Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹
9.29K subscribers
16.8K photos
230 videos
16 files
486 links
This is the official Telegram page of Ministry of Urban and Infrastructure
Download Telegram
ለሁሉም የሚዲያ ተቋማት
ጉዳዩ፡- የሚዲያ ጥቆማ
የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስቴር ከአለም ባንክ እና ከጃፓን መንግስት ጋር በመተባበር ጥራት ያለው የመሠረተ-ልማት ኢንቨስትመንት አተገባበር ዙሪያ ሀገር አቀፍ አውደ ጥናት ከጥቅምት 28-29 ቀን 2016 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ያካሄዳል፡፡
በአውደ ጥናቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ አለም አቀፍ መንግስታዊ ያለሆኑ ድርጅት ተወካዮች፣ የዩኒቨርስቲ ምሁራን፣ በግንባታ መሠረተ ልማት ላይ የተሰማሩ የዘርፉ ተዋናዮች ይሳተፉበታል፡፡
ስለሆነም በተጠቀሰው ቦታና እለት ከጧቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ መርሃ-ግብሩ ስለሚከናወን መረጃውን ለህዝብ ታደርሱልን ዘንድ የዘወትር ትብብራችሁን እንጠይቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በሞባይል ቁጥር 0911850060 ወይም 0920716850 ደውሎ ተጨማሪ መረጃ ማገኘት ይቻላል
👍2
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የፈረንሳይ የልማት ድርጅት (AFD) የሥራ ኃላፊዎችን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ
አዲስ አበባ
ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ/ም (ከመልሚ)

የፈረንሳይ የልማት ድርጅት በሀገራችን ኢትዮጵያ ሀገራዊ የኃይል አቅርቦትን በማስፋፋትና በማጠናከር፣ ታዳሽ ኃይልን በማስፋፋት፣ የከተማ ነዋሪዎችን የኑሮ ሁነታ በማሻሻል፣ የከተማ የቆሻሻ አወጋገድ ስርአትን በማሻሻል፣ የትራንስፖርት እና የቄራ አገልግሎትን በማዘመን፣ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እና የውሃ የንፅህና አጠባበቅ ስራዎችን በገጠራማ የሀገራችን አካባቢዎች እየሰራ ያለ የፈረንሳይ መንግስት የልማት ድርጅት ነው ።


የፈረንሳይ የልማት ድርጅት AFD የኢትዮጵያ ዳይረክተር Mr. Louis-Antoine Souche እና ምክትል ዳይሬክተራቸው Mrs. Sonia Lioret በውይይቱ ወቅት እንዳሉት ከከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር ያለንን የስራ ግንኙነት አጠናክረን መቀጠል እና የከተማ ልማት ዘርፉን በፋይናንስ እና በአቅም ግንባታ መደገፍ እንፈልጋለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የፈረንሳይ የልማት ድርጅት ከ 1997 ጀምሮ ኢትዮጵያ ዘላቂ ኃይልን እና ተጨማሪ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ፕሮጀክቶችን ለማዳበር የምታደርገውን ጥረት በመደገፍ እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በጋራ በመሥራት ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማረጋገጥ ወደ ፊት በሰፊው ለመስራት ጊዜው አሁን እንደሆነ እርግጠኛ መሆናቸውን ልዑካኑ ገልጸዋል።

ክብርት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በውይይቱ ወቅት እንዳሉት የፈረንሳይ መንግሥት ከሀገራችን ኢትዮጵያ ጋር ያለውን የረዥም ጊዜ የሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት እና የልማት ታሪክ በቀጣይ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አምናለሁ በማለት ገልጸዋል፡፡
የፈረንሳይ የልማት ድርጅት (AFD) ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኤጀንሲ ቢኖረውም ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ በሀገሪቱ ለተለያዩ የልማት ስራዎች የፋይናንስ አቅርቦትን በማመቻቸት ሲሰራ ቆይቷል። በተለይ በኢነርጂ፣ በውሃና በከተማ ልማት ዘርፎች ላይ ያተኮረ እንዲሁም ለግሉ ሴክተር ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ ላይ የሚገኝ የልማት ድርጅት በመሆኑ በቃጣይ ይሄው ተጠናክሮ በተለይ የከተማውን ዘርፍ ለመደገፍ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ቃል መግባታቸውን ገልጸዋል።

ሪፖርተር ኮከቤ ቢፍቱ
የካሜራ ባለሙያ ፈዬ ደሜ