አጉልዞ ጥያቄ
3.62K subscribers
2.4K photos
28 videos
391 links
ይህ ቻናል በወለጋ አንገር ጉትንና በዙሪያው ለሚገኙ ህዝቦች የሚወያዩበት፣ መረጃ የሚለዋወጡበት እንድሆን ታስቦ የተከፈተ ህዝባዊ ቻናል በመሆኑ በሓላፊነት ስሜን፣ በሰከነ መንገድ ለህዝባችን ሠላም፣ ፍቅር፣ አንድነት እና መቻቻል ተግቶ ይሰራል።
Download Telegram
የዛሬውን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ፣ ለኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ለዶክተር አብይ አህመድ የተፃፈ መልዕክት ነው።

ይነበብ👇👇👇👇

ዛሬ ላይ ይህንን አጭር፣ ግልጽ፣ እውነታና እርሰዎንና አስተዳደረዎን በደንብ አድርጎ የሚፈትሹበት መልዕክት፣ በስራ ብዛት፣ ወይ እረፍት እጦትና ወይም በሌላ ምክንያት ወይ በእርሰዎ በኩል፣ ወይ ደግሞ በአማካሪዎቹ በኩል፣ ወይ ደግሞ የሚድያ መልዕክት አስተዳደር በኩል ተነቦ ችላ ብለውት ሊሆን ይችላል!! ነገር ግን አንድ ቀን እርሰዎም ስህተተዎን መመዘኛ ጊዜ ሲያገኙ፣ ሊቆላጩበት ይችላል። ስለዚህ ቢችሉ፥ ወደተግባር ለመቀየር በሚቻልበት መንገድ ጊዜ ሳያጠፉ ቢያርሙና ቢሰሩበት ያተርፉበታል።

በየት በኩል ሰላም ይምጣ ክብርነተዎ!! እነሆ ህዝቡ በተደጋጋሚ ሰላም ፈላጊ ብቻ ሳይሆን፣ ሰላም ወዳድ መሆኑን አረጋግጧል። እስኪ ሰላም በእርሰዎ የአስተዳደር ዘመን ቃል ከመሆን የዘለለ ምን ተሰርቷል!? የእርስዎን መልካም የኢትዮጵያዊነት የሠላም፣ የእድገት እና የአንድነት ንግግረዎትን በመስማት ስንቱ፣ በካድሬዎችዎ አማካኝነት የመከራ ሲሳይ ሆኖ ቀረ!? ስንቱ ንግግረዎትን አምኖ ለእስራት፣ ለመሰደድ፣ ለቅጣት...... ወዘተ ተዳረገ!?

እርሰዎ በአስተዳደር ዘመነዎ ማንም ተሳዳጅ!" ማንም ተሳዳጅ እንደማይሆን ነግረውን ነበር። ነገር ግን እስከ በወለጋ ያለውን ማህበረሰብ ስንቱ ቤት፣ንብቱንና ቤተሰቡን ገብሮ ተሳዶ በየሜዳው ቀረ?! ይሔንን ሐቅ ለአመታት ከዛሬ ነገ የተሻለ ነገር ይመጣል ብሎ በማሰብ በየመጠለያጣቢያዎቹ፣ በየጎዳናውና በየበረንዳው ከቀያቸው ወጥተው እንደቀሩ አያውቁምን እናም ክብርነተዎ!" እርሰዎ ምክር፣ ሐሳብ፣ ጥቆማና አስተያየት አይወዱም። አይሰሙም። የሁሉም ነገር ፈላጭ ቆራጭ አዋቂ ነዎት። የተሰማንን፣ ያየነውንና በመሬት ያለውን ሐቅ ስንነግረዎት ከመመለስ፣ ከማረም ይልቅ አሳዶ ማሰርን ነው የሚመርጡት። ስለዚህ በቃ ከአቅማችን በላይ ሲሆን ፈራነዎት። ሰጋን። ተሸማቀቅን። በሆዳችን ብቻ ማጉረምረም፣ በከንፈራችን መምጠጥ ሆነ ስራችን።

እርሰዎ የዘመናት የህዝብ ጥያቄዎችን በቁርጠኝነት ለመመለስ በአስተዳደረዎ ዝግጁ መሆኑን በአደባባይ ሲነግሩን አምነን፣ ወንበረዎን ለማጽናትና በሒደት ጥያቄያችንን በሠላማዊ መንገድ፣ በሰለጠነ፣ በበሰለና ሁላችንንም አሸናፊ በሚያደርግ መንገድ፣ እኛም የልዩ ዞንነት ጥያቄ አነሳን። ይህ ጥያቄ ለብጥብጥ፣ ለግጭት የሚዳርግ አይደለም። መንግስትዎ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ዝግጁ ቢሆን ኖሮ፣ እኛን እንደችግር ፈጣሪ፣ እንደግጭት ቀስቃሽ አድርገው አይናገሩም ነበር።

ክብርነተዎ የእርሰዎ አስተዳደር ካድሬዎች የጥያቄውን መነሻና መዳረሻ ሊያሳጣቸው ከሚችለው ስልጣንና ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን በማሰብ፣ የኦሮሞን ህዝብ በሐሰት የልዩ ዞንነት ጥያቄ የሚያነሱት የኦሮሞን መሬት ቆርሶ ለመውሰድ በመሻት፣ ነፍጠኞች ሊወሯችሁ ነው!" በማለት ለግጭትና ለቁርሾ መነሻ ተጠቅመውበታል። እርሰዎም ይህንን ያውቃሉ። ዝምታን የመረጡት ጥያቄው አግባብነት ያለው በህግና በህግ ብቻ የሚፈታ መሆኑን እያወቁ፣ በሰላማዊ መንገድ በመነጋገር ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ፣ እንድባባስ ፈቅደዋል። ክብርነተዎ በዚህ ገፅ ምክንያት ስንቱ ታስረዋል፣ ተደብድበዋል፣ ተሰደዋል። ነገር ግን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለውን ጥያቄ ይህንን ሁሉ ነገር በመፈጸም ሐሳቡን ማጥፋት አይቻልም።

ክብርነተዎ!! በወለጋ ከኦነግ ሸኔ እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ታጥቀው፣ ሰልጥነው በህጋዊ አደረጃጀት እርሰዎ እውቅና በሰጡበት የሚኒሻ አደረጃጀት አፍርሰው፣ ገሚሱ ታስሮ፣ ገሚሱ በገንዘቡ የገዛውን ጠበንጃ ተቀምቶም ተሳዶም። 85% በላይ የአማራ ህዝብ ባለበት አከባቢ ከአንድ ብሔር ብቻ ሰልጥኖ ታጥቆ፣ ሌላው ከምንም ነገር ተገልሎና ተገፍቶ፣ እያወቁ በችልታ ዝምታን መርጠው ተቀምጠው፣ ህዝቡ ግን እንድህ መደረጉ ምንም ሰላም እንደማያመጣና እንደውም ለበለጠ መኮራረፍና ስጋት የሚዳርግ መሆኑን በየመድረኮቹ የኦሮሞ ወንድሞቻችን እየተናገሩ፣ በየጊዜው ግን ሰላም ሰላም በማለት ይውላሉ። እርሰዎ ከሁሉም ወገን ተዋቅሮ ሚኒሻኳን ቢኖር ለእርሰዎ መንግስት ምን ስጋት ይፈጥርብዎታል⁈

ክብርነተዎ!! አንድ ነገር አይተው ዝምታን መርጠዋል። እርሰዎ በፌስቡክ ገፀዎ በተቻለዎት መጠን በሶስት ቋንቋ መልዕክተዎን ለህዝቡ በሚረዱበት መንገድ ያስተላልፋሉ። ከክልሉ ጀምሮ የዞን፣ የወረዳ፣ የከተማ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን የፌስቡክ ገፅች ግን በእልህ በኦሮምኛ ቋንቋ ብቻ ያስተላልፋሉ። በእነዚህ በተጠቀሱት ሁሉ በርካታ አማርኛ ተናጋሪ በርካቶች ናቸው። አማርኛ የሐገራችን የስራ ቋንቋ ነው። ሌሎች በክልሉ የሚገኙ የኢትዮጵያ ብሔርብሔረሰቦችም አብዛኞቹ አማርኛ ተናጋሪዎች ናቸው። እነዚህ የመንግስትና የህዝብ የስራ ሐላፊነት ያላቸው የፌስቡክ ገፆች ግን በኦሮምኛ ቋንቋ ብቻ በመግለፅ ሌላውን አግልለዋል። እርስዎ ይሔን እንዴት ይገመግሙታል በጉዳዩ ዙሪያ መልስና ማስጠንቀቂያ ሰጥተውስ ያውቃሉ

እናም ሰላምን ለማምጣት ከእርሰዎና ከአስተዳደረዎት ፍቃድ ባለመኖሩ እንጂ፤ ትናንትም፣ ዛሬም ወደፊትም ህዝቡ ሰላም ወዳድና አብሮ መኖርን፣ ተካፍሎ መብላትን፣ መረዳዳትንና መተዛዘንን ባህሉ፣ እምነቱ ያደረገ ድንቅ ህዝብ ነው። ስለሰላም ህዝቡ ከእርሰዎና ከአስተዳደረዎ ካድሪዎት ስብከትን አይፈልግም። የኖሩበት በመሆኑ ፍቃደኝነተዎን እንደግለሰብ ሳይሆን፣ እንደመንግስት አስበው ዛሬውኑ በሁሉም ጎራ ያሉት ተቀራርበው እንድነጋገሩ እንድወያዩ በቀጥታ ስም እየጠሩ በዝርዝር ቀነገደብ ሰጥተው ጥሪ በማድረግ አቀራርቡ። ህዝቡ ከተቀራረበ፣ ከተነጋገሩ የሐገራችን ሰላም ለመመለስ የአንድ ጀንበር ጊዜ አይፈጅም ነበር። እናም ያስቡበት።

ክብርነተዎ!! የእርሰዎ ከክልሉ ጀምሮ እስከቀበሌ የዞንና የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ፥ ይፈትሻቸው። የሰውን ሞት በውሸት ሪፖርት ለመደበቅ ቢሞክሩም፣ የሰው ሞት ዛሬም ድረስ አልቆመም። ዛሬስ በምን ሊደብቁት ይችላሉ!? ሁላችንም በየተወለድንበት፣ በየአከባቢዎቻችን ያየናቸውን የታዘብናቸውን፣ እውነታዎች ስንገልጽ፣ እያባሉን፣ እያበጣበጡን፣ እያጋጩን ነው፣ በማለት የራሳቸውን ድክመት ለሌሎች ለማላከክ ይሞክራሉ። ነገር ግን ሁሉም ነገር ከህዝብ የተደበቀ አይደለም። ቀርበው ያነጋግሩ። በአሁኑ ሰዓት ህዝቡ ለዳግም ረሐብና ስደት እየተዳረገ ነው። ክብርነተዎ ይህንን መልዕክት የምጽፈው፥ ለአንድ ብሔር ወግኜ አይደለም። ችግሩ የጋራ በመሆኑ፣ እንደህዝብ በወለጋ የገጠመንን ነው። ስለዚህ ወደአንድ ወገን አድልቼ እንዳልፃፍኩ በዚሁ አጋጣሚ ላስታውሰዎት።

እናም ህዝቡ ሊያሳዝነዎት ይገባል። ምላሽ ሊሰጡት ይገባል። ካቢኔዎትን ሊፈትሿቸውም ይገባል።

አጉልዞ ጥያቄ ነኝ ከወለጋ
ህዳር 05-2017ዓ.ም
ተጠባቂው የዛሬ ምሽት የቦክስ ፍልሚያ!!

ሕዳር 6፣ 2017ዓ.ም። ዕለተ-አርብ (ጁመዓ)
[አጉልዞ_ጥያቄ]

ከዚህ የቦክስ ፍልሚያ ምን ልንማር እንችላለን የዚህ ቦክስ ግጥሚያ እኛን ለማዝናናት ብቻ አይደለም ከአመት ጀምሮ ቀጠሮ የተያዘለት። እንድንማርበት ነው። የዛሬውን የቦክስ ውድድር ከወድሁ መገመት እንደሚቻለው፣ በቦክስ ፌደሬሽን ህግ መሠረት የ58ዓመት ግለሰብ ከ27 ዓመት ወጣት ፕሮፌሽናል ቦክሰኛ ጋር ግጥሚያ የማድረግ ህግ የለም። ነገር ግን ወጣቱ ፕሮፌሽናል ቦክሰኛ #ጄክ ጆሴፍ ፖል ዛሬ ለሱ እዚህ እነ #ማይክል_ታይሰን አርዓያ ነበሩ። ይህም ማለት በወቅቱ ለአእምሯችን መዝናናትንና ዘመን ተሻጋሪ ተጨባጭ ስራዎችን በጊዜው ያበረከቱልንን ግለሰቦችን ጊዜ ጣላቸው፣ አረጁ ወደቁ ብለን እንዳንዘነጋቸውና ለኛ እዚህ መድረስ አስተዋጽኦቸው ቀላል አለመሆኑን ለማስታወስና ለማክበር፣ ለመዘከር ነው።

ዛሬ በሚካሄደው የወጣቱ ቦክሰኛና አንጋፋው ስመጠሩ ማይክል ታይሰን ውድድር ላይ በእርግጠኝነት ወጣቱ ፕሮፌሽናል ጄክ ጆሴፍ ፖል በማይክል ታይሰን በተሰነዘረበት ቦክስ ሲዘረርና ሲሸነፍ እናያለን። ምክንያቱም ዋናው አላማ ታላቅን ማክበርና በእድሜያቸው ምክንያት እስፖርት እንደሌላው የሚያረጅና የሚደበዝዝ አለመሆኑን ለማሳየትና ለማስተማር ነው፥ ለአንድ አመት ያህል ዛሬ ለምናየው የቦክስ ውድድር ዝግጅት (ሾው) ረጅም ጊዜ ተሰቶት እንድንማርበትና ታላላቆቻችን ያበረከቱትን የማክበርና የመጠበቅ ልምምድ እንድኖረን እንድንማር ዝግጅት ማድረግ የተፈለገው።

ስለሆነም ይሔንን አዝናኝና አስተማሪ የቦክስ ውድድር ወደ በሐገራችን አምጥተን ስንመለከተው፤ አንተ በሰዎች መልካም ስራና ተግባር በመደሰት ለተተኪው ትውልድ ሳይሸራረፍና ሳይጓደል፣ ከነሙሉ ክብሩ እንድቀመጥ፣ የሰው የሆነን ስራና ዝና እንድሁም ተፈጥሯዊ ሐብት ተሽቀዳድሞና ባለቤቱን ክብሩንና መልካም ስሙን በመጥፎ አንስቶ ለራስ ለመውሰድ መሞከር የነበረውን ልምምድ አቁመን፣ ወደቦታውና ወደትውልድ ለማስተላለፍ መስራት ይኖርብናል ማለት ነው።

ያንተ ያልሆነን ስምና ዝና በቲፎዞ ብዛትና በሐሰት ውዥንብር ከእውነት ጋር በፍጹም ከማይቀራረቡ፣ የውሸት ትርክቶችንና ማደናገሪያዎች ለመደበቅና የሌላውን ስራና ስም ለመውሰድ መሞከር፥ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር፥ መጋለጡና በዋሸኻቸው ህዝቦች፣ ማህበረሰብና ግለሰቦች ፊት መዋረድህ አይቀርም። ምክንያቱም አንተ የወሰድከው፣ የራስህ ለማድረግ የሞከርከው የሰውን ስራና ተፈጥሯዊ ሐብት እንጂ፤ የራስህ ባለመሆኑ ነውና ከዚህ ውድድር ትማሩበት ዘንድ በቀጥታ ስርጭት በተቻለን መጠን ለማስተላልፋለን።

ታላቅን ማክበር፣ መዘከርና መታዘዝን ባህላችን እናድርግ!! 🙏🙏🙏🙏

አጠቃላይ የሁለቱ ዝርዝር ጉዳዮች ይህንን ይመስላል👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የ58 ዓመቱ ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ከ27 ዓመቱ ፕሮፌሽናል ቦክሰኛ ጄክ ጆሴፍ ፖል ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ ዛሬ ምሽት በአሜሪካ ቴክሳስ አርሊንግተን ይካሄዳል፡፡

ከዓመታት በፊት ቀጠሮ በተያዘለት ፍልሚያ የዓለም የቦክስ ባለታሪኩ ማይክ ታይሰን እና በ1997 ማይክ ታይሰን ልደቱን ካከበረለት ፕሮፌሽናል ቦክሰኛ እና ዩቲዩበር ጄክ ጆሴፍ ፖል ጋር ይደረጋል፡፡

ከውድድሩ አስቀድሞው አንጋፋው ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን “ታይሰን አላረጀም አሁንም ጠንካራ ቡጢውን ተጋጣሚ ላይ ማሳረፍ የሚችል አቅም አለው” ሲል ስለእራሱ ተናግሯል፡፡

የቦክስ ፍልሚያውን የአሜሪካው ኔትፍሊክስ የስርጭት ማዕከል በቀጥታ የሚያስተላልፈው ሲሆን ከ280 ሚሊየን በላይ ሰዎች ይመለከቱታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምሽት 5 ሰዓት ላይ በቴክሳስ አርሊንግተን ኤቲ ኤንድ ቲ ስታዲየም የሚደረገውን ፍልሚያ ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች ስታዲየም ገብተው ይመለከቱታል ተብሎ እንደሚጠበቅ አዘጋጅ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

የዓለማችን የምንጊዜም ታላቁ ቦክሰኛ ማይክል ጄራርድ ታይሰን በፈረንጆቹ ከ1985 እስከ 2005 ባደረጋቸው 56 ፕሮፌሽናል ግጥሚያዎች በ50ዎቹ ድል ሲቀዳጅ በ6ቱ ብቻ ተሸንፏል፡፡

“አይበገሬው”፣ “ብረቱ ማይክ” እና “አውሬው” በሚሉ ቅጽል ስሞች የሚጠራው ቡጢኛ ከድሎቹ ውስጥ 44ቱን ያስመዘገበው በዝረራ አሸንፎ ነው፡፡

ከማይክ ታይሰን ጋር የሚፋለመው ወጣቱ ቦክሰኛ ጆሴፍ ፖል 10 ፕሮፌሽናል ውድድሮችን አድርጎ ዘጠኙን ሲያሸንፍ በአንዱ ብቻ ተሸንፏል፡፡
"ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው!" አንተ/ቺ ዛሬ ላይ ሆነህ፣ ለቀጣዩ የሆነ ነገር አስበህ ይሆናል። ነገር ግን ሐሳብህንና እቅድህን የሚያሳካውም የሚያቋርጠውም ፈጣሪ ብቻ ነው። ከምንም ነገር በላይ ደግሞ ጤና (አፊያ) ይቀድማል። ደግሞም የልጅ የጤና እክል የገጠመው ሰው ከገጠመህ፥ እውነቱን ልንገርህ፥ የምር አሳዛኝ ነው። ወንድሜ አግዘው። እህቴ አግዣቸው። አጅሩን ከአላህ (ከፈጣሪ) ታገኙታላችሁ🙏🙏🙏🙏

ወንድማችን የ 3 ወር ልጁ ታማበት ለማሳከም እጅ ያጠረው አባት😭 ነው😥😥😥
━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━
እንተባበር፣ እንደጋገፍ፣ የበኩላችንን እናበርክት

ፉአድ ቢላል እባላለው ልጄ አቲካ ፉአድ ገና የ3 ወር ልጅ ስትሆን ውስብስብ በሆነ የልብ ህመም (CHD) ትሰቃያለች። CHD ልብ በማህፀን ውስጥ በትክክል ካልዳበረ የልብ ጉድለቶች ስብስብ ነው። ኬዙ ከብዙ ህፃና አንዱ ላይ የሚከሰት ሲሆን የልብ ክፍተት እና የልብ ቦታ መቀያየር እና የልብ ቧንቧ ጥበትን ያካትታል እቺ የምታይዋት ልጄ በዚህ የልብ ህመም እየተሰቃየች ትገኛለች ሴት ልጄን ለማዳን 20 አሰከ 30 ሺህ ዶላር ያስፈልገኛል በእኛ ማለትም በኢትዮጵያ 3 ወይም 4 ሚሊየን ገደማ ማሰባሰብ አለብኝ። ልጄ አቲካ የሚያስፈልጋት የቀዶ ጥገና ሕክምናዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ስለማይገኙ ለቀዶ ጥገና ወደ ህንድ ወይ ቱርክ መሄድ አለብን። ቀዶ ጥገናው ካልተሳካ, የልብ ንቅለ ተከላ ያስፈልጋታል. ገቢው ለህክምና ቪዛ፣ፓስፖርት እና የቀዶ ጥገና ወጭ ለመድሀኒት ውጪ ለሶስት ሳምንታት ቆይታ ይውላል ይሄን ያህል ወጪ ለኔም ሆነ ለቤተሰቤ ከአቅም በላይ አና አዳገች ስለሆነ የእርዳታ እጃችሁን እንድዘረጉልኝ ስል በፈጣሪ ስም እማፀናቹሀለው
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000657672215
ፉአድ ቢላል አህመድ
አቢሲኒያ ባንክ
56374701
ፉአድ ቢላል አህመድ
📲0986555658
📲0923504468
https://gofund.me/6cd42e94