Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹
9.97K subscribers
18.7K photos
276 videos
16 files
510 links
This is the official Telegram page of Ministry of Urban and Infrastructure
Download Telegram
የከተሞች ልማታዊ ሴፍትኔት የስራ ፕሮጀክት ያለፉትን አመታት ስራዎች እና 3ኛ ዙር ተጨማሪ በጀትን አስመልክቶ በፕሮጀክቱ ከታቀፉ ሁሉም ከተሞችና ባለድርሻ አካት ጋር  የውይይት መድረክ አካሄደ 

ሐዋሳ፣ መስከረም 11 ቀን፣2019 ዓ.ም (ከመልሚ) á‹¨áŠ¨á‰°áˆžá‰˝ ልማታዊ ሴፍትኔት የስራ ፕሮጀክት ያለፉትን አመታት አፈጻጸምና 3ኛ ዙር ተጨማሪ ፋይናንስ አስመልክቶ በፕሮጀክቱ ከታቀፉ ሁሉም ከተሞችና ባለድርሻ አካት ጋር የጋራ የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡

የሐዋሳ ከተማ ም/ከንቲባ እንጂ.ቸርነት ፍላቴ  በእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸው የሐዋሳ ከተማ እንደሀገር በአዲስ አበባ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ሀገራዊ አቅጣጫ ተግባራዊ ለማድረግ ሌት ተቀን ከባለድርሻ አካላትና ከሕብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት በከተማው ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ለከተማው ለውጥ ከመምጣቱ ባሻገር በዝቅተኛ ኑሮ የሚገኙ ዜጎችን ዘላቂ ኑሮአቸውን በማሻሻል ከተረጅነት ወደ አምራችነት መለወጥ እንደተቻለ ም/ል ከንቲባው ገልጸው በከተሞች ልማታዊ ሴፍትኔት የስራ ፕሮጀክት የተመደበላቸውን በጀት በአግባቡ በመጠቀም በፕሮጀክቱ የታቀፉ ዜጎችን ለዘላቂ ዕድገትና  ለውጥ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በከተማና መሠረተ ለማት ሚኒስቴር የከተሞች ምግብ ዋስትናና ሴፍትኔት ጽ/ቤት ኃላፊ  አቶ ብርሃኑ ተሾመ እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ  በሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች በተመረጡ 88 ከተሞች በፍሐዊነትና በግልጽነት የተለዩ ጾታን፣ ዕድሜን እና አካል ጉዳተኝነትን  ልዪነት ሳይፈጥር ዜጎችን በዘላቂነት ኑሮአቸውን ባማሻሻል ከተረጅነት ወደ አምራችነት እየቀየረ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ ፕሮጀክት እደሀገር ከ3 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች እውቀትን፣ ክህሎትንና የስራ ባህልን በማሳደግ ራሳቸውን ከተረጅነት አውጥተው ቤተሰቦቻውንና ለሌሎች ወጣቶች ዘላቂ የሥራ እድል በመፍጠር የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ እንደሆነ ሀላፊው ተናግረዋል ፡፡ 

ከውይይት መድረኩ በተጨማሪ  በሐዋሳ ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ጉብኝት ተካሂዷል፡፡ በተለይ የኮሪደር ልማት፣ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች፣ የትምህርት ቤት ግንባታዎችን እና መሠል በፕሮጀክቶች ተጎብኝተዋል።

በሌላ በኩል ያለፈውን በጀት ዓመት እንደሀገር በፕሮጀክቱ የተከናወኑ አበይቲ ክንውኖችን አስመልክቶ በተመረጡ ከተሞች ሪፖርት በዝርዝር ቀረቦ ከቤቱ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

መርሃግብሩ ለተከታታይ ቀናት እንደሚቀጥል በመርሃ-ግብሩ ተመልክቷል፡፡
👍5❤4