Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹
9.97K subscribers
18.7K photos
276 videos
16 files
510 links
This is the official Telegram page of Ministry of Urban and Infrastructure
Download Telegram
የከተሞች ልማታዊ ሴፍትኔት የስራ ፕሮጀክት ያለፉትን አመታት ስራዎች እና 3ኛ ዙር ተጨማሪ በጀትን አስመልክቶ በፕሮጀክቱ ከታቀፉ ሁሉም ከተሞችና ባለድርሻ አካት ጋር  የውይይት መድረክ አካሄደ 

ሐዋሳ፣ መስከረም 11 ቀን፣2019 ዓ.ም (ከመልሚ) á‹¨áŠ¨á‰°áˆžá‰˝ ልማታዊ ሴፍትኔት የስራ ፕሮጀክት ያለፉትን አመታት አፈጻጸምና 3ኛ ዙር ተጨማሪ ፋይናንስ አስመልክቶ በፕሮጀክቱ ከታቀፉ ሁሉም ከተሞችና ባለድርሻ አካት ጋር የጋራ የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡

የሐዋሳ ከተማ ም/ከንቲባ እንጂ.ቸርነት ፍላቴ  በእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸው የሐዋሳ ከተማ እንደሀገር በአዲስ አበባ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ሀገራዊ አቅጣጫ ተግባራዊ ለማድረግ ሌት ተቀን ከባለድርሻ አካላትና ከሕብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት በከተማው ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ለከተማው ለውጥ ከመምጣቱ ባሻገር በዝቅተኛ ኑሮ የሚገኙ ዜጎችን ዘላቂ ኑሮአቸውን በማሻሻል ከተረጅነት ወደ አምራችነት መለወጥ እንደተቻለ ም/ል ከንቲባው ገልጸው በከተሞች ልማታዊ ሴፍትኔት የስራ ፕሮጀክት የተመደበላቸውን በጀት በአግባቡ በመጠቀም በፕሮጀክቱ የታቀፉ ዜጎችን ለዘላቂ ዕድገትና  ለውጥ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በከተማና መሠረተ ለማት ሚኒስቴር የከተሞች ምግብ ዋስትናና ሴፍትኔት ጽ/ቤት ኃላፊ  አቶ ብርሃኑ ተሾመ እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ  በሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች በተመረጡ 88 ከተሞች በፍሐዊነትና በግልጽነት የተለዩ ጾታን፣ ዕድሜን እና አካል ጉዳተኝነትን  ልዪነት ሳይፈጥር ዜጎችን በዘላቂነት ኑሮአቸውን ባማሻሻል ከተረጅነት ወደ አምራችነት እየቀየረ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ ፕሮጀክት እደሀገር ከ3 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች እውቀትን፣ ክህሎትንና የስራ ባህልን በማሳደግ ራሳቸውን ከተረጅነት አውጥተው ቤተሰቦቻውንና ለሌሎች ወጣቶች ዘላቂ የሥራ እድል በመፍጠር የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ እንደሆነ ሀላፊው ተናግረዋል ፡፡ 

ከውይይት መድረኩ በተጨማሪ  በሐዋሳ ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ጉብኝት ተካሂዷል፡፡ በተለይ የኮሪደር ልማት፣ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች፣ የትምህርት ቤት ግንባታዎችን እና መሠል በፕሮጀክቶች ተጎብኝተዋል።

በሌላ በኩል ያለፈውን በጀት ዓመት እንደሀገር በፕሮጀክቱ የተከናወኑ አበይቲ ክንውኖችን አስመልክቶ በተመረጡ ከተሞች ሪፖርት በዝርዝር ቀረቦ ከቤቱ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

መርሃግብሩ ለተከታታይ ቀናት እንደሚቀጥል በመርሃ-ግብሩ ተመልክቷል፡፡
👍5❤4
ከፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ እና ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን፣ በጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኝ እና ታላቅ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት የሆነውን አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታን ዛሬ ይፋ አድርገናል።
‎
‎ ፕሮጀክቱ በሁለቱም ጫፎች ላይ በሚገነቡ የማከማቻ ተርሚናሎች የተደገፈ ሲሆን፤ ይህ ታሪካዊ መሰረተ ልማት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በዳንጎቴ ግሩፕ ጥምረት የሚተገበር ነው።
‎
‎የሎጂስቲክስ ወጭንና መዘግየትን በመቀነስ፣ የኢነርጂ ዋስትናን ያጠናክራል፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ-ጅቡቲ የንግድ መስመርን ፍጥነት እና ዘላቂነትን ያሳድጋል።
‎
‎መሰረተልማቱ ከነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መሾመር ዝርጋታ በላይ፣ የአፍሪካውያንን ኢንቨስትመንት እና በጋራ መልማትን ማዕከል ያደረገ፣ ለዘላቂ እድገት፣ ለቀጣናዊ ትስስር እና ይበልጥ አስተማማኝ ለሆነ የጋራ ኢኮኖሚያዊ እጣ ፈንታ የሚደረግ ሰፊ ኢንቨስትመንት ነው።
❤1⚡1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Together Djibouti, Ethiopia and the Dangote Group will develop a 120-kilometre pipeline
connecting Damerjog to Dewele, with more than one million cubic meters of combined storage capacity at the two ends.
👏2
ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከመስከረም 18/2019 ዓ.ም ጀምሮ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አድርገው መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ያለፉትን የለውጥ ዓመታት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴርን በሚኒስትርነት የመሩት ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ የከተማው ዘርፍ ካለበት ውስብስብ ችግሮች ወጥቶ በሰው ተኮር ስራዎች ላይ እንዲያተኩር እና የከተማው ማሕበረሰብ የልማትና የአገልግሎት ጥያቄ እንዲመለስ፤ መንግስት በተለየ መንገድ ለከተሞች ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ እና የአሰራር ስርአቶች እንዲዘምኑ፤ አሁን ላይ በከተሞች ለመጣው ለውጥና እድገት ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይሉ በመስራት ዘርፉን ለውጠውታል።

ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ብርቱ፣ ባለመልካም ስብዕና፣ ሠለቸኝ ደከመኝ የማይሉ ለሁሉም እናት ለሁሉም የቅርብ እና አድማጭ ናቸው።

ዘርፉን በተሻለ የአመራር ብቃት በመምራት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ቤተሰብ እንዲሁም መላው የከተማ ነዋሪ ያመሠግኖታል በሚሄዱበት ሁሉ መልካም ሁሉ እንዲገጥምዎ ከልብ ይመኛል፡፡

መልካም የሥራ ዘመን!!
❤22🙏5