዜ ነው ሰልጣኞቹን ያስመረቀው፡፡
ተቋሙ እስካሁን ከ9 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ማስመረቁን የኮሌጁ አካዳሚክ ምክትል ዲን ምንይችል ገነት ገልጸዋል።
ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ArsiUniversity
የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል ከአሰላ ከተማ የተመረጡ 50 የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ማሰልጠን ጀምሯል።
ተማሪዎቹ ለፈጠራ ተነሳሽነት ያላቸው እና በትምህርት ደረጃቸው እንዲሁም በሳይንስ የትምህርት አይነቶች ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት የተመረጡ ናቸው።
ተማሪዎቹ የሚሰጣቸው ስልጠና የፈጠራ ክህሎታቸውን ለማጎልበትና የሚማሩትን በተግባር በመሞክር ወደ ፈጠራ ሥራ እንዲቀይሩ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡