ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ
3.04K subscribers
188 photos
80 videos
30 files
807 links
https://t.me/mukamil

የዪቲዩብ ቻናሌን ሰብስክራይብ ያድርጉ👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@Mukamil123
Download Telegram
አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም
ሙሥሊም እኅትና ወንድሞቼ ዒድ ሙባረክ እንኳን አደረሳችሁ!
ተቀበል አሏሁ ሚና ወሚንኩም🌴
መጦም አይችሉምን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው

የረመዳንን ወር ጦም መጦም ከእሥልምና መሰረቶች ውስጥ አንዱ ነው።
አምላካችን አሏህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጦም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡
[2:183]

ይህም የጦም ወር የረመዳን ወር ነው።

شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖ وَمَن كَانَ
مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَر
 (እንድትጦሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጡመው፡፡ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጦም አለበት፡፡
[2:185]

ይህን የረመዳን ወር ጦምን መጦም በሁሉም ሙሥሊም ላይ ግዴታ ነው ዑዝር ካለው ሰው በስተቀር ዑዝር ያለው ሰው ረመዳን ላይ ያልጦማቸውን ቀኖች ቆጥሮ ከረመዳን ቦኋላ መጦም አለበት።

ይህ ሆኖ ሳለ አንዳንድ ጥራዝ ነጠቅ ወገኖቻችን በእሥልምና ሴቶች ከባሎቻቸው ፍቃድ ውጭ የረመዳን ጦምን መጦም አይችሉም ብሎ ይቀጣጥፋሉ።

ለዚህ ቅጥፈታቸው የሚያቀርቡት ሐዲስ ቦኻሪ ላይ ያለን ያልተሟላ ዘገባን በመጥቀስ ነው።

لا تَصُومُ الْمَرْأَةُ وَبَعْلُهَا شَاهِدٌ إِلا بِإِذْنِهِ
ሚስት ቦሏ እያለ ከእርሱ ፍቃድ ውጭ መጦም አትችልም።
[ቦኻሪ 5192]

ይህ ሐዲስ አንድም ነቢዩﷺ የተናገሩት ሙሉ ቃላቸውን አልያዘም ሆኖም ግን በዚህ ሐዲስ ላይ የትኛው ሀይለ ቃል ነው ሚስት ከባሏ ፍቃድ ውጭ ግዴታ ጦምን መጦም አትችልም የሚለው?? ቅጥፈት አይሰለቻችሁም??

ቅሉ ግን ሐዲሱ የሚናገረው ስለ "ሱና" ጦሞች እንጂ ስለ ግዴታው የረመዳን ወር ጦምን አይደለም።

ከላይ ያለውን ሐዲስ በተሟላ መልኩ ቲርሚዚ ዘግቦታል።
የተሟላው ሐዲስ እነሆ

  أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ تَصُومُ الْمَرْأَةُ وَزَوْجُهَا شَاهِدٌ يَوْمًا مِنْ غَيْرِ شَهْرِ رَمَضَانَ إِلاَّ بِإِذْنِهِ ‏
"‏
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦"ነቢዩ"ﷺ እንዲህ አሉ፦ "አንዲት ሴት ከረመዷን ወር ውጪ ባሏ እያለ ከእርሱ ፈቃድ በስተቀር አንድ ቀን መጦም አትችልም"።
[ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 101]

ምን ትፈልጋለህ?? የሱና ጦም መጦም ምንዳን የሚያስገኝ ሥራ ቢሆንም የሱና ጦም አለመጦም ግን አያስጠይቅም።

ሚስቶች በባሎቻቸው ላይ መብት እንዳላቸው ሁሉ ለባሎችም በሚስቶቻቸው ላይ መብት አላቸው።
ለምሳሌ ሚስት ግዴታ ያልሆነውን የሱና ጦም ስትጾም ቦሏን ሳታስፈቅድ ከሆነ ባሏ ግን ያንን የሱና ጦም የማይጦም ከሆነ ምናልባት እርሷ ጦም ላይ ኹና ባሏ ግንኙነት ማድረግ ልፈልግ ይችላል ስለዚህ ሚስት የሱና ጦም መጦም በፈለገች ጊዜ ባሏን ማስፈቀድ አለባት።

በጣም የሚገርመው ደግሞ ሚስት የሱና ጦም መጦም ፈልጋ ባሏን ብታስፈቅደውና ባሏ ባይፈቅድላት ራሱ ሦስት አጅር (ምንዳ) ታገኛለች!

:-አንድም ጦሙን ለመጦም በማሰቧ እንደጦመች ይቆጠርላታ።
ስራ የሚመዘነው "በኒያ" ነውና።
ቦኻሪ መጽሐፍ 1,ሐዲስ 1

:-ሁለትም ባሏን እሺ ብላ በመታዘዟ ምንዳን ታገኛለች እንደውም ባሏን እሺ ብላ በመታዘዟ ምክንያት የገነት በሮች ተከፍቶላት በፈለግሽው በር ግቢ ትባላለች።
[ሙስነድ አሕመድ 1661]
(ሰሒሑል ጃሚዕ 660]

:-ሦስትም ከሀላል ባሏ ጋር ግበረ ሥጋ ግንኙነት በማድረጋቸው ምክንያት "ምንዳን" ያገኛሉ።
[ኢማሙ ሙሥሊም 1006 ።]


ግዴታ ያልሆነውን ባይጦሙት ቅጣት የሌለበትን የሱና ጦም ለመጦ ባሏን ማስፈድ ነው ጉዳት ወይስ ባሏን እሺ ብላ በመታዘዟ ምክንያት ከላይ የጠቀስናቸውን ሁሉ ትሩፋት ማግኘት ነው የሚሻለው??

ወገኖቼ ሆይ እሥልምናን እና ሙሥሊሙን ለመተቸትና ለማብጠልጠል ቀንና ለሊት ከምትፍጨረጨሩ እሥልምናን በሰከነ መንፈስ አጥንታችሁ ወደዚህ ብርሃን ወደ ሆነ እምነት እንድትመጡ
አሏህ ጤነኛ አዕምሮ ይስጣችሁ።

ولله اعلم


ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12
🔴👉እነዚያ ከአላህ ዉጭ የምትጠሯቼዉ  ዝንብን መፍጠር አይችሉም እንደዉ ቢሰባሰቡምኳ ::

قال الإمام ابن القيم - رحمه الله تبارك و تعالىٰ - :

قَـالَ تَعـالىٰ :
﴿يا أَيُّهَا النّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌ فَاستَمِعوا لَهُ إِنَّ الَّذينَ تَدعونَ مِن دونِ اللَّهِ لَن يَخلُقوا ذُبابًا وَلَوِ اجتَمَعوا لَهُ وَإِن يَسلُبهُمُ الذُّبابُ شَيئًا لا يَستَنقِذوهُ مِنهُ ضَعُفَ الطّالِبُ وَالمَطلوبُ﴾.

⬅️ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌حقيق على كل عبد أن يستمع قلبه لهذا المثل ويتدبره حق تدبره فإنه يقطع مواد الشرك من قلبه .

⬅️وهذا المثل من أبلغ ما أنزله الله سبحانه في بطلان الشرك وتجهيل أهله، وتقبيح عقولهم .

‌‌‏📚 بدائع التفسير  (٢ / ٢٢١)】



t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
“እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤”
— ዕብራውያን 5፥7


የዝንብ እግር ይዛ በር ክፈቱልኝ አለች አሉ።

ራሱን ማዳን ተስኖት አምላኬ ሆይ እባክህ ከሞት አድነኝ እያለ አቤቱታ ሲያቀርብ የነበረውን ኢየሱስን ሺህ ጊዜ ኢየሱስ ያድናል ብትል የሰው መሳለቂያ ትሆን ይሆናል እንጂ ማን ይሰማካል?🙈

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12
የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ

በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 12ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ!

"ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በዱኑል ኢሥላም እና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው።

፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
1.በነገረ ሥላሴ ጥናት"Triadogy"
2.በነገረ ክርስቶስ ጥናት"Christology"
3.በነገረ ማርያም ጥናት"Mariology"
4. በነገረ መላእክት ጥናት"angelology"
5. በነገረ ምስል ጥናት"Iconlogy" ላይ ነው።

፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
1.በአህሉል ኪታብ"People of the Book"
2.በመጽሐፍት"scriptures"
3. በመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation"
4.በመጽሐፍት ልኬት"Standardization"
5. በባይብል ግጭት"Contradiction"
6. በኦሪት"Torah"
7. በወንጌል"Gospel" ላይ ነው።

አባሪ ኮርሶች፦
1. ዐቂዳህ"creed"
2. ሥነ ምግባር"ethics"
3. ሥነ አመክንዮ"logic"
4. ሥነ ልቦና"psychology"
5. ሥነ ቋንቋ"linguistics" ናቸው።

ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ!
ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://t.me/arhmanu
እኅት ሰላም፦ http://t.me/SeuweSe
አኅት ዘሃራ፦ https://t.me/Zhara_mustefa
እኅት አበባ፦ http://t.me/selemtewa

ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ!
ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዘላለም ሕይወት በኢየሱስ ስቅለት አይደለም።😊
ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል ማን ናቸው?
قال أحمدُ بنُ محمَّدِ بنِ حَنبَلٍ رحمه اللهُ: لقيتُ الرِّجالَ، والعُلَماءَ، والفُقَهاءَ، بمكَّةَ والمدينةِ والكوفةِ والبَصرةِ والشَّامِ والثُّغورِ وخُراسان، فرأيتُهم على السُّنَّةِ والجماعةِ، وسألتُ عنها الفُقَهاءَ؟ فكُلٌّ يقولُ: القُرآنُ كلامُ اللهِ، غيرُ مخلوقٍ، منه بدأ، وإليه يعودُ

[📚እኽቲሷሱል ቁርአን 1691]
Audio
ኢሥላም የተማረኩ ሴቶችን አስገድዳችሁ ድፈሩ ይላልን?

ለቀጣፊ ክርስቲያን ወገናችን መልስ

🎙ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12
አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

ያ ጀመዓህ! "የተደበቀው እውነት" የሚለው ስድስተኛው መጽሐፌ በገበያ ላይ ውሏል። "የተደበቀው እውነት" የሚያውጠነጥነው ስለ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት በተውራት እና በኢንጂል ተነግሮ የመጽሐፉ ሰዎች ይህንን እውነት እንዴት እንደደበቁት የሚገልጥ እና የሚያጋልጥ ነው። ዝርዝሩን መጽሐፉ ላይ ያንብቡ እና ለሎች የሂዳያህ ሠበብ እንዲሆን አስነብቡ!

መጽሐፉን መርካርቶ አንዋር መሥጂድ ኢሥላማዊ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ያገኙታል፥ የበለጠ ለመረጃ +251920781016 ዐብዱ ብለው ይደውሉ!

መጽሐፉ ተደራሽነት እንዲኖረው ባለው የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ!

ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
የነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ነቢይነት

ክፍል 4

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው!

وَيَقُولُ الَّذِينَ كَفَرُوا لَسْتَ مُرْسَلًا ۚ قُلْ كَفَىٰ بِاللَّهِ شَهِيدًا بَيْنِي وَبَيْنَكُمْ 
[ ሱረቱ አል- ረዕድ፥ - 43 ]
እነዚያም የካዱት ሰዎች «መልክተኛ አይደለህም» ይላሉ፡፡ «በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በአላህ በቃ በላቸው።

ወዳጄ ሁሌም እንደምለው ስለ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ነቢይነት ለማወቅ በመጀመሪያ እነዚያ በጥላቻ የተሞሉ የውሸት ጓንዳዎች ያጠለቁልህን የሻገተ መነጽርህን አውልቀህ ጣለውና ረጋ ሰከን ባለ ስሜት በጥንቃቄ አጥና! ያኔ እውነቱ ፍንትው ብሎ ታገኘዋለህ።

በክፍል ሦስት ቅኝታችን ቁርአንን ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ከአለማቱ ጌታ ከአላህ ዘንድ የተቀበሉት መሆኑን ቁርአኑንም ከተቀበሉ በኋላ ቁርአን የፈጣሪ ቃል አይደለም የሚሉ ሰዎችን እንግዲያስ ቁርአን የፈጣሪ ቃል ሳይሆን የነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ድርሰት ነው ካላችሁ እስቲ እናንተም የቁርአንን አምሳያው አምጡ ብሎ (ተሐዲ) አቅርቦላቸው ማምጣት አለመቻላቸውን አይተን ነበር።
ይህም የሚያሳየው አንድም ቁርአን እውነተኛ የፈጣሪ ቃል መሆኑን
ቁርአንን የተቀበሉት ነቢይ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) እውነት የፈጣሪ ነቢይ መሆናቸውንና ቁርአን ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ከተሰጣቸው ትላልቅ ተአምራት ዋነኛው መሆኑን ያሳያል።

አንድ ነቢይ ለእውነተኛ ነቢይነቱ እንደ ማስረጃ ሆነው ከሚቀርቡ ነገራቶች ውስጥ አንዱ ተአምር ማሳየት እንደሆነ ይታወቃል።

ነቢዩ ሙሐመድም (ሰዐወ) እውነተኛ የፈጣሪ ነቢይ እንደመሆናቸው የተሰጣቸው ተአምር ቁርአን ብቻ ሳይሆን ብዙ ናቸው።
እስቲ ዛሬ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ከፈጣሪ ዘንድ ከተሰጣቸው ከቁርአን ቀጥሎ ካሉ ትላልቅ  ተአምራት ውስጥ አንዱን እንመልከት።

ነቢያች ነቢይ ሆነው በተነሱበት ጊዜ የቁረይሽ ሰዎች ነቢዩ ሙሐመድን እስቲ አንተ እውነተኛ የአላህ ነቢይ ከሆንክ ተአምር አሳየን አሉት ነቢዩ ሙሐመድም ጨረቃን ለሁለት በመካፈል ትልቅ ተአምር አሳይቷቸዋል።

اقْتَرَبَتِ السَّاعَةُ وَانشَقَّ الْقَمَرُ
(ሱረት አል-ቀመር - 1)
ሰዓቲቱ (የትንሣኤ ቀን) ተቃረበች፤ ጨረቃም ተገመሰ፡፡

أَنَّ أَهْلَ مَكَّةَ سَأَلُوا رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنْ يُرِيَهُمْ آيَةً، فَأَرَاهُمُ انْشِقَاقَ الْقَمَرِ‏.

አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረ.ዐ) እንደተረከው
የመካ ሰዎች የአላህን መልዕክተኛ (ﷺ) ተዓምር እንዲያሳዩአቸው ጠየቁት፣ እሳቸውም ጨረቃን ለሁለት በመክፈል አሳያቸው።

(📚 ቡኻሪ መጽሐፍ 61, ሐዲስ ,141)

በሌላም ዘገባ እንዲህ ተዘግቧል!
ኢብኑ ሙጥዕም ከአባቱ ይዞ
انْشَقَّ الْقَمَرُ عَلَى عَهْدِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم حَتَّى صَارَ فِرْقَتَيْنِ عَلَى هَذَا الْجَبَلِ وَعَلَى هَذَا الْجَبَلِ فَقَالُوا سَحَرَنَا مُحَمَّدٌ فَقَالَ بَعْضُهُمْ لَئِنْ كَانَ سَحَرَنَا مَا يَسْتَطِيعُ أَنْ يَسْحَرَ النَّاسَ كُلَّهُمْ

በነቢዩ ዘመን ጨረቃ በዚህ እና በዚያ ተራራ ላይ ሁለት እስክትሆን ድረስ ተሰንጥቃ ታየች፣ ቁረይሾችም ‟ነቢዩ በእኛ ላይ አስደግሞብን ነው” አሉ፣ ከፊሎቹ ደግሞ ‟በእኛ ላይ አስደግሞብን ከሆነ ሁሉም ሰው ላይ ማስደገም አይቻለውም” አሉ።
(📚ትርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ, 341)

ተጨማሪ ማስረጃ ከፈለክ !
Sahih al-Bukhari, 3868
Sahih al-Bukhari, 4867
Sahih Muslim, 2802
Sahih Muslim, 2803
ወዘተ... ተመልከት

ታላቁ አሊም ኢብኑ ከሲር ይህን ሐዲስ ሲያብራራ እንዲህ ብሏል!

انشقَّ القمرُ بمكةَ حتى صار فرقتَينِ فقال كفارُ قريشٍ لأهلِ مكةَ هذا سحرٌ سحرَكم به ابنُ أبي كبشةَ انظروا  السُّفَّار فإن كانوا رأوا ما رأيتُم فقد صدق وإن كانوا لم يرَوا مثلَ ما رأيتُم فهو سِحرٌ سحركم به قال فسُئل ا السُّفَّارُ قال وقدِموا من كل وِجهةٍ فقالوا رأَينا.

በመካ ጨረቃ ሁለት እስክትሆን ድረስ ተከፈለች፣ የቁረይሽ ካፊሮች ለመካ ነዋሪዎች ይህ ኢብኑ አቢ ከበሻ (ሙሐመድ) ያስደገመባችሁ ድግምት ነው፣ ከውጪ የሚመጡትን ተጓዢዎች ስለ ነገሩ ጠይቁአቸው፣ እናንተ የተመለከችሁን ነገር እነርሱም ከተመለከቱ በእርግጥም እውነት ነው፣ ያልተመለከቱ ከሆነ ደግሞ ድግምት ነው አሏቸው። ከዚያም ከሁሉም አቅጣጫ የመጡትን ተጓዦች ጠየቁ እነርሱም ‟አዎ አይተናል” ብለው መሰከሩ።

(📚አል-ቢዳያ ወኒሃያ ለኢብኒ ከሲር 3/119)

ይህ ክስተት እንዲሁ ተረት ተረት ሳይሆን በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በስጋ ዓይናቸው የተመለከቱት ክስተት ነው።

ወደ ዋናው ነጥቤ ስመለስ አንድ ሐሰተኛ ነቢይ ጨረቃን የሚያክል ግዙፍ ፍጥረት ለሁለት መካፈል ይችላልን?? በጭራሽ አይችልም።
ታዲያ ነቢዩ ሙሐመድ ይህን ማድረግ እንዴት ቻሉ? መልሱን ለራስህ!!


[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[
[[ይቀጥላል,, ኢንሻ አላህ   ]]
[[                                   ]]
[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ
https://t.me/mukamil12
ስላሴ
ABU HANIF ISLAMIC APOLOGETICS CENTER || አቡ ሀኒፍ ዕቅበተ–ኢስላም ማዕከል
◆▮ውይይት▮◆

📌  ሥላሴ የባይብል አስተምህሮ ነውን?!
📌 ሥላሴ ቃሉም ሆነ ቃሉን የወከለው ሐሳብ በባይብል ይገኛልን?!

◍ ወንድም ኢብራሂም
          🆅🆂
◍ ወገናችን ፓስተር አቡከር
إصدار جميع ليالي بن طالب رمضان ١٤٤٥
የአላህ ስጦታ የልብ መስከኛ ፤
➴ማን አለን እንደሱ ለእኛ መዳኛ፤
➴የልብ ሰኪና የሚሰጥ ማከሚያ፤
➴ቁርአን ነዉጂ የሆነን  መለያ፤
ሀቅና ባጢሉን አበጥሮ ማያ፤

=

t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአለም ላይ ያሉ ክርስትያኖች አንድ ፓኪስታናዊ ሙሥሊም ወንድማችንን ኢየሱስ ነህ እያሉ ስላስቸገሩት መልዕክት አለው 😊

የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”
— ማቴዎስ 13፥9

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ
https://t.me/mukamil12
ለአስተዋዮች ብቻ!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
😁!

🦘ጴንጤዎች አምልኮ ላይ ናቸው😁
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መምህር ዘበነ ማርያም እግዚአብሔርን ልጅ ልጄ እያለች እሹሩሩ ማሙ እሹሩሩ እያለች ነው ያሳደገችው እያለ ነው🙈

የፈጣሪ ትግሥቱ ይደንቃል በእውነት😔

سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ
[ ሱረቱ አልሷፍፋት - 159 ]
አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡
Forwarded from ASHRAF COMPARATIVE
የኩፋሮች ባዶነት😁
ዛሬ እግር ጥሎኝ በ ኢንግሊሽኛ ቋንቋ ንጽጽር ወደ ሚያደርጉ ልጆች ጋ ጎራ ብየ ሚጠያየቁትን ማየት ጀመርኩ ብዙም ሳልሔድ ይችን አየኹ፥
ሙስሊም ኹፋሩን ኢየሱስ የቱጋ ነው አምልኩኝ ያለው ብሎ ይጠይቀዋል የዛኔ ሚንተባተበውን ከተንተባተበ በዋለ አላህ የቱ ጋ ነው አምልኩኝ ያለው ብሎ ጠየቀው የኔ ትዝብት እዚህ ጋ ነው ካሁን በፊት የኢትዮጵያ ኹፋሮች ይችን ጥያቄ እራሷን አንስተው ነበር😁 ለካ ሲጠየቅ ሰምተው ነው የጠየቁት በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ ኹፋሮች ጥያቄ እንኳ ፈጥረው መጠየቅ አይችሉም አሳዛኝ ገጠመኝ ነበር።
ለማነኛውም መልሱ እነሆ

إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي
«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡
❮አል ጣሓ ፦ 20:14❯
https://t.me/ashraf_com1
ውይይት
ABU HANIF ISLAMIC APOLOGETICS CENTER || አቡ ሀኒፍ ዕቅበተ–ኢስላም ማዕከል
ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ በባይብል
ዘዳግም 18:18

🎙 ቅዱስ

🎙 ሙከሚል

https://t.me/mukamil12
:-አምላኬ ሞተልኝ ብየ በዓሉን የማከብርለት አምላክ ስለሌለኝ አልሐምዱሊላህ።

:-እኔ የማመልከው አምላክ የማይተኛ የማያንቀላፋ ነው።
[📗 2:255]

የማይደክም ነው።
[2:129]

የማይራብ የማይጠማ ነው።
(📗6:14 ) {📗22:37} {📗51:57}

የማይሞት ሕያው አምላክ ነው።
{📗2:255} {📗3:2} {📗25:58}


وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ ۚ 

:-በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡
[25:58]

አልሐምዱሊላህ! ዓላ ኒዕመተል ኢሥላም😊

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12