Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹
9.97K subscribers
18.7K photos
276 videos
16 files
510 links
This is the official Telegram page of Ministry of Urban and Infrastructure
Download Telegram
የፕሬስ መግለጫ

እንኳን ለጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀን አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

ኢትዮጵያ የብልጽግና ትልሞቿን በፅኑ መሠረት እየገነባች ነው፡፡ ኢትዮጵያ በመደመር መንግሥት ፖሊሲዎች እና ዕቅዶች እየተመራች ለኹለንተናዊ ብልጽግና እየተጋች ትገኛለች፡፡ በየዘመን አንጓዉ ያጋጠሟትን ፈተናዎች በተደመረ ዐቅም እየተሻገረች፤ ከችግሮች እና ፈተናዎች ዕድሎችን መንጭቃ እያወጣች፤ ነገዋን በጠንካራ መሠረት ላይ እያጸናች ነው፡፡

ለዘመናት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ከዓድማስ እስከ ዓድማስ የሚያውለበልበው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነገዉን ታሳቢ አድርጎ እንደ ቢሾፍቱ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ባሉ መሠረተ ልማቶች እና ኹለንተናዊ ለውጦች ውስጥ እያለፈ ነው፡፡ ፡፡ ነባር እና ዐዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች እየለሙ እና ተደራሽነታቸዉ እያደገ ነው፡፡ ግብርናችን ከዝናብ ጥገኝነት እየተላቀቀ እና የገጠሩም የከተሜዉም የሥራ ዕድል እየኾነ ነው፡፡ የታዳሽ ኃይል አማራጮቻችን ከውኃ፣ ከነፋስ፣ ከፀሐይ፣ ከጂኦተርማል እና ከኑክሊየር ኃይል እንዲኾኑ የመደመር መንግሥት ሌት ተቀን እየሠራ ነው፡፡

ከተሞቿ ጎስቋላ ገጽታቸዉ እየተቀየረ እና ነገን እየዋጁ፤ መሠረተ ልማቶቿ እየተስፋፉ እና እየተቀናጁ፤ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ዐቅሟ እየተጠናከረ፤ የቀጣናዉ የታዳሽ ኃይል ማእከልነቷ እያደገ፤ የማዕድን ሀብቶቿን በላቀ ደረጃ ጥቅም ላይ እያዋለች ለመጪዉ ትውልድ ኹለንተናዊ ብለጽግና እየሠራች ነው፡፡

የኢትዮጵያን ማንሰራራት የሚያበስሩ፤ እመርታዊ ዕድገቷን የሚያፋጥኑ ፅኑ መሠረቶች ላይ እየተገነቡ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያንም ሥርዐቱን ለማጽናት እና መሻታቸዉን እውን ለማድረግ ያላቸዉን ቁርጠኝነት በመንግሥት ጥሪዎች በሚያሳዩዋቸው ተሳትፎዎች እየገለጹ ነው፡፡

በ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ከሌሊት እስከ ሌሊት ፈተናዎችን ተቋቁመዉ ድምፅ መስጠታቸዉ እና ውጤቱን በደስታ መቀበላቸው፤ በአረንጓዴ ዐሻራ በየዓመቱ እያደገ የመጣ ተሳትፎ እና ስኬት ማስመዝገባቸው፤ የልዩነት ሐሳቦችን በሰላማዊ መንገድ ለመግራት ሀገራዊ ምክክርን መምረጣቸው ኢትዮጵያውያን በመደመር መንግሥት ትልሞች ላይ የያዙትን የጋራ ተስፋ እና ለስኬቱም እያደረጉ ያለዉን ርብርብ የሚያሳይ ነው፡፡

የዴሞክራሲ ሥርዐትን በማንበር፤ ብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚን በመከተል፤ የከተሞችን ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ ወደ ገጠር በማላመድ፤ የታዳሽ ኃይል አቅርቦትን በመሻሻል፤ የትራንስፖርት መሠረተ ልማቱን በማዘመንና በማስፋፋት ለኢትዮጵያ ኹለንተናዊ ብልጸግና ፅኑ መሠረት እየተቀመጠ ነው፡፡ ለዚህም ነው ጳጒሜን 2ን “የማንሰራራት ቀን” በሚል ስያሜ እያከበርን የምንገኘው፡፡

ጳጒሜን 2 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ
#FGCA
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከፌደራል የመንግስት የግዥና ንብረት ባለስልጣን ጋር በመተባበር የግዥ በጊዥ መመሪያ ላይ ለአመራሩ የግንዛቤ ማስቸበጫ ስልጠና ሰጠ

አዳማ፣ ነሐሴ 30 ቀን፣2018 ዓ.ም (ከ.መ.ል.ሚ) የግንዛቤ ማስቸበጫ ስልጠና የታለመለትን ግብ እዉን ለማድረግ በሁሉም ስራ ክፍሎች በ2019 በጀት ዓመት ጊዥዎች በመመሪያው ብቻ እንዲከናወን ተገልጿል።

በስልጠናው ላይ የስራ አመራር ዋና ሾል አስፈጻሚ አቶ አበራ አመንታ እንደተናገሩት ሁሉም ሾል ክፍሎች  የግዥ ዕቀድን ሲያቅዱ ሁሉንም የህግ ማዕቀፎችን ጠንቅቀው በማወቅ በጀትን በጊዜ፣ በዋጋ፣ በጥራት እና በጥንቃቄ እንዲሁም በተጠያቂነት ማዘጋጀት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

የዕለቱን የግዥ አጠቃላይ የህግ ማዕቀፎችን አስመልክተው ስልጠና የሰጡት የፌደራል መንግሰት የግዥና ንብረት ባለስልጣን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዳብራሩት ተቋማት ከዘልማዳዊ የግዥ ስርዓት ወጥተው መንግስት በሚፈለረገውና በዘረጋው የድጅታል አሰራርን ተከትለው መሄድ እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥተው፡፡

በአሁኑ ወቅት በሁሉም ፌደራል ተቋማት ግዥ መፈጸም ያለበት በኤሌክትሮን ግዥ መሆኑን ጠቅሰው በተለያዩ ምክንቶች የተቋም የበላይ አመራር ከፈቀደ ብቻ መካናወን እንደሚቻል ለሰልጣኞች አብራተዋል፡፡

የስልጠና ተሳታፊዎች በአተገባበር ወቀት የሚጋጥማቸውን ተግዳሮት ለአስልታኞች በጠየቁት መሠረት ተገቢው ምላሽ ማብራሪያ ተሰጥቶቸዋል፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የማንሠራራት ቀን

"ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ!

ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት፣ ከቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ ሀገራዊ መነቃቃታችን በተግባር ተመስክሯል። ይህ ለውጥ በዜጎቻችን የኑሮ ደረጃ፣ በከተሞች መዘመንና የሥራ ዕድል ላይ እውነተኛ ብርሃን ከመሆኑም በላይ ለልጆቻችን የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ ታላቅ ርዕይ ነው። ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም! በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።" -  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የማንሰራራት ቀን በቢሾፍቱ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ስፍራ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 2፣ 2018፣ የማንሰራራት ቀን በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ስፍራ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ በቱሪዝም፤ ግብርና፤ ማዕድንና ነዳጅ፤ ውሀና ኢነርጂ፤ ትራንስፖርት እንዲሁም በከተማና መሰረተ ልማት ዘርፍ የተገኙ ስኬቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያስቃኝ የፎቶ አውደ ርዕይ የተከፈተ ሲሆን፤ የመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች የግንባታ ሂደቱን ጎብኝተዋል፡፡

#FMC