Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹
9.97K subscribers
18.7K photos
276 videos
16 files
510 links
This is the official Telegram page of Ministry of Urban and Infrastructure
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የማንሠራራት ቀን

"ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ!

ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት፣ ከቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ ሀገራዊ መነቃቃታችን በተግባር ተመስክሯል። ይህ ለውጥ በዜጎቻችን የኑሮ ደረጃ፣ በከተሞች መዘመንና የሥራ ዕድል ላይ እውነተኛ ብርሃን ከመሆኑም በላይ ለልጆቻችን የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ ታላቅ ርዕይ ነው። ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም! በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።" -  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የማንሰራራት ቀን በቢሾፍቱ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ስፍራ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 2፣ 2018፣ የማንሰራራት ቀን በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ስፍራ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ በቱሪዝም፤ ግብርና፤ ማዕድንና ነዳጅ፤ ውሀና ኢነርጂ፤ ትራንስፖርት እንዲሁም በከተማና መሰረተ ልማት ዘርፍ የተገኙ ስኬቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያስቃኝ የፎቶ አውደ ርዕይ የተከፈተ ሲሆን፤ የመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች የግንባታ ሂደቱን ጎብኝተዋል፡፡

#FMC
ጳጉሜን -2 የማንሰራራት ቀን
የከተሞች ኮሪደር ልማት ለአደባባይ በዓላትና ቱሪዝም

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2018 ኢትዮጵያ ዓለም በአግራሞት የሚያያቸው ተፈጥሯዊ፣ ሃይማኖታዊና የባሕል ሀብቶች እንዲሁም የቀደምት ስልጣኔ ባለቤትነቷን የሚያመለክቱ ጥበቦችን የታደለች ሀገር ናት፡፡

ይህ የበለፀገ ማንነት በአደባባይ በሚከበሩ በዓላት ላይ በደማቅ ሁኔታ ይገለጣል፤ በዓላቱም ትውፊትን ከአሁኑ ትውልድ፣ ታሪክን ከዘመናዊ ኑሮ እና ባህልን ከቱሪዝም የሚያስተሳስሩ የሀገር ሀብቶች ናቸው።

በዚህ የባህል ድምቀት ላይ የከተሞች ዘመናዊ ልማት ሲጨመርበት፣ በዓላት የሚከበሩባቸው አደባባዮችና አካባቢዎች የሀገርን ቅርስና ውበት ለዓለም የሚያሳዩ መድረኮች ይሆናሉ።

በዚህም በዓላትን መጠበቅና ማሳደግ ባህልን ብቻ ማስቀጠል ሳይሆን፣ የከተሞችን ገጽታ ማሳመር፣ ጎብኚዎችን መሳብ እና የቱሪዝም ኢኮኖሚን ማጠናከርም ጭምር መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

እንደ መስቀል፤ ኢሬቻ ፣ጥምቀት፣ ዮዮ ጊፋታ፣ የሹዋል ኢድ ፌስቲቫል፣ፊቼ ጫምባላላ፣ የሶማሌ ማህበረሰብ የዳኝነት ሥርዓት (ሄር ኢሴ) ያሉት በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ካስመዘገበቻቸው የማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል ናቸው፡፡

የእነዚህ የአደባባይ በዓላት መከበር የማህበረሰቡን ባሕልና እሴት ከማሳየት ባሻገር የውጪ ጎብኚዎችን ቀልብ በመሳብ የኢትዮጵያን የቱሪዝም እድገት የሚያፋጥኑ ናቸው፡፡

ከዚህ አኳያ በተለያዩ ከተሞች እየተተገበሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ደግሞ ፅዱ አካባቢን በመፍጠር የማህበረሰቡን የዕለት ተዕለት ኑሮ ከማቅለል ባሻገር እነዚህ የአደባባይ በዓላት በተመቻቼ ሁኔታ እንዲከበሩ እና የተለየ ድምቀት እንዲላበሱ ያደርጋሉ፡፡

ከተሞች የሀገር ገፅታ ዋነኛ ማሳያ በመሆናቸው በአደባባይ በዓላት አማካኝነት በሀገሪቱ እየተሰሩ ያሉ እና የከተሞችን ውበት እንደ አዲስ የቀየሩ ያሉ ውጤታማ የኮሪደር ልማት ስራዎች ለዓለም እንዲገለጡ እና ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ የነበራት መጥፎ ገጽታ እንዲሻር መልካም እድል ይፈጥራሉ፡፡

በተጨማሪም የከተሞች መልማት በዓሉን ለማክበር የሚመጡ ጎብኚዎችን ቆይታ በማራዘም እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ተዘዋውሮ የመጎብኘት ተነሳሽነትን በመጨመር ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ዘርፍ የምታገኘውን ገቢ ያሳድጋል፡፡